Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
TGAA
Member+
Posts: 5598
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ከፍ ሲል ኢትዮጵያዊ ዝቅ ሲል አማራ ነዉ” ኮኔሬል ደመቀ ዘዉዱ

Post by TGAA » 05 Jun 2023, 04:42

የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ከፍ ሲል ኢትዮጵያዊ ዝቅ ሲል አማራ ነዉ” ኮኔሬል ደመቀ ዘዉዱ

በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ሁመራ እና ማይካድራ ከተሞች ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዷል። ሰልፈኞቹ የወልቃይት እና የራያ አማራ ማንነት ጥያቄን የርእስት ማስመለስ ስም በመስጠት ወደ ኋላ መመለስ አይቻልም፣ ሀገር ርእስት ነዉ፣ ለርእስት መሞት ደግሞ ክብር ነዉ ብለዋል። በበጀት ክልከላ የሚጣል ማንነት፣ በፈተና ብዛት የሚዝል አማራነት የለም ሲሉም አስገንዝበዋል።

የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አዲሱ ማለፊያዉ ለሰልፈኞቹ ባስተላለፉት መልእክት የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ሕዝብ አሁናዊ ኹኔታዉ ፈተና ያለበት መኾኑን ተናግረዋል። በተለይም ለረጂም ጊዜ የማንነት ጥያቄው መልስ ያልተሰጠው፣ በጀት እስካሁን ያልተለቀቀለት እንዲሁም በአካባቢዉ የፍትሕ ሥርዓት ያልተዘረጋለት መኾኑን አንስተዋል። እነዚህን መሰል ችግሮች እንዲፈቱም ጠይቀዋል። በሰልፉ ተገኝተዉ ንግግር ያደረጉት የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ምክትል አሥተዳዳሪ እና የሰላም እና ጸጥታ መምሪያ ኃላፊ ኮሎኔል ደመቀ ዘዉዱ የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ከፍ ሲል ኢትዮጵያዊ ዝቅ ሲል አማራ ነዉ፤ የሕዝቡ የወሰን እና የማንነት ጥያቄም በተገቢዉ መልኩ ምላሽ ሊሰጠው ይገባል ብለዋል።

የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ሕዝብ ጥያቄ በዋለ ባደረ ቁጥር ለሐሰት ፕሮፖጋንዳ፣ ለኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች እና ዓለም አቀፍ ተቋማት አድሏዊ ፍርድ እየተጋለጠ መሆኑንም አንስተዋል። እንደ ኢትዮጵያዊነታችን በጀት፣ እንደ አማራነታችን ደግሞ ማንነታዊ እውቅና እንዲሰጥ በዚህ ሰልፍ እጠይቃለሁ ብለዋል። በሰልፉ የከተማዋ ነዋሪዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና የከተማ አሥተዳደሮች እንዲሁም የዞን የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል