Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Educator
Member
Posts: 2004
Joined: 03 Jun 2021, 00:14

አርሶ አደሮች የቲማቲም ማሳቸውን ወደ በጋ ስንዴ እንዲቀይሩ መገደዳቸውን ተናገሩ

Post by Educator » 03 Jun 2023, 12:34

የቲማቲም ገበያ
ቢዝነስዜና
አርሶ አደሮች የቲማቲም ማሳቸውን ወደ በጋ ስንዴ እንዲቀይሩ መገደዳቸውን ተናገሩ
ሔለን ተስፋዬ

ሔለን ተስፋዬ
May 31, 2023
‹‹የአመለካከት ችግር ተፈጥሮ ካልሆነ በስተቀር ስንዴ በሌሎች ምርቶች ላይ ተፅዕኖ አላሳደረም››
የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን ዱግዳ ወረዳ አርሶ አደሮች፣ የቲማቲምና የአትክልት ማሳቸውን ወደ በጋ መስኖ ስንዴ እንዲቀይሩ መገደዳቸውን ተናገሩ፡፡

ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ አንድ አርሶ አደር ለሪፖርተር እንደተናገሩት በወረዳው ቲማቲም፣ ሽንኩርትና ፍራፍሬ ማምረት ተከልክሏል፡፡

በዚህም ሳቢያ የአትክልትና ፍራፍሬ አቅርቦት ችግር በመኖሩ የዋጋ መናር መከሰቱን ገልጸው፣ በቅርቡ የቲማቲም ዋጋ ጣሪያ የነካው ያልተጠበቀ ዝናብ እንዳለ ሆኖ የበጋ ስንዴ መዝራት ግዴታ መሆኑ አንዱ ምክንያት ነው ብለዋል፡፡

በዱግዳ ወረዳ መቂ ዙሪያ አትክልትና ፍራፍሬ ማምረት ተከልክሎ እንደነበር የገለጹት አርሶ አደሩ፣ ተክለው የተገኙትም እንደተነቀለባቸውና የታሰሩም ጭምር መኖራቸውን ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

በወረዳውና በአካባቢው ስንዴ መዝራት ግዴታ መሆኑን፣ ከተቆጣጣሪዎች ተደብቀው ቲማቲም የተከሉም ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ ምክንያት እንደወደመባቸው ገልጸዋል፡፡

በዚሁ ወረዳ ከተቆጣጣሪዎች ተደብቆ ተዘርቶ የነበረው ማሳ ከ40 እስከ 60 ሔክታር የሚገመት እንደነበር፣ የቲማቲም ምርቱ በረዶ በቀላቀለ ዝናብና በጎርፍ ሳቢያ ከጥቅም ውጪ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የወረዳው አርሶ አደሮች የበጋ መስኖ ስንዴ መዝራት ግዴታ በመሆኑ የቃሪያ፣ የቲማቲም፣ የሽንኩርትና የሌሎች አትክልቶች ዋጋ መወደዱ ከዚህ ጋር ያያይዙታል፡፡

እንደ አርሶ አደሮቹ ገለጻ፣ በወረዳው ለስንዴና ለሌሎች ምርቶች እኩል ትኩረት ቢሰጣቸው የዋጋ መናሩ አይከሰትም ነበር፡፡

አሥራ ስምንት ሔክታር የበጋ መስኖ ስንዴ መዝራታቸውን የጠቆሙት ሌላኛው አርሶ አደር፣ ከፍላጎታቸው ውጪ ወደ ስንዴ ምርት መግባታቸውን ገልጸዋል፡፡

ሌላኛው የቲማቲም ዋጋ መናር ምክንያት ብለው ያስረዱት፣ ከዚህ ቀደም 0.50 ሳንቲም ሲሸጥ የነበረው የቲማቲም ችግኝ ወደ ስምንት ብር ከፍ በማለቱ ነው ይላሉ፡፡

የቃሪያ ችግኝም አንድ ብር ሲሸጥ የነበረው አሥር ብርና ከዚያ በላይ በመጨመሩ ለዋጋ መወደድ ምክንያት መሆኑን ያስረዳሉ፡፡

እንደ ችግር ያነሱት ከዓመት በፊት ከአንድ እስከ ሁለት ሺሕ ብር ሲሸጥ የነበረው ኬሚካል አሁን ግን 4,000 እና 5,000 ብር በመሆኑ፣ ገበያ ለሚወጡ ምርቶች መወደድ ምክንያት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አንድ ሔክታር መሬት በሰብል ለመሸፈን ከዚህ ቀደም እስከ 200 ሺሕ ብር እንደሚያስፈልግ፣ አሁን ግን እስከ 600 ሺሕ ብር ለግብዓት ብቻ እንደሚያወጡ ተናግረዋል፡፡

የዱግዳ ወረዳ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ገመቹ ኮራጂ፣ በወረዳው በ2015 ዓ.ም. 25,771 ሔክታር መሬት በዘር መሸፈኑን፣ ከዚያ ውስጥ 25,721 ሔክታር የበጋ መስኖ ስንዴ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

በወረዳው ቲማቲምና ሽንኩርት፣ ሌሎች የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች ከሚያመርቱ አርሶ አደሮች ጋር ውይይት ተደርጎ የበጋ ስንዴ መዘራቱን አስረድተዋል፡፡

ስንዴው ከተሰበሰበ በኋላ ወዲያው የአትክልትና ፍራፍሬ ምርት ወደ ማምረት እንደሚገቡ ገልጸው፣ ምንም ዓይነት ችግር ሳይገጥማቸው እየሠሩ መሆኑን አቶ ገመቹ ተናግረዋል፡፡

ምናልባት ሊገጥም የሚችለው የምርት እጥረት መሆኑን ጠቁመው፣ አሁን ግን የስንዴ ምርት ተሰብስቦ ወደ አትክልትና ፍራፍሬ ምርት መዞሩን አክለዋል፡፡

የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ በሪሶ ፋይሳ ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ በ2015 ዓ.ም. የበጋ መስኖ ስንዴ በአንድ ሚሊዮን ሔክታር መሬት ላይ ለማልማት ታቅዶ ነበር፡፡

በዚህም 38 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ለመሰብሰብ ታቅዶ ወደ ሥራ መገባቱን የገለጹት አቶ በሪሶ፣ 1.1 ሚሊዮን ሔክታር መሬት በዘር ተሸፍኖ እስካሁን 34 ሚሊዮን ኩንታል ያህል መሰብሰቡን ተናግረዋል፡፡

በአንዳንድ አካባቢዎች ምርት የሚሰበስብበት ጊዜ ገና መሆኑን፣ ምርቱ በአጠቃላይ ሲሰበሰብ ካለፈው ወቅት በተሻለ ሁኔታ ውጤታማ እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡

በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ሰብሎች የሚሸፈን 7.4 ሚሊዮን ሔክታር መሬት መኖሩን፣ ከዚህ ውስጥ 1.1 ሚሊዮን ሔክታሩን በበጋ መስኖ ስንዴ መሸፈኑንና በበልግ ወቅትም 1.12 ሚሊዮን ሔክታር መሬት በተለያዩ አዝርዕት መሸፈኑን አስረድተዋል፡፡

በቀጣይም የተለያዩ የአስተራረስ ዘዴዎችን በመጠቀምና ምርትን አፈራርቆ በመዝራት፣ 11 ሚሊዮን ሔክታር መሬት በተለያዩ አዝዕርት ለመሸፈን እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡

የክልሉ የግብርና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ የበጋ መስኖ ስንዴ አዋጭነቱ በጥናት ተረጋግጦ፣ ለአገር የውጭ ምንዛሪ ማግኘትን ታሳቢ ተደርጎና መሠረታዊ ነገሮች ከግምት ውስጥ በማስገባት ወደ ሥራ መገባቱን ተናግረዋል፡፡

አርሶ አደሮችንና ባለሙያዎች አምነውበት የገቡበት መሆኑን፣ ወቅቱን ጠብቆ ምርቶችን በማፈራረቅ በመዝራት እንደሚቻል ከስምምነት ተደርሷል ብለዋል፡፡

ገበያን ለማረጋጋትና ያለውን ፍጆታ ለማሟላት እየተሠራ መሆኑን፣ በዚህም ከ500,000 ሔክታር መሬት በላይ ሌሎች ምርቶች መመረታቸውን ገልጸዋል፡፡

የበጋ መስኖ ስንዴ በሌሎች ምርቶች ላይ ተፅዕኖ አላሳደረም የሚሉት ምክትል ኃላፊው፣ ትኩረት ተደርጎ ስንዴ ላይ በመሠራቱ የአመለካከት ችግር ተፈጥሮ ሊሆን እንደሚችሉ አክለዋል፡፡

ከስንዴ ምርት ጋር ተጓዳኝ የሆኑ ምርቶችን ማምረት ያስፈልጋል ያሉት አቶ በሪሶ፣ የሚነሱ ጥያቄዎች በጥናት እየተለዩ ይፈታሉ ብለዋል፡፡ ለ2016 ዓ.ም. የበጋ ስንዴ ለመዝራት እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ ጥናት እየተካሄደ መሆኑን፣ በጥናቱ መሠረት ችግሮች እየተለዩ መፍትሔ ይሰጠዋል ሲሉም አስታውቀዋል፡፡

በማስገደድ ስንዴ ለምን ትዘራላችሁ ለሚለው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት ኃላፊው፣ ‹‹በማስገደድ ሥራ ተሠርቶ ውጤታማ አይኮንም፤›› ብለዋል፡፡ የአትክልትና ፍራፍሬ ዋጋ ለመናሩ የበጋ መስኖ ስንዴ ተፅዕኖ የለውም? ለሚለው ጥያቄ በሰጡት ምላሽም፣ ተፅዕኖ አለው፡፡ የለውም ለማለት በጥናት ማስደገፍ ይገባል፤›› ብለዋል፡፡

በ2016 ምርት ዘመን በክልሉ የታቀደው 2.5 ሚሊዮን ሔክታር መሬት በበጋ መስኖ ስንዴ ለመሸፈንና 50 ሚሊዮን ኩንታል ለማግኘት መታቀዱን አስረድተዋል፡፡

ስንዴአትክልትና ፍራፍሬኦሮሚያ
Previous article
ለውጭ ገበያ ሳይላክ ለቀረ ቡና ላኪዎች ታክስ እስከ ወለዱ እንዲከፍሉ ተወሰነ
Next article
የባንኮች ብድር አሰጣጥ ፍትሐዊና ብዙኃኑን ያማከለ እንዲሆን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አሳሰበ
- Advertisement -
Anbesa Insurance
Previous
Next
በማህበራዊ ሚዲያዎች ይከታተሉን
ከ ተመሳሳይ አምዶች
ቢዝነስ
ሐበሻ ቢራ ባለፈው በጀት ዓመት 310 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ
ምሕረት ሞገስ - May 31, 2023
የአንድ አክሲዮን ሽያጭ ዋጋ 2,900 ብር እንዲሆን ተወስኗል የሐበሻ ቢራ ፋብሪካ አክሲዮን ማኅበር በ2022 በጀት ዓመት 310 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡ የኩባንያውን ዓመታዊ ክዋኔ...
ቢዝነስ
የባንኮች ብድር አሰጣጥ ፍትሐዊና ብዙኃኑን ያማከለ እንዲሆን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አሳሰበ
ዳዊት ታዬ - May 31, 2023
ባንኮች የብድር አገልግሎታቸውን በተቻለ መጠን ፍትሐዊ፣ የብዙኃኑን ተጠቃሚነት ያማከለና በተለይም የአምራች ዘርፉን እንዲደግፍ ለማድረግ በትኩረት መሥራት እንደሚጠበቅባቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምሕረቱ...
ቢዝነስ
ለውጭ ገበያ ሳይላክ ለቀረ ቡና ላኪዎች ታክስ እስከ ወለዱ እንዲከፍሉ ተወሰነ
ኤልያስ ተገኝ - May 31, 2023
ገቢ ሰብሳቢ ተቋማት ቡና ላኪዎች የሚያቀርቧቸውን ሰነዶች መርምረው ወደ ውጭ ሳይላክ የቀረ ቡና መኖሩን ካረጋገጡ፣ ሊከፈል የሚገባውን የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ ገዥው ወይም ላኪው ከእነ...
ዜና
የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ በሽግግር ፍትሕና ተጠያቂነት ላይ ለመነጋገር ኢትዮጵያ ሊመጡ ነው
ሳሙኤል ቦጋለ - May 31, 2023
የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር (አምባሳደር)፣ የሽግግር ፍትሕና ተጠያቂነትን ለማስፈን የሚደረጉ ጥረቶች የደረሱበትን ደረጃ በሚመለከት ለመነጋገር ኢትዮጵያ ሊመጡ ነው፡፡ ከረቡዕ ከዛሬ ግንቦት 23...
ቢዝነስ
መቀሌ በሚገኙ ሦስት የነዳጅ ማደያዎች የድጎማ ሥርዓት ተግባራዊ መሆን ጀመረ
ኤልያስ ተገኝ - May 31, 2023
ከሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት መልስ በትግራይ ክልል ለመጀመርያ ጊዜ በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ የነዳጅ ግብይት ትግበራ በመቀሌ ከተማ በሚገኙ ሦስት የነዳጅ ማደያዎች ላይ ተግባራዊ መሆን እንደጀመረ ታወቀ፡፡ በመላው...
ቢዝነስ
የአዲስ አበባ ከተማ የኤሌክትሪክ አገልግሎት 15 አመራሮችና ሠራተኞች ከሥራ መሰናበታቸው ተገለጸ
ሲሳይ ሳህሉ - May 31, 2023
የአዲስ አበባ ከተማ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብልሹ ድርጊት ውስጥ ተሳትፈው የተገኙ 15 አመራሮችና ሠራተኞችን ከሥራ ማሰናበቱን አስታወቀ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ኤሌክትሪክ አግልግሎት ዋና...
Zemen Bank AdvertisementZemen Bank Advertisement
Previous
Next
አዳዲስ ጽሁፎች
ስፖንሰር የተደረጉ
የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በአዲስ አበባ በድምቀት ተከበረ
ማስታወቂያ - May 31, 2023
የአዛርባጃን ኤምባሲ የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በትላንትናው ዕለት አከበረ። ሰኞ ግንቦት 21 ቀን 2015 ዓም በስካይ ላይት ሆቴል በተከበረው በዚሁ በዓል ላይ በርካታ አምባሳደሮችና ሌሎች...
ክቡር ሚኒስትር
[ክቡር ሚኒስትሩ አምሽተው ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው ‹‹ፈተናዎችን ወደ ዕድል በመቀየር ሕዝባችንን እናሻግራለን›› የሚለውን የቴሌቪዥን ዜና ተመልክተው ለብቻቸው ሲስቁ አገኟቸው]
በጋዜጣዉ ሪፓርተር - May 31, 2023
ስልክ እያወራሽ ነበር እንዴ? ኧረ በጭራሽ... ምነው? ታዲያ ምንድነው ብቻሽን የሚያስቅሽ? አይ... በቴሌቪዥኑ የሚቀርበው ነገር ነዋ። ምንድነው? ድሮ ድሮ ዜና ለመስማት ነበር ቴሌቪዥን የምንከፍተው፡፡ አሁንስ? አሁንማ ቀልዱን ተያይዘውታል... አንተ ግን በደህናህ...
ፖለቲካ
የመንግሥትና የሃይማኖት ልዩነት መርህ በኢትዮጵያ
ዮናስ አማረ - May 31, 2023
እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች የሃይማኖት ተቋማት አዎንታዊ ሚና የጎላ መሆኑ ተደጋግሞ ይወሳል፡፡ ሃይማኖቶች ማኅበረሰቡን በሞራል ከማነፅ ጀምሮ ለአገር ግንባታ ያበረከቱት አስተዋጽኦ የማይተካ ነውም ይባላል፡፡...
ቢዝነስ
ሐበሻ ቢራ ባለፈው በጀት ዓመት 310 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ
ምሕረት ሞገስ - May 31, 2023
የአንድ አክሲዮን ሽያጭ ዋጋ 2,900 ብር እንዲሆን ተወስኗል የሐበሻ ቢራ ፋብሪካ አክሲዮን ማኅበር በ2022 በጀት ዓመት 310 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡ የኩባንያውን ዓመታዊ ክዋኔ...
ቢዝነስ
የባንኮች ብድር አሰጣጥ ፍትሐዊና ብዙኃኑን ያማከለ እንዲሆን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አሳሰበ
ዳዊት ታዬ - May 31, 2023
ባንኮች የብድር አገልግሎታቸውን በተቻለ መጠን ፍትሐዊ፣ የብዙኃኑን ተጠቃሚነት ያማከለና በተለይም የአምራች ዘርፉን እንዲደግፍ ለማድረግ በትኩረት መሥራት እንደሚጠበቅባቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምሕረቱ...
ታክሲ
የነፃነት ዋጋ እንዴት ይተመናል?
በጋዜጣዉ ሪፓርተር - May 31, 2023
የዛሬው ጉዞ ከሳሪስ አቦ ወደ ቃሊቲ መናኽሪያ ነው። የሰው ልጅ ለኑሮ የሚያደርገው እንቅስቃሴ ጎዳናውን ሕይወት ዘርቶበታል። እንደ ወትሮው የኑሮ ንረት እያፍገመገመን እዚህ ደርሰናል። ‘ኑሮ...
በማህበራዊ ሚዲያዎች ይከታተሉን
Anbesa International BankOromia Bank Advertisement on Reporter Amharic-728x89-min
PHONE NO : - +251-116-616-184 / 85

E-MAIL : - [email protected]

© COPYRIGHT - MEDIA AND COMMUNICATIONS CENTER