

ውታፍ ነቃይ መሳይ መኮነን ከዛሬ 8 ወራት በፊት ከኢትዮጵያ ህዝብ ለቀረበለትና መልስ በመስጠት ንስሃ እንዲገባ ለቀረበለት ከኦህዴድ ባለስልታን ጋር ያደረገውን እና ከላይ ለለተጠቀሰው ድብቅ እና ሚስጥራዊ ውይይት በዛሬው እለት በይፋ መልስ በመስጠት እና በመናዘዝ ንስሃ ገብቷል!!Wedi wrote: ↑24 Jun 2022, 14:49
24 Jun 2022
መሳይ አንተ ከነበርክበት ከፍታ ወርደህ የተፈጠፈጥከው የኢትዮጵያ ህዝብ ድምጽ በመሆን ፈንታ የአብይ አህመድ እና የኦሮሙማ ድምጽ ከሆንክበት ቀን ጀምሮ ነው!!
አንድ ነገር በእግዚአብሔር ስም የምለምንህ ግን "እናንተ የምትሏት ኢትዮጵያ እና እኛ ልንገነባት የምንፈልጋት ኢትዮጵያ የሰማይ እና የምድር ያልክ ልዮንት አላት" ብሎ የነገርህን የብል(ጽ)ግና/ኦህዴድ ባለስልጣን ስምና እና ዝርዝሩን ለኢትዮጵያ ህዝብ ይፋ እንድታደርግ ነው፡፡


መሳይ መኮነን ዛሬ የሰጠው መልስ፦
"ከአንድ ዓመት በፊት የብልጽግና አመራር አባል የሆኑትና የኦሮሞ ብልጽግና መሀንዲስ ተብለው ከሚጠሩት አንዱ ከዶ/ር ቢቂላ ሁሪሶ ጋር በዋትስ አፕ የተመላለስነው መልዕክት ትዝ አለኝ። ''ብልጽግና የሚታገልላት ኢትዮጵያ እናንተ ፍሬም ካደረጋችኋት ኢትዮጵያ የሰማይና የምድርን ያህል ትራራቃለች'' የሚል ነበር የዶ/ር ቢቂላ የዋትስ አፕ መልዕክት። በእርግጥ ገብቶኛል። አሁን የጃዋር ፍኖተ ካርታ ደግሞ የበለጠ ግልጽ አደረገልኝ። አረ እንደውም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኦሮሞ ብልጽግና የሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎችና የሚያቀነቅናቸው ትርክቶች የምትገነባው ''ኢትዮጵያ'' ምን ልትመስል እንደምትችል ፍንትው አድርገው አሳይተውኛል።"

Please wait, video is loading...