Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

"2.5 ሚልዮን ብር በብላክ ተመዝሮ ወደ አሜሪካ አሽሽተናል" አንዳርጋቸው ጽጌ ሕገወጥ የገንዘብ ሽሽት መፈጸሙ ያመነበት ቪድዮ በAndafta ተላለፈ

Post by sarcasm » 21 Mar 2023, 17:24




"ከዚህ ከአገርቤት እንደለመድነው ገንዘብ በብላክ (black market) እየመነዘርን [ወደ አሜሪካ እየላክን] subsidize እናደርገዋለን" አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ

የኢትዮጵያ ሕግ ስለ ሕገወጥ የገንዘብ ምንዛሬ ምን ይላል?
የኢትዮጵያ ሕግ ስለ ሕገወጥ የዶላር ወደ ውጭ አገር ሽሽት ምን ይላል?


sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: "2.5 ሚልዮን ብር በብላክ ተመዝሮ ወደ አሜሪካ አሽሽተናል" አንዳርጋቸው ጽጌ ሕገወጥ የገንዘብ ሽሽት መፈጸሙ ያመነበት ቪድዮ በAndafta ተላለፈ

Post by sarcasm » 28 Mar 2023, 08:18

አቶ ኣንዳርጋቸው ስለ ሕግና ሕጋዊነት ምን እያሉ ነው ሰሙኑን? መንግስት ስ ለምንድነው የኣገሪቱ ሕግ ስለመስበሩ በግልጽ በሚድያ ጥፋቱን ላመነ ሰው ወደ ሕግ ፊት የማያቀርበው?

sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: "2.5 ሚልዮን ብር በብላክ ተመዝሮ ወደ አሜሪካ አሽሽተናል" አንዳርጋቸው ጽጌ ሕገወጥ የገንዘብ ሽሽት መፈጸሙ ያመነበት ቪድዮ በAndafta ተላለፈ

Post by sarcasm » 02 Apr 2023, 10:17

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎትና ብሔራዊ ባንክ ህገወጥ የውጭ ምንዛሪና የገንዘብ ዝውውር ተዋናዮችን በጥናት በመለየት ቀጣይ እርምጃ እንደሚወሰዱ አስታወቁ
****************************
የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎትና ብሔራዊ ባንክ ህገወጥ የውጭ ምንዛሪና የገንዘብ ዝውውር ተዋናዮችን በጥናት በመለየት ቀጣይ እርምጃ እንደሚወሰዱ አስታውቀዋል።
የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት በህገወጥ የገንዘብ ዝውውርና ህገወጥ የውጭ ምንዛሪ እንቅስቃሴ ዙሪያ ያካሄደው ሰፋ ያለ ጥናት ዛሬ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ይፋ ሆኗል።
አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ ለኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ የብሔራዊ ባንክ ገዢ ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት፣ የተለያዩ የመንግስት ተቋማት የሥራ ሃላፊዎች፣ ኮሚሽነሮች እንዲሁም የደኅንነት እና የፀጥታ ተቋማት ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት በተሳተፉበት የውይይት መድረክ የቀረበው ጥናት በዘርፉ ያሉትን ችግሮች እንዲሁም የተለያዩ የውጭ ሀገራትን ተሞክሮም ጭምር በጥልቀት የዳሰሳ ነበር።
የጥናቱን ግኝቶች መነሻ በማድረግ ህገወጥ የውጭ ምንዛሬና የገንዘብ ዝውውርን ሰንሰለት ለመበጠስ እንዲሁም የድርጊቱ ተዋናዮች ላይ እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል የፖሊስ፣ የሥርዓትና የተጠያቂነት መፍትሄዎችን የሚጠቁሙ ምክረ ሐሳቦችን እንዲሁም በቀጣይ ሊወሰዱ የሚገባቸውን ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃዎችንም አመላክቷል።
በጥናቱ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውርና ህገወጥ የውጭ ምንዛሬ ገበያዎች የሀገርን ኢኮኖሚ በማዳከም፣የኑሮ ውድነትን በማናርና ሙስናን በማስፋፋት ሀገርን ለከፋ አደጋ እያጋለጡ እንደሚገኙ ተጠቁሟል።
በህገወጥ ተግባራቱ መንግሥታዊና የግል ተቋማት አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም የውጭ ሀገር ዜጎች ጭምር የሚሳተፉ መሆኑን የጠቆመው ጥናቱ፤ ከውጭ ሀገራት እስከ መሀል ሀገር የተዘረጋው ህገወጥ የጥቅም ትስስር በደላሎች፣ በድርጅቶች፣ በኩባንያዎችና በባንክ ሥርዓቱም ጭምር እንደሚደገፍ አመልክቷል።
ይህም በሀገራችን እየታየ ላለው ቅጥ ያጣ የዋጋ ንረትና ማህበራዊ ችግር አንዱ ቁልፍ ምክንያት መሆኑን አሳይቷል።
የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀኔራል አቶ ተመስገን ጥሩነህ እንዳሉት፤ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውርና ህገወጥ የውጭ ምንዛሬ ንግድ የሀገርን ህልውናና የህዝብን ጥቅም እየተፈታተነ ያለ ብሔራዊ አደጋ መሆኑን በመረዳት አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ በልዩ ትኩረት እየሠራ ይገኛል።
ችግሩን ከመሠረቱ ለመፍታት በሚደረገው ጥረት ውስጥ ሁሉም መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ የንግዱ ማህበረሰብና ህዝቡ በትብብርና በቅንጅት መሥራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
በጥናቱ የተለዩና ችግሩ በስፋት በሚስተዋልባቸው አካባቢዎች፣ተቋማትና ግለሰቦች ላይ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እርምጃ በቀጣይነት የሚወሰድ መሆኑን ነው የገለፁት።

ህገወጥነትን በመቆጣጠር፣ የሀገርንና የህዝብን ህልውና በመታደግ ትግሉ ውስጥ የፀጥታና ደኅንነት ተቋማት፣የፋይናንስ ተቋማት፣የህግ አካላትና ጉዳዩ የሚመለከታቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በሙሉ ተቀናጅተውና ተናበው ሊሠሩ እንደሚገባም አቶ ተመስገን ጥሩነህ አሳስበዋል።
የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ከብሔራዊ ባንክ ጋር በመቀናጀትና ሌሎች አካላትን በማሳተፍ ችግሩ እስኪቀረፍ ድረስ በትኩረት እንደሚሠራም ጠቁመዋል።
የብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ በመድረኩ ላይ እንደተናገሩት፤ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውርና ህገወጥ የውጭ ምንዛሬ ንግድ ባንኩ የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠርና
የውጭ ምንዛሬ ግኝትን በአግባቡ ለማስተዳደር እንዳይችል እንቅፋት ሆነዋል፡፡
ችግሩን ከመሠረቱ ለመፍታት ጥረት እየተደረገ ነው።
የውጭ ምንዛሬ ብቻ ሳይሆን የብር እንቅስቃሴውም ከባንክ ሥርዓት ውጭ በመዘዋወር ላልተፈለገ ዓላማ እየዋለ መሆኑ ተደርሶበታል ያሉት የብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ፤ በርካታ የብር ኖቶችን ከባንክ ሥርዓት ውጭ በማንቀሳቀስ ላልተፈለገ ዓላማ በሚያውሉ ወንጀለኞች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ተናግረዋል።
በቀረበው ጥናት ላይ ውይይት ያደረጉ የብሄራዊ ባንክ ገዢን ጨምሮ የመድረኩ ተሳታፊዎች የቀረበው ጥናት አጠቃለይ ችግሩን፣የችግሩን ተዋንያን እና የመፍትሄ ሐሳቦችን በሚገባ ያመላከተ በመሆኑ ለአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ምስጋና ማቅረባቸውን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በላከው መረጃ አመልክቷል።

sesame
Member+
Posts: 5927
Joined: 28 Feb 2013, 17:55

Re: "2.5 ሚልዮን ብር በብላክ ተመዝሮ ወደ አሜሪካ አሽሽተናል" አንዳርጋቸው ጽጌ ሕገወጥ የገንዘብ ሽሽት መፈጸሙ ያመነበት ቪድዮ በAndafta ተላለፈ

Post by sesame » 02 Apr 2023, 12:28

What is the matter with these Agames? Why are they so stupid? Sarko, your TPLF leaders stole 30 billion US dollar which they have siphoned in foreign banks. And yet you think there is traction in this idiotic post about Andarkachew Tisge? What is 2.5 million birr, 50,000 US dollars, right? Sibhat Nega has probably spent that much on his medical expenses in one week. God, I can't stand these idiots!

Post Reply