በ መስጂድም በኩልም ተጠግቶ መጣ፣ ማለፍ አልተቻለዉም፣
ወደ ገዳምም ሄደ እዚያም ተጠግቶ ለማለፍ ሞከረ፣ በዚያም አልተቻለዉም፣
ይልቁንም ማቃብሩን ቆፈረ
እዚያም ተቀበረ፣ በዉስጡ ታፍኖ በዉስጡም አረረ።
በሚንሊክ አደባባይም ተጠግቶ ለማለፍ በግፍ ተሞከረ፣ ማለፍ ግን አልተቻለም።
እስከአሁን ያልቀነሰዉ ኡኡታዉ ብቻ ነዉ፣ እንደ ነበረ ያለዉ፣
ለጊዜዉ እሱም እዚያዉ መፅናናት ይፈልግ፣ ራሱን አግልሎ።
የሕግ ማስከበሩ ስራ ይቀጥላል ይልቁንም ተጠናክሮ፣
የሕግ የበላይነት ይስፈን በአገሪቷ ወደ ፊትም ተጠናክሮ