Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

የአብይን መንግስት ስትደግፉ ከርማችሁ ዛሬ የተገለበጣችሁ አካላት . . . .

Post by sarcasm » 19 Mar 2023, 16:22

በነዚህ ጉዳዮች እናንተም ተጠያቂ እንደሆናቹ ሳትዘነጉ ተጠያቂነትቹ ኣትርሱ

የአብይን መንግስት ስትደግፉ ከርማችሁ ዛሬ የተገለበጣችሁ አካላት አንድ ምክር ስሙኝ። የአብይ መንግስትን ለመቃወም ከታች የተዘረዘሩትን ጉዳዮች አጀንዳ ባደረጋችሁ ቁጥር እራሳችሁን ከማዋረድ በቀር ትርፍ ስለሌለው ወይ አፋችሁን ዝጉ ወይ አጀንዳ ቀይሩ!! በነዚህ ጉዳዮች እናንተም ተጠያቂ ስለሆናችሁ አፋችሁን በከፈታችሁ ቁጥር እኛ የሚታየን ወንጀላችሁ እና ውርደታችሁ ነው።

1. ህዝብን በጅምላ ወንጀለኛ ማድረግ።
2. የሀሳብ ልዩነት ያላቸውን ጋዜጠኞች እና ፖለቲከኞች ማፈን።
3. አንድን ብሄር ከቦታ ወደ ቦታ በነፃነት እንዳይንቀሳቀስ ማገድ ወደ ማጎሪያ ማስገባት።
4. የጠሚው የንጉስነት ጉዞ።
5. የጠሚው ፕሮጀክቶች እና መፅሃፎች።
6. የኑሮ ውድነት።
7. ብልፅግና ፓርቲ እና አደረጃጀቱ።
8. የዜጎች ሞት እና መፈናቀል።
9. ለተከፋይ ጋዜጠኞች፣ ሚዲያዎች እና አክቲቪስቶች ብቻ የመናገር እና የመረጃ ነፃነት መፍቀድ።
10. ከደባል ተቃዋሚ ፓርቲዎች ውጪ የሚፈፀም መሳደድ።
11. በራሳችሁ ላይ ለደረሰው ውርደት።
Please wait, video is loading...