Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30911
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የብርሃኑ ነጋ 2 ጽኑ በሽታዎች፡ ፓቶሎጂካል ኦቢሲቲ & ፓቶሎጂካል የፖለቲካ መጃጀት !!

Post by Horus » 27 Mar 2023, 01:38

ብርሃኑ የባለ ሆቴሉ ነጋ ቦንጋ ልጅ ነው! ብዙ ምግብ ሲያይና ሲበላ እያየ ያደገ ልጅ ነው ። ምግብ ማብሰል እንደ ሚወድና ምግብ መስራት ለሱ ቴራፒው እንደ ሆነ ባዳባባይ ነግሮናል ! ዛሬ ላይ ግን እሱ ለ31 ሚሊዮን ወጣት ምሳሌ ሳይሆን የምግብ ጀንኪዎች ምሳሌ ነው! በቃ ብርሃኑ ነጋ አፉንና ሆዱን መቆጣጠርና ዲሲፕሊን ማድረግ ሳይችል ጉራጌ እንዴ መደራጀት እንዳለበት መዝለፍ የተማረው ካለቃው ከዚያ ትዕቢተኛ ወጠጤ ነው !

የብርሃኑ ነጋ ወቅታዊ እጅግ ክሪቲካል በሽታ የፖለቲካ መጃጀት ፖሊቲካል አልዛይመር ነው ። አንድ አይምሮው በትክክል የሚሰራ ሽማግሌ በፖለቲካ ውስጥ ከ15 አመቱ ጀምሮ የኖረ አንድ ሕዝብ ይህን እፈልጋለሁ ሲል ቢያንስ ቢያንስ እሺ እንግዲያው ይህ ሃሳብ የብዙሃኑ ለመሆኑ ሬፈረንደም ወይም ፕሌፕሳይት ይደረግ ያላል እንጂ አይ ይህ ሃሳብ ለዚህ ሕዝብ ጥሩ አይደለም ፣ አይገባቸውም የሚል የፖለቲካ መርህ ሜሞሪው በአልዛይመር የተደለተ ሆኖ ሲገኝ አይደልም ማናደድ እጅግ ያሳዝናል! ትራጂክ ነው !

ጉራጌ ስንትና ስንት ብሩህ ወደፊት ህይወት ያለው ታላቅ ሕዝብ፣ ትሁት ሕዝብ፣ ትጉህ ና የፍቅር ሕዝብ፣ ጽኑ ሕዝብ ነው ! አቢይና ብርሃኑ ለግርጌ ማስታውሻ ፉት ኖት የማይበቁ የታሪክ ጤዛዎች ናቸው ! ጉራጌ ይቀጥላል! ኢትዮጵያ ዘላለማዊ ! ይህ ነው የሆረስ አቋም !! እኔ ብርሃኑንም አቢይንም የተሟገተሟገትኩላቸው ኢትዮጵያን ወደ ፊት ይገፋሉ ብዬ ነው ! በኔ እምነትና ሕይወት ደሞ ከጉራጌ በላይ ኢትዮጵያዊ የለም! ከጉራጌ የተሻለ ኢትዮጵያዊ አቢይና ብርሃኑ ሄደው ከማርስ ሊያመጡ ይችላሉ ! ጉራጌ ማለት የዜጋ ፖለቲካ ማለት ነው ! ጉራጌ ባሪያ ሆኖ የዜጋ ፖለቲካ የለም ! ብርሃኑ ነጋ የፖለቲካ ሞት ሞቶዋል ! ኬር !!!!

Wedi
Member+
Posts: 7993
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: የብርሃኑ ነጋ 2 ጽኑ በሽታዎች፡ ፓቶሎጂካል ኦቢሲቲ & ፓቶሎጂካል የፖለቲካ መጃጀት !!

Post by Wedi » 27 Mar 2023, 02:08

Horus wrote:
27 Mar 2023, 01:38

Horus በጣም የሚገርመው እና የሚያሳዝነው ነገር ደግሞ ተምረው የፕሮፌሰርነት ደረጃ ደርሰናል የሚሉና ቀን ከሌት ስለ ዲሞክራሲና ስለ ሰው ልጅ መብት ሲያስተምሩ የሚውሉና እና የሚያድሩ ሰዎች የሚናገሩትን እና የሚሉትን ሆነው አለመገኘታቸው እና ከእናንተ የበለጠ እኛ ነው ለእናንተ የሚሆነውን ነግር ሁሉ የምወስንልላችሁና የምንሰጣችሁ ማለታቸው ነው፡፡ በተጨማሪም በዲሞክራሲ የማያምኑ አሳፍሪዎች መሆናቸው ነው፡፡

የጉራጌ ህዝብ የጠየቀው እኮ ቀላል ጥያቄ ነው፡፡ እነ ብርሃኑ ነጋን እና አብይ አህመድን እያለ ያለው ራሳችሁ የጻፋችሁትን እና አገሪቱን እያስተዳደራችሁ ያለበትን ህገመንግስት አክብሩ ነው፡፡
የግራጌ ህዝብ እየጠየቀ ያለው የኢትዮጵያ ህገመንግስት በሚፈቀደው መሰረት በጉራጌ የክልልነት ጥያቄ ላይ ህዝበ ወሳኔ ይካሄድና ህዝቡ የወሰነው ተቀበሉ ነው እያለ ያለው!!

በእውነት ለመናገር ከእነ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ እና አብይ አህመድ የበለጠ ፀረ ዲሞክራሲ ሰው የሆነ በኢትዮጵያ ምድር ውስጥ ይገኛል? እጅግ አሳፍሪ ሰዎች!!

Tiago
Member
Posts: 2050
Joined: 30 Jul 2018, 02:09

Re: የብርሃኑ ነጋ 2 ጽኑ በሽታዎች፡ ፓቶሎጂካል ኦቢሲቲ & ፓቶሎጂካል የፖለቲካ መጃጀት !!

Post by Tiago » 27 Mar 2023, 02:23

Why can't EZEMA party members demand his expulsion from the party?
the track record of this man shows us he is a very arrogant and selfish individual.

Horus
Senior Member+
Posts: 30911
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የብርሃኑ ነጋ 2 ጽኑ በሽታዎች፡ ፓቶሎጂካል ኦቢሲቲ & ፓቶሎጂካል የፖለቲካ መጃጀት !!

Post by Horus » 27 Mar 2023, 02:37

Wedi,
በትክክል! እኔ እዚህ ሼልፌ ውስጥ የነጻነት ጎህ ሲቀድ ብሎ የጻፈው የብርሃኑ ድጓ ፊቴ ላይ አለ! አፈርኩ ! ግን እኔም የፖለቲካ ሳይንስ ተማሪ ስለሆንኩ (አንዱ ዲግሪዬ) ማንኛውንም ፖለቲካን የሚነዳው ገፊ ነጂ ሞቲቬሽን ስልጣን፣ ገንዘብ፣ ዝና እና ክብር (ማንነት) እንደ ሆኑ አውቃለሁ ! ስለዚህ አንድ ተምሪያለሁ የሚል ፖለቲከኛ እነዚህ 4 ነጂ ፍላጎቶችን በንቃተ ህሊና መለጎም አለበት ። ልብ በል ብርሃኑ ጉራጌን የሚቃወመው አቢይ ከስልጣን እንዳያነሳው ነው! ይህን የሚያደርገው አሲምባ ውስት የነበረው የኢ ህ አ ፓው ብርሃኑ ነው ! ይህን ነው የፖለቲካ አልዛይመር ያልኩት ! ያሳዝናል ያሳፍራል ! አንደ የፖለቲካ ሰው ታሪኩን እንዲህ ስያጎድፍ !! ጉራጌ ደግፈን አላሉትም! ለምን ብሎ የጉራጌ ጥያቄያን እንደ ጠላት የሚቃወመው ? ለዚህ ደሞ በቂ ምላሽ እንስጠዋለን !!!!

Horus
Senior Member+
Posts: 30911
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የብርሃኑ ነጋ 2 ጽኑ በሽታዎች፡ ፓቶሎጂካል ኦቢሲቲ & ፓቶሎጂካል የፖለቲካ መጃጀት !!

Post by Horus » 29 Mar 2023, 01:50

አቢይና ብልጽግና የጉራጌ ሕዝብን መብት ለመንፈግ ያቀረቧቸው ድብቆቹን ትተን ቅልጽ ምንክያቶች የሚከተሉት ናቸው ።
(1) የአገር መፍረስ
(2) የሕዝብ ቁጥር ትንሽነት
(3) የባጀት እጦት
(4) የመባረር ፍርሃት
(5) የዕድገት መፋጠን
(6) ትግዕስትና ተስፋ

የአገር መፍረስ
የመጀምሪያው የአቢይ ክርክር ክልል ለጠየቀ ሁሉ ክልል መንስጠት አገር ያፈርሳል የሚል ነው ። የጉራጌ መልሶ መጠይቅ ትግሬ፣ አፋር፣ አማራ፣ ኦሮሞ፣ ባኒሻንጉል፣ ጋምቤላ፣ ሲዳማ፣ ሱማሌ እና ሃረሬ ክልል ሲሆኑ ኢትዮጵያ ፈረሰች ወይ? መልሱ አው ከሆነ አቢይ በቅድሚያ ማድረግ ያለበት እነዚህን 9 ክልሎች አፍርሶ ኢትዮጵያ እንዳትፈርስ ማድረግ ነው። ይህን ሃቅ ወደ ጎን አድርጎ 60% ሕዝቡ ከጉራጌ ክልል ውጭ ነው የሚኖረው የተባለው ጉራጌ ክልል መሆን ኢትዮጵያን ያፈሳል የሚለው ሽባ ምክንያት ማሸማቀቂያ ዘዴ ይባላል ። ጉራጌ እጅግ አድርጎ ኢትዮጵያን ስለሚወድ አገር ልታፈርስ ነው ብለን እናስፈራራው እናእማቅቀው እንደ ማለት ነው ።

በዚህ ምክንያት ስር አቢይ አህመድ አዳማጭ ማግኘት ከፈለገ አሁን ያሉትን 10 ክልሎች በአስቸኳይ አፍርሶ አዲስ የፌዴራል ሲስተም የሚቀርጽ የሕገ መንስት ምሻሻያ ረቂቅ ለመላ የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ለፖለቲካ ፓርቲዎችና ለፓርላማ ካቀረበ ብቻ ነው ። ይህ እስካልሆነ ድረስ የአገር መፍረስ ማስፈራሪያ የጉራጌ ሕዝብን ሕጋዊ መብት ማፈኛ የዕብሪት ክርክር ነው ።

የሕዝብ ቁጥር ትንሽነት
ሌላው በግልጽ የማይባለው የአቢይ አህመድ ጸረ ጉራጌ ምክንያት የጉራጌ ሕዝብ ቁጥር ትንሽ ስለሆነ ክልልነት አይገባውም የሚል ነው። የአንድ አገር ሕዝብ ባማካይ በየ20 አመት በእጥፍ ያድጋል ። ስለጉራጌ ቁጥር ሲነሳ ሁልግዜ ተደጋግሞ የሚጠቀሰው የዛሬ 50 እና 40 አመት ይባል የነበረውን ነው ። ይህን ምክኛት አቢይ የምር የሚያምንበት ከሆነ በመላ ኢትዮጵያ ስንት ጉራጌ እንዳለ እንዲቆጠር ያድርግ ። በአንድና ሁለት ወር ውስጥ የሚሰራ ስራ ነው ። ማንም ሃቀኛ ኢትዮጵያዊ እንደ ሚያውቀውና እንደ ሚገምተው ጉራጌ በሕዝብ ብዛት በኢትዮጵያ 4ኛው ወይም 5ኛው ሕዝብ ነው ። ስለሆነም ክልል የሚሰጠው በሕዝብ ብዛት ከሆነ ጉራጌ 4ኛው ወይም 5ኛው ክክል መሆን ነበረበት፣ አለበት ።

የባጀት እጦት
ሌላውና ትልቁ የአቢይ አህመድ ጸረ ጉራጌ ክልልነት ምክንያት ጉራጌ ከዞንነት ከፍ ብሎ ክልል ከሆነ የጉረጌ ክልል መንግስት ደሞዝናና የጉራጌ ክልል እድገት ባጅት አይኖረም የሚል ነው ። የጉራጌ ሕዝብ ይህን የመንግስትና የእድገት ወጪ ምን እንደ ሆነ ሳያስብ አይደለም ለ31 አመተት ክልልነት የጠየቀው ። ጉራጌ ክልል በመሆን የማይገባውን ፌዴራል ባጀት ለማግኘት አይደለም ክልል ለመሆን የፈለገው ። ጉራጌ ከምንም በላይ ሕዝባዊ ሕልውናውን፣ እራሱን የማስተዳደር መብቱን፣ እራሱን በራሱ የማልማት ችሎታውን እና ቋንቋና ባህሉን ለመጠበቅ ነው ክልልነት የሚፈልገው። ስለባጀት ከሆነ ክልሉ ሕጋዊ ሲሆን ከፌዴራል መንግስቱ ጋር የሚያደርገው ድርድር እንጂ የጉራጌ ሕዝብን ሕጋዊና ፍትሃዊ ራስ የመግዛት መብት በምንም መንገድ ከመንግስት ሰራተኛ ደሞ ጋር አይቋለፍም ። ከዚያ በተረፈ ጉራጌ በራሱ ገንዘብ የመንግስቱ ሰራተኞችን ደሞዝ መክፈል የሚችል ሕዝብ ነው ።

የመባረር ፍርሃት
በተለይ የናዝሬቱ ጉራጌ ብርሃኑ ነጋ ጉራጌ ክልል ከሆነ ከየቦታው ስለሚባረር ጉራጌ የትም ሄዶ እንዲሸቅል ማንነቱን ማንሳት፣ መብቱን መጠየቅ ፣ እንደ ሕዝብ ባህልና ቋንቋውን መከላከል የለበትም ይለናል ። ይህ በመሰረቱ አሳፋሪ ምክንያት ብቻ ሳይሆን ሺመልስ አብዲሳ እንኳን ይህን አላለም ። ብርሃኑ ይህን አጎብዳጅ ህሳቤ ሲሰነዝር የካደው ነገር ጉራጌ ክልል ሳይሆንም የጎሳ ሁከት በተነሳ ቁጥር ከሌሎች አማራዎች ወላይታዎች ስልጤዎች ጋር እንደ ሚዘረፍና እንደ ሚነቅል ነው እሱ የካደው ። ለዚህ ደሞ ቢያንስ ማለት የነበረበት ጉራጌ ክልል የመሆን ሬፈረንደም ሲያደርግ ከጉራጌ ዞን ውጭ በመላ ኢትዮጵያ አሉ የሚባሉት 60%ች ድምጽ መስጠት አለባቸው ቢል ነበር ሰው የሚሰማው ። የጉራጌ ሕዝብ በመባረር ፍርሃት ማንነቱን ክዶ በባርነት የሚኖር ሕዝብ አይደለም ። የብርሃኑ ችግር ጉራጌ ምን አይነት ሕዝብ እንደ ሆነና ሳይኮሎጂው ምን እንደ ሆነ የማያውቅ ሰው ነው ።

የዕድገት መፋጠን
ሌላው ትልቁ የአቢይና ብልጽግና ፓርቲ ምክኛት ለተፋጠነ እድገት ሲባል በኩታ ገጠም ክለስተር መዋቀር አስፈላጊ ነው የሚል ነው ። ይህ ከሳይንስ የራቀ ህሳቤ ነው ። አዲስ አበባ፣ ናዝሬት፣ አዋሳ፣ ድሬደዋ አሰላ ወዘተ ያደጉት ኩታ ገጠም ስለሆኑ ሳይሆን የሁሉም ታታሪና ፈጣሪ ኢትዮጵያዊ በሰላምና ፍቅር መናሀሪያ ስለነበሩ ነው ። በጉልበት ተጨፍልቀው ክለስተር የሆኑ ሕዝቦችና ከተሞች የሁከትና፣ የጥላቻና የውድመት ማ ዕከሎች ናቸው ። ዛሬ ላይ ተጨቁነው ነው እንጂ ወልቂጤና ቡታጀራ ያን የመሰሉ የሰላምና ትጋት መናሀሪያዎች ናቸው ። ጉራጌ ክልል ሲሆን የሚሆነው ያ ነው ። በሌላ በኩል በትክክልም በደምና በታሪክ የተሳሰሩ ጎሳዎች በፈቃዳቸው በአንድ ክልል እንደራጅ ካሉ ያ ትክክለኛ መንገድ ነው ። ለምሳሌ ነገር ስልጤ ተነስቶ በጉራጌ ክልል አንድ ዞን መሆን እፈጋለሁ ካለ ጉራጌ በደስታ የቀበለዋል። እስከ የዛሬ 30 አመት ድረስ አንዱ የጉራጌ ጎሳ ስለነበሩ ማለት ነው ።

ስለዚህ ጉራጌ በውድም ሆነ በግድ ክልል የሚሆነው ዛሬ ላይ እንደ ሕዝብ የመጥፋት፣ እንደ ባህል እንደ ካልቸር የመሞት፣ መሬቱ የመወረር፣ ቋንቋና እሴቱ የመደምሰስ፣ እንደ ሕዝብ የመበተን፣ የማደግና የመዘመን እምቅ ሃይሉና ብቃቱ ባክኖ የመክሰም ግዙፍ እጅግ ግዙፍ አደጋ ላይ ያለ ሕዝብ ስለሆነ ነው ። ይህም እጅግ አስፈሪና አሳዛኝ የጉራጌ ሕዝብ ፍርሃትና ጭንቀትን ነው አቢይ አህመድ አሊና ብርሃኑ ነጋ ቦንጋ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ሊሸፋፍኑ የሚባክኑት ። አይሳካላቸውም ! የኢትዮጵያ ሕዝብ ከጉራጌ ጎን ቆሞዋልና!!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
ሆረስ ነኝ

DefendTheTruth
Member+
Posts: 9914
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

Re: የብርሃኑ ነጋ 2 ጽኑ በሽታዎች፡ ፓቶሎጂካል ኦቢሲቲ & ፓቶሎጂካል የፖለቲካ መጃጀት !!

Post by DefendTheTruth » 29 Mar 2023, 13:35

According to your own ranting here and there Guraghe is the Aborigines of Ethiopia and where else in this world do Aborigines have got their own Kilil to administer for themselves?

Prof. Berhanu understands what is viable and not viable, the big difference between you and the Prof.

Keep badmouthing everybody around you, the sign of mental deterioration and lack of self-esteem.

Wedi
Member+
Posts: 7993
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: የብርሃኑ ነጋ 2 ጽኑ በሽታዎች፡ ፓቶሎጂካል ኦቢሲቲ & ፓቶሎጂካል የፖለቲካ መጃጀት !!

Post by Wedi » 29 Mar 2023, 15:01

Horus wrote:
27 Mar 2023, 01:38
የብርሃኑ ነጋ 2 ጽኑ በሽታዎች፡ ፓቶሎጂካል ኦቢሲቲ & ፓቶሎጂካል የፖለቲካ መጃጀት !!
:P
አሳፋሪ ብርሃኑ ነጋ ታዋቂው የጎራጌ ህዝብ መብት ተሟጋች የሆነው እና የክልል ምክር ቤት አባላ የሆነው አቶ Tarekegn Degife ከኢዜማ አባረረ!!
:!:
Please wait, video is loading...

Post Reply