Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ጉራጌ ለአቢይ አህመድ ጸረ ጉራጌ አቋሙ ያለው መልስ

Post by Horus » 28 Mar 2023, 00:00

አቢይና ብልጽግና የጉራጌ ሕዝብን መብት ለመንፈግ ያቀረቧቸው ድብቆቹን ትተን ቅልጽ ምንክያቶች የሚከተሉት ናቸው ።
(1) የአገር መፍረስ
(2) የሕዝብ ቁጥር ትንሽነት
(3) የባጀት እጦት
(4) የመባረር ፍርሃት
(5) የዕድገት መፋጠን
(6) ትግዕስትና ተስፋ

የአገር መፍረስ
የመጀምሪያው የአቢይ ክርክር ክልል ለጠየቀ ሁሉ ክልል መንስጠት አገር ያፈራል የሚል ነው ። የጉርጌ መልስ መጠይቅ ትግሬ፣ አፋር፣ አማራ፣ ኦሮሞ፣ ባኒሻንጉል፣ ጋምቤላ፣ ሲዳማ፣ ሱማሌ እና ሃረሬ ክልል ሲሆኑ ኢትዮጵያ ፈረሰች ወይ? መልሱ አው ከሆነ አቢይ በቅድሚያ ማድረግ ያለበት እነዚህን 9 ክልሎች አፍርሶ ኢትዮጵያ እንዳትፈርስ ማድረግ ነው። ይህን ሃቅ ወደ ጎን አድርጎ 60% ሕዝቡ ከጉራጌ ክልል ውጭ ነው የሚኖረው የተባለው ጉራጌ ክልል መሆን ኢትዮጵያን ያፈሳል የሚለው ሽባ ምክንያት ማሸማቀቂያ ዘዴ ይባላል ። ጉራጌ እጅግ አድርጎ ኢትዮጵያን ስለሚወድ አገር ልታፈርስ ነው ብለን እናስፈራራው እናእማቅቀው እንደ ማለት ነው ።

በዚህ ምክንያት ስር አቢይ አህመድ አዳማጭ ማግኘት ከፈለገ አሁን ያሉትን 10 ክልሎች በአስቸኳይ አፍርሶ አዲስ የፌዴራል ሲስተም የሚቀርጽ የሕገ መንስት ምሻሻያ ረቂቅ ለመላ የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ለፖለቲካ ፓርቲዎችና ለፓርላማ ካቀረበ ብቻ ነው ። ይህ እስካልሆነ ድረስ የአገር መፍረስ ማስፈራሪያ የጉራጌ ሕዝብን ሕጋዊ መብት ማፈኛ የዕብሪት ክርክር ነው ።

የሕዝብ ቁጥር ትንሽነት
ሌላው በግልጽ የማይባለው የአቢይ አህመድ ጸረ ጉራጌ ምክንያት የጉራጌ ሕዝብ ቁጥር ትንሽ ስለሆነ ክልልነት አይገባውም የሚል ነው። የአንድ አገር ሕዝብ ባማካይ በየ20 አመት በእጥፍ ያድጋል ። ስለጉራጌ ቁጥር ሲነሳ ሁልግዜ ተደጋግሞ የሚጠቀሰው የዛሬ 50 እና 40 አመት ይባል የነበረውን ነው ። ይህን ምክኛት አቢይ የምር የሚያምንበት ከሆነ በመላ ኢትዮጵያ ስንት ጉራጌ እንዳለ እንዲቆጠር ያድርግ ። በአንድና ሁለት ወር ውስጥ የሚሰራ ስራ ነው ። ማንም ሃቀኛ ኢትዮጵያዊ እንደ ሚያውቀውና እንደ ሚገምተው ጉራጌ በሕዝብ ብዛት በኢትዮጵያ 4ኛው ወይም 5ኛው ሕዝብ ነው ። ስለሆነም ክልል የሚሰጠው በሕዝብ ብዛት ከሆነ ጉራጌ 4ኛው ወይም 5ኛው ክክል መሆን ነበረበት፣ አለበት ።

የባጀት እጦት
ሌላውና ትልቁ የአቢይ አህመድ ጸረ ጉራጌ ክልልነት ምክንያት ጉራጌ ከዞንነት ከፍ ብሎ ክልል ከሆነ የጉረጌ ክልል መንግስት ደሞዝናና የጉራጌ ክልል እድገት ባጅት አይኖረም የሚል ነው ። የጉራጌ ይህን የመንስትና የእድገት ወጪ ምን እንደ ሆነ ሳያስብ አይደለም ለ31 አመተት ክልልነት የጠየቀው ። ጉራጌ ክልል በመሆን የማይገባውን ፌዴራል ባጀት ለማግኘት አይደለም ክልል ለመሆን የፈለገው ። ጉራጌ ከምንም በላይ ሕዝባዊ ሕልውናውን፣ እራሱን የማስተዳደር መብቱን፣ እራሱን በራሱ የማልማት ችሎታውን እና ቋንቋና ባህሉን ለመጠበቅ ነው ክልልነት የሚፈልገው። ስለባጀት ከሆነ ክልሉ ሕጋዊ ሲሆን ከፌዴራል መንግስቱ ጋር የሚያደርገው ድርድር እንጂ የጉራጌ ሕዝብን ሕጋዊና ፍትሃዊ ራስ የመግዛት መብት በምንም መንገድ ከመንግስት ሰራተኛ ደሞ ጋር አይቋለፍም ። ከዚያ በተረፈ ጉራጌ በራሱ ገንዘብ የመንግስቱ ሰራተኞችን ደሞዝ መክፈል የሚችል ሕዝብ ነው ።

የመባረር ፍርሃት
በተለይ የናዝሬቱ ጉራጌ ብርሃኑ ነጋ ጉራጌ ክልል ከሆነ ከየቦታው ስለሚባረር ጉራጌ የትም ሄዶ እንዲሸቅል ማንነቱን ማንሳት፣ መብቱን መጠየቅ ፣ እንደ ሕዝብ ባህልና ቋንቋውን መከላከል የለበትም ይለናል ። ይህ በመሰረቱ አሳፋሪ ምክንያት ብቻ ሳይሆን ሺመልስ አብዲሳ እንኳን ይህን አላለም ። ብርሃኑ ይህን አጎብዳጅ ህሳቤ ሲሰነዝር የካደው ነገር ጉራጌ ክልል ሳይሆንም የጎሳ ሁከት በተበሳ ቁጥር ከሌሎች አማራዎች ወላይታዎች ስልጤዎች ጋር እንደ ሚዘረፍና እንደ ሚነቅል ነው እሱ የካደው ። ለዚህ ደሞ ቢያንስ ማለት የነበረበት ጉራጌ ክልል የመሆን ሬፈረንደም ሲያደርግ ከጉራጌ ዞን ውጭ በመላ ኢትዮጵያ አሉ የሚባሉት 60%ች ድምጽ መስጠት አለባቸው ቢል ነበር ሰው የሚሰማው ። የጉራጌ ሕዝብ በመባረር ፍርሃት ማንነቱን ክዶ በባርነት የሚኖር ሕዝብ አይደለም ። የብርሃኑ ችግር ጉራጌ ምን አይነት ሕዝብ እንደ ሆነና ሳይኮሎጂው ምን እንደ ሆነ የማያውቅ ሰው ነው ።

የዕድገት መፋጠን
ሌላው ትልቁ የአቢይና ብልጽግና ፓርቲ ምክኛት ለተፋጠነ እድገት ሲባል በኩታ ገጠም ክለስተር መዋቀር አስፈላጊ ነው የሚል ነው ። ይህ ከሳይንስ የራቀ ህሳቤ ነው ። አዲስ አበባ፣ ናዝሬት፣ አዋሳ፣ ድሬደዋ አሰላ ወዘተ ያደጉት ኩታ ገጠም ስለሆኑ ሳይሆን የሁሉም ታታሪና ፈጣሪ ኢትዮጵያዊ በሰላምና ፍቅር መናሀሪያ ስለነበሩ ነው ። በጉልበት ተጨፍልቀው ክለስተር የሆኑ ሕዝቦችና ከተሞች የሁከትና፣ የጥላቻና የውድመት ማ ዕከሎች ናቸው ። ዛሬ ላይ ተጨቁነው ነው እንጂ ወልቂጤና ቡታጀራ ያን የመሰሉ የሰላምና ትጋት መናሀሪያዎች ናቸው ። ጉራጌ ክልል ሲሆን የሚሆነው ያ ነው ። በሌላ በኩል በትክክልም በደምና በታሪክ የተሳሰሩ ጎሳዎች በፈቃዳቸው በአንድ ክልል እንደራጅ ካሉ ያ ትክክለኛ መንገድ ነው ። ለምሳሌ ነገር ስልጤ ተነስቶ በጉራጌ ክልል አንድ ዞን መሆን እፈጋለሁ ካለ ጉራጌ በደስታ የቀበለዋል። እስከ የዛሬ 30 አመት ድረስ አንዱ የጉራጌ ጎሳ ስለነበሩ ማለት ነው ።

ስለዚህ ጉራጌ በውድም ሆነ በግድ ክልል የሚሆነው ዛሬ ላይ እንደ ሕዝብ የመጥፋት፣ እንደ ባህል እንደ ካልቸር የመሞት፣ መሬቱ የመወረር፣ ቋንቋና እሴቱ የመደምሰስ፣ እንደ ሕዝብ የመበተን፣ የማደግና የመዘመን እምቅ ሃይሉና ብቃቱ ባክኖ የመክሰም ግዙፍ እጅግ ግዙፍ አደጋ ላይ ያለ ሕዝብ ስለሆነ ነው ። ይህም እጅግ አስፈሪና አሳዛኝ የጉራጌ ሕዝብ ፍርሃትና ጭንቀትን ነው አቢይ አህመድ አሊና ብርሃኑ ነጋ ቦንጋ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ሊሸፋፍኑ የሚባክኑት ። አይሳካላቸውም ! የኢትዮጵያ ሕዝብ ከጉራጌ ጎን ቆሞዋልና!!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
ሆረስ ነኝ


Post Reply