Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum

DefendTheTruth
Member+
Posts: 9914
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

Re: በኢትዮጵያ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ሙሉ በሙሉ ጠፍተዋል!

Post by DefendTheTruth » 06 Jun 2023, 16:22

በኢትዮጵያ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ሙሉ በሙሉ ጠፍተዋል
I think they deserved it, they are after power, not after any sort of a change (an ideology) or improvement (party program). Over the time they brewed their own misrable downfall, as an example EZEMA, your most favored party.


TGAA
Member+
Posts: 5626
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

Re: በኢትዮጵያ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ሙሉ በሙሉ ጠፍተዋል!

Post by TGAA » 06 Jun 2023, 20:17

Horus wrote:
06 Jun 2023, 13:53
https://www.youtube.com

የዛሬውን የኢዜማ መግለጫ ስሰማ ከአይምሮ ውስጥ የመጣው ኢዜማ ምን ያህል የብርሀኑን ስነልቦና እንደተላበሰ ነው፡፡
ድርጅቱ ክሬዲት ሊወስድባቸው የደረደራችው ምክንያቶች ፤ ኢትዮጵያን ከመፈራረስ አትርፈናል ; ጀርባ አጥንት የሌለው የኦሮሙማ ፈረስ በመሆኔ ኢትዮጵያን አተረፍኩ ብሎ ክሬዲት ለመውሰድ ይሞክራል / ኢትዮጵያን ያተረፈው የኢትዮጵያ ህዝብ ነው ወደፊትም የሚያተርፈው የኢዜማ ወይንም ሌላ የኦሮሙማ አጨብጫቢ የ"ፖለቲካ ድርጅት አይደለም ፤ አሁንም የኢትዮጵያ ህዝብ በአንድ ተነስቶ ይህንን ኦሮሙማ የጥላቻ ፖለቲካ ካላጠፋ የኢትዮጵያ ዘለቄታ አልተረጋገጥም ፡፡
ሌላው የሚገርመው ደግሞ ኢዜማም ጽንፈኞች ከመሀሉ ፍልጎ ማግኝቱ ነው ፤ ከአህያ ጋር የዋለች ግደር ይምትማረው ያው "ፈ"
ሌላው ደግሞ የሚገርው የኢዜማ መግለጫ በኢቢሲና በፋና መስተላለፉ ነው ፤
አብይና ኢዜማ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የተጫወቱት ፖለቲካ በቆራጥ የኢትዮጵያ ልጆች ከተወገዱ በኋላ ኢቲክስ የሌላቸው ፓርቲዎች ምን ያህል ህዝብን ለሶቆቆ እንደሚያበቁ ትልቅ ትምህርት ለሚቀጥለው ትውልድ ማስጠንቀቂዎች ናቸው ፤

አብይ በተሰበሰበ ቁጥር ብርሀኑን ካቢኔት ውስጥ መክተቱን የዲሞክራሲ ምልክት ነው እያለ ይሸቅጥበታል ፤ ብርሀኑ ለአብይ አጨብጭቦ ያለውን የፖለቲካ ፕሪንስፕል በሞላ በስሙኒ ሸጦ አብሮ በአደባባይ መንጎማለሉን ኢትዮጵያን የማዳን ስራ አድርጎ ይፖለትካል ፤ ምን አይነት ዝቅጠት እንደሆነ መለካት እንኳን አይቻልም ፡፡

Horus
Senior Member+
Posts: 30911
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: በኢትዮጵያ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ሙሉ በሙሉ ጠፍተዋል!

Post by Horus » 06 Jun 2023, 21:45

የኢዜማ መግለጫ አልሰማሁትም ። እኔ እድሜዬም ሙሉ ስለ ፖለቲካ ሳስብ የኖርኩ ሰው ነኝ ። ኢዜማ እንደ አማራጭ የፖለቲካ ኮንሴፕት ያበቃለት ድርጅት ነው ። በውን ድርጅት ካለው ያ ሊሆን የሚችለው መንግስታዊ ፓርቲ ማለት የ ፒፒ አጋር ወይም ቅንጅት ፓርቲ ነው ። ከዚህ በኋላ በፍጹም አማራጭ ፓርቲ አይሆንም ።

ከፒፒ ጋራ ተመካክረው ለምርጫ ቀርቦ እንዳሁኑ ከፒፒ ጋር አናሳ ፓርትነር ሆኖ ይኖር ይሆናል! ወረሙማ ከፈቀዱለት ።

የኢዜማ ወሬ በEBC እና FANA ላይ መውጣቱ እጅግ እጅግ አስገራሚና ትክክለኛ ነገር ። እኔ ሰሞኑን በኢዜማ መፍረስ ማነው ይበልጥ የሚጎዳው ብዬ ሳስብ የደረስኩበት መደምደሚያ አቢይ ነው የሚል ነው ።

ኢዜማ መታገል ካቆመና የሕዝብ ድምጽ ፣የሕዝብ ኃይል መሆን ካቆመ ሰንብቷል ። ስለዚህ ከሕዝቡ አሁናዊ ትግል አንጻር ፋይዳ ቢስ ድርጅት ነው ። እንዲያውም ሰው ኢዜማ አለልን ከሚለው ባዶ ተስፋ ነጻ መውጣቱ ትልቅ ጥቅም አለው የኢዜማ መክሸፍ።

በኢዜማ መፍረስ አዝኖ ያለቀሰው ሕዝባዊ ሚዲያው አይደለም ፤ የአቢይ ሚዲያ ነው ። ለምን ቢባል ኢዜማም እንደ ፒፒ መጠላትና መፍረስ በቀጥታ የሚጎዳው አቢይን እንጂ ሕዝቡን አይደለም ! ሕዝቡማ ከኢዜማ ሳንቲም ጥቅም ካጣ ዘመን አለፈው !

አሁን ፒፒና ኢዜማ ግምና ግም አብረህ አዝግም እንደሚባለው ነው ! ላንድ ስራ ሁለት ሰው ከቀጠርክ አንዱን አባርር ይላል የማኔጅመንት ሕግ! ኢዜማ ሟች ፓርቲ ነው! It has no reason for existence.

ኢዜማ የዘመናችን መኢሶን!


sun
Member+
Posts: 9325
Joined: 15 Sep 2013, 16:00

Re: በኢትዮጵያ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ሙሉ በሙሉ ጠፍተዋል!

Post by sun » 06 Jun 2023, 22:08

Horus wrote:
06 Jun 2023, 13:53
ato horear$$

When looking at your vulgar and vagabond power hungry extremist non stop ranting and barking session we Ethiopians feel like vomiting and can only say fackoff from the political stage until you and similar extremist vagabonds can learn the ways of peaceful political activities by competing peacefully after receiving/not receiving popular mandate from the Ethiopian people. Otherwise Go To Hell!




Right
Member
Posts: 2823
Joined: 09 Jan 2022, 13:05

Re: በኢትዮጵያ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ሙሉ በሙሉ ጠፍተዋል!

Post by Right » 06 Jun 2023, 22:57

አሁን ፒፒና ኢዜማ ግምና ግም አብረህ አዝግም እንደሚባለው ነው ! ላንድ ስራ ሁለት ሰው ከቀጠርክ አንዱን አባርር ይላል የማኔጅመንት ሕግ! ኢዜማ ሟች ፓርቲ ነው! It has no reason for existence.
You are a pragmatic person. Why it took you this long to figure out EZEMA is irrelevant at this juncture.
What is important is that you are politically mature enough not to defend the indefensible.
This is the kind of political culture we have to develop.

Horus
Senior Member+
Posts: 30911
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: በኢትዮጵያ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ሙሉ በሙሉ ጠፍተዋል!

Post by Horus » 07 Jun 2023, 01:14

Right wrote:
06 Jun 2023, 22:57
አሁን ፒፒና ኢዜማ ግምና ግም አብረህ አዝግም እንደሚባለው ነው ! ላንድ ስራ ሁለት ሰው ከቀጠርክ አንዱን አባርር ይላል የማኔጅመንት ሕግ! ኢዜማ ሟች ፓርቲ ነው! It has no reason for existence.


You are a pragmatic person. Why it took you this long to figure out EZEMA is irrelevant at this juncture.
What is important is that you are politically mature enough not to defend the indefensible.
This is the kind of political culture we have to develop.


አቶ ራይት፣

እኔ አይደለም ከዘመነ ኢ ህ አ ፓ ጀምሮ የማውቀውን ብርሃኑን ትተህ ትላንት መልኩን ብቻ በምስል ያየሁትን አቢይን የደገፍኩ ሰው ነኝ። የእኔ መለኪያ የኢትዮጵያ ጥቅምና የሰው መብት ነው ። የእነዚህ ሁለት እንቁዎች ተሟጋች ስትሆን እኔ ከሰማይ ውረድ ከምድር ውጣ ደግፌህ እቆማለሁ! ከዚህ ዝንፍ ስትል ታላቅ ወንድሜ ታናሽ እህቴ ልትሆን ትችላለህ፣ ከኔ መጽሃፍ እፍቅሃለሁ! በቃ ሌላ ምንም ሮኬት ፊዚክስ የሚሻ ቲኦሪ የለኝም!

ኢዜማ እንደ አማራጭ ፓርቲ አንድ ቀን በኦሮሙማ የጭለማ አገዛዝ ላይ አይደለም፣ አድማ፣ አይደለም ስራ ማቆም ፣ሰላማዊ ሰልፍ ጠርቶ አያውቅም። ስለዚህ መላ የኢትዮጵያ ሕዝብ በአቢይ ድብቅ የወረሞ ፕላን መታለሉን ተቀብሎ ሲነቃ ኢዜማም አብሮ መንቃት ነበረበት ። ችግሩ ስልጣን አጠገብ የደረሰ ንኡስ ከበርቴ ሁሉ ያቺ የስልጣን፣ የቢሮ የደሞዝ ስሌት ትብታብ ውስጥ ስለሚወድቅ፣ አንተ ሳታውቀው ጉዞ ወደ አድር ባይ አጎብዳጅነት ይሆናል። ይህ የፖለቲካ ሕግ ነው ።

ዛሬ እንኳ ከመሳይ ጋር የተከራከረው የኢዜማ ሰው እጅግ እግጅ መሰረታዊ የፍልፍናና የሶሺያል ቢሄቪየር ስሀተት ሲሰራ ነበር ።

ኢትዮጵያ የምትባል አገር በእውን አለች ወይ ለሚለው መልስ የሰጠው የሕዝቡ ልብ ሳይሆን የራሱ የባለ ቢሮ፣ የባለ ደሞዝ መልስ ነው ። ያ እንደየ ሰዉ ነው አለ። ሰዉ ምን እያለ ነው ሲለው እሱን ለማጥናት እየሞከርን ነው አለ። ይህ እጅግ እጅግ አሳፋሪ ነው ለአንድ መሪ ነኝ፣ ያገር መሪ መሆን እችላለሁ ለሚል የምሁር ስብስብ!

አንድ ኢትዮጵያዊ ኢትዮጵያ በምትባል አገር መኖር ካልቻለ፣ መንቀሳቀስ ካልቻለ፣ ቤት ንብረት መያዝ ካልቻለ ያ የሱ አገር አይደለም! ለዚያ ሰው ኢትዮጵያ የምትባል የሱ የሆነች አገር የለችውም። ይህን መሰል የ3ኛ ክፍል ጽንሰ ሃሳብ በውል ያልገባው ሰው ነው ጮክ ብሎ መሳይ መኮንን የሚያክል ኢንሳይኮሎፒዲያ ጋር ሲነታረክ የነበረው ።

እኔ ሰውን ሁሉ የምለካው፣ የምወደውና የምጠላው በተግባሩ ነው ። ለማንኛውም ኢዜማ ግለሰቦች ፐርሰናል ኢፖለቲካዊ ጥላቻ የለኝም! እኔ ዛሬ ላይ ኢትዮጵያ እንደ ሃምሌ ገደል እየፈረሰች ያለች አገር ነች ። ቢሮና ደሞዝ ለነከሰው ንኡስ ከበርቴ ግ ን ኢትዮጵያ ወደ ብልጽኛ ማማ እየከነፈች ነው! ይህ የመደብ አመለካከት ይባላል። ኢዜማ ከወዲሁ የገዢ መደብ ሜንታሊቲ ውስጥ እየዋኘ ነው፣ ይህ ምናብ ደሞ ከወረሙማ ጋር አብሮ አያስኖረውም ፣ ቢፈልግ እንኳ! ለዚህ ነው የሞተ ፓርቲ ነው ያልኩት!

ፈረንጆች relationship follows behavior ይላሉ ። ይህ ምን ማለት እንደ ሆነ መርምረው ! የኔ መመሪያ ያ ነው !
Last edited by Horus on 07 Jun 2023, 01:43, edited 1 time in total.

kibramlak
Member
Posts: 2155
Joined: 26 Sep 2013, 09:27

Re: በኢትዮጵያ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ሙሉ በሙሉ ጠፍተዋል!

Post by kibramlak » 07 Jun 2023, 01:41

የሆነ ተንታኝ ማን መንግስት የሚባል (ስሙን በትክክል አላስታወኩትም) ያለውን ከሰማህ ታስታውሰው ይሆናል፣ ቂጣችፕውን ቂቤ ተቀብተዋል ያለውን ሰምተኸው ይሆን? ነገሩ እንደዛ ነው፣፣ አብይ በእነ እስክንድር አምርሮ ያበደው አምርረው ስለሚታገሉት ነው፣፣ ሌሎቹ ግን ቂጣቸውን ቂቤ ስለተቀቡ አፋቸውን ዘግተዋል
Horus wrote:
06 Jun 2023, 13:53

Post Reply