Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30829
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

አቢይ አህመድ ርዕዮተ ዓለም ምን እንደ ሆነ አያውቅም

Post by Horus » 07 Jun 2023, 23:27

እኔ ሆረስ ቃላት በመፍለጥ ሰው አላሰለችም። አቶ አቢይ አህመድ መደመር የሚባል ርዕዮተ ዓለም አለ ብሎናል ። አለ ብሎም ባለብዙ ዝባዝንኬ መጻህፍት አሳትሟል ። ታዲያ አይዲኦሎጂ ምንድን ነው? አይዲኦሎጂ ከየት ነው የሚመጣው?

አይዲኦሎጂ የሁለት ቃላት ጥምር ነው ፤ አይዲያ እና ሎጎስ። የአማርኛው ቃል ርዕዮተ ዓለም ሎጎስ የሚለውን በአለም ተክቶታል። በጣም ጥሩ ነው። ሎጎስ ቃል ወይም ጥናት ወይም የአንድ ነገር ሎጂክ ማለት ስለሆነ እሱን እንተወው ።

ዋናው ቃል አይዲያ ወይም ርዕዮት የሚለው ቃል ነው ። ይህ ቃል ከግሪክ ስልጣኔ ጀምሮ እስከ ዛሬ ብዙ ፍልስፍና የተቀመረበት ስልሆነ ማንም በቀላሉ የሚያምታታው ጽንስ አይደለም ። ቃሉ ፕሌቶ እንዳለው ባዶ፣ ንጹህ፣ ከምንም ነባራዊ ነገር ያልተያያዘ ሃስብ ሳይሆን አሪስቶትል እንዳረመው የነገር ቅጂ ምስል ማለት ነው ።

አይዲያ ወይም ርዕዮት የአንድ ነገር ማለት ነባራዊ ነገር፣ የአንድ ሪያሊቲ ግልባጭ ፣ ቅጂ፣ ኮፒ ፎርም፣ ቅርጽ፣ ምስል፣ ስዕል ማለት ነው። በአንድ ቃል የሌለ ነገር፣ ህያው ያልሆነ ነገር፣ ህልውና የሌለው ምናብ ምስል የለውም። ኢሉዝን፣ ወይም ንጹህ ኢማጂኔሽንልብ ወለድ ፋንሲ ርዕዮት አይደለም ። ስለዚህ ርዕዮት ከሰዎች አይምሮ፣ ከሰዎች ህልም በዘፈቀደ ተመኝቶ ያንን ባዶ ምናብ የሪያሊቲ ቅርጽ ነው፣ የአለም ፎርም ነው፣ የነዋሪ ነገር ምስል ነው ማለት ፍጹም ስህተት ብቻ ሳይሆን አደገኛ የሳይኮሎጂ ፓቶሎጂ ነው ።

ስለሆነም ስለ አንድ የማሀበረ ሰብ ርዕዮተ ዓለም ወይም ምስለ አለም፣ ወይም ስዕለ አለም ስናወራ ያ ምስል ህያው ከነበረ ፣ ከኖረ ፣ ሊኖር ከሚችል ማህበራዊ ስርዓት የተቀዳ ምስል እንጂ ከሰው አይምሮ የተፈበረከ ኢሉዝን ፣ ሚራክል ወይም ታምር የሚቀዳ አይደለም ። ስለዚህ ነው ስለ ፖለቲካ ር ዕዮተ አለም (ምስለ አለም) ስናስብ በአለም ላይ የነበሩና ያሉ ፖለቲካ ሲስተሞችን ምሳሌዎች፣ ምስሎች የምናጠናው እንጂ ከባዶ አንጎላችን ህልምና ኢሉሽን እያየን ያንን እንደ አይዲኦሎጂ መስበክ ድንቁርና ብቻ ሳይሆን እብደት ነው።

ስለዚህ የአቶ አቢይ መደመር ርዕዮተ ዓለም አይደለም ። ከምንም ነባራዊ አገር፣ ፖለቲካ ፣ ስራዓት የተቀዳ ምስል አይደለም ፣ የምንም ስራት ስዕል አይደለም፣ የአንድ ሰው ባዶ ሃስቦች በፊደል የተጻፈ ህልምና ምናብ ነው ።መደመር የሚባል የኢኮኖሚ፣ ፖለቲካ ሶሺያል ርዕዮተ ዓለም፣ ምስለ ፖለቲካ፣ ርዕዮተ መንግስት በየትኛውም አገር አልኖረም ።

ኢትዮጵያ ውስጥ እከሌ የሚባሉ ምሁራን ካሉ ይህን መረን የለቀቀ ኢሉዥን መርምረው ጸሃይ ላይ ማስጣት አለባቸው ። በኢትዮጵያ ምንም ነገር የማይሰራው መደመር በተባለ የአንድ አላዋቂ መሪ ጭለማ ውስጥ አገር ስለሚታመስ ነው ።

በአለም ላይ ያሉት የኢኮኖሚና ፖለቲካ ስርዓት አይነቶች ይታወቃሉ ። መደምር የሚባል ግን የለም !