Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Thomas H
Senior Member
Posts: 12606
Joined: 27 Jan 2007, 16:30
Location: Kaliti
Contact:

Graphic ! ትውልደ ወላይታ ካህን ጎንደር ውስጥ ተገደሉ

Post by Thomas H » 27 Mar 2023, 08:39

Hailemichael Tadesse
3h

ቆሞስ አባ ወልደገብርኤል ትናትና በጎንደር አገልግሎት ላይ እያሉ በጥይት ተመትተው ህይወታቸው ማለፉን ከቤተሰቦቻቸው የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ቆሞስ አባ ወልደገብርኤል ይባላሉ፤ የተወለዱት በዎላይታ ዳሞት ጋሌ ቦድቲ አካባቢ ሲሆን ከልጅነታቸው ጀምሮ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን በተለያዩ ቦታዎች ያገለገሉ ሲሆን ለረጅም ጊዜ ትናንት ህይወታቸው እስካለፈበት ድረስ በጎንደር ጩጌ ማርያም ገዳም እያገለገሉ ነበር።
"ዛሬ በዋልድባ ገዳም ሥርዓተ ቀብራቸው የተፈፀመ ቢሆንም ነገ የባልያ ሥነስርዓት እትብታቸው በተቀበረችበት በዎላይታ አካባቢ ጫዎ ካሬ በሚባል ቦታ ደርሳችሁ ቤተሰቦቻቸው እንድታፅናኑ" ስሉ ቤተሰቦቻቸው በላኩት መረጃ ጥሪ አቅርቧል።
Wolaita Times
በተመሳሳይ ሁኔታ ቀሲስ ዐባይ መለሰ በሸገር ከተማ በድንጋይ ተደብድበው እንደሞቱ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ከሰጠው መግለጫ መረዳት ችለናል።
የሁለቱንም ነፍስ አምላክ በገነት ያኑር።
ነገር ግን በሸገር ለሞቱት አባት በተሰጠ ትኩረት ልክ በጎንደር ለተገደሉት የወላይታው አባት ምንም ትኩረት አልተሰጠም። በተለይ የቤተክርስቲያን መሪዎች እና መዋቅሮች የወላይታውን አባት ጉዳይ አስመልክቶ ምንም ሲሉ አልተስተዋሉም። ምንም መግለጫ ከጎንደር ሀገረ ስብከት አልተሰማም። በማኅበራዊ ሚዲያም ሆነ በሌሎች ሚዲያዎች ከWolaita Times ውጭ ሌሎች ሚዲያዎች የወላይታውን አባት ጉዳይ ሲዘግቡ አልተስተዋለም። የሁሉ እናት የሆነች ቤተክርስቲያንን ገጽታ የሚያበላሽ የዚህ ዓይነቱ አካሄድ ተገቢነት የለውም።
ጎዶልያስ!