Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

ይቅርታን የተጸየፈው የሲኖዶሱ ይቅርታ…

Post by sarcasm » 06 Jul 2023, 18:20

Please wait, video is loading...

Full discussion



sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: ይቅርታን የተጸየፈው የሲኖዶሱ ይቅርታ…

Post by sarcasm » 06 Jul 2023, 18:38

የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ሲኖዶስ ዛሬ ለትግራይ ህዝብ ባቀረበው የይቅርታ ደብዳቤ: ይቅርታ እንዲጠይቅ እንደ ምክንያት ካስቀመጣቸው ነጥቦች አንዱ እንዲህይ ይላል "ጦርነቱ እንዲቆም በወቅቱ መግለጫ ባለመሰጠቷ"

እኛ እያልን ያለነው ደግሞ: ዋናው ችግር የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ቤተክርስትያን "ጦርነቱ እንዲቆም በወቅቱ መግለጫ ባለመሰጠቷ" ሳይሆን፤ ጦርነቱ በይፋ መደገፏ ነው። የደገፈችበት መረጃ እኮ በየኢንተርኔቱ በዜና መልክ አለ ማንንም ማታልል አይቻልም።
"የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን "ከ ሀገር መከላከያ ጎን እንቆማለን" በሚል ለሰራዊቱ ያላት ድጋፍ ገለጸች። "ከ ሀገር መከላከያ ጎን እቆማለን" በሚል መሪ ቃል የተላለፈው ጥሪ በመቀበል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት ለመከላከያ ሰራዊቱ ያለውን ድጋፍ ገለጸ..." የ EBC ዜና! (November 17, 2020)!
ምንጭ 👇
https://shorturl.at/fsvxS

እውነት መናገር እና መቀበል ያስፈልጋል። እውነትን በመደፍጠት ፍትህ እና ይቅርታ ሊገኝ አይችልም


- ጦርነቱ እንዲቆም በወቅቱ መግለጫ ባለመሰጠቷ፣
- በጦርነቱ መካከል ወደ ትግራይ ክልል መግባትና መውጣት በሚቻልበት ወቅትም በክልሉ የሚገኙ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንንና መላው #ሕዝበ_ትግራይን በአካል በቦታው ተገኝታ ባለመጠየቋና ባለማጽናናቷ፣
- ጦርነቱ ቁሞ በአገር አቀፍ ደረጃ እርቀ ሰላም ከወረደበት ጊዜ ጀምሮ ለደረሰው ጉዳት በቅዱስ ሲኖዶስ የተወሰነውን ሰብአዊ ድጋፍ በውሳኔው መሠረት በወቅቱ ማድረስ ባለመቻሏ፣
በዚሁም የተነሣ በቤተ ክርስቲያኗና በመላው ሕዝበ ትግራይ መካከል ለተፈጠረው ቅሬታና አለመግባባት ቅዱስ ሲኖዶስ በይፋ ይቅርታ ጠይቋል።
=========|||||||||||||||||||||||||||||||
የ ዮም ፖስት መልእክት:
ጅምሩ ባይከፋም የኢትዮጵ ኦሮቶዶክስ ቤተክርስትያን በትግራይ ህዝብ ላይ ያደረሰችው ግፍ እንዲሁ በቀላሉ በይቅርታ ብቻ የሚታለፍ አይደለም። ምክንያቱም:
(ሀ): የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ቤተክርስትያን "ጦርነቱ እንዲቆም በወቅቱ መግለጫ ባለመሰጠቷ" ሳይሆን መባል ያለበት፤ ጦርነቱ በይፋ በመደገፏ መባል አለበት!
"ከ ሀገር መከላከያ ጎን እቆማለን" በሚል መሪ ቃል የተላለፈው ጥሪ በመቀበል የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት ለመከላከያ ሰራዊቱ ያለውን ድጋፍ ገለጸ! (November 17, 2020)!
👇
https://shorturl.at/DJRT1
(ለ): የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ሲኖዶስ ብውስጧ የተሰገሰጉ ጥላቻ እና ጦርነት ሰባኪ ጳጳሳት ይዛ እስከቀጠለች ድረስ፣ ማንም የሚያከብራት እና seriously የሚወስዳት ሰው አይኖሮም። በከፍተኛ ደረጃ ጥላቻ እና ጦርነት የሰበኩ የሲኖዶስ አባላት የሆኑ ጳጳሳት:
1. "አንድ አምስት መቶ ሺህ (500,000) የሚሆኑ የወያኔ ካድሬዎች እና ደጋፊዎች ፈርተው ሄደዋል እንጂ የተፈናቀለ የለም። ... አክሱም ላይ ሰው ተገደለ የሚባለው፣ አንድም ሰው ሲናገር አልሰማሁም። ውጭ ያሉ የሚያራግቡት ነው" የሲኖዶስ አባል አቡነ ጴጥሮስ! Video 👇
https://www.facebook.com/YomePost/video ... 424505889/
"ቤተክርስትያን ጦርነቱ ለምን አላወገዘችም ይላሉ፤ ምኑ ነው የምታወግዘው? ጦርነቱ የከፈተው እኮ ህወሓት ነው።" የሲኖዶስ አባል አቡነ ጴጥሮስ! Video 👇
https://www.facebook.com/fitwi.meles/vi ... 3870582735
"ህወሃት ተመልሶ ይመጣል ብላችሁ አትጠብቁ። ይህ መርዶ ነው። ህወሓት ተመልሶ አይመጣም ቁርጣችሁን እወቁ" የሲኖዶስ አባል አቡነ ጴጥሮስ! Video 3 👇
https://www.facebook.com/10000108560522 ... 8731346843
2. "ሰይጣን ቢገዛን ይሻላል..." የሲኖዶስ አባል ኣቡነ ሚካኤል!
Video 👇
https://www.facebook.com/ermias.haile.5 ... 9429656622
3. "ኢትዮጵያን ኢትዮጵያ ያሰኛት እኮ አማራ ነው። ዋልድባ የማን ነው? ዋልድባን አስረክበህ እዚ ቁጭ ብለህ ጠላ እየጠጣህ ወሬ ማውራት ምን ይጠቅመሃል? ... ክላሽ ያዝ ... ከውስጣችሁ ጁንታዎች አሉ መሰለኝ ... " የሲኖዶስ አባል አቡነ መቃርዮስ!
Video 👇
https://shorturl.at/jBLOP
4. "አቡነ ማትያስ የትግራይ ህዝብ እንዲኖር አልተፈቀደለትም ሲሉ ሰማሁዋቸው፤ በጣም አዘንኩኝ፣ ተሸማቀቅኩ። . . . ከህወሓት ጋር መናጋገር አያስፈልግም..." የሲኖዶስ አባል ኣቡነ ፋኑኤል! 👇
https://shorturl.at/qAIN1
5. "የአቡነ ማትያስ ንግግር ቤተክርስትያን አይወክልም" በማለት አቡነ ማትያስ እንዳይናገሩ ማይክ የቀሟቸው የሲኖዶስ አባል አቡነ ዮሴፍ! 👇
https://www.facebook.com/watch/?v=730609234301793
6. በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ቤተክርስትያን ሲያገለግሉ የነበሩ ተጋሩ፣ በማንነታቸው ምክንያት እንዲታሰሩ እና ከ ስራቸው እንዲባረሩ ያደርጉ የሲኖዶስ አባል ኣቡነ መልከጼዲቅ።
👇
https://shorturl.at/eLMQT
.
.
.
ሌሎች ጻጻሳትም አሉ።
እውነት መቀበል ያስፈልጋል። ከዛ በይቅርታ የሚታለፍ ጥፋት በይቅርታ ይታለፋል፣ የሚያስቀጣ ጥፋት ከሆነ ደግሞ ተገቢ ቅጣት መስጠት ያስገልጋል። ያለ እውነተኛ ፍትህ እውነተኛ ይቅርታ ሊገኝ አይችልም!




Please wait, video is loading...

TGAA
Member+
Posts: 5626
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

Re: ይቅርታን የተጸየፈው የሲኖዶሱ ይቅርታ…

Post by TGAA » 06 Jul 2023, 19:31

እፍረት የማታውቁ አረመኔዎች ናቸሁ ፤ ቤተክርሲትያኗማ ተኝቶ ያረዳችሁትን ሰራዊት አውጉዛ ሀገሩን ለመከላከል የቆመውን የኢትዮጵያ ሰራዊት አታወግዝም ፤ እያንዳንዱ ያንን ያቀነባበሩ የወያኔ መሪ በሞላ መጀመሪያ ተንበርክኮ የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ መጠየቅ ይገባው ነበር ፤ እንደአብይ አይነት ሞራል ያለው ሽልፋጣ መሪ ባይኖር ኖሮ ፤ ወያኔ ለጀመረው ጦርነት መጀመሪያ ይቅርታ መጠየቅ የሚገባው ወያኔ ነው ፤ ቤተክርስቲያኖ ከኢትዮጵያ ስራውትን መደገፏ እጅግ አግባብነት አለው ፤ 1 ሚሊየህ ትግራዋይ አስጭፍጭፋችሁ አሁን ይህ ሁሉ መግተርተር በትግራይ ህዝብ ላይ የሰራችሁትን ወንጀል ለመሽፈን ነው፤ ቤተክርስትያኖ ይቅርታ የምትጠይቀው ለትግራይ ህዝብ ያላትን ሀዘን ለመግልጽ እንጂ የወያኔ ወንጀል ለመረከብ አይደለም፤ የናተ አይናውጣነት ግን !? ወቸው ጉድ ወያኔ የሚያሰኝ ነው ፤

Post Reply