Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Thomas H
Senior Member
Posts: 12530
Joined: 27 Jan 2007, 16:30
Location: Kaliti
Contact:

Breaking News : ዓብይ አህመድ በአዲሱ የበጀት ዓመት አዳዲስ የመንግሥት ሠራተኛ ቅጥር አንፈፅምም አለ

Post by Thomas H » 09 Jun 2023, 09:12

Wazema Radio ዋዜማ ሬዲዮ - መንግስት ከአንድ ወር በኋላ ሃምሌ 2015ዓ.ም በሚጀምረው አዲሱ የ2016 ዓ.ም በጀት አመት ምንም አይነት የመንግስት ሰራተኛ ቅጥር እንደማይፈጸም የገንዘብ ሚንስቴር አስታወቀ፡፡ በየአመቱ አዳዲስ የስራ እድል አይፈጠርም በሚል የሚቀጥል ከሆነ ተመራቂዎችና ዜጎች ተስፋ በመቁረጥ ለአላስፈላጊ ስደት እንዳይዳረጉ ስጋት አለኝ ሲሉ አንድ የምክርት አባል ቅሬታ አሰምተዋል፡፡ የምክር ቤት አባሏ አክለውም ይህ አሰራር የመልካም አስተዳደር ችግር እንደሚሆን ጠቅሰው‹‹ ምስኪን አርሶ አደሮች ብዙ መስዋዕት ከፍለው ነው ልጆቻቸውን አስተምረው የሚያወጡት ፣ በመንግስት መስሪያ ቤት በየአመቱ ይቀጠሩ የሚል እምነት ባይኖረኝም በምን መልኩ ነው አሁን የተማሩ ምሁራንን ወደ ስራ ማስገባት እና ማሰማራት የምንችለው ›› ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

በተመሳሳይ የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ መምህርና የምክር ቤት አባሉ ዶ/ር ዘገየ ሙሉየ ሲናገሩ ለዜጎቹ ስራ መፍጠር አንዱ የመንግስት ሃለፊነት መሆኑን ጠቅሰው ስራ ባለመፍጠር የትም ሊደረስ አይችለም ብለዋል፡፡ ይህን በመዝጋት ዘላቂ የሆነ ስራ መስራት አይቻለም ስለዚህ መንግስት የገቢ አሰባሰቡን ስርዓት በማስተካከልና የመንግስትን ወጭ በተገቢው ቦታ በማዋል ጠበቅ ተደርጎ ካልተሄደ በቅርብ ጊዜ ከችግር ሊወጣ አይችለም ብለዋል፡፡

በቅርቡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል፣ የስምንት ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን ሲቀርቡ
በስምንት ወራት ውስጥ ለ2.6 ሚሊዮን ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ ለሁለት ሚሊዮን ዜጎች መፍጠሩን ገልጸው፡ ነገር ግን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ከ አሥራ ስድስት ሚሊዮን በላይ ስራ አጥ ዜጎች መመዝገባቸውን ተናግረው ነበር፡፡