Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 11128
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

የአማራ ህዝባዊ ግንባር (አህግ) ድምፅ ሬድዮ በቅርቡ ስርጭት ይጀምራል የሚል ፍንጭ አለ።

Post by Abere » 29 May 2023, 11:28

የአማራ ህዝባዊ ግንባር (አህግ) ድምፅ ሬድዮ በቅርቡ ስርጭት ይጀምራል የሚል ፍንጭ አለ።

ከተሞክሮ እንደምናውቀው አንድ ግንባር ለህዝብ ተደራሽነቱን ለማሳካት የሬድዮ ስርጭት ከፍተኛ ሚና ይጫዎታል። በተለይም አሁን በምንገኝበት ዘመን በርካታ ዩቲዩበሮች የተለያየ ደረጃውን ያልጠበቀ ብቻ ሳይሆን ሆን ተብሎ አሳሳች ወሬዎችን ስለሚያሰራጩ የግንባሩ የእራሱ የሆነ የሬድዮ ስርጭት መኖሩ ህዝብን ከውዥንብር ማዳን ብቻ ሳይሆን ህዝባዊ ቅቡልነትን በማጎለበት ትግሉን እንድሰምር ይረዳዋል። በተለይም የኢትዮጵያ ህዝብ 97% ገበሬ እንድሁም በግምት 0፡5% (ግማሽ ፐርሰንት) ያነሰው ዜጋ የኢንተርኔት ሚዲያ ተጠቃሚ በላመሆኑ ሬድዮ ስርጭት የላቀ ተደራሽነት፤ተአማኒነት ይኖረዋል። የእራሱን ቃል-አቀባይ በመጠቀም በትግል ሜዳው ላይ ስላለው ሁኔታ ለዜጎች ይሁን በዓለም አቀፈ ደረጃ ለተለያዩ መንግስታት፤ሰብዐዊድርጅቶች ይሁን የዜና እውታሮች ተጨባጩን እውነታ ያስረዳል። የአህግ ሬድዮ ስርጭት በቅርብ እንድጀመር የሚደረገው ጥረት የሚበረታታ እና የሚመሰገን ነው። አቶ አብይ አህመድ እና ተከፋይ YouTubers ህዝብን በሰፊው ከማደናገራቸው በፊት ይህ ስርጭት የትክክለኛ መረጃ ምንጭ መሆን ይኖርበታል።