Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30901
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ጾም በጉራጌኛ

Post by Horus » 30 Mar 2023, 01:48

ኩዳዴ አልቆ ፊቸ (ፋሲካ) ላይ እየደረስን ነው! ዛሬ ስለ ጾም ስረ ቃልና ስነ ቃል አንድ ሁለት ነገር ጀባ ልበላችሁ !

ግዕዝ
ጸመ = ጦመ፣ ጦማ፣ ጦም = ከሁሉ ነገር ተለየ፣ ተገለለ፣ ተቆጠበ፤ ብቻ ሆነ፣ ተነጠለ፣ ከሰው ተለይቶ መጸለይ

ጉራጌኛ ፤
ጦማ = ብቻ፣ ራስ፣ ብቸኛ። አሎን
ቱባ ፣ አንድ ብቸኛ ያልተደባለቀ ንጹህ
ቱማ ፣ ለብቻው የተተከል ዕጽ
ሱማ ፣ ለብቻው የተተከለ ትንሽ ህጻን እንሰት ወይም እንሰት
ሱባ ፣ ሱባኤ፤ ለብቻ ከሰው ተለይቶ የሚደረግ ጾም ወይም ጸሎት
ሰብ፣ ሰው፣ አንድ ብቸኛ ፍጡር፤ ኢንዲቪጇል
ጫቦ፣ ጩባ ከላይ እንዳለው ቱባ፣ ንጹ
ጨቦ ጉራጌ፣ ራስ ገዝ ብቸኛ ጉራጌ
በጮ፣ በቾ ፣ ጨቦ ከቀኝ ግራ ሲጻፍ
ሙጫ ፣ ለብቻ፣ አንድ ሰው ለብቻው
ቁና = አንድ፣ ነጠላ፣ ሲንግል
እያለ ይረባል !!!





Horus
Senior Member+
Posts: 30901
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ጾም በጉራጌኛ

Post by Horus » 30 Mar 2023, 01:59


Post Reply