Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Wedi
Member+
Posts: 7993
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

ጌች እኛስ ከዚህ የተለዬ ምን አለነ?

Post by Wedi » 30 Mar 2023, 16:49

ጌች እኛስ ከዚህ የተለዬ ምን አለነ?
:lol: :lol:
Please wait, video is loading...

Abere
Senior Member
Posts: 11120
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: ጌች እኛስ ከዚህ የተለዬ ምን አለነ?

Post by Abere » 30 Mar 2023, 17:20

ትግርኛ በአማርኛ የሚናገረው ጌቾ በሃራጅ አማራን ሊሸጥ የተመለመለ ይሁዳ ነው። የራያ ልጅ አማራ እንጅ ትግሬ ሁኖ አያውቅም። የራያ አማርኛ ደንበኛ የወሎ አማርኛ አነጋገር ነው። የሚመች አማርኛ፤ ለመሆኑ እርሱ ብቻ ነው እንደ የራያ ዘመድ ፤ ባልንጀራ እና ቤተሰብ ያለው? ከእርሱ የበለጠ ማለት እንችላለን። አዎን፤ ራያ አማራ ወሎ ነው።

sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: ጌች እኛስ ከዚህ የተለዬ ምን አለነ?

Post by sarcasm » 30 Mar 2023, 19:23

Wedi wrote:
30 Mar 2023, 16:49
ጌች እኛስ ከዚህ የተለዬ ምን አለነ?
:lol: :lol:
Please wait, video is loading...


ወልቃይትና ራያ ከ1940ዎቹ በፊት የበጌምድርና ወሎ አካል ኣልነበሩም፤ በጌምድርና ወሎም ወጥ የአንድ ብሄር ክፍለ ሃገሮች አልነበሩም። (ተፃፈ በ ዳግም ዉልደት)!

~~~~~~======~~~~~=====~~~~~=====
ይህ በጣም ጠቃሚ ፅሁፉ ከማንበባችሁ በፊት፣ እነዚህ ተመልከቱ።

1. ወልቃይትና ራያ የማንነት ጥያቄ አለ? 👇
https://bit.ly/4039cq9

2. አሜሪካ ስለ አማራ ሀይሎች ምን አለች? 👇
https://bit.ly/3ndK29Q

3. HRW & AI on Amhara Forces 👇
https://bit.ly/3JJCgvM

አሁን ወደ ዋናው ጽሁፍ እንግባ። መልካም ንባብ ይሁንላችሁ!

I. ከጦርነቱ መነሻ ጋር ግንኙየት የሌለው የወልቃይትና የራያ ጉዳይ
======
የትግራይ ሃይል ህግ ይከበር ፈላጭ ቆራጭነት ይቅር በማለቱ በሁሉም የመከላከያ ዕዞችና ክ/ጦሮች ተከቦ የኤርትራም ሰራዊት ኣንድም ሳይቀር ትግራይን ተባብሮ ወሮ ከዛም ኣልፎ የኤርትራን ህዝብ ታይቶ በማይታወቅ ኣፈሳ ኣስገድዶ ኣሰልፎ ባለበት ሁኔታ የትግራይ ህዝብም በታሪኩ ኣይቶት የማያውቅ ፈተና በሚያሳለፍ ግዜ: "ከሰላሙ ስምምነት ጀርባ ያሉ ሃይሎች": "ኣማራ ሊወረር ነው"፣ ከጦርነቱ መነሻ ጋር ምንም ግንኙነት የሌለው "ወልቃይትና ራያ እንዲህና እንዲያ ሆኖ ይተዳደር" ወዘተ ... የሚሉ ድምፆች እየተሰሙ ነው።

ብዙ ጊዜ መነሻ የምታደርጉትም የትግራይ ሃይል መከላከያን መታ የሚለው ትርክት ሃቅን ካለማወቅ ኣለዚያም ሆን ብሎ ከማጣመም ይነሳል:: ህወሓትና ብልጽግና ባለመስማማታቸው የሰሜን ዕዝ ከኤሪትራ ድንበር እንዲነሳ፣ ኣዳዲስ የሰሜን ምዕራብና ማዕከላዊ ዕዞች ጎንደርና ወልድያ ላይ እንዲቋቋሙ ሲወሰን፣ የኤሪትራ ሰራዊትም ወደ ድንበር ሃይሉን በሙሉ Game Over የሚል ፉከራን ታጅቦ ሲያስጠጋ "የትግራይ ህዝብ ኣደጋ ኣልነበረበትም፣ የትግራይ ሃይልም ራሱን መከላከል ኣልነበረበትም" ማለት ሃቅን ሽምጠጣ ብቻ ነው።

ከብዙ ማስረጃዎች መካከል የኤሪትራው የቀድሞ መከላከያ ሚ/ር ኣቶ መስፍን ሓጎስ ሁለቱ ኣምባገነኖች በያገራቸው ያለን ማንም የህዝብ የዲሞክራሲ ጥያቄ ተባብረው ለማፈን ባላቸው ስምምነት የሰሜን ዕዝ ትግራይን ለመውጋት ምስጢራዊ ዝግጅት ላይ የነበረ መሆኑን ለማሳየት፣ ትግራይ በ360 ዲግሪ ተከባ በመካከል እንድትሟሟ ፕላን ተደርጎ (as hammer & anvil) የተሰራበት መሆኑን ዘርዘር ኣድርጎ ጽፏል።

Link: https://eritreahub.org/mesfin-hagos-eritreas-role-in

በዚህ ሁኔታ ውስጥ ትግራይ ተዳክማለችና ጊዜው ኣሁን ነው በሚል የጭካኔ ፈሊጥ፣ በመከላከያና ኤሪትራ ስራዊቶች ጀርባ ወደ ትግራይ የገባው የኣማራ ክልል ታጣቂ፣ ከጦርነቱ መነሻ ጋር ምንም ግንኙነት የሌለው የትግራይን መሬት ይዞ ርስቴ ነው ሲል ከታሪካዊ ሃቅ፣ ከህግ ከርትዓዊነትም የራቀ ነው፣ ጭካኔም፣ ታሪካዊ ክዳትም ነው:: ይህን ስል ኢትዮጵያ ኣሁን ካለው የማንነት መዋቅር የተለየ፣ ካሁን በፊት ከነበሩት ኣወቃቀሮች የተለየ ኣዲስ ኣወቃቀር፣ በሃይል ሳይሆን በሁሉም ህዝቦች ስምምነት ቢኖራት ቅር የሚለኝ ሆኖ ሳይሆን፣ በኣንድ በኩል የማነንት ፖለቲካና መዋቅር ይቅር ብለው በሌላ በኩል ደግሞ ወልቃይትና ራያ "ኣማራ ነው" የሚሉ ኣባባሎች እርስ በርስ የሚጋጩ ከሃቅም የራቁ ስለሆኑ፣ የኣማራ ልሂቅ ሃቁን እንዲያውቅና ወደ ጥላቻና ግጭት ከሚያመራ ለላውን ህዝብ ሳይሆን የዛን ህዝብ መሬት ብቻ ከሚያፈቅር ኣካሄድ ነጻ መሆን ስላለበት ነው።

ካለፉት ሁሉ ስርዓቶች የተለየ ኣወቃቀር በጉልበት ሳይሆን በጋራ መግባባት ከኣዲስ ህገ መንግስት ጋር እስኪፈጠር ግን ግጭትና ጥላቻ መቆም ስላለበት ያለውም ህግ መከበር ስላለበት ያለውን የህግ ማዕቀፍ ኣክብሮ መነጋገር ግድ ይሆናል።

በመሰረቱ ኣንድ ክልል የማዕከላዊ ስልጣንን ከያዘ ኣንድ ፓርቲ ጋር ስለ ተጋጨ ሌላ ክልል፣ በመከላከያና በውጭ መንግስት ሰራዊቶች ታዝሎ ተደርቦ ገብቶ ኣንድን ክልል በድካሙ ጊዜ ማጥቃት መሬት ይዞ ርስት ኣስመለስኩ ማለት ነውርና ታላቅ ታሪካዊ ክህደት ነው:: ኣሁን የጦርነቱ መነሻ በሰላም ስምምነት በመቋጨቱ ወደ ወልቃይትና ራያ ጉዳይ ልመለስ።

II. ሪፈረንደም ?
======

የራያ በተለይም የወልቃይት ህዝብ ጄኖሳይድ ተፈጽሞበት ኣልቆ የቀረውም ወደ ቀረው የትግራይ ክፍልና ጥቂቱ ደግም ወደ ሱዳን ተሰዶ ኣሁን በምድሩ በሌለበት ሁኔታ ኣዲስ ህዝብ ከኣማራ ክልል መጥቶ በር በርግዶ ገብቶ ቤትና መሬት በሃይል እንዲይዝ ተደርጎ ኣማራ ነኝ እያለ በየቀኑ ሰልፍ እየወጣ የቱ ህዝብ ስለሚያደረገው ሪፈረንደም ነው የምታወሩት?

IV. ወልቃይትና ራያ ዕውን የበጌምድርና ወሎ ኣካል ነበሩ? በጌምድርና ወሎስ ኣማራ ነበሩ? እውን ትግራይ ተከዜን ኣያልፍም?
======

1) ወልቃይትና ራያ በ1940ዎቹ ወደ በጌምድርና ወሎ ክ/ሃገራት ከመጠቃለላቸው በፊት የነዚህ ክ/ሃገራት ኣካል ኣልነበሩም:: ወልቃይትና ራያ የጎንደርና ወሎ ኣካል ስለ ነበሩ ኣማራ ናቸው የሚለው ትርክት በሁለት ምክንያቶች ስግብግብና ውሸት ነው::
ሀ) ወልቃይት ስሜንና ራያ የትግራይ ኣካል ነበሩ
ለ) የድሮዎቹ ክ/ሃገሮች ማንነትን መሰረት ያደረጉ ኣልነበሩም።
በዝርዘር እንያቸው:
ሀ) ወልቃይትና ራያ የትግራይ ኣካል ነበሩ።

ከዓጼ ዮሃንስ ሞት በኋላ እስከ ሃይለስላሴ ባለው ጊዜ ወልቃይት ስሜን: በማንነት ወይም ኣማራነት ሳይሆን ለንጉሶቹ ቤተሰቦች ግብር ማስገቢያ (ለምሳሌ እቴጌ ጣይቱ) ከዛም ለኣስተዳደር ኣመችነት በሚል ከትግራይ በተለያየ ጊዜ ተወስደው ለብቻቸው እንደ ጠ/ግዛቶች እንዲቆሙ ከዛም ወደ በጌምድር ተወስደው ኣንድ ላይ "በጌምድር እና ስሜን" ተብለው በ1943 እንዲዋቀሩ (ኋላ ላይ "በጌምድር እና ስሜን" ጎንደር ተብሏል) ከመደረጉ በቀር በታሪክ በጌምድር ወይም ጎንደር ሆነው ኣያውቁም::

ሃጋይ አርሊክን (1996 እ.ኤ.አ) እንደዘገበው የዓጼ ዮሃንስን መስዋዕትነት ተከትሎ የትግራይ መሳፍንቶች፣ ማለትም ራስ መንገሻ ዮሃንስ፣ ራስ ኣሉላ፣ ራስ ሓጎስን እና ራስ ወልደሚካኤልን ልዩነት ፈጥረው በ1894 ኣዲስ ኣበባ ድረስ በመሄድ ከኣፄ ምኒሊክ ጋር ለእርቅ የተገናኙ ሲሆን እርቁ የተሟላ እንዲሆን እና ለታማኝነታቸው ማረጋገጫ ሲባልም በቅድሚያ እንዲፈጸም ካቀረቡላቸው ኣራት ቅድመ ሁኔታዎች ሁልቱን ለመጥቀስ ኣንድ፡ ‘’እስከ ዛሬ ድረስ የራስ ሓጎስ ግዛት የነበረው ፀለምቲ እና ወልቃይት ፀገዴ በጉልትነት ወደ እቴጌ ጣይቱ እንዲተላለፍ’’ የሚል ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ፡ ‘’የራስ ኣርኣያ ሥላሴ ዮሃንስ ጉልት የነበረው እንደርታም በጉልትነት ለልዕልት ዘውዲቱ ሚኒሊክ እንዲሰጥ’’ የሚሉ ነበሩ። እዚህ ላይ ፀለምቲ፣ ወልቃይት ፀገዴ እና እንደርታ በግዛትነቱ የትግራይ ሆነው የቀጠሉ ቢሆንም በጉልትነት ግን ለእቴጌ ጣይቱ እና ለልዕልት ዘውዲቱ ግብር ኣገልግሎት እንዲውል ነበር የተባለው።
ለዚህም ከህዝቡ ጥንታዊ ማንነት በተጨማሪ: የወልቃይት ስሜን መንደር ስሞች በሙሉ ትግርኛ መሆናቸው ራሱ ምስክር ነው (ማይ ጋባ : ማይ ጨዓ : ማይ ጥምቀት : ማይ ሑመር : ማይ ጸብሪ : ማይ ካድራ : ዓዲ ረመጽ : ዓድ ፍልሖ : ዓዲ ጋባ : ዓዲ ወርቂ : ምድሪ ወይዘሮ : ሰላሳ ዓይና : እንዳቦ : ክሳድ ደለሳ : ሩባ ለሚን : ቤት ሙሉ : ብላምባ ቅርሺ : ብላምባ ሚኪኤል : መጉእ : ቃሌማ : ሽሬላ : ደጀና : ወዘተ)። ህዝቡ ትግርኛ ተናጋሪ የትግራይም ኣካል ስለነበር በኣዲሱ የ1983 የብሄሮች ፌድሬሽን የወልቃይት ስሜንና ጸገደ ጸለምቲ ህዝብ በከፊል ወደ ትግራይ መልሶ ተካለለ:: ትግርኛ ረስቶ ኣማርኛ የለመደው ጠለምትና ጠገደ በሚል ስያሜ ወደ ኣማራ ክልል ተካለለ::
የራያም ያው ነው:: የሃይለስላሴ ልጅ ኣስፋወሰን (ኣምሃስላሴ) "መስፍነ ወሎ/Duke of Wello" ተብሎ ሲሾም በ1940ዎቹ ትንሹ የወሎ ኦሮሞ ጠ/ግዛት ሌሎችን ጠ/ግዛቶችን ጨምሮ፣ ትልቁ ወሎ እንዲፈጠር ተደረገ:: ይህም በማንነት ወይም ኣማራነት ሳይሆን ለንጉሱ ልጅ ግዛት ለማስፋት ሲባል ብቻ ነበር:: በ1983 ደርግ ሲወድቅ ትግርኛ ያልረሳው ራያ ዓዘቦ ወደ ትግራይ ሲካለል ትግርኛ ረስቶ ኣማርኛ የለመወደው ራያ ቆቦ ክፍል ግን ወደ ኣማራ ተካለለ:: በሁለቱም በኩል ትግራይ የድሮ ህዝብና መሬቷን ጠለምትና ጠገደ እንዲሁም ራያ ቆቦ: ትግርኛ ረስቶ ኣማርኛ በመልመዱ ምክንያት : ሳታስመልስ ቀረች እንጂ ትርፍ የወሰደችው ህዝብና መሬት የለም:: በተጨማሪም በ1983 ሂደት ትግራይ ግማሽ የመሬት ስፋቷን ለዓፋር ክልል ኣሳልፋ ሰጥታለች : ምክንያቱም ዓፋርኛ ተናጋሪ ስለ ነበር:: የወሎ ኣገው ህዝብ ሁለት ቦታ እንዳይከፋፈል : ትግራይ ለኣማራ ክልል ያስረከበቸው የወሎ ኣገው ውሱን ክፍልም ኣለ:: ባጠቃላይ ትግራይ በጉልበት የወሰደችው ህዝብና መሬት የለም ብቻ ሳይሆን ባጠቃላይ ያጣችው ይበልጣል::
ለ) የድሮዎቹ ክ/ሃገሮች ማንነትን መሰረት ያደረጉ ኣልነበሩም::
እስከ ደርግ ውድቀት የነበሩት 14ቱ ክ/ሃገራት ረጅም ጊዜ ያልነበሩ በኣብዛኛው ከ1940ዎቹ ጀምሮ ቅርጽ የያዙ ሲሆን ማንነትን መሰረት ያደረጉ ኣልነበሩም:: ከ1940ዎቹ እስከ 1983 የዘለቁት ክ/ሃገራት የተለያዩ ህዝቦች የሚኖሩባቸው ነበሩ:: ለምሳሌ ሸዋ የኣማራ : ኦሮሞ : ዓፋር: ጉራጌ : ስልጤ : ከምባታ : ሃዲያ : ወዘተ ህዝቦችን ያጠቃለለ ነበር:: "በጌምድርና እና ስሜን" (በኋላ ጎንደር የተባለው) ክ/ሃገር የኣማራ : ቅማንት : ሽናሻ : ጋፋት : ፈላሻ : ኋላም ከትግራይ የተወሰደው የወልቃይት ስሜን ህዝቦች ይኖሩበት ነበር:: ወሎን በተመለከተም ኣዲስ ነገር የለም:: ትንሹ የወሎ ኦሮሞ ጠ/ግዛት ቀርቶ ትልቁ ወሎ የተፈጠረው የወሎ ኦሮሞ የሚበዛበትን ጠ/ግዛት : ከኣማራ ሳይንት ጠ/ግዛት : ከዋግ ጠ/ግዛት : ከላስታ ጠ/ግዛት ከደንከል ጠ/ግዛት : ከትግራይ ከተወሰደው ራያና : ከኣርጎባ ህዝብ ጋር በማጠቃለል ነበር:: ትግራይም ቢሆን ከላይ እንዳልኩት ግማሽ መሬቱ ዓፋርኛ ተናጋሪ ህዝብ ነበረበት : ስለሆነም ወደ ኣዲሱ ዓፋር ክልል ሄደ:: በዚህ ክስተት ግን የትግራይ ህዝብ በዓፋር ነጻ ኣውጭ ተወርሬ ጄኖሳይድ ተፈጽሞብኝ መሬቴ ተወሰደ ኣላለም:: ምክንያቱም ደርግ በነበረበት ጊዜም ሆነ ከደርግ ውድቀት በኋላ : ከደርግ ጋር ጦርነት ኋላም ማንነትን መሰረት ያደረገ ማካለል እንጂ ጄኖሳይድ ብሎ ነገር ኣልነበረም::
2) 1.2 ሚልዮን የወልቃይት ህዝብ ባለፉት 2 ዓመታት በመከላከያና ኤሪትራ ሰራዊቶች ታዝሎ በገባው የኣማራ ክልል ታጣቂ ተገድሎ ተፈናቅሎ በቦታው የለም:: ከጅምላ ርሸና የተረፈው የወልቃይት ኣብዛኛው ህዝብ ተፈናቅሎ በቀረው የትግራይ ክፍል ኣለ ጥቂቱም ሱዳን ተሰዶ ይገኛል:: ስለሆነም የቱ ህዝብ ነው በትግራይ ስር የመብት ኣለዚያም የማንነት ጥያቄ ኣለው የሚባለው? በመከላከያና በኤሪትራ ሰራዊት ጀርባ የኣማራ ክልል ከሃዲ ኣመራር ታዝሎ ገብቶ ኣዲስ ህዝብ ኣስፍሮ እኛ ኣማራ ነን በማስባል ሰልፍ ማስወጣት የትም ኣያደርስም:: የኣማራና ትግራይን ህዝብ ደም ከማቃባት በኣገሪቱም ተመላላሽ ጦርነት በማስቀጠል የኣገሪቱን የኣመራሩን ስም ከማጠልሸት ኢኮኖሚውን ከማድቀቅ በቀር ፋይዳ ኣይኖረውም:: የወልቃይትን ጉዳይ ያንበለበለው ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ሲሆን ኣባቱ ኣቶ ዘውዱ "ኧረ ኣምጡልኝ ልንገረው ከነዘር ማንዘሩ ትግሬ ነው" ሲሉ በሚድያ ኣይተናል:: ደመቀ ዘውዱ የህወሓት ታጋይ ማለትም የትግራይ ህዝብ የብሄራዊ ትግል ኣካል ሆኖ ጸረ ደርግ የታገለ ዋጋ የከፈለ : በኋላ ግን በኣስተዳደራዊ ጉዳዮች ኣኩርፎ ኣማራ ነኝ ያለ ሰው እንጂ የቀረው የወልቃይት ህዝብ በማንነቱ ችግር ያለበት ኣይደለም፣ ኣለኝ ብሎም ኣያውቅ:: ካለም አሁን ከተፈናቀለበት ከስደት ተመልሶ ተጠይቆ ሊናገር የሚችል ነው:: የወልቃይት ህዝብ የማንነት ጥያቄ ኣለው የሚሉት ጎጃምና ጎንደር ያሉት ጥቂት ልሂቃን በተለይም የዘይት ፋብሪካ ባለቤቶችና የነሱ ቅምጥ ባለስልጣናት ተከፋይ ኣክቲቪስቶች : ኣለፍ ሲልም በዚህ 2 ዓመት ነባሩን ህዝብ ገድለውና ኣባረው የሰፈሩ ሰዎች እንጂ የወልቃይት ህዝብ ኣይደለም::
3) ከህግ ውጭ ኣንድን ክልል ኣይደለም ታዝሎ ገብቶ : በቀጥታ በሃይል ወሮም ቢሆን በመያዝ የባለቤትነት መብት የማይሰጥ ቢሆንም : ወልቃይትና ራያን በሃይል ይዘናል የሚለው ውሸት ነው:: የጎረቤት ኤሪትራ/ህግደፍ ወራሪና ቂመኛ ሰራዊት ከብልጽግና መራሹ የኢትዮጵያ መከመላከያ ጋር በታንክና ድሮን በተደገፈ ጦርነት : ከቦ በማስራብም ተደግፎ በፈጸመው ወረራ ታዝሎ ገብቶ ርስት ኣስመለስኩ ማለት ቅዠትና ስግብግብነትና የኣሳማ ፖለቲካ ብቻ ነው::
4) ህወሓት ወልቃይትና ራያን ወሮ ነው የያዘው የሚለውን መሰረተ ቢስ ቅጥፈት በተመለከተ ህወሓት ወልቃይትና ራያን ለመያዝ ከኣማራ ህዝብም ሆነ ከማንም ጋር የተዋጋው ጦርነት ኣልነበረም:: ያፈናቀለውም ህዝብ የለም:: በርግጥ ህወሓት ከኢዲዩ፣ ደርግና ኢህኣፓ ጋር ባደረገው ጦርነት የተፈናቀለ ሰው ይኖራል:: የተፈናቀለው ግን ጥቂት በከተሞች የሚኖር ባለሃብት እንጂ በየመንደሩ የሚኖር የወልቃይት ትግራዋይ ህዝብ ኣለነበረም:: ይህም ቢሆን ግን ብሄርን የለየ ኣልነበረም:: ኣይደለም ኣማራና ትግራዋይ ኣራሽ : ሱዳናዊ ኤሪትራዊም ኣራሽ ነበር:: ለዚህ ማስረጃው የትግራዩ መንገሻ ስዩም የሚመሩት የትግራይ ባለሃብቶች የሚበዙበት ኢዲዩ ነበር:: ብዙ ኣራሽ ባለሃብት በደርግ፣ በኢድዩ፣ በኢኢህኣፓና በህወሓት የማያቋርጥ ጦርነት ተፈናቅሏል:: ለዚህም ነው ብዙዎቹ ብሄር ሳይለዩ በምዕራባውያን ከተሞች በተለይም በሲያትል የሚገኙት::
የትግራይና የኣማራ ወሰን የተወሰነው በፌድሬሽኑ ህገ መንግስት መሰረት ቋንቋና ባህልን መሰረት ባደረገ መልኩ ሲሆን እንደ ኣስፈላጊነቱም ህዝቡ ከዚህም ከዛም ተሳትፎበት ብዙ የትግርኛ ስም ያላቸው ግን የትግርኛ ቋንቋና ባህልን በሂደት የረሱ መንደሮችና ከተሞች ወደ ኣማራ ክልል ተወስደዋል (ዓዲ ኣጋግ : ዓዲ ኣርቃይ : ዛና : ዛሬማ : ጎሊማ : ሰቋር : ዓዲ ርሕጻን : ሓውዛ...):: የወሰን መካለልን በተመለከተ ጥያቄ ኣለ ከተባለ በኋላም : በጠ/ይ ሚ/ር ደሳለኝ ዘመን : የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት ኣቶ ኣባይ ወልዱና የኣማራ ክልል ፕሬዝደንት ኣቶ ገዱ ኣንዳርጋቸው የመሯቸው ኮሚቴዎች ብዙ ጥናት ኣድርገው ህዝቡን ኣነጋግረው ወዲያና ወዲህ የሚሄዱ ጥቂት ቀበሌዎችን ወስነው ተፈራርመው ከእንግዲህ የወሰን ጉዳይ ተዘግቷል ከኣሁን በኋላ በኣንድነት ወደ ልማት ተሸጋግረናል ብለው ደምድመዋል::
"ወልቃይትና ራያ የኣማራ ናቸው" የሚለው ሸፍጥ መሰረቱ : ህወሓትን ጠላን በሚል ሸፋን : የትግራይን ህዝብ መሬት በተለይም ከተራሮቹ ባለፈ ያለችውን ትንሽ ታራሽ ሜዳ መሬት ለመንጠቅ የሚደረግ ሰይጣናዊ ክህደት ነው:: ትግራይን ሲመራ የነበረው ህወሓት የፌደራልን ስልጣን ከሚቆጣጠረው ብልጽግና በተለይም ከ ጠ/ሚ/ሩ ጋር ግጭት ውስጥ በመግባቱ እና የትግራይ ህዝብም ችግር ላይ መውደቁ እንደ ዕድል በመጠቀም : በዚህ ወንድም ህዝብ ላይ መንገድ ዘግቶ ተደርቦ መውጋት፣ በሚልዮን የሚቆጠር ህዝብ ማንፈናቀል፣ ተደርቦ ወሮ መሬት ይዞ ርስት ኣስመለስኩ ማለት ነውርና ክህደት ብቻ ነው:: ያልተፈታ ጥያቄ ኣለ ቢባል እንኳን በኣገር ሽማግሌዎች ከዛም ባለፈ በህጋዊ መንገድ መነጋገር እንጂ በዚህ መልክ በክህደት የኣማራ ክልል ታጣቂ የትግራይን ህዝብ ከሌላ ወጊ ጋር ተደርቦ መውጋት ኣልነበረበትም::
V. የኣቻምየለህ ታምሩ መጽሓፍ ትግራይ ተከዜን ኣያልፍም የሚል ቅጥፈት
======
"ወልቃይትና ራያ የኣማራ ናቸው" የሚለው ትርክት ለማስደገፍ ኣቻምየለህ ታምሩ ዋነኛ ማስረጃዎች በሁለት ይጠቃለላሉ::
1) ከደርግ ውድቀት በፊት መደበኛ የህዝብ ቆጠራ
2) ዓጼ ዮሃንስ ድንበሬ ከተከዜ ምላሽ ነው ማለታቸው
1) መደበኛ የህዝብ ቆጠራ - በልዩ ጥናት ካልሆነ በስተቀር ከደርግ ውድቀት በፊት መደበኛ የህዝብ ቆጠራ ማንነትን ማለትም ብሄር መሰረት ያደረገ ኣልነበረም ብቻ ሳይሆን ሁሉ የኢትዮጵያ ጠ/ግዛቶችና ክ/ሃገሮች ወደዱም ጠሉም ኣማርኛ የስራ ብቻ ሳይሆን ብሄራዊ ቋንቋቸውም ነበር:: ስለሆነም በህዝብ ቆጠራ ወቅት የኢትዮጵያ ህዝብ ለማንነቱ ወይም ብሄሩ ቅድሚያ ሰጥቶ ማለት ለይቶ እኔ ኣማራ፣ ትግሬ፣ ኦሮሞ፣ ወዘተ ነኝ የሚልበት ኣግባብ ኣለበረም:: የሰሜኑን በተለይም የኤሪትራና ትግራይን ጦርነቶችና ትኩሳት ለመፍታት: ከብሄሮች የself-autonomy ና የመሬት ላራሹ ጥያቄ ጋር ኣያይዞ ለመፍታት ደርግ ባስጠናው ልዩ ጥናት ግን ምንም እንኳን ከ1940ዎቹ ብቻ ጀምሮ ወደ በጌምድርና ወሎ ቢሄድም : የወልቃይት ስሜንና ራያ ህዝብ ዋና ቋንቋው ትግርኛ መሆኑን የደርጉ ራሱ ሰነድና ካርታ ራሱ በግልጽ ያሳያል:: ሆኖም ደርግ ግን ይህን ወደ ኣስተዳደር ወይም ኣከላለል ብቀይር ሌላውም የኢትዮጵያ ክፍል ተመሳሳይ ጥያቄ ያነሳል ብሎ በመፍራት በተግባር ላይ ሳያውለው ቀርቷል::
2) ዓጼ ዮሃንስ ድንበሬ ከተከዜ ምላሽ ነው ማለታቸው - ዓጼ ዮሃንስ ስለ ተከዜ ያነሱት ገና ንጉሰ ነገስት ሳይሆኑ ከዋጉ ዓጼ ተክለ ጊዮርጊስ ጋር የነበራቸው ተገዳዳሪነት በማሰብ ነበር። በርግጥም የትግራይና የዋግ ኣገው ድንበር ተከዜ ነው:: ከቀረው የኣማራ ህዝብ ጋር ግን ድንበሬ ተከዜ ነው ኣላሉም:: የታሪክ ማስረጃዎችም የሚገልጹት ሌላ ሃቅ ነው:: Abyssinia and its People, or, Life in the land of Prester John በሚል እ.ኤ.አ 1868 የተፃፈው የ John C. Hotten መፅሃፍ ላይም ዋልድባ ትግራይ ውስጥ ከሚገኙት እና በኣቢሲኒያ ውስጥ ችግር፣ ጦርነት፣ ኣስፈሪ ሁኔታ ባጋጠመበትና ሰላም በጠፋበት ጊዜ የማይደፈሩ ከነበሩ ኣምስት መጠጊያ የእምነት ቅዱስ ስፍራዎች ኣንዱ እንደነበር በመፅሃፉ ገፅ 48 ላይ ይጠቅሳል። ዋልድባ ከተከዜ ወዲያ ማዶ የዛሬው የትግራይና ኣማራ ድንበር ኣካባቢ በትግራይ ክልል ወሰን ያለ ገዳም ነው::
ሌላ ምሳሌ Samuel G. እና Robert B (1850: ገፅ 37) Abyssinia and its Inhabitants በተሰኘው መፅሃፋቸው ላይ አንዳሰፈሩት የወቅቱ [ዘመነ መሳፍንት] ኣቢሲኒያ በሶስት ትልልቅ ነፃ መንግስታት፣ ማለትም ትግራይ፣ ኣማራ እና ሸዋ/ይፋት የቆመች ሲሆን: መጀመሪያ የተጠቀሱት ሁለቱም በጣም ሰፋፊና በከፊል በተከዜ፣ በተወሰነ ደግሞ እስከ ላሰታ የተዘረጋው ሰንሰለታማ የሰሜን ታራሮች ከፍታዎቹ ላይ ይዋሰናሉ ይላል። የሰሜን ተራሮች ላይኛው ከፍታዎች ደግሞ የትግራይ ግዛት እንደነበር ከፍ ብሎ በማስረጃ ቀርበዋል። ‘’... Separated partly by the river Tacazze and partly by the lofty mountains of Samen...’’ የሚለው ተከዘ የኣማራና የትግራይን ህዝብ በከፊል እንጂ ከጫፍ እስከ ጫፍ እንዳማያዋስን ግልፅ ያደርገዋል። ራስ ደጀንን የሚጨምረው የሰሜን ተራሮች የትግራይና ኣማራ ህዝቦች ድንበር ነበሩ ማለት ትግራይ ከተከዜ ማዶም የነበረ መሆኑን ማሳያ ነው:: ወንዞች ህዝቦችን የሚከፍሉ ቢሆን ኖሮ ታላቁ የኣባይ ወንዝና በረሃ ኣንዱን የጎጃም ህዝብ ለሁለት ባልከፈለው ነበር:: ኣባይ ወዲህና ወዲያ ማዶ ሁለት የተለያዩ ህዝቦች ይሆኑ ነበር:: ዋቢ ሸበሌም ዓፋርን ለሁለት መሰንጠቅ ሳይሆን ሁለት የተለያዩ ህዝቦችን ይፈጥር ነበር:: ናይልም ኣንዱን የካርቱምን ህዝብ ኣንዱን የካይሮን ህዝብ ሳይሆን ብሄሮችን ወይም ኣገሮችን ይከፍል ነበር:: ስለ ኣውሮፓ ከተሞች ታላላቅ ወንዞችም ማውራት ይቻላል::
Manoel Barradas የተባለ እ.ኤ.አ 1624 ዓ/ም በትግራይ ይኖር የነበረ የፖርቹጋል ልኡክ Tractatus Tres Historico-Geographici (እ.ኤ.አ በ1634 ዓ.ም) በሚለው መፅሃፉ የትግራይ ስፋት ኣሁን ካለበት በኣራት እጥፍ ይበልጥ እንደነበረ ያሳያል። እንደ ጸሃፊው ኣገላለፅ በዚህ የምስራቅ ኣፍሪካ ክፍል ከነበሩት ኣገሮች መካከል ትግራይ እጅግ ሃያልና ጠቃሚ የነበረ የንጉሰ ነገስት ግዛት ነበረ። በግዛቱ ስር የነበሩትም በሰሜን በኩል ከሓማሴን ጫፍ እስከ እንደርታ ሲሆን፣ በምስራቅ በኩል ከደናክል (ዓፋር) እስከ ደቡባዊ የቀይ ባህር ጫፍ ሆኖ ከሰሜኑ ጋር ሲነፃፃአር ተመሳሳይ የግዛት ስፋት ነበረው ይላል። በምዕራብ በኩልም በሰሜን ተራሮች በኩል ያለውን የተከዜ ወንዝ የሚዋሰን ሆኖ ወደ ምዕራብ በኩል ኣቅጣጫ ግን እስከ ለማለሞ (ኣሁን ሊማሊሞ) ድረስ የተዘረጋ ሲሆን ከሰሜኑ እና ከምስራቁ ተመሳሳይ የግዛት ስፋት ነበረው። “Among all the kingdoms that the Emperor of Ethiopia possesses today one of the greatest and most important is the Kingdom of Tygre. From north to south, that is from the limits of the Amacens [ሓማሴን ] to Enderta, it covers an area of from ninety to one hundred leagues; and from east, which is beside Dancali [ዓፋር], located at the entrance to the southern end of the Red Sea, to the west, bounded by the Tacasse [ተከዘ ] River beside the [deleted], it covers an area of similar size, so that the kingdom has a nearly circular shape; unless we wish to extend it, some maintain should be done, as far as Lamalmon mountain range...’’ (Gelawdewos Araya: IDEA Staff, 10/13/2004). እዚህ ላይ ‘’Lamalmo mountain’’ ዛሬ ሊማሊሞ ተራራ በሚል ቢተካም ጥንታዊ የትግርኛ ስሙ ለማልሞ [Lamalmo] እንደነበር Manoel Barradas ከፃፈው መረዳት ይቻላል።
ሃጋይ አርሊክን (1996 እ.ኤ.አ) እንደዘገበው የዓጼ ዮሃንስን መስዋዕትነት ተከትሎ የትግራይ መሳፍንቶች፣ ማለትም ራስ መንገሻ ዮሃንስ፣ ራስ ኣሉላ፣ ራስ ሓጎስን እና ራስ ወልደሚካኤልን እ.ኤ.አ በ1894 ኣዲስ ኣበባ ድረስ በመሄድ ከኣፄ ምኒሊክ ጋር ለእርቅ የተገናኙ ሲሆን እርቁ የተሟላ እንዲሆን እና ለታማኝነታቸው ማረጋገጫ ሲባልም በቅድሚያ እንዲፈጸም ካቀረቡላቸው ኣራት ቅድመ ሁኔታዎች ሁልቱን ለመጥቀስ ኣንድ፡ ‘’እስከ ዛሬ ድረስ የራስ ሓጎስ ግዛት የነበረው ፀለምቲ እና ወልቃይት ፀገዴ በጉልትነት ወደ እቴጌ ጣይቱ እንዲተላለፍ’’ የሚል ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ፡ ‘’የራስ ኣርኣያ ሥላሴ ዮሃንስ ጉልት የነበረው እንደርታም በጉልትነት ለልዕልት ዘውዲቱ ሚኒሊክ እንዲሰጥ’’ የሚሉ ነበሩ። እዚህ ላይ ፀለምቲ፣ ወልቃይት፣ ፀገዴ እና እንደርታ በግዛትነቱ የትግራይ ሆነው የቀጠሉ ቢሆንም በጉልትነት ግን ለእቴጌ ጣይቱ እና ለልዕልት ዘውዲቱ ርስትነት ተወሰነዋል። ይህ ኣሰራር በነገስታቱ ዘመን በየትኛውም ጠ/ግዛት የተለመደ የጉልተኝነትና የገቢ ግብር ማስገባት ኣካሄድ እንጂ ከማንነት ጋር ምንም ግንኙነት የሌለው መሆኑን ማስመር ያስፈልጋል::
ከጣልያን መውጣት ጋር ተያይዞም ጣሊያን የመሰረተው የማንነት ኣስተዳደር ቀርቶ ኢትዮጵያ በጣም ትንንሽ ግን ብዙ ጠ/ግዛቶች እንዲኖሯት ሲደረግ ወልቃይት ስሜንም ከትግራይ ተለይተው ብቻቸውን እንደ ጠ/ግዛቶች እንዲቆሙ ሆነ። ከታች ያለውን ካርታ ይመልከቱ (ምስል 1)። በዓጼ ሃይለስላሴ ዘመንም ትንንሾቹ ጠ/ግዛቶች ወደ ትልልቅ ጠ/ግዛቶች (ኋላ ክ/ሃገር የተባሉት ሲጠቃለሉ) በማንነት ሳይሆን "ለኣስተዳደር ኣመችነት" ከዛም ኣልፎ ለንጉሱ ልጆችና ዘመዶች "መስፍነ ወሎ" "መስፍነ ሃረር" : የዚህ ወይም የዛ ጠ/ግዛት ገዥ: ወዘተ ማዕረግ ሲባል ብቻ ነበር ወሎ የተለቀው፤ በጌምድር የትግራይ የነበሩት ወልቃይት ስሜን ተጣብቀውለት ወደ "በጌምድር እና ስሜን" የተለቀው፤ ሸዋ ጉራጌን ከምባታን ጃንጀሮን የምን ያጠቃለለው፤ እነ ሲዳሞ : ከፋ : ኢሉባቦር የተለቁት፤ ጭራሽ ያልነበረው ጋሞጎፋ የተፈጠረው... ወዘተ በዚህ መልክ ነበር። ኣንዳቸውም የኣንድ ብሄር ጠ/ግዛት (ክ/ሃገር) ኣልነበሩም።
ለንጽጽር: 14ቱ ጠ/ግዛቶች (ክ/ሃገሮች) ከመፈጠራቸው በፊትን የነበሩትን ትንንሽ ብዙ ጠ/ግዛቶችና የህዝቦችን የማንነት (ቋንቋና ባህልን መሰረት ያደረገ) ኣሰፋፈር በግልጽ ካቀረቡት መካከል J Spencer Trimingham (Islam in Ethiopia, 1952) በሚል መጽሓፉ ይገኝበታል። ምስሉን ከታች ይመልከቱ (ምስል 2)።
ታዲያ ኣቻምየለህ: "ወልቃይት ስሜንና ራያ ከጥንትም ከትግራይ ጋር ኣልነበረም ከ በጌምድርና ወሎ ጋር ነበር ኣማራ ነው: ትግራይ ተከዜን ተሻግሮ ኣያቅም..." የሚል ቅጥፈቱን ከዬት ኣመጣው?
ማጠቃለያና ከብዙ በጥቂቱ ማስረጃዎች
==================
ለማጠቃለል በወረራ ለዛውም ተደርቦ የኣንድን ክልል መሬት ይዞ ርስት ኣስመለስኩ ማለት የነውርም ነውር ነው። የትግራይ ህዝብ ታፍኖ ሌላው ወገን ስለጮኸ እውነት የሚሆንበት ምክንያት የለም።
ከብዙ ማስረጃዎች በጥቂቱ:
1) የወልቃይት መንደሮች የትግርኛ ስሞች ከጥንት እስከ ዛሬ (የስሞቹን ዝርዝር ከዚህ ጽሑፍ ግርጌ ይመልከቱ)
2) ከብዙ የውጭ ጸሓፊዎችም መካከል: ከላይ ያልጠቀስኩት ወልቃይትን በስም ጠቅሶ የትግራይ ኣካል የነበረ መሆኑን የጻፈው: የMichael Russel (1833) መጽሓፍ
3) የደርጉን የ1971 ብሄሮች ጥናት ኢንስቲትዩት የሰሜን ብሄረሰቦች ጥናት ሰነድና ካርታ
4) በዓጼ ሃይለስላሴ ዘመን : የትግራይ ጠ/ግዛት ከኣላማጣ ቀረጥ ሲሰበስብበት የነበረ ሰነድ ማስረጃ
5) በኣጼ ሃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግስት የሽሬ ኣውራጃ ህዝብ እንደራሴ እና የወቅቱ የፓርላማ ኣባል የነበረው ኣቶ ገሠሠ ኣየለ: በጊዜው ወልቃይት ስሜንና ራያ ከትግራይ ኣለ ኣግባብ መወሰዳቸውንና መመለስም ያለባቸው መሆኑን በመግለጽ በዝርዝር ለኣፄ ኃይለ ሥላሴ መንግስት ያቀረበው ኣቤቱታ
6) የደርጉ ብ/ጄ ኣብዱላሂ ሁሴን እና ሜ/ጄ ኣስራት ብሩ የወልቃይትና ስሜን ህዝብ ትግርኛ ተናጋሪ በመሆኑ ለህወሓት የትጥቅ ትግል መመቸቱና መደገፉና ኣቅፎ መያዙንም የገለጹበት ደብዳቤ
7) በኣፄ ዮሃንስ ዘመነ መንግስት ከሽሬ እስከ ወልቃይት ፀገዴ እና መተማ ሲያስተዳደሩ የነበሩት የራስ ሓጎስ የልጅ ልጅ የሆኑት እና በወሎና በትግራይ ጠቅላይ ግዛቶች እንዲሁም በደቡብ በነበሩ ክ/ሃገሮች በተለያዩ የመንግስት ሃላፊነቶች ያገለገሉት: ኣቶ ህዝቂያስ በላይ: ወልቃይት በታሪክ ሲተዳደር የነበረው በራስ ደጌና ሲሆን ቆይቶም በራስ ሓጎስ፣ በራስ ጉግሳ ኣርኣያ እና በራስ ስዩም ሲሆን : እስከ ጣሊያን ወረራ ድረስ ደግሞ በራስ ስዩም የተሾሙ ሹማምንቶች ሲተዳደር የነበረ መሆኑን የገለጹበት ምስክርነት
Link: https://www.youtube.com/watch?v=jyPA45sd5Eo
8 ) በኣጼ ኃይለ ሥላሴ ኣገዛዝ ዘመን የፓርላማ ኣባል እና ከ14ቱ የንጉሱ ኣማካሪ ሹመኞች መካከል ኣንዱ፣ የኣገሪቱ የመወሰኛ ምክርቤት ምክትል ፕሬዚዳንት፣ እና የተለያዩ የግዛቱ ኣካባቢዎች ኣስተዳዳሪ የነበሩት ፊታውራሪ ሙዑዝ በየነ የራያ ግዛት በትግራይ ስር ይተዳደር እንደነበር በማያሻማ መንገድ የሰጡት ምስክርነት:
Link: https://www.youtube.com/watch?v=lY99s9vGlB8
ወይም
Link: https://www.youtube.com/watch?v=BSTexxPppaY
"ትግራይ የሚዋሰነው ኣልውሃ ምላሽ ነው። ኣልውሃ ምላሽ ማለት ወልዲያ ኣጠገብ ያለው ወንዝ ማለት ነው። ልዑል ኣልጋ ወራሽ የእሳቸው [ኣጼ ሃይለ ሥላሴ] ልጅ ናቸው። የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት ወራሽ ናቸው። ወሎ በሳቸው ስር ስለነበር ለወሎ ግዛት እንዳያንስ ተብሎ ከቆቦ ጀምሮ ኣንድ ኣውራጃ ለወሎ ተሰጥተዋል። "በዛን ጊዜ ልዑል ራስ ስዩም ነበር የሚያስተዳድሩት። በኛ እድሜ የተደረገ ነው የምነግርህ። የቆየ ታሪክ ኣይደለም።"
9) ልዑል ራስ መንገሻ ስዩም ከVOA ጋር ባደረጉት ቃለ መጠየቅ የቀረበላቸው ጥያቄ በርስዎ ዘመን ወልቃይትና ራያ የትግራይ ኣካል ነበር? የሚል ነበር:: ልዑሉ ኣይደለም ብለው በትክክል መለሱ:: በኣባታቸው ዘመን ግን ሃቁ ሌላ የነበረ መሆኑን ወልቃይት ስሜንና ራያ የበጌምድርና ወሎ ኣካል የሆኑት በ1940ዎቹ መሆኑን በግልጽ ለትግራይ ሚድያ ዘርዝረው ተናግረዋል። Link: https://www.youtube.com/watch?v=Ueh8YnWvFF4&t=38s
10) ራያ ቆቦ ወደ ወሎ በመወሰዱና የትግራይ ክ/ሃገር በተለይም የትምርት ሚ/ሩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ገቢ በመቀነሱ: ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዋናው የሚ/ር መ/ቤት የ10 ወደ ትግራይ የተመደቡ መምህራንን ደሞዝ እንዲሸፍን በ1940ዎቹ የጠየቀበት ደብዳቤ
ወዘተ ... ሌሎችም ብዙ ማስረጃዎች ተሰንደው በብዙ ሰዎች እጅ ይገኛሉ::
የወልቃይት ስሜን መንደሮች ከጥንት እስከ ዛሬ የትግርኛ ስሞች
=============================
ማይ ጋባ
ማይ ጨዓ
ማይ ጥምቀት
ማይ ሑመር ላዕላይ
ማይ ሑሞር ታሕታይ
ማይ ጸብሪ
ማይ ካድራ
ማይ ድንሽ (ማይ ቤት ፅምብላይ)
ዓዲ ረመጽ (ማይ ቤት ሕዱግ)
ዓዲ ፍልሖ
ዓዲ ጋባ (ማይ ቤት ሻኩር)
ዓዲ ኮኾብ (ማይ ቤት ኮኾብ)
ዓዲ ሳግላ
ዓዲ ሰላም
ዓዲ ጃሞስ
ዓዲ ፍልሖ
ማይ ጥምቀት
እንዳ ኣቦ
ዓፍራታት
ሞጉእ
ዓዲ ወርቂ
ዓፍራታት
ሞጉእ
ምድሪ ወይዘሮ
ሰላሳ ዓይና
ክሳድ ደለሳ
ደለሳ ቆቋሕ
ሩባ ለሚን
ቤት ሙሉ
ዕዳጋ ሰሉስ
ዓዲ ወርቂ
ብላምባ ቅርሺ
ሽሬላ (ማይ ቤት በላይ)
ብላምባ ሚኪኤል
ላምባ ኩሊታ
መጉእ
ቃሌማ
ዋልድባ
መዘጋ
ታቦር
ዓዲ ገምጢላ
ሶላ
ቃፍታ
ሸሪፍ ሓመድ
ደጀና (ማይ ቤት ለኣከማርያም)
ፅልዕሎ (ማይ ቤት ባይሩ)
ኣውራ (ማይ ቤት ጋድ)

ተፃፈ በ ዳግም ዉልደት 👇
https://bit.ly/3yRZv1O
Please wait, video is loading...

Post Reply