Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

"አንድነት ኃይሉን ፍለጋ" | ኢትዮጵያዊው ብሔርተኛ በጎሳ ፖለቲካ አራማጆች h3ኛ ጊዜ እንደተሸነፈ መቀበል አለብን። ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ (አደባባይ ሚድያ)

Post by sarcasm » 27 May 2023, 07:14

"አንድነት ኃይሉን ፍለጋ" .....
++++
ኢትዮጵያዊው ብሔርተኛ በጎሳ ፖለቲካ አራማጆች h3ኛ ጊዜ እንደተሸነፈ መቀበል አለብን

1ኛ. በግንቦት 20/1983 ዓ.ም= በማታለልና በጉልበት፤

2ኛ. በ1997 ዓ.ም ምርጫ= በጉልበት፤

3ኛ. በ2015 ዓ.ም ወያኔ የቀሰቀሰው ጦርነት ባለቀ ማግሥት= አሁንስ በምን? በጉልበት? በብልጠት? በማታለል?
** ሲጠቃለል፦

1. ጠ/ሚ ዐቢይ እና ብልጽግና የጎሳ ፖለቲካን ይከላከላሉ ብለን ያለምነው ሕልም መክኗል።

2. ሕወሓት ታጥባ፣ ታጥና፣ ተከሽና መጥታለች። የግብር ልጆቿም የበላይነት አግኝተዋል።

3. ከኢዜማና ከቀሩት ፓርቲዎች ጠብ የሚል ነገር የለም።

4. የኦሮሞ አክራሪዎች የጀመሩት እነርሱን የምትመስል ኢትዮዽያ መፍጠር ካልሆነም የራሳቸውን መንግሥት ይዞ መውጣት ነው::

5. የሕዝቡ ሰቆቃስ እንዴት ሊያበቃ ይችላል?

(ከMarch 25/2023 የግል ማስታወሻዬ)
sarcasm wrote:
24 Oct 2022, 20:27


The Neguse Negest system is an organic federalist system devised by Ancient Tigrayans in Axum. The core foundations of the system are respect for autonomy, self-rule and differences. Hence, the Abyssinia / Ethiopian Empire has always been a federalist arrangement.

The Neguse Negest system is a federalist system where the Neguses have autonomy on their territories and pay taxes to the Neguse Negest (federal government). The Neguse Negest looks after common defense and international relations. Actually, it looks like it was HSI who ended the federalist system when he fired the Neguses but still kept the Neguse Negest title. He introduced a centralized state system into a country that has always been a federalist structure. Mengistu continued the madness of unitary state which resulted in Eritrea's independence.

The Isaias, Abiy & Amhara Elite / fake 'Ethiopianist' alliance have plunged the country into another bloody war after 30 years in order to re-install a centralized / unitary state system and end the existing Constitutional Federalism. Tigray has single-handedly defeated the Alliance and forced PM Abiy & his PP to commit to keep Constitutional Federalism.

Please wait, video is loading...
Please wait, video is loading...

sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: "አንድነት ኃይሉን ፍለጋ" | ኢትዮጵያዊው ብሔርተኛ በጎሳ ፖለቲካ አራማጆች h3ኛ ጊዜ እንደተሸነፈ መቀበል አለብን። ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ (አደባባይ ሚድያ)

Post by sarcasm » 04 Jun 2023, 10:42

Eyob Seyoum
የተመጠነ እውነት !!!

Mintewab Bezabih
ye Ethiopianistu camp opportunist mehonm astewatso adrgoal. Akuam yelesh mehon, gifin ayto endalaye malef, yemola simeslachew atinageru malet (sile mircha, sile tornet), be achberbariwoch memerat. Ehe hulu yemanim tifat aydelem.

sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: "አንድነት ኃይሉን ፍለጋ" | ኢትዮጵያዊው ብሔርተኛ በጎሳ ፖለቲካ አራማጆች h3ኛ ጊዜ እንደተሸነፈ መቀበል አለብን። ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ (አደባባይ ሚድያ)

Post by sarcasm » 18 Jun 2023, 10:04

ህብረ-ብሄራዊ አንድነትንና ዘላቂ ሰላምን ለመገንባት የፌደራል ስርዓቱ ቁልፍ መሳሪያ ነው - አፈ-ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ
**********************************
በኢትዮጵያ ህብረ-ብሄራዊ አንድነትንና ዘላቂ ሰላምን ለመገንባት የፌደራል ስርዓቱ ቁልፍ መሳሪያ መሆኑን የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ ገለጹ።


ለትግበራውም በንቃት መሳተፍ እንደሚገባ አፈ-ጉባኤዋ ገልጸዋል።

የአማራ ክልል ምክር ቤት ከፌደራል ሕገ-መንግስት እና ፌዴራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል ጋር በመተባበር በፌዴራሊዝም፣ ህብረ-ብሔራዊ ፌዴራሊዝምና የመንግስታት ግንኙነት ዙሪያ በኮምቦልቻ ከተማ ስልጠና እየሰጠ ነው።
የምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ፋንቱ ተስፋዬ በስልጠናው ላይ እንዳሉት ጠንካራና ህብረ-ብሄራዊ ሃገር ለመገንባትና ለማስቀጠል የፌዴራሊዝም ስርዓት የተሻለ አማራጭ ነው።

በስርዓቱ ሁሉም ብሄር ብሄረሰብ በቋንቋው ከመጠቀም ባለፈ ቋንቋና ባህሉን እንዲያሳድግ እድል የፈጠረ በመሆኑ ባለው ጸጋና ሃብት ልክ ብልጽግናን ማረጋገጥ የሚያስችል መሆኑንም አስገንዝበዋል።

በአማራ ክልል የተለያዩ ቋንቋዎችን የሚናገሩ ብሄረሰቦች መኖራቸውን ጠቁመው፤ ብሔረሰቦቹ ራሳቸውን በራሳቸው በማስተዳደርና ባህላቸውን በማሳደግ በኩል የፌዴራሊዝም ስርአቱ ተጠቃሚ እንዳደረጋቸው ገልጸዋል።

ስርዓቱ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በሰለጠነ መንገድ በውይይትና በንግግር በመፍታት በጋራ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትና ዘላቂ ሰላም መጠበቅ የሚያስችል መሆኑንም ተናግረዋል።

እየተሰጠ ያለው ስልጠናም በየደረጃው ያሉ የምክር ቤት አባላትና አመራሮችን በፌዴራሊዝም ስርዓቱ ላይ የጋራ ግንዛቤ ኖሯቸው ኢትዮጵያን እንዲያጸኑ ያለመ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ሀሊማ ይማም በበኩላቸው የፌዴራሊዝም ስርዓቱ በቋንቋቸው ከመጠቀም ባለፈ "ባህልና ወጋችንን በማሳደግ ተጠቃሚ አድርጎናል" ብለዋል።
በክልሉ የሚገኙ ብሄረሰቦች በራሳቸው እንዲተዳደሩ በማድረግ ክልሉ ፌዴራሊዝምን በተግባር ያረጋገጠ መሆኑንም ገልጸዋል።
"የሚገጥሙንን ፈተናዎች ለመሻገር ህብረ ብሄራዊ ፌዴራሊዝምን በተሻለ መተግበር ይገባል" ያሉት ደግሞ በምስራቅ ጎጃም ዞን የሉማሜ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ መልካሙ ጤናው ናቸው።
በኮምቦልቻ ከተማ ለአንድ ቀን በሚሰጠው በዚሁ ስልጠና ላይ የክልል፣ የዞን፣ የወረዳና የከተማ አስተዳደር ምክር ቤቶች አፈ ጉባኤዎች፣ ቋሚ ኮሚቴዎችና ባለድርሻ አካላት በመሳተፍ መሆናቸው አሚኮ ዘግቧል።

Please wait, video is loading...

Sam Ebalalehu
Member
Posts: 3639
Joined: 23 Jun 2018, 21:29

Re: "አንድነት ኃይሉን ፍለጋ" | ኢትዮጵያዊው ብሔርተኛ በጎሳ ፖለቲካ አራማጆች h3ኛ ጊዜ እንደተሸነፈ መቀበል አለብን። ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ (አደባባይ ሚድያ)

Post by Sam Ebalalehu » 18 Jun 2023, 10:52

ገበሬውን በማዳበሪያ መያዣ ይዛችሁ ፣ መሬት አትሸጥም አትለውጥም ብላችሁ ፣ የሚመርጠውን አይደለም የሚበላውን የሚቆጣጠር ካድሪ በላዩ ላይ ጭናችሁ ብሄራዊ ፓርቲ የማሸነፍ እድሉ አለው ብላችሁ መገመታችሁ ያሳፍራል።
Last edited by Sam Ebalalehu on 18 Jun 2023, 10:55, edited 2 times in total.

Sam Ebalalehu
Member
Posts: 3639
Joined: 23 Jun 2018, 21:29

Re: "አንድነት ኃይሉን ፍለጋ" | ኢትዮጵያዊው ብሔርተኛ በጎሳ ፖለቲካ አራማጆች h3ኛ ጊዜ እንደተሸነፈ መቀበል አለብን። ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ (አደባባይ ሚድያ)

Post by Sam Ebalalehu » 18 Jun 2023, 10:52

ገበሬውን በማዳበሪያ መያዣ ይዛችሁ ፣ መሬት አትሸጥም አትለውጥም ብላችሁ ፣ የሚመርጠውን አይደለም የሚበላውን የሚቆጣጠር ካድሪ በላዩ ላይ ጭናችሁ ብሄራዊ ፓርቲ የማሸነፍ እድሉ አለው ብላችሁ መገመታችሁ ያሳፍራል።

sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: "አንድነት ኃይሉን ፍለጋ" | ኢትዮጵያዊው ብሔርተኛ በጎሳ ፖለቲካ አራማጆች h3ኛ ጊዜ እንደተሸነፈ መቀበል አለብን። ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ (አደባባይ ሚድያ)

Post by sarcasm » 21 Jun 2023, 15:47

በውድም በግድም ፣ በእልህም ፣ በትንቅንቅም ... ባሻዬን ከአሃዳዊ ወደ የፌደራሊዝሙ ጠበቃ ተደርጎ እንደ አዲስ ማንነቱ እየተሰራ ነው .. በቅርቡ ደግሞ ለህገመንግስቱ ጥብቅና ገና ሰልፍ ይወጣታል !!

By Finfinne Press



እኛ አገው ፣ ቅማንት ክልል እንዲሆኑ ማንነታቸው እንዲከበር ፣ የእራስን በራስ የማስተዳደር ህገመንግስታዊ መብታቸው እንዲከበር የምንናገረው ... ጥያቄው በህዝቡ ፣ በልሂቃኑ ፣ በምሁራኑ የሚነሳ የዘመናት ጥያቄና መብት ስለሆነ ነው።

ከእነሱ የተነሳውን ጥያቄ የማስተጋባት መብቶቻቸው እንዲከበር የፌደራሉን ስርዓት ተመስርተን ጥያቄዎቻቸውን እንደግፋለን።
ባሻዬ ይህንን አይቶ ... በእሱ ቤት መከፋፈሉ ነው 😂 .. የወለጋ ፣ የተምቤን ፣ የእንደርታ ፣ የጅማ ፣ የቱለማ ክልል የሚል ዘመቻ ጀምሯል። በእሱ ቤት እኮ የፖለቲካ ሊቅ መሆኑ ነው ...

በአማራ ክልል የአገው ፣ የቅማንት ፣ የወሎ ህዝብን በማንነታቸው ምክንያት በመጮቆን ፣ በማፈናቀል ፣ የአስተዳደር ሆነ ተቋማት ላይ በማግለል ስንት በደል ሰርቶ ..

ማንነታቸውን ፍቆ ለመጨፍለቅ በአማራ ልዩ ሀይል ስንተ ዘመቻና ውድመት ካደረሰ በኃላ ... የእራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ ላይቀለበስ አፋፉ ላይ ሲደርስ ... የእራሱን ክልል እሳት ትቶ ..

ወደ ኦሮሚያና ትግራይ ፊቱን አዙሮ ክልል አድላለሁ እከፋፉላለሁ ብሎ ይወራጫል 😂 ... የፖለቲካ ካልኩሌሽን መሆኑ እኮ ኖ ..

ከሁሉም ደስ የሚለኝ ግን በውድም በግድም ፣ በእልህም ፣ በትንቅንቅም ... ባሻዬን ከአሃዳዊ ወደ የፌደራሊዝሙ ጠበቃ ተደርጎ እንደ አዲስ ማንነቱ እየተሰራ ነው .. በቅርቡ ደግሞ ለህገመንግስቱ ጥብቅና ገና ሰልፍ ይወጣታል !!

Please wait, video is loading...

sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: "አንድነት ኃይሉን ፍለጋ" | ኢትዮጵያዊው ብሔርተኛ በጎሳ ፖለቲካ አራማጆች h3ኛ ጊዜ እንደተሸነፈ መቀበል አለብን። ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ (አደባባይ ሚድያ)

Post by sarcasm » 01 Jul 2023, 13:51

Please wait, video is loading...

Sam Ebalalehu
Member
Posts: 3639
Joined: 23 Jun 2018, 21:29

Re: "አንድነት ኃይሉን ፍለጋ" | ኢትዮጵያዊው ብሔርተኛ በጎሳ ፖለቲካ አራማጆች h3ኛ ጊዜ እንደተሸነፈ መቀበል አለብን። ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ (አደባባይ ሚድያ)

Post by Sam Ebalalehu » 01 Jul 2023, 14:48

ስለዚህ ፀጋየ አራርሳ ትንሽ ነገር አውቃለሁ። በሱ ምድብ ከነበሩ የ አዲስ አበባ ህግ ተማሪዎች የትምህርት ውጤቱ ከመሀከለኛው ተማሪም ወረደ ያለ ነበር። ግን ያቅበት ነበር የ ትራይባል ሲስተሙን ለግል ፉለጎቱ እንዴት እንደሚጠቀምበት።
ብሩህ ላለመሆኑ መረጃውን ከላይ አንብብ። በአንዲት አገር ውስጥ በትራይባል ሲስተሙ የሚተዳደሩ ክልሎችና በዛ የማይተዳደሩ ክልሎች አብረው መኖር ይችላሉ እያለን ነው።
እነዚህ ፌዴራሊዝም ቢግቱአቸው የማይዋጥላቸው ትራይባል ካድሬዎች ስለ ፌዴራሊዝም የኢትዮጵያን ህዝብ ሌት ተቀን ሲያደነቁሩ ስትሰማ ለኢትዮጵያ ህዝብ ማዘንህ አይቀርም።

sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: "አንድነት ኃይሉን ፍለጋ" | ኢትዮጵያዊው ብሔርተኛ በጎሳ ፖለቲካ አራማጆች h3ኛ ጊዜ እንደተሸነፈ መቀበል አለብን። ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ (አደባባይ ሚድያ)

Post by sarcasm » 22 Jul 2023, 07:59

የኢትዮጵያዊነት / የዜግነት ፖለቲካ ተበትኗል፤ ድርጅት የለውም። ማህበራዊ መሰረቱ እየጠበበ መጥቷል። - አቶ ልደቱ አያሌው



sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: "አንድነት ኃይሉን ፍለጋ" | ኢትዮጵያዊው ብሔርተኛ በጎሳ ፖለቲካ አራማጆች h3ኛ ጊዜ እንደተሸነፈ መቀበል አለብን። ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ (አደባባይ ሚድያ)

Post by sarcasm » 30 Aug 2023, 19:09

Moges Zewdu Teshome ዛሬ ባሰፈረው ፅሁፍ በሰላም ይቋጫል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት ጦርነት መጠናቀቁን ተከትሎ አጠቃላይ ሀገራዊ ጉዳዮችን ወደ ኋላ የተመለሱ፣ በከፊል ወደ ኋላ የተመለሱ እና ወደ ኋላ ሊመለሱ የማይችሉ በሚል በሶስት ከፍሎ አስፍሯቸዋል።

የሱ ሀሳብ እንደተጠበቀ ሆኖ ወደ ኋላ ሊመለሱ የማይችሉ ብሎ ባስቀመጠው ካታጎሪ ውስጥ የኔን ሀሳብ ልጨምር።

በዚህ ጦርነት ሂደት እና የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ አንድ ጎልቶ የወጣ እውነት አለ። ከጦርነቱ በፊት እና በተለይ በዘመነ ኢህአዴግ ጊዜ የብሄር ፖለቲካን እንፀየፋለን በማለት "የኢትዮጲያዊነት ፖለቲካ" በሚል ማዕቀፍ ውስጥ ሲንቀሳቀስ የነበረው ሀይል ሙሉ በሙሉ ማለት በሚቻል ደረጃ የለየለት ብሄርተኛ ከፍ ካለም ዘረኛ መሆኑን በራሱ ያስመሰከረበት ነው።


ይህ ሀይል ከዚህ በኋላ በኢትዮጲያዊነት ፖለቲካ በሚል ካባ ተመልሶ ለመምጣት የሚችልበት እድል በዜሮ የተባዛ ሆኗል።


ይሄ ሀይል በኢትዮጲያ ስም የአንድ ብሄር ፖለቲካ እና ጥያቄ የሚያራምድባቸው አደረጃጀቶች በፖለቲካ፣ በሚዲያ፣ በሲቪል ማህበራት፣ በዲያስፖራ ማህበራት፣ በሀይማኖት ተቋማት፣ በሰብአዊ መብት ተቆርቋሪነት፣ እና በመሳሰሉት ነው።

እንደ እስክንድር ነጋ በኢትዮጲያዊነት ተሞሽሮ በአማራነት መልስ የተጠራ፣ እንደ መስከረም አበራ የብሄር ፖለቲካን ያነወረ መፅሃፍ አሳትሞ መርዝ ዘረኛ ሆኖ የወጣ፣ እንደ ተመስገን ደሳለኝ ኢትዮጲያ ኢትዮጲያ እያለ ኢትዮጲያያ ከአንድ ጎጥ ውጪ ማየት የተሳነው፣ መላው ኢትዮጲያ አንድነት ድርጅት ብለህ ከአማራ ውጪ ወደ ውጪ የምትል፣ የኢትዮ-ምናምን የሚል ህብረት ፈጥረህ ከኢትዮጲያን አማራን የሚያስቀድም፣ እነዚህ ምሳሌ እንጂ ዘርዝረን አንጨርሰውም።

ሲጠቃለል ለአማራ ህዝብ መብት መታገል ያለውን አስፈላጊነት ማንም አይክድም። በኢትዮጲያዊነት ስም ለአንድ ብሄር መታገል ግን ላይመለስ የተቀበረ ስልት በመሆኑ በይፋ ብሄርተኝነቱን ተቀላቅለው ለአማራ ህዝብ መታገል አማራጫቸው ነው።

ይሄ ማለት ግን በኢትዮጲያዊነት ስም ፖለቲካ አይኖርም ማለት አይደለም። በኢትዮጲያዊነት ስም ሊመጣ የሚገባው ፖለቲካ ግን በአዲስ ሀሳብ፣ በአዲስ ቅርፅ፣ በአዲስ መንፈስ ሁሉንም ኢትዮጲያዊ በእኩልነት የሚቀበል፣ ለሁሉም ኢትዮጲያዊ በእኩልነት የሚታገል፣ ብሄር እና ሀይማኖት የማያበላልጥ የእኩልነት ትግል የሚያደርግ ብቻ ነው። ከዚህ ውጪ ያለው የኢትዮጲያዊነት ካባ ባለፉት ጥቂት አመታት በራሱ ጊዜ ተቀዳዶ ወልቋል። መልሰህ ልትለብሰው አትችልም። ብትችልም ቀዳዳው ብዙ ነው።
Please wait, video is loading...

Post Reply