


በእኛ ቲቪ ላይ በወቅታዊ ጉዳይ ትንታኔ የሚሰጠው አቶ ንጉሴ ብርሃኑ በኦሮሚያ አፋኞች ታፍኖ ክፍኖ መቀጥቀጡ ታወቀ
የእኛ ቲቪ ቌሚ እንግዳ ተንታኝ አቶ ንጉሴ ብርሃኑ ባለፈው ማክሰኞ ምሽት በአዲስ አበባ ምክር ቤት ላይ በአዳነች አቤቤ ቀርቦ በነበረው ዘረኛና አፓርታይዳዊ ገለጻ ላይ ውይይት ባደረገ ማግስት ረቡእ እለት መካኒሳ ላይ ታፍኖ አይኖቹን በጨርቅ ተሸፍኖ ለአራት ሰዓት የዘለቀ ከፍተኛ ድብደባ ከፈጸሙበት በኋላ ገላን ላይ ጥለውት እንደሄዱ የእኛ ቲቭ አዘጋጅ እንግዳወርቅ ለገሰ ገልጿል።
አይኔን በጨርቅ ሸፍነው መኪና ውስጥ ካስገቡኝ በሃላ ኦሮሚኛ ለምን አትናገርም ፋኖን በገንዘብ ትደግፋለህ እያሉ በሰደፍ ቀጠቀጡኝ ብሎ ነው የነገረኝ የሚለው የእኛ ቲቪ ጋዜጠኛ እንግዳወርቅ ዳግመኛ በሚዲያ ላይ ካየነህ እንግድልሃለን በማለት ለአራት ሰዓት የፈጀ ቅጥቀጣ ከፈጸሙበት በኋላ አቶ ንጉሴ ብርሃኑን ገላን ላይ ጥለውት ሄደዋል በማለት ይናገራል።
በእኛ ቲቪ ላይ ቌሚ እንግዳ በመሆኑ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ምሁራዊ እይታውን በማጋራት የሚታወቀው አቶ ንጉሴ በማክሰኞው እለት የመወያያ አጀንዳቹው የአዳነች አቤቤን የአማራን ሕዝብ ነጥላና ለይታ መንግስት ለመገልበጥ ወደ አዲስ አበባ እየጎረፈ ያለ ነው ብላ የገለጸቺውን ፍረጃ እንደተቸ አዘጋጁ ገልጿል። አቶ ንጉሴ ተደብድቦ ከተጣለ በሃላ በመታከም ላይ እንዳለ ማወቅ ተችሏል።
Please wait, video is loading...