Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 10890
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

የአማራ ህዝባዊ ግንባር (አህግ)ዝግጅቱን አጠናቆ የሳቴላይት ቴሊቭዥን ስርጭት በአገር ውስጥ እና አገር ውጭ ሊጀምር ነው። እንኳን ደስ ያላችሁ!

Post by Abere » 03 Jun 2023, 11:12

የአማራ ህዝባዊ ግንባር (አህግ)ዝግጅቱን አጠናቆ የሳቴላይት ቴሊቭዥን ስርጭት በአገር ውስጥ እና አገር ውጭ ሊጀምር ነው። እንኳን ደስ ያላችሁ! መረጃ ኃይል ነው። ኃይል የሚሆነው መረጃው እውነት ሲሆን ብቻ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ግን በእራሱ የግብር ገቢ ብልጽግና ኦሮሙማ የተቆጣጠረው ETV/EBC/ ውሸት እና ቅጥፈት ሲነዛበት ኑሯል። በርካታ ውሸቶች ተነገረውበታል - ለምሳሌ መከላከያ ከትግራይ ተሸንፎ ሲወጣ ትግራይ ውስጥ አንዳችም መሣርያ ጥሎ እንዳልወጣ፤ ወያኔም ከእጇ ላይ ምንም እንዳልቀራት፤ ወዘተ። ወለጋ ላይ የኦሮሞ ልዩ ሃይል አማራን እየገደለ ሸኔ ነው በማለት ሸኔንም በ1 ሳምንት እንደደመሰሳቸው ወዘተ፡ ቅጥፈት። ሰሞኑ አማራ ክልል በመቶዎች ያለቀው የኦሮሞ መከላካያ (ኦነግ) ሆስፒታል ሲያጨናንቅ ወይም በየመንገዱ ሲደመሰስ ግን ትንፍሽ አይባልም። በምትኩ የተሳሳተ እና ህዝብን ለማጭበርበር የሀሰት እና የድራማ ቪድዮ ወይም መረጃ ይለቀቃል። ይህ ሁሉ ግን የሚተወነው በህዝብ ግብር በሚተዳደረው የኢትዮጵያ ቲሌቭዥን ተበትየው ነው። የኦሮምያ ቴሊቭዥን እንጅ የኢትዮጵያ አየደለም።

አሁን ህዝብ ውሸቱን እንደ ግርድ እይንጓለለ እውነቱን የሚያውቅበት የአ.ህ.ግ. ሳቴላይት ቴሌቭዝን ሊያገኝ ነው - ይህ ትልቅ ለውጥ እና እድል ነው። በአገር ውስጥ ከትግል ዐውዱ ላይ እውነቱ ይደመጣል-የኦሮሙማ ቅጥፈት ይጋለጣል። በአለም ዙርያ ላሉ ኢትዮጵያዊያንም ከሳንቲም ለቃሚ ተደገፊ ውታፍ ነቃይ ዩቲዩቦች (coin predator YouTubers) እና ለጣጣፊዎች ( like Natnael Mekonnen) የፈጠራ ወሬ ይጠበቃሉ። ሳይማረኩ ማረክን፤ሳይገድሉ ገደልን፤ ወዘተ የፈጠራ እና ምስል ድራማ የሚበትኑት የአብይ አህመድ ተከፋዮች እንጀራቸው ይዘጋል።

ድል ለአማራ ህዝባዊ ግንባር!