Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30657
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የኢትዮጵያን ምግብ ችግር የፈታው ኤርትራዊ! ወንዳታ!!! ተስፋ ድራር !!

Post by Horus » 25 Mar 2023, 01:01

ኒው ሜክሲኮ የበርበሬ አገር ነው !!! ልክ እንደ ማረቆ ማለት ነው። ከመገረም በስተቀር ምን ማለት ይቻላል???? ሰማችሁ ይህ ሰው ምን እንደሚል? አሚሪካ ለእርዳታ የሚልከውን [deleted] ስንዴ ትቶ ተስፋ ጤፍ በምትኩ እንዲልክ ካሜሪካ ዩኤ ኤ አይ ዲ ጋር እየተነጋገረ ነው ! ድንቅ!

Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የኢትዮጵያን ምግብ ችግር የፈታው ኤርትራዊ! ወንዳታ!!! ተስፋ ድራር !!

Post by Meleket » 25 Mar 2023, 04:45

ይሄ ጀግና፡ ወደ ሃገሩ ወደ ኤርትራም ትኩረት በማድረግ፡ ሃገሩ ላይ ይህ ነው ሊባል ዬሚችል የልማት ስራ እንዲሰራ ቢጠይቅ መልካም ነው። ምክንያቱም ሃገረ ኤርትራ ውስጥ በህዝብ ገንዘብ የተገነቡ ግድቦችን በሙሉ፡ ተሃዳሲ የሃይል ኣቅርቦት በመትከል፡ ለልማትና ለኢንዱስትሪያዊ ልማት መዋል ይገባቸዋልና።

የኤርትራዊው ተስፉ ድራርና የኢትዮጵያዊው ኤርሚያስ ጠቅል ኣመልጋም የስራ ባህርይና ቁርጠኝነት እጅግ የሚያኮራ ነው። ዬሚያሳዝነው "ነቢይ በሃገሩ ኣይከበርም" ሆነ እንጂ ነገሩ! የኛው ወደል ካድሬ ዘሜ Zmeselo እና መሰል ሪሞርኬ ካድሬዎቹ ይህን ዓይነቱን ጀግና ኤርትራዊ በኤርትራዊ ሚዲያ ሲያስተዋውቁት ሰምተን ኣናውቅም። እነሱ ትኩረታቸው ብስክሌትና ኳስ ተጫዋች ላዪ እንዲሁም ተወዛዋዥና የፋሽን ሸው ሰዎች ላዪ ብቻ ይመስላል። ያሳዝናል ዬካድሬ ነገር!
:mrgreen:
Horus wrote:
25 Mar 2023, 01:01
ኒው ሜክሲኮ የበርበሬ አገር ነው !!! ልክ እንደ ማረቆ ማለት ነው። ከመገረም በስተቀር ምን ማለት ይቻላል???? ሰማችሁ ይህ ሰው ምን እንደሚል? አሚሪካ ለእርዳታ የሚልከውን [deleted] ስንዴ ትቶ ተስፋ ጤፍ በምትኩ እንዲልክ ካሜሪካ ዩኤ ኤ አይ ዲ ጋር እየተነጋገረ ነው ! ድንቅ!

Digital Weyane
Member+
Posts: 8407
Joined: 19 Jun 2019, 21:45

Re: የኢትዮጵያን ምግብ ችግር የፈታው ኤርትራዊ! ወንዳታ!!! ተስፋ ድራር !!

Post by Digital Weyane » 25 Mar 2023, 05:01

ጁንታዋይ ዎንድሜ Meleket በቡዙ አጋጣሚዎች በተደጋጋሚ እንዳብራራው ፣ በትግራይ የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ ስላልቻልን ነው እስካሁን መገንጠል ያልተቻለን። ሻዕዉያው ገበሬ በአሜሪካ አገር ጤፍ አምርቶ ዎደ ትግራይ በእርዳታ መልክ የሚልክልን ከሆነ ትግራይን የመገንጠል ዓላማችን ሊሳካ ይችላል ብለን እናምናለን። አሜሪካ ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ! ጆ ባይደን ጀግና ነው! :roll: :roll:

Selam/
Senior Member
Posts: 11549
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: የኢትዮጵያን ምግብ ችግር የፈታው ኤርትራዊ! ወንዳታ!!! ተስፋ ድራር !!

Post by Selam/ » 25 Mar 2023, 05:49

ሻቢያ እና ጁንታ እየተባባላችሁ በአማርኛ መከራከራችሁን ወድጄዋለሁ። ለእኛ ምን ያህል እንደምትጨነቁልን ነው የሚያሳየው። የዩክሬንና ራሽያ ካድሬዎች ያላስተርጓሚ ለዓለም ታዳሚዎቻቸው በእንግሊዘኛ ሲከራከሩ እንደማየት ማለት ነው።

Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የኢትዮጵያን ምግብ ችግር የፈታው ኤርትራዊ! ወንዳታ!!! ተስፋ ድራር !!

Post by Meleket » 27 Mar 2023, 09:40

ወዳጃችን Selam/ እነማን ናቸው “ሻቢያ እና ጁንታ” እየተባባሉ የተከራከሩት? እላይ ሁለቱንም ቃላቶች ያወጣው አንድ ሰው መሆኑ ምስክር ኣያስፈልገውም። ክርክር ሳይሆን ውይይቱ በኣማርኛ መሆኑን እንኳን ወደድሽው። ዓላማችን 120 ሚልዬን ሰው ማንቃትና የኤርትራውያንን ኣቋም (የጦርነት ጥቅመኞችን ኣያጠቃልልም) ለሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ ማስጨበጥ መሆኑን ዘንግተሻል። :mrgreen:

እኛ ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ ለማንኛውም ሰላም ወዳድ ኣካል ድጋፋችንን ስንለግስ፡ ማንኛውም ጦር በመስበቅ ብቻ በንጹሓንና በምስኪኖች ደም ‘ቦለቲካ በመስራት” ስልጣን ላይ ሊፈናጠጥ ለሚሻ የጦርነት ጥቅመኛና (ጦ.ጥ.) ምድረ ካድሬ፡ እንቅልፍ ኣልሰጠውም። ለማንኛውም ወራሪ ኣካላትን (ሩሲያን ጭምር) እያወገዝን፡ እግረመንገዳችንንም “እንኳን ኢትዮጵያዉያን ቦተሊከኞች በታላቁ ኣብዪ ኣሕመድ ኣመራር፡ ችግራቸውን በጠረጴዛ ዙርያና በሰላም ለሚፈቱበት ግዜ ኣደረሰሽ” ስንል፡ በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር ደስታችንን እንገልጽልሻለን።

መቼም “ኣማርኛ” ያፍሪካ ህብረት ቋንቋ ይሆን ዘንድ እዬተሰራ ኣይደል፤ እኛም ኤርትራውያኑ ሙሉ ድጋፋችንን እየሰጠን ነው . . . ደስ ይበልሽ ታለም! ለኢትዮጵያ ህዝብ እኛ ሰላም ወዳድ ኤርትራውያን ያልተጨነቅንለት ማን ይጨነቅለት፡ ምድረ ኢትዮጵያዊና ኤርትራዊ ካድሬና የጦርነት ጥቅመኛ እንደሆን፡ ሥልጣን ላይ ፊጢጥ ለማለት ነው፡ በዬቦታው ሁከትና ጥላቻ እዬዘራ ህዝብን እርስበእርስ ለማባላት ቢላዋ የሚስለው! ኣይደለም እንዴ ታለም?
:mrgreen:
Selam/ wrote:
25 Mar 2023, 05:49
ሻቢያ እና ጁንታ እየተባባላችሁ በአማርኛ መከራከራችሁን ወድጄዋለሁ። ለእኛ ምን ያህል እንደምትጨነቁልን ነው የሚያሳየው። የዩክሬንና ራሽያ ካድሬዎች ያላስተርጓሚ ለዓለም ታዳሚዎቻቸው በእንግሊዘኛ ሲከራከሩ እንደማየት ማለት ነው።

Post Reply