Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Selam/
Senior Member
Posts: 11549
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

HORUS!

Post by Selam/ » 07 Jun 2023, 08:26

ethiopianunity
Member+
Posts: 9075
Joined: 30 Apr 2007, 17:38

Re: HORUS!

Post by ethiopianunity » 07 Jun 2023, 09:19

What is the Effn going on? I think the Shabia influence of pp government is changing Ethiopia to Italian colony!! These a holes! That is it they are destroying this country, meaning OLF latin language is spreading all over the South. Either say you are colonized or not!!! Tell me what the OLF or Somalia writing Latin did to them? Go to Somalia, nothing! somalia is as backward today as it was before! This is saying goodbye to the Ethiopoian culutre, language, faith. Look at these, majority are muslims too, this is a sign of rejecting Orthodox, Ethiopia. The Oromuma will not stop here especially the radical Protestand and Muslim

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: HORUS!

Post by Horus » 07 Jun 2023, 12:14

Selam,
በሌላ ሌላ ነገር ባልጠመድ በዚህ ርዕስ ላይ ብዙ ለማለት እፈልግ ነበር። የነገሩ እምብርት ቀቤና የኩሽ ዘር ስለሆነ በሴም ፊደል መጻፍ የለበትም የሚል ነው ። በአንድ ያልተጽፈ ቋንቋ ውስጥ ያለን ድምጽ የሚገልጸ (የሚወክለው ምልክት) ፊደል ከሌለው አዲስ ይፈጠርለታ ፣ በቃ ሌላ ምስጢር የልውም ። ስለዚህ ልክ ጉራጌኛ በግ እ ዝ ፊደል ላይ ምልክቶች በመጨመር የጉራጌኛ ፊደል ገበታ እንደሰሩት ቀቤናም ይችል ነበር ።

ነገሩ ፖለቲካ እንጂ ሊንጉዊስቲክስ አይደለም ።

ትልቁና አሳፋሪው ኩምክና ግ ን ይህ ነው ። (ሃ) ቀቤና ሙስሊም ነው ። ቅዱስ መጽሃፋቸው ቁርአን ነው ፣ አረብኛ ነው ። ማለትም የቀቤና ነፍስ የሚገለጸው ቃሉን እንኳ መለወጥ በማይቻለው አረብኛ ነው። የሴም ቋንቋ ነው ። ቁራን የአላህ ቃል ስለሆነ ቃሉ ቴክስቱ እንኳ መለወጥ አይቻልም ። (ለ) አሁን የቋንቋ ሊቅ ነኝ ፣ ምርምር አድርጌአለሁ ያለው የቀቤና ተመራማሪ ቀቤና በላቲን ፊደል ይጻፍ ሲል እራሱ የላቲን ፊደል ከፊኒቄ (ፊኒሺያዊ)፣ ከሳቢያን እና ግእዝ ተለቅሞ እንደ ተሰራ ያልተማረ ሰው ነው (አንድ ኮርስ እንኳ ሂስቶሪካል ሊንጉዊስቲክስ) አልወሰደም ማለት ነው ። የላቲን ፊደል ከሴም ፊደል ነው የተቀዳ፣ ይህ እራሳቸው ሮማዊያን ይነግሩታል ።

ስለዚህ ወደ ፊት የሚያፍሩ አዳዲስ የቀቤና ምሁራን ይሽሩታል ። ትልቁ ጥያቄ የግእዝ ፊደል ነው ወይስ ላቲን ፊደል የቀቤናን ቋንቋ ሙሉ በሙሉ ሊገልጽ የሚችል ለሚለው ጥያቄ ዛሬ ላይ እራሳቸው የላቲን ፊደል ሊቃውን የግእዝን በላጭነት በመቀበል ግራጁዌት ሌቭል ኮርስ በትላልቅ ኡኒቨርሲቲዎች እየሰጡ ነው ።

የሰው ልጅ አለምን የሚለየው በማየት (ምስል/ፊደል)፣ በመስማት (ድምጽ)፣ በመንካት ፣ በጣእም እና ሽታ ነው ል እድሜ ለቴክኖሎጂ ፊደል ብቻ ሳይሆን በነዚህ 5 ቴክኖሎጂዎች ቋንቋ እየፈጠረ ነው ። የቀቤና ምሁር ችግር አዲስ ግ እ ዝ ን ተጠቅሞ አዲስ ፊደል መቅረጽ አለማቻሉ ነው ። ወደ ላቲን በመሸሽ ከሴም ፊደል መፋታት አይችሉም! ላቲንም ሴሚቲክ ነው!!!! ላቲን የኩሽ ፊደል አይደልም!

አንድ ቋንቋ ከሌላው የሚለየው በድምጽ እንጂ በምልክቶች መለያየት አይደለም ቀቤና እና Qebiena አንድ ቃል ነው ። ጀርመኛና እስፓኝ በላቲን ይጻፋሉ ግ ን በዝርያቸው የተለያዩ ናቸው ። ማለትም የተለያዩ ቋንቋዎች በአንድ ፊደል ይጻፋሉ ። ቀቤናና ጉራጌኛ በግእዝ ፊደል ይጻፋሉ ! አበቃሁ!

https://lcf.lau.edu.lb/images/phoenicia ... series.pdf
Last edited by Horus on 07 Jun 2023, 14:42, edited 4 times in total.

TGAA
Member+
Posts: 5598
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

Re: HORUS!

Post by TGAA » 07 Jun 2023, 12:45

የኔን ግንዛቤ ትንሽ ለመጭመር ያህል ፤ አንተ እንዳልከው ይህ የኦሮሙማ ፖለቲካ እየሰረሰረ የሚያመጣው ግእዝን በመጥላት ከእውቀት የመሸሽ መገለጫ ነው፡፡ ዋናው ቁምነገር በአሁኑ ሰአት ብዙው የእውቀት ክምችት የተጻፈው በአማርኛ ነው ፤ ይህም እውቀት የተጻፈውና የዳበረው በአማሮች ብቻ ሳይሆን በሁሉም ኢትዮጵያን ነው፤ እንደውም የአማርኝ መዳበር ከአማራው ህብረተሰብ በላቀ በሌላው የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ትልቅ አስተዋጸ ነው የመጠቀው ፤ በአለፈው በኦሮምያ የተፈጸመውን አሁን ደግሞ በሌሎች ኢትዮጵያዊያ ላይ እውቀትን ባገላገነዘበ መልኩ በቀላሉ ሊያገኝት የሚችሉትን እውቀት እንዳያገኙ እያደረጋቸው ነው ፤ መጨረሻ ተጎጂው ያንን በጎሳ አጥር ውስት የሚወሽቁት ህብረተሰብ ነው፤ ኢትዮጵያ ውስጥ እንግሊዘኛ ትምህርቱ ሞቷል ፤ አሁን ደግሞ በአማርኛ ያለውን እውቀት እንዳይካፈ እያደረጉት ነው፤ የሚተኩት ነገር ሳይኖራቸው ያለውን እያጠፉት ነው ፤ አማርኛ የሚማረው ህብረተሰብን ሊጉዱ ቢያስቡም የሚጎዱት የሚያጥሩት ህብረተሰብን ነው ፡፡ እኔ በቁቤም አስተማሩም አላስተማሩ ለውጥ ያለው አይመሰለኝም ፤ የደሮውን አውጥተው የሚተክሉት ቋንቋ እውቀትን ለህብረተሰቡ ማምጣት ይችላል ወይ ? አይደለም በአለም አቀፍ ደረጃ አገሬቱ እስካሁን ካከማቸችው እውቀት ይህ ህብረተሰብ መካፈል እንዲችል ማድረግ ይቻላልው ወይ ? የጎሰኛ ፖለቲካ ደንቆሮን ከመፈልፈል አልፎ የሚሰራው ነገር የለም ፡፡

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: HORUS!

Post by Horus » 07 Jun 2023, 13:19

TGAA wrote:
07 Jun 2023, 12:45

ይህኮ የትም የማይሸሹት ነባር ሃቅ ነው ። በግእዝና አማራኛ የተከማቸው እውቀትና ካልቸር ለመጋራት ፣መጋራትም አለባቸው በግድ ፊደልን ይጠቀማሉ፣ አማርኛም ይማራሉ ። የቀቤና ትልቁ አለም ኢትዮጵያ ነች ። የኢትዮጵያ አለም ቀቤና ወረዳ አይደለም። ኦሮሞ ወይም ሃዲያ መሆን ከፈለጉም ምብታቸው ነው ። የወረሞም የእሃዲያ አለምም ኢትዮጵያ ናት ። ይህን መለወጥ አይቹም ። በካልቸር እድገትም ብናየው ካልቸር የሚያድገውና የሚዘምነው ከሌላ ካልቸር ጋር ባለው ግንኙነትና ቴክኖሎጂ ትራንስፈር ነው ። ካልቸር ቴክኖሎጂ ማለት ነው ። ጉራጌ ዶሮ ወጥ መስራት ካማራ ተማረ ማለት ቴክኖሎጂ ትራንስፈር ነው ። አማራ ከጉራጌ ክትፎ መስራት ተማረ ማለት ቴክኖሎጂ ትራንስፈር ነው ። በቃ የካልቸር እድገት ሃሁ ይህ ነው ። ቀቤናም ካልከው የድንቁርና አጥር መውጣት ሲጀምር ይህን ሃሁ መከተል የግድ ይለዋል ፣እስከዚያ በጭለማው ዘመን ውስጥ በመተራመስ ይቆያል ! ወግ ነው ሲዳሩ ማልቀስ ይባላል፣ የማንም ባለትንሽ እውቀት ህዝቡን አዳራሽ ወስጥ ሰበሰበ ማለት አንድ ጭብጥ ፋይዳ አመጣ ማለት አይደለም! የዘመኑ ማንነት ፕለቲካ ድራማ ነው! ብዙም ዋጋ አልሰጠውም!

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: HORUS!

Post by Horus » 07 Jun 2023, 14:05

Selam/
Senior Member
Posts: 11549
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: HORUS!

Post by Selam/ » 07 Jun 2023, 15:26

ያሳፍራል፣ ያሳፍራል፣ ያሳፍራል፦!

አረብኛን ቢወስዱ አይደንቀኝም ነበር ቢያንስ የሃይማኖቱ ድልድልይ ስላለ።
ፊደሉ የት እንደተፈጠረና ላቲን የሚለው ቃል ራሱ ምን ማለት እንደሆነ ለማያውቅ ሰው ራንደምሊ randomly በዚህ ነው የምትማረው ብሎ በላዩ ላይ መጫን፣ የባሰ ድንቁርናን ነው የሚያመጣው። የፈረንጅ ፊደል ብልፅግና ያመጣል ብለው ከዛሬ ፴ አመት ጀምሮ ፪፮ ቱን አልፋቤቶች የተሸከሙት እንኳን አንዲት ጸዳ ያለች የፈረንጅ ቋንቋ ዓርፍተ ነገር መስራት አይችሉም።

ቀውጢው አብይን፣ ጎታታዋ አዳነችንና ድልቡ ሽመልስን ተመልከት። የፈረንጅ ቋንቋ ሲያያቸው ይበረግጋል። እነሱ ግን የሙጥኝ ብለው እንደ ፎጣ ከላይ ተከናንበውታል። ‘በራሳችሁ የማትኮሩ አሳፋሪዎች’ ብሎኛል አንዱ ግልፅ ቻይናዊ።
Horus wrote:
07 Jun 2023, 13:19
TGAA wrote:
07 Jun 2023, 12:45
የኔን ግንዛቤ ትንሽ ለመጭመር ያህል ፤ አንተ እንዳልከው ይህ የኦሮሙማ ፖለቲካ እየሰረሰረ የሚያመጣው ግእዝን በመጥላት ከእውቀት የመሸሽ መገለጫ ነው፡፡ ዋናው ቁምነገር በአሁኑ ሰአት ብዙው የእውቀት ክምችት የተጻፈው በአማርኛ ነው ፤ ይህም እውቀት የተጻፈውና የዳበረው በአማሮች ብቻ ሳይሆን በሁሉም ኢትዮጵያን ነው፤ እንደውም የአማርኝ መዳበር ከአማራው ህብረተሰብ በላቀ በሌላው የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ትልቅ አስተዋጸ ነው የመጠቀው ፤ በአለፈው በኦሮምያ የተፈጸመውን አሁን ደግሞ በሌሎች ኢትዮጵያዊያ ላይ እውቀትን ባገላገነዘበ መልኩ በቀላሉ ሊያገኝት የሚችሉትን እውቀት እንዳያገኙ እያደረጋቸው ነው ፤ መጨረሻ ተጎጂው ያንን በጎሳ አጥር ውስት የሚወሽቁት ህብረተሰብ ነው፤ ኢትዮጵያ ውስጥ እንግሊዘኛ ትምህርቱ ሞቷል ፤ አሁን ደግሞ በአማርኛ ያለውን እውቀት እንዳይካፈ እያደረጉት ነው፤ የሚተኩት ነገር ሳይኖራቸው ያለውን እያጠፉት ነው ፤ አማርኛ የሚማረው ህብረተሰብን ሊጉዱ ቢያስቡም የሚጎዱት የሚያጥሩት ህብረተሰብን ነው ፡፡ እኔ በቁቤም አስተማሩም አላስተማሩ ለውጥ ያለው አይመሰለኝም ፤ የደሮውን አውጥተው የሚተክሉት ቋንቋ እውቀትን ለህብረተሰቡ ማምጣት ይችላል ወይ ? አይደለም በአለም አቀፍ ደረጃ አገሬቱ እስካሁን ካከማቸችው እውቀት ይህ ህብረተሰብ መካፈል እንዲችል ማድረግ ይቻላልው ወይ ? የጎሰኛ ፖለቲካ ደንቆሮን ከመፈልፈል አልፎ የሚሰራው ነገር የለም ፡፡
ይህኮ የትም የማይሸሹት ነባር ሃቅ ነው ። በግእዝና አማራኛ የተከማቸው እውቀትና ካልቸር ለመጋራት ፣መጋራትም አለባቸው በግድ ፊደልን ይጠቀማሉ፣ አማርኛም ይማራሉ ። የቀቤና ትልቁ አለም ኢትዮጵያ ነች ። የኢትዮጵያ አለም ቀቤና ወረዳ አይደለም። ኦሮሞ ወይም ሃዲያ መሆን ከፈለጉም ምብታቸው ነው ። የወረሞም የእሃዲያ አለምም ኢትዮጵያ ናት ። ይህን መለወጥ አይቹም ። በካልቸር እድገትም ብናየው ካልቸር የሚያድገውና የሚዘምነው ከሌላ ካልቸር ጋር ባለው ግንኙነትና ቴክኖሎጂ ትራንስፈር ነው ። ካልቸር ቴክኖሎጂ ማለት ነው ። ጉራጌ ዶሮ ወጥ መስራት ካማራ ተማረ ማለት ቴክኖሎጂ ትራንስፈር ነው ። አማራ ከጉራጌ ክትፎ መስራት ተማረ ማለት ቴክኖሎጂ ትራንስፈር ነው ። በቃ የካልቸር እድገት ሃሁ ይህ ነው ። ቀቤናም ካልከው የድንቁርና አጥር መውጣት ሲጀምር ይህን ሃሁ መከተል የግድ ይለዋል ፣እስከዚያ በጭለማው ዘመን ውስጥ በመተራመስ ይቆያል ! ወግ ነው ሲዳሩ ማልቀስ ይባላል፣ የማንም ባለትንሽ እውቀት ህዝቡን አዳራሽ ወስጥ ሰበሰበ ማለት አንድ ጭብጥ ፋይዳ አመጣ ማለት አይደለም! የዘመኑ ማንነት ፕለቲካ ድራማ ነው! ብዙም ዋጋ አልሰጠውም!

Abere
Senior Member
Posts: 10891
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: HORUS!

Post by Abere » 07 Jun 2023, 16:20

ከቀቤና ቀጥሎ በላቲን ወይም በቁቤኛ የሚጽፈው ማን እንደሆነ መገመት ይቻላል። ትግራይ ክፍለ ሀገር በላቲን ፊደል መጻፍ ይከተላል። የትምህርት መገልገያ መጻህፍት ወዘተ ትግራይ ውስጥ ቁቤ ይሆናል። አድርባይነት በምድረ ወያኔ ዘንድ ወግ ባህል ነው። አሁን ቀቤና በላቲን ጻፈ አልጻፈ የእራሱ እራስ ምታት ነው። አማርኛ እንደሆነ የበለጠ እያደገ አህጉራዊ እና አለም አቀፍ ቋንቋ እየሆነ መጥቷል። ቀሽር ፊደል፤ቀሽር ቋንቋ፤ ማንኛውንም ሀሳባዊ ይሁን ቁሳዊ ክስተት ለመግለጽ እና ለማስረዳት ቃላት ይሁን አባባል ወይም ስዋሰው የማይገደው።

አንድ ያሳቀኝ ነገር ግን አለ - የቀቤና ቁቤ ምርጫ በተመለከተ። ማንበብ እና መጻፍ የማይችል ህዝብ ሁሉ ድምፅ በመስጠት ቁቤኛ (ላቲን) ሸጋ ነው ለቀቤና ሲሉ ምኑን እንደት አውቀውት ነው። አጃ ኢብ ነው። ይህም ለሽመልስ አብዲሳ እና ለኦሮሙማ እወደድ ባይ ለመሆን ሲባል ቀቤናን ጭዳ አደረጉት። እራሳቸውን እና ትውልድን ነው የገደሉት - የኋላ ኋላ ወደ ሳባ(ኢትዮጲክ) ፊደል እንመለስ ይሉናል - ዱዳ ሁነው ከጨረሱ በኋል። ያXXXXXX መስሎ እንደ አጥር የተደርዶሮ የተጻፈው ቀቤና ተብየው መጻህፍት ሁሉ አቃጥሉሉኝ ይመጣል። አንድ ወዳጎዳ የሚባል ቤተ ሙከራ ሰምቸ ነበር ደቡብ አካባቢ - መጽሀፍ ማቃጠል ነበር የመጨረሻው እጣ።

ኦሮምኛ ቋንቋ እራሱ በሚያሳዝን ሁኔታ ጠፍቷል።

1ኛ) የወለጋ ኦሮምኛ ከባሌ ወይም ከሀረርጌ፤ ወይም ከአሩሲ ወይም ከሚሴ ወረዳ ከሚነገርው የተለየ ነው ፤ለሌላውም እንድሁ። አሁን የፈጠራ ቋንቋ ለሁሉም በትምህርት ቤት ወዘተ ስለሚሰጥ ኦሪጅናል እና የአካባቢው መለያ የሆነው ኦሮምኛ ጠፍቷል

2ኛ) ቁቤ የሚባለው ባለ 100 እግር ፊደል እንኳን ወረቀት መንገድ አይበቃውም። አንብቦ ለመረዳት ለብዙዎች አስቸግሯል።

3ኛ) የኦሮሙማ የግድ ቋንቋየን ተማሩ ተጽኖ በመጥላት ሌሎች የቋንቋው ተናጋሪዎች አይደለም መማር መስማት አይፈልጉም።

euroland
Member+
Posts: 7818
Joined: 08 Jun 2018, 12:42

Re: HORUS!

Post by euroland » 07 Jun 2023, 17:41

Aganeunity
It is your beloved Weyane who are the cause of all these evil in Ethiopia. Agames like are always trying to blame Shaebia; however, Ethiopians were not born yesterday; they know you agames are the main culprit of the evilness we see in Ethiopia today.

ethiopianunity wrote:
07 Jun 2023, 09:19
What is the Effn going on? I think the Shabia influence of pp government is changing Ethiopia to Italian colony!! These a holes! That is it they are destroying this country, meaning OLF latin language is spreading all over the South. Either say you are colonized or not!!! Tell me what the OLF or Somalia writing Latin did to them? Go to Somalia, nothing! somalia is as backward today as it was before! This is saying goodbye to the Ethiopoian culutre, language, faith. Look at these, majority are muslims too, this is a sign of rejecting Orthodox, Ethiopia. The Oromuma will not stop here especially the radical Protestand and Muslim

ethiopianunity
Member+
Posts: 9075
Joined: 30 Apr 2007, 17:38

Re: HORUS!

Post by ethiopianunity » 08 Jun 2023, 00:54

Horus,

I doubt they are trying to turn Latin in Amara or Tigray. You don't get it it, the Oromumua through Liberation Fronts had agreed I think to separate the Northern (Tigray, Amara) vs Oromiya, South). They are trying to create two different nations, probably Afar maybe taken over by Oromiya Kube writing as they already embraced it with Oromiya under Tplf. If Affar is not part of Geez, I don't know what will. The other issue is also separating the Muslims from Christians seems the goal. The south part is showing heavy Islam influence domination is indication of that. Where would Protestant be? Mix of Protestant and Islam = are illuminati origin. In Tigray and Eritrea= the leadership had changed to Illuminati since their hay days

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: HORUS!

Post by Horus » 08 Jun 2023, 01:05

ethiopianunity wrote:
08 Jun 2023, 00:54

አንተ እብድ ትግሬ ምነው ትንሽ አደብ ብትገዛና በተነሱ ነገሮች ላይ ቀንክን ብታባክን? ደቡብ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አለ፣ ፕሮቴስታንት አለ። ሙስሊም አለ! በቃ ስርዓት ያዝ ! ያንተ ሌቦች 27 አመት ሰርቀው አብቅተዋል! አሁን ያንተ ወጥ እያረረ ነው! ያን ብታቁላላ ነው የሚሻለው ! ደቡብን ለደቡብ ተው!

Selam/
Senior Member
Posts: 11549
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: HORUS!

Post by Selam/ » 08 Jun 2023, 23:02

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: HORUS!

Post by Horus » 09 Jun 2023, 01:06

ሰላም፣
በእኔ እምነት ቀቤናዎች እራሳቸው ከትንሽ ግዜ መባከን በኋላ እርግፍ አድረገው ይተዉታል ። አሁን ቁቤ ቁቤ የሚሉት ከወረሞ ጋር ያስጠጋናል፣ እስታተስ ይሰጠናል የሚል ማንነት ቁፋሮ እንጂ ላቲን ከትምህርትም ፣ ከእውቀትም ጋር የተያያዘ አይደለም ። ቀቤና በፊደል ጻፈም በላቲን ለጉራጌ የሚፈይደው ነገር የለም ። ሰባት ቤት ጉራጌኛ 100% በሚባል ደረጃ ግእዝ ፊደል ተቀርጾለት በስነ ጽሁፍ እያበበ ያለ ቋንቋ ነው ። ጉራጌ ባስቸኳይ ማድረግ ያለበት ህጻናት ባ5ና 6 አመታቸው የጉራጌኛ ፊደል ገበታ ማስቆጠርና ከአማራኛ እኩል እንዲጽፉት ማስተማር ነው ። በዚህ ወደ ኋላ ቀርተናል ። ከዚያ ባለፈ ቀቢያ የተባለ ጎሳ የጉራጌ፣ ከምባታ፣ ሲዳማና ኦሮሞ ድብልቅ ጎሳ በጉራጌ ብሄር እድገት ላይ ይህ ነው የሚባል ልወጥ አያማጣም። ጉራጌ ክልል ከሆነ ቀቤና ልዩ ዞን ነው የሚሆነው በቃ ።

Selam/
Senior Member
Posts: 11549
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: HORUS!

Post by Selam/ » 09 Jun 2023, 07:44

ሆረስ
አንድ ከደቡብ ኢትዮጵያ የመጣ የቆየ ዘመድ የዛሬ ሶስት አመት አምቦ ከተማ አግኝቼ ነበር። ድሮ ሁሉም ዘመዳሞች የምንግባባው በአማርኛ ነበር፣ የእያንዳንዱ ሰው የየራሱ ቋንቋ እንደጠበቀ ሆኖ። በኋላ ግን ላቲን የሚባል ነገር ገብቶባቸው ፣ ልጆቹ አንድም አማርኛ አይሰሙም፣ አያነቡም፣ አይናገሩም። እናም በጣት ቋንቋ ብቻ ተጠቋቁመን ተለያየን።

ሀይማኖታቸውም ግራ የተጋባ የጴንጤና የሀገረሰብ የሚመስል ጉራማይሌ ሆኗል። እንደምገምተው የአካባቢው ሰው ሁሉ እንደዛ ይመስለኛል። የራስ ቋንቋን ማዳበር መልካም ሆኖ ሳለ፣ ሰዎች በአካባቢያቸው ብቻ እንዲወሰኑ ማድረግ ሃጥያትም ድንቁርናም ነው። በቁቤ ስለፃፉ ኑሯቸውም እውቀታቸውም አሽቆለቆለ እንጂ አንድም አልተሻሻለም። ሰው ሲሰለጥን ሁለት ሶስት ቋንቋ ተምሮ ወዲህ ወዱያ እያለ እንደልቡ ይንቀሳቀሳል። እነዚህ ሰዎች ያተረፉት ነገር ቢኖር፣ እራሳቸውኅ በአካባቢያቸው መወሰናቸውና ሌላውን ባህል ለማወቅ አስተርጓሚ መፊለጋቸው ነው።

ኢትዮጱያ የምትተዳደረው በቡዳ ፖለቲካ ነው።

Horus wrote:
09 Jun 2023, 01:06
ሰላም፣
በእኔ እምነት ቀቤናዎች እራሳቸው ከትንሽ ግዜ መባከን በኋላ እርግፍ አድረገው ይተዉታል ። አሁን ቁቤ ቁቤ የሚሉት ከወረሞ ጋር ያስጠጋናል፣ እስታተስ ይሰጠናል የሚል ማንነት ቁፋሮ እንጂ ላቲን ከትምህርትም ፣ ከእውቀትም ጋር የተያያዘ አይደለም ። ቀቤና በፊደል ጻፈም በላቲን ለጉራጌ የሚፈይደው ነገር የለም ። ሰባት ቤት ጉራጌኛ 100% በሚባል ደረጃ ግእዝ ፊደል ተቀርጾለት በስነ ጽሁፍ እያበበ ያለ ቋንቋ ነው ። ጉራጌ ባስቸኳይ ማድረግ ያለበት ህጻናት ባ5ና 6 አመታቸው የጉራጌኛ ፊደል ገበታ ማስቆጠርና ከአማራኛ እኩል እንዲጽፉት ማስተማር ነው ። በዚህ ወደ ኋላ ቀርተናል ። ከዚያ ባለፈ ቀቢያ የተባለ ጎሳ የጉራጌ፣ ከምባታ፣ ሲዳማና ኦሮሞ ድብልቅ ጎሳ በጉራጌ ብሄር እድገት ላይ ይህ ነው የሚባል ልወጥ አያማጣም። ጉራጌ ክልል ከሆነ ቀቤና ልዩ ዞን ነው የሚሆነው በቃ ።

Selam/
Senior Member
Posts: 11549
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: HORUS!

Post by Selam/ » 09 Jun 2023, 23:13

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: HORUS!

Post by Horus » 10 Jun 2023, 01:04

Selam,

ዛሬኮ ኢትዮጵያ ውስት የማይታይ ነገር የለም ። በነገራችን ላይ የጉራጌ ጴንጤ ዘፋኞች አንዳንዶቹ አለማዊ ዘፋኞችን ይበልጣሉ በድምጽ! ታ ከላይ ያለው ሌባ ጩፌ አይነት ነው ። ይህቺ ደሞ ቋንቋውንም በደምብ አታውቀም ። 'ክርስቶስ አሺነፈም ' ትላለች?? ቃሉ 'ክርስቶስ ጮኘም ' ብቻ ምን ያረጋል ሁሉም ትርምስ ነው ።

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: HORUS!

Post by Horus » 10 Jun 2023, 01:10

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: HORUS!

Post by Horus » 10 Jun 2023, 01:45

Selam/
Senior Member
Posts: 11549
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: HORUS!

Post by Selam/ » 10 Jun 2023, 08:12

ጴንጤ ዘፋኞች አንዳንዶቹ አለማዊ ዘፋኞችን ይበልጣሉ በድምጽ
:lol: :lol: :lol:

Horus wrote:
10 Jun 2023, 01:04

Post Reply