Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Right
Member
Posts: 2732
Joined: 09 Jan 2022, 13:05

Taye Denda’s article about PP corruption and destruction. Report.

Post by Right » 28 May 2023, 18:44

· << የቱለማን መሬት ሽጦ ለሴተኛ አዳሪ ተጫርቶ የከፈለውና ሚሊዮኖችን ቲፕ/ጉርሻ የሰጠው ማነው? >> – በታዬ ደንደአ

· << የቱለማን መሬት ሽጦ ለሴተኛ አዳሪ ተጫርቶ የከፈለውና ሚሊዮኖችን ቲፕ/ጉርሻ የሰጠው ማነው? >> //በታዬ ደንደአ////

ትርጉም: ኢልመ-ቢያ በተለይ ለአዲስ ዘይቤ //

አሸብሽቦ አዳሪው፣ የሌባና የሴረኛ ተላላኪ፣ በቅርቡ በቱለማ መሬት ስም ይፎክር ይዟል። በቱለማ ላይ ስለተፈጸመው ዘረፋ ደጋግሞ አጀንዳ ያደርጋል። መስኪዶችና ሌሎች የእምነት ቤቶች የፈረሱት የቱለማን መሬት ለማዳን እንደሆነ ይናገራል። ይሄንና ይሄንን መሰሉ ነገር የፖለቲካ ቁማር ያሉትን ነገር ይመስላል። በቁማሩ ቱለማን አሲዞ ለማስበላት ይራወጣል። አስቀድሞ የቱለማን መሬት ሽጦ ይበላል፣ አሁን ደግሞ ቱለማን ለመስበላት ያሴራል ። ሌባውና ሴረኛው ቱለማን ከቀዬው የነቀለው ሳያንሰው ወደ ወንድሞቹ የተጠጋውን ሊያስበላ ይጋጋጣል። ይሄ በጭራሽ አይሳካም!

አዎን እውነት ነው! ቱለማ ከመሬቱ መፈናቀሉ ሐቅ ነው። ይህ ወንጀል መቆም ነበረበት። ይሁንና ማነው ቱለማን አፈናቅሎ ለማኝና ተፈናቃይ ያደረገው? ሌላ ኃይል ቢኖርም እንኳ በአብላጫው ቱለማን ከቀዬው ያፈናቀለው ሌባና ሴረኛው ነው። ባለፉት አምስት ዓመታት በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ ከተሞች ውስጥ የሆነውን የማያውቅ የለም። በገበሬ ስም ማነው የአዲስ አበባን መሬት የተቀራመተው? የቱለማን መሬት ሽጦ ለሴተኛ አዳሪ ተጫርቶ የከፈለውና ሚሊዮኖችን ቲፕ/ጉርሻ የሰጠው ማነው? ሌባውና ሴረኛው ነው። ቀን ቀን የቱለማን ድኻ ያስለቅሳሉ፣ ማታ ውስኪ ቤት ይጨፍራሉ። ይቅርታ የማያሰጥ ወንጀል እየፈጸሙ ዛሬ ላይ እራሳቸውን የቱለማ ጠበቃ አድርገው ያቀርባሉ። ቱለማን ጭምብል በማድረግ ከወንጀላቸው ለመደበቅ ይጥራሉ። ይሁንና የሌባና የሴረኛ ተንኮል እራሱን ይበላው ይሆናል እንጂ ወንድማማቾችን አይነጣጥልም።

ቱለማ ለረጅም ዓመታት ተቸግሮ ኖሯል። ሲብስበት ደግሞ ወደ ወንድሞቹ ተሰድዷል። ዛሬ ላይ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የቱለማ ልጆች በአርሲ፣ በጅማ፣ በባሌ፣ በሐረርጌ፣ በኢሉ እና በመሳሰሉት ይኖራሉ። በወንድሞቹ ቤት የሚፈጠር ችግርም መከራንም አብሮ ይካፈላል። በሚኖርበት ሁሉ ከሙስሊም ወንድሞቹ ጋር በፍቅርና በመከባበር ይኖራል። አሸብሽቦ አደሩ ግን ቱለማን ከሙስሊም ወንድሞቹ ጋር ሊያጣላ ይጋጋጣል። እስኪ “ለቱለማ ብለን ነው መስኪዶችን ያፈረስነው” ማለት ምን ማለት ነው? የመስኪዶችን መፍረስ የቱለማን መሬት በማገናኘት የህዝብን አንድነት ለማፍረስ ያለመ ነው። ኦሮሞን በመነጣጠል፣ ለየብቻው ለመሰልቀጥ የተሸረበ ሴራ ነው። በተለይ ደግሞ በቱለማ ልጆች ኪሳራ ሌቦችና ሴረኞች የፈጸሙትን ወንጀል መከለል ነው የተፈለገው። የቱለማ መሬት ስላላጠረቃው ቱለማን ለመብላት አንሰፍስፏል። ይህም እንጂ አይሳካም! ይሄ በመጀመሪያ ሙከራ ነው የከሸፈው።

ህግን ማክበርና ማስከበር ተገቢ ነው። የእምነት ሥፍራዎችን ጨምሮ ሁሉንም መገንባቱ በሥርዐትና በቅደም ተከተል መከናወን ይገባዋል። ነገር ግን ስርዓት ማስከበር በጠዋቱ ነው። ህገወጥ ግንባታን መከልከል ገንዘብ እና ጉልበት ሳይባክን በፊት ነበር። የእራሳቸውን መሬት ሽጠው፣ ቤት ሲሰራ ዝም ብለው፣ እራሳቸው መብራትና ውኃ ሲያስገቡ ከርመው ከፍተኛ የሀገር ኃብት መሬት ላይ ከፈሰሰ በኋላ በህግ ስም በድኾችን ቤቶችን፣ የእምነት ተቋማትን ማፍረስ ትርጉም አይሰጥም።

ስለሆነም የድኾች ቤቶችን እና የእምነት ተቋማት ማፍረሱ ቱለማን አይመለከተውም። ይሄንን አጀንዳ ከቱለማ ላይ አውርዱ። ሲጠቃለል የጉዳዩ ባለቤቶች በአምቻና በጋብቻ እንዲሁም በሚዜነት ስም የተደራጁት ሰዎች ይሆናል።

እኛ ሰላምን እንሻለን! እግዚአብሔር ሰላምን ይስጠን!

————————————————————————-

የአሮሚያ ብልፅግና አመራር እና የሰላም ሚኒስትር ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት አቶ ታየ ደንድአ በፌስቡክ ገፃቸው ያሰፈሩት ፅሁፍ ነው።

Right
Member
Posts: 2732
Joined: 09 Jan 2022, 13:05

Re: Taye Denda’s article about PP corruption and destruction. Report.

Post by Right » 28 May 2023, 22:52

It is about Taye Denda and what he said about his government.
Nobody cares about TPLF vs EPLF. Better, for you two to solve your problems on the battlefield.
TPLF is boasting about capturing Asmara and Issias in the near future.

sun
Member+
Posts: 9313
Joined: 15 Sep 2013, 16:00

Re: Taye Denda’s article about PP corruption and destruction. Report.

Post by sun » 28 May 2023, 23:17

Right wrote:
28 May 2023, 18:44
· << የቱለማን መሬት ሽጦ ለሴተኛ አዳሪ ተጫርቶ የከፈለውና ሚሊዮኖችን ቲፕ/ጉርሻ የሰጠው ማነው? >> – በታዬ ደንደአ

· << የቱለማን መሬት ሽጦ ለሴተኛ አዳሪ ተጫርቶ የከፈለውና ሚሊዮኖችን ቲፕ/ጉርሻ የሰጠው ማነው? >> //በታዬ ደንደአ////

ትርጉም: ኢልመ-ቢያ በተለይ ለአዲስ ዘይቤ //

አሸብሽቦ አዳሪው፣ የሌባና የሴረኛ ተላላኪ፣ በቅርቡ በቱለማ መሬት ስም ይፎክር ይዟል። በቱለማ ላይ ስለተፈጸመው ዘረፋ ደጋግሞ አጀንዳ ያደርጋል። መስኪዶችና ሌሎች የእምነት ቤቶች የፈረሱት የቱለማን መሬት ለማዳን እንደሆነ ይናገራል። ይሄንና ይሄንን መሰሉ ነገር የፖለቲካ ቁማር ያሉትን ነገር ይመስላል። በቁማሩ ቱለማን አሲዞ ለማስበላት ይራወጣል። አስቀድሞ የቱለማን መሬት ሽጦ ይበላል፣ አሁን ደግሞ ቱለማን ለመስበላት ያሴራል ። ሌባውና ሴረኛው ቱለማን ከቀዬው የነቀለው ሳያንሰው ወደ ወንድሞቹ የተጠጋውን ሊያስበላ ይጋጋጣል። ይሄ በጭራሽ አይሳካም!

አዎን እውነት ነው! ቱለማ ከመሬቱ መፈናቀሉ ሐቅ ነው። ይህ ወንጀል መቆም ነበረበት። ይሁንና ማነው ቱለማን አፈናቅሎ ለማኝና ተፈናቃይ ያደረገው? ሌላ ኃይል ቢኖርም እንኳ በአብላጫው ቱለማን ከቀዬው ያፈናቀለው ሌባና ሴረኛው ነው። ባለፉት አምስት ዓመታት በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ ከተሞች ውስጥ የሆነውን የማያውቅ የለም። በገበሬ ስም ማነው የአዲስ አበባን መሬት የተቀራመተው? የቱለማን መሬት ሽጦ ለሴተኛ አዳሪ ተጫርቶ የከፈለውና ሚሊዮኖችን ቲፕ/ጉርሻ የሰጠው ማነው? ሌባውና ሴረኛው ነው። ቀን ቀን የቱለማን ድኻ ያስለቅሳሉ፣ ማታ ውስኪ ቤት ይጨፍራሉ። ይቅርታ የማያሰጥ ወንጀል እየፈጸሙ ዛሬ ላይ እራሳቸውን የቱለማ ጠበቃ አድርገው ያቀርባሉ። ቱለማን ጭምብል በማድረግ ከወንጀላቸው ለመደበቅ ይጥራሉ። ይሁንና የሌባና የሴረኛ ተንኮል እራሱን ይበላው ይሆናል እንጂ ወንድማማቾችን አይነጣጥልም።

ቱለማ ለረጅም ዓመታት ተቸግሮ ኖሯል። ሲብስበት ደግሞ ወደ ወንድሞቹ ተሰድዷል። ዛሬ ላይ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የቱለማ ልጆች በአርሲ፣ በጅማ፣ በባሌ፣ በሐረርጌ፣ በኢሉ እና በመሳሰሉት ይኖራሉ። በወንድሞቹ ቤት የሚፈጠር ችግርም መከራንም አብሮ ይካፈላል። በሚኖርበት ሁሉ ከሙስሊም ወንድሞቹ ጋር በፍቅርና በመከባበር ይኖራል። አሸብሽቦ አደሩ ግን ቱለማን ከሙስሊም ወንድሞቹ ጋር ሊያጣላ ይጋጋጣል። እስኪ “ለቱለማ ብለን ነው መስኪዶችን ያፈረስነው” ማለት ምን ማለት ነው? የመስኪዶችን መፍረስ የቱለማን መሬት በማገናኘት የህዝብን አንድነት ለማፍረስ ያለመ ነው። ኦሮሞን በመነጣጠል፣ ለየብቻው ለመሰልቀጥ የተሸረበ ሴራ ነው። በተለይ ደግሞ በቱለማ ልጆች ኪሳራ ሌቦችና ሴረኞች የፈጸሙትን ወንጀል መከለል ነው የተፈለገው። የቱለማ መሬት ስላላጠረቃው ቱለማን ለመብላት አንሰፍስፏል። ይህም እንጂ አይሳካም! ይሄ በመጀመሪያ ሙከራ ነው የከሸፈው።

ህግን ማክበርና ማስከበር ተገቢ ነው። የእምነት ሥፍራዎችን ጨምሮ ሁሉንም መገንባቱ በሥርዐትና በቅደም ተከተል መከናወን ይገባዋል። ነገር ግን ስርዓት ማስከበር በጠዋቱ ነው። ህገወጥ ግንባታን መከልከል ገንዘብ እና ጉልበት ሳይባክን በፊት ነበር። የእራሳቸውን መሬት ሽጠው፣ ቤት ሲሰራ ዝም ብለው፣ እራሳቸው መብራትና ውኃ ሲያስገቡ ከርመው ከፍተኛ የሀገር ኃብት መሬት ላይ ከፈሰሰ በኋላ በህግ ስም በድኾችን ቤቶችን፣ የእምነት ተቋማትን ማፍረስ ትርጉም አይሰጥም።

ስለሆነም የድኾች ቤቶችን እና የእምነት ተቋማት ማፍረሱ ቱለማን አይመለከተውም። ይሄንን አጀንዳ ከቱለማ ላይ አውርዱ። ሲጠቃለል የጉዳዩ ባለቤቶች በአምቻና በጋብቻ እንዲሁም በሚዜነት ስም የተደራጁት ሰዎች ይሆናል።

እኛ ሰላምን እንሻለን! እግዚአብሔር ሰላምን ይስጠን!

————————————————————————-

የአሮሚያ ብልፅግና አመራር እና የሰላም ሚኒስትር ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት አቶ ታየ ደንድአ በፌስቡክ ገፃቸው ያሰፈሩት ፅሁፍ ነው።
Taye is becoming a pathological divisive barking Dog just like you. He seems to love himself above all else. He might have been wanting the position of the PM. When he couldn't get it he seems to have been wanting the position of Oromiyya region presidency but again couldn't get that probably for lack of trust from others. Now then, he seems to be conducting his clandestine attacks by other means from the side. It seem that it is all about him, him alone! Nothing else! Very funny character! :lol:

Noble Amhara
Senior Member
Posts: 11627
Joined: 02 Feb 2020, 13:00
Location: Abysinnia Highlands

Re: Taye Denda’s article about PP corruption and destruction. Report.

Post by Noble Amhara » 28 May 2023, 23:47

Can taye denda even travel to his home village safely? :roll: :roll:

Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: Taye Denda’s article about PP corruption and destruction. Report.

Post by Meleket » 29 May 2023, 10:14

በዚህ ግልጽና ቁምነገረኛ ምልከታቸው ምክንያት፡ ምንም እንኳ የጐረቤት ሃገር ባለሥልጣን ቢሆኑም፡ ለአቶ ታዬ ደንድኣ ኣክብሮታችንን እንሰጣለን፡ እኛ ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር! :mrgreen:
Right wrote:
28 May 2023, 18:44
. . . ቤት ሲሰራ ዝም ብለው፣ እራሳቸው መብራትና ውኃ ሲያስገቡ ከርመው ከፍተኛ የሀገር ኃብት መሬት ላይ ከፈሰሰ በኋላ በህግ ስም በድኾችን ቤቶችን፣ የእምነት ተቋማትን ማፍረስ ትርጉም አይሰጥም።

Post Reply