Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Misraq
Senior Member
Posts: 12407
Joined: 27 Sep 2009, 19:43
Location: Zemunda

በዘር በተቧደነ ቀመር ሥልጣንና በጀት በሚሰራበት ሃገር ብርሃኑ ጉራጌን በዘር አትደራጁ አለ

Post by Misraq » 26 Mar 2023, 17:31

.
.
.
ግን እነዚህ ሰዎች ምን ያህል ማሰቢያቸው ቢደፈን ነው?

Horus
Senior Member+
Posts: 30851
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: በዘር በተቧደነ ቀመር ሥልጣንና በጀት በሚሰራበት ሃገር ብርሃኑ ጉራጌን በዘር አትደራጁ አለ

Post by Horus » 26 Mar 2023, 20:02

ብርሃኑ ነጋ አባቱ ናዝሬት ስለከበሩ ውሃ የሌለው ጉራጌ ክልል አይሁን ያለ የፖለቲካ አልዛመር የደረሰበት ሰው ነው ! እሱ አንድም ቀን ዉሃ አጥቶ አያውቅም፣ ለዚህ ነው ስለማያውቀው ጉራጌ እኔ ነኝ የተሻለ መፍትሄ አለኝ የሚለው ! እነአፋር፣ እነኦሮም እነሱማሌ የራሳቸው ዝሆን የሚያክል ክልል እስከ ጦሩ ይዘው በቅዳሜ ቀን ጉራጌ ድረስ ሄደው ጉራጌ አያስፈልግህም አሉት! ከዚህ የላቀ ስድብ ከየት ይመጣል!

እነዚህ የብልጽግና ወፍራም ድመቶች ወደዱም ጠሉም ጉራጌ ትግሉን ይቀጥላል ! እነሱም በሰላም አይገዙም !!

Abere
Senior Member
Posts: 11071
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: በዘር በተቧደነ ቀመር ሥልጣንና በጀት በሚሰራበት ሃገር ብርሃኑ ጉራጌን በዘር አትደራጁ አለ

Post by Abere » 26 Mar 2023, 20:22

ሆረስ፤

በመጀመሪያ የሚናገረው ነገር ፍጹም የተጣረሰ/የተፋለሰ ነው። ውሸት የሆነ ሀሳብን ለመደገፍ እንደ መከራከር አስቸጋሪ ነገር አይቸ አላውቅም። ይህን ያልኩበት ምክንያት። ጉራጌ ክልል መሆን የለበትም የሚለው እኮ የአብይን ፍላጎት የማርካት ነው እንጅ ጉራጌ በሌላ ክልል ውስጥ ሲዋጥ እሳት ካየው ምን ለየው አይነት ነው እኮ። አስከትሎት የሄደው አብይ አህመድ ለምን ኦሮሞ ክልል አያስፈልገውም አይልም ነበር። ለኦሮሞ የሚጣፍጠው ለጉራጌ ይመረዋል ብሎ ነገር አለ እንደ? እንደ ሰወኛ ሲታሰብ። ዶ/ር ብርሃኑ የገረመኝ ደግሞ የጉራጌን በልማት ወደ ኋላ መቅረት እራሳቸውን መከላከል በማይችሉ የዞኑ መሪዎች ላይ ያሳብባል። ዋናው ምክንያት ግን ጉራጌ ክልል ባለመሆኑ እንደ ዞን የሚያገኘው በጀት በጣም ትንሽ ናት እንደ ክልል ሲሆን ግን 1ኛ) የቢሮክራሲ ሰንሰለቱ አጭር ይሆንለታል 2ኛ) እንደ እራሱ ህዝብ ብዛት በቂ በጀት ያገኛል። ትውልዱ የእራሱን ክልል የማልማት እድል ይኖረዋል።

Horus wrote:
26 Mar 2023, 20:02

Post Reply