Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 5543
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

የሚገርም ታሪክ፣ እንዳይዘነጋ ወይም እንዳይዛባ

Post by Naga Tuma » 26 May 2023, 16:39

የዐመታት በፊት ግርምት ነዉ። ኣሁን ታሪክ ነዉ ማለት ይቻላል። ታሪክ የሚዘነጋ ወይም የሚዛባ መሆን የለበትም።

ከኣንድ ማህበረስብ አባላት የቡና እንጠጣ ጥሪ ኣግኝቼ እሺ ብዬ ሄድኩኝ። በትንሽ ከተማ ቡና እየተጠጣ ማዉራት ተጀመረ እና ስለማህበረሰቡ ዉይይት ቀጠለ። በቅንነት ይጠነክራል ብዬ ተስፋ ስለነበረኝ ማህበረሰብ ተስፋ እንደሌለዉ አይነት ዉይይትን ሳስተዉል ማህበረሰቡን ኣንድ ላይ ማጠንከር ይሻላል ብዬኣቸዉ ብዙም ሳልቆይ ወደቤቴ ተመለስኩኝ።

ከስብሰባዉ በኋላ ቀናት ሳያልፉ የቅርብ ዘመድ ድንገተኛ አደጋ መርዶ ስለሰማሁ ቀኑ የማይዘነጋ ነዉ።

እስከዛሬ ድረስ የማላዉቀዉ የዛ ስብሰባ አላማ ከስብሰባዉ በፊት በሚድያ ሰምቼ እና ኣንብቤ የታዘብኩት የፖለትካ ቡድን አካል ጥንስስ መሆኑን ወይም ኣለመሆኑን ነዉ።

ማህበረሰቡን በነበረኝ አቅም ለማጠንከር ያሰብኩኝ በስብሰባዉ ላይ መሳተፍ ጀምሬ ብዙም ሳልቆይ ነበር። በኣጋጣሚ ትምህርት ቤት እያለሁ በሁለት አባላቱ መካከል ኣለመስማምትን በእንተርኔት ዉስጥ ኣንብቤ ነበር።

ዐመታት ኣልፈዉ የማህበረሰቡን ስብሰባ ኣየሁ። ዉይይቱን ኣስተዉዬ ኣንድ ቀን ከስብሰባ በኋላ ማህበረሰቡን ማጠንከር ይችላል ብዬ በቅንነት የማይስማሙ የነበሩትን ሁለት አባላቱን ለማግባባት ተነሳሁ። ሌሎች ሁለት የማህበርሰቡን አባላት ኣማክሬ ኣንድ ቀን ተሰብስበን መግባባት ላይ ተደረሰ።

ተሳካ ብለን ወደቤቶቻችን ተመለስን።

ቃናት ሳያልፉ በሁለቱ አባላት መካካል እንደገና ኣለመስማማትን ሰመሁ። ጊዜ ሳላጠፋ ስልክ ኣነሳሁ። እንደገና የኣለመስማማቱ ምንጭ ስህተት ነዉ የሚባል መልስ ቢሰጠኝም እንደተዋሸሁ ገባኝ። ታዘብኩ እና ማህበረሰቡን ለማጠንከር ሌላ ምክንያት መሆኑን ኣመንኩኝ።

ሌላ ግዜ ከማህበረሱቡ መሪ ኮምቴዎች አባል ማህበረሰቡን ስለማጠንከር ሌላ ጥሪ ኣግኝቼ እሺ ብዬ ያለኝን አስተያያት በቅንነት ማካፈል ጀመርኩኝ።

የማህበረሰቡ አባላት የተስማሙበት ዉይይት ነዉ ቢባልም ተጀምሮ የነበረ አጀንዳ ያልዘለቀ ሆነ።

ከዛም ሌሎች የማህበረሰቡን አባላት ስለነበረኝ አስተያያት መንገር ፈልጌ ተሰበሰብን። ማዉራት ጀመርኩ እና በመሃል ክርከር ሲነሳ ይህ ማህበረሰብ ሊከፈል ይችላል ኣልኩኝ። ኣንዱ ይህቺን ወድያወ ቀለብ ኣደረገ እና ይሀዉ ከፈለ ብሎ ወቀሰኝ። አጠገቡ የነበሩት እዉነቱን ነዉ ብለዉ ተቀብለዉት ይሁን ኣይሁን እስከዛሬ ኣላዉቅም።

ግርምቱ ቅዝምዝም ወዲህ ምን ወደዝያ እንደሚባለዉ ነዉ። እኔ ሊከፈል ይችላል ያልኩት ከቡና እንጠጣ ጥሪ ማህበረሰቡን ኣንድ ላይ ማጠንከር ይሻላል ብዬ ወደቤቴ የተመለስኩኝን በማሰብ ነዉ። ይህንን ነዉ እሱ ይሀዉ ከፈለ ብሎ የወቀሰኝ።

ታሪክ እንዳይዘነጋ ወይም እንዳይዛባ።