Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30908
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

አቢይ አህመድ አሊ ከጉራጌዎች ጋር ሃሙስ ሊሰበሰብ ነው! ለምን አሁን?

Post by Horus » 21 Mar 2023, 00:29

የሆረስ ግምት ልንገራችሁ! አቢይ የጉራጌ ሃብታሞችና ጥቂት አጎብዳጅ ምሁራኖችን ሰብስቦ ያስፈራራል ! ጉራጌን ለመከፋፈል ብዙ ብዙ እንደ ሚል እነጠብቀዋለን !!ያ ጉራጌ አይቀበለውም! ጉራጌ አንድ ጥያቄ አለው! ክልል መሆን ነው ! ኦሮሞች የጉራጌን ክልልነት እንደ አላማቸው የሚቃወሙ ከሆነ ጉራጌ ደሞ ይህን የግፍ አገዛዝ እንዲፈርስ በመላው ኢትዮጵያና አለም ላይ ትግሉን በእልፍ እጥፍ ያቀጣጥላል ! ጉራጌ ክልል ነው ! አቢይ አህመድ በሌላ ድራማ ግዜህን አታባክን


Horus
Senior Member+
Posts: 30908
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አቢይ አህመድ አሊ ከጉራጌዎች ጋር ሃሙስ ሊሰበሰብ ነው! ለምን አሁን?

Post by Horus » 21 Mar 2023, 01:22

የጉራጌ ድምጽ በኦሮሞች ተባባሪነት ለ27 አመት ታፍኖ ኖሮዋል ! ኦ ኤል ኤ ከመለስ ጋር ሆኖ መላ ጉራጌን በኦሮሚያ ስር ለማካለለ ተነስቶ ሲያቅተው ሶዶ ጉራጌን ለሁለት ከፍሎ ሶዶ ጂዳ የሚባሉ የጉራጌ ኦሮምችን ፈጥሮ በመለስ መንግስት ውስት ግዙፍ ስልጣን በኦሮሞ ስም የተሰጣቸው እነ ፕሪዜዳንት ግርማ፣ እነ ግርማ ብሩ የዛሬው ቢይ ቁልፍ አማካሪዎች እና ሌሎችም ፤ ስልጤን ከጉራጌ ገንጥለው የዛሬውን ሬድዋንን የፈለፈሉ የትግሬ ወያኔዎች ናቸው ።

ዛሬ ይህን ስጽፍ ሺመልስ አብዲሳ 3 የጉራጌ ወረዳዎችን በጉልበት ሞሮሚያ ጋር ስለቅጧል ፤ ታሪካዊው አማውቴ (አጼ አምደ ጽዮን) የጻፈለት የጉራጌ አገር ፣ አጨበር (ልክ እንደ አጨፈር) የታሪካዊው አይመለል ምድር እን ኩቱ !!1 ይህ እየታካሄድ ነው አቢይ አህመድ ጉራጌዎችን ለማስፍራራት ሃሙስ ስብሰባ የጠራቸው !

ይህ ሁሉ የሚሆነው በምርጫ ቦርድ የታወቀ ሕጋዊ አገር አቀፍ የጉራጌ ቃል ኪዳን ፓርቲ ጎጎት በታወጀ በሳምቱ ነው !!! ብቻ ጉራጌ የሆንክ ሁሉ አቢይ ወዳጅህ እንዳሆነ አውቀህ ግባ! ዞሮ ዞሮ የጉራጌን ፍትሃዊ ጥያቄ አቢይ ሸወደው፣ ሃብታም ሸወደው ለውጥ አያመጣም ። ትግሉ ይብሳል እንጂ ማንም አያመክነውም ! መፍትሄው የጉራጌን ሕዝባዊ ሬፈረንደም መፍቀድና ጉዳዩን ለብርቱካን መስጠት ነው !!! በቃ ! ያቢይ ውሃ ተሸካሚ እርስቱ ገና ማነንቱ ከጉራጌት በእርግማን ይሰረዛል !!!

THE PEOPLE AND THE PEOPLE ALONE ARE THE MAKERS OF HISTORY !!!

Post Reply