Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4063
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

የ ኦሮሚያ ፖሊስ የግሪኩን አምባሳደር ገፈታትሮና ደብድቦ ከግሪክ ኮሚኒቲ ትምህርት ቤት አባረረ - ኤሊያስ መሰረት

Post by Za-Ilmaknun » 08 Jun 2023, 15:34

ኤልያስ መሠረት ስለሁኔታው የፃፈው ነገር ውሸት ነው"--- ዳይሬክተር ጸጋ ዋቅጅራ

"ድርጊቱ መከሰቱ ትክክል ነው፣ ሆኗል"--- የግሪክ ኤምባሲ

"በአይናችን አይተናል፣ ቪድዮም አለ"--- በስፍራው የነበሩ ሰዎች

የግሪክ ኮሚኒቲ ትምህርት ቤትን በተመለከተ ሰኞ እለት አንድ መረጃ አጋርቼ ነበር። ታድያ በዚህ መረጃ ላይ በትምህርት ቤቱ ካለው አስተዳደራዊ ውዝግብ ጋር ተያይዞ ቅዳሜ እለት ፖሊስ ግቢውን እንደተቆጣጠረ፣ ጉዳዩን ሰምተው ወደ ስፍራው ያቀኑት በኢትዮጵያ የግሪክ አምባሳደርም እንደተገፈተሩ እና ከግቢው ለቀው እንዲወጡ እንደተደረጉ ገልጩ ነበር።

ይሁንና በዚህ ዙርያ ትናንት መግለጫ የሰጡትን የጠቅላይ አቃቤ ህግ በወንጀል የተገኘ ሀብት ማስመለስ ዳይሬክተር ፀጋ ዋቅጅራ Arts TV ጠይቆ "ኤልያስ መሠረት ስለሁኔታው የፃፈው ነገር ውሸት ነው... የግሪክ አምባሳደር ቦታው ላይ ተገኝተው አያውቁም" ብለው መልስ እንደሰጡ ዘግቧል።

እውነታው ታድያ የቱ ነው? እስቲ ዛሬ ራሴን ልከላከል 😅

1. የግሪክ ኤምባሲ በኢሜይል ባደረሰኝ መረጃ "ድርጊቱ መከሰቱ ትክክል ነው፣ ሆኗል" ብሏል (ስክሪንሾት ተያይዟል)።

2. የግሪኩ Defense Point Greece ድረ-ገፅ አምባሳደሯ ላይ ምን እንደተከሰተ በዝርዝር በትናንትናው እለት ዘግቧል (በ Google Translate ማንበብ ይቻላል: defence-point.gr/news/simantike…)

3. ዛሬ በግል በደረሰኝ መረጃ መሰረት ጉዳዩ ግር መሰኘት ብቻ ሳይሆን ያስደነገጠው አቴንስ የሚገኘው የግሪክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ለኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዚህ ዙርያ ሜሞ ፅፎ አስገብቷል።

4. በመጨረሻም፣ ዋናው ማስረጃ ራሱ ቪድዮው ነው። ቪድዮው ተገኝቷል፣ ግን ከባለቤቱ ለህዝብ እንዳጋራው ፈቃድ ጠይቄ መልስ እየጠበቅኩ ነው፣ ፍቃድ እንደተገኘ ይቀርባል።

#Note Arts TV የተባለው ሚድያ "ዳይሬክተሯን ጠይቀናቸው ውሸት ነው አሉ" ብሎ 'ከርፋፋ' የሆነ ዜና ከመስራት በጋዜጠኝነት መርህ መሰረት ኤምባሲውን ወይም አምባሳደሯን፣ ወይም በስፍራው የነበሩ ሰዎችን ማናገር ይገባው ነበር።

Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4063
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

Re: የ ኦሮሚያ ፖሊስ የግሪኩን አምባሳደር ገፈታትሮና ደብድቦ ከግሪክ ኮሚኒቲ ትምህርት ቤት አባረረ - ኤሊያስ መሰረት

Post by Za-Ilmaknun » 08 Jun 2023, 15:46

"To a man with a hammer, everything looks like a nail" :mrgreen: :lol: The only way the OPDO gov't tries to sort out problems is by brute force. The deplomatic community is not spared, so it seems, from the harm.

Post Reply