Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Wedi
Member+
Posts: 7993
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

ጎጎት - ለጉራጌ አንድነት እና ፍትህ ፓርቲ ተመሰረተ!!

Post by Wedi » 10 Mar 2023, 11:16



:!:
ጎጎት - ለጉራጌ አንድነት እና ፍትህ ፓርቲ ተመሰረተ!!
:!:

የጉራጌ ብሄረተኛ ፓርቲ ይፋ ሊደረግ ነው
By wazema radio
Mar 10, 2023

ዋዜማ- “ የጉራጌን ህዝብ እየደረሰበት ካለው አስተዳደራዊ በደል እና ስጋት ለመታደግ” መደራጀት አስፈልጎኛል ያለ ብሄረተኛ ፓርቲ የፖለቲካ ፓርቲ ይፋ ሊደረግ ነው ።

”ጎጎት ለጉራጌ አንድነት እና ፍትህ ፓርቲ” የሚል ስያሜን የያዘው አደረጃጀት እሁድ መጋቢት 03 /2015 ዓ. ም የምስረታ ጉባኤውን በማካሄድ የፖርቲውን የስራ አስፈጻሚዎችንና ማዕከላዊ ኮሚቴዎችን ይመርጣል።

”ጎጎት” የጉራጊኛ ቃል ሲሆን የጉራጌ አባቶች ህዝቡ በ18 መቶ ክፍለ ዘመን ገጥሞት ከነበረው የመበታተን አደጋ ለመውጣት ቃልኪዳን ያሰሩበት ስፍራ መሆኑንና አሁንም ከእንዲህ አይነቱ ስጋት ለመዳን በማሰብ ስያሜው መመረጡን ዋዜማ ሰምታለች።

በተለይ ጉራጌ የክልልነት ጥያቄ ካነሳ በኋላ እየደረሰበት ያለው እንግልትና አፈና ለፓርቲው መመስረት አንዱ ምክንያት መሆኑን አስተባባሪዎቹ ነግረውናል። ።

ከዚህ በተጨማሪ በፓርቲ መደራጀት ያስፈለገው የጉራጌ ህዝብን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታውን ለማስጠበቅ ነው።

ፓርቲው የክልልነት ጥያቄን አንድ ጉዳይ አድርጎ የሚመለከተው ሲሆን፤ የጉራጌ ህዝብ በሀገረ መንግስት ግንባታውና በታሪክ የነበረውን ሚና አስጠብቆ ለማስቀጠል የሚታገል መሆኑን የፖርቲው አደራጅ ኮሚቴ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ጀሚል ሳኒ ለዋዜማ አስረድተዋል።

የጉራጌን ህዝብ በመላ ሀገሪቱ ተበታትኖ የሚኖር ሆኖ ሳለ በእንዲህ አይነት የብሔር አደረጃጀት ውስጥ ማስገባቱ ለምን አስፈለገ? ስትል ዋዜማ ላነሳችው ጥያቄ

እንዲያውም እስካሁን የጉራጌ ህዝብ ” ኢትዮጰያ” ብቻ እያለ በመዝለቁ በብሔር በተደራጁ የፓለቲካ ሀይሎች ዱላው በርትቶበት ዘልቋል ሲሉ መልሰዋል።

ፓርቲው በመላ ሀገሪቱ ተበትኖ ያለውን የጉራጌ ህዝብ በደሉ እና ድምፁ እንዲሰማ ለማድረግ እሰራለሁ ብሏል።

እስካሁን የጉራጌ ህዝብ ለተቀበለው በደል ሀገራዊ ፓርቲ ነን ብለው ከሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ሳይቀር እዚህ ግባ የሚባል ትኩረት አልተሰጠውም የሚል እምነት አላቸው የፓርቲው አደራጆች። በእነዚህና በሌሎች ምክኒያቶች መደራጀቱ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ሲሉ ነግረውናል።

የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ዞኑ በክልል የመደራጀትን ምክረ ሀሳብን በ2011 ዓ.ም ማጽደቁ ይታወሳል። ቀጥሎም ነሃሴ 05/2014 ከመንግስት የቀረበለትን በክላስተር የመደራጀት ውሳኔን ውድቅ አድርጓል።

ይህን ተከትሎ በአካባቢው በመንግስት እና የራስ ገዝ መብት በሚጠይቁ ነዋሪዎች መካከል ተከታታይ ግጭቶች የታዩ ሲሆን በቅርቡም በርካታ ሰዎች ለእስር ተዳርገዋል።

[ዋዜማ]
Last edited by Wedi on 10 Mar 2023, 14:18, edited 1 time in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 30901
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ጎጎት - ለጉራጌ አንድነት እና ፍትህ ፓርቲ ተመሰረተ!!

Post by Horus » 10 Mar 2023, 14:16

ጎጎት (ትርጉም፡ ቃል ኪዳን)፤ ጉራጌን ከመጥፋት ከመጥፋት ያተረፈው የመላ ጉራጌ በጎጌቲ የተደረገው የአንድነት የቃል ኪዳን ጉባኤ! በዛሬ አጭር ትርጉሙ ጎጎት የአንድነት ቃል ኪዳን ማለት ነው!

Wedi
Member+
Posts: 7993
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: ጎጎት - ለጉራጌ አንድነት እና ፍትህ ፓርቲ ተመሰረተ!!

Post by Wedi » 10 Mar 2023, 14:20

Horus wrote:
10 Mar 2023, 14:16
ጎጎት (ትርጉም፡ ቃል ኪዳን)፤ ጉራጌን ከመጥፋት ከመጥፋት ያተረፈው የመላ ጉራጌ በጎጌቲ የተደረገው የአንድነት የቃል ኪዳን ጉባኤ! በዛሬ አጭር ትርጉሙ ጎጎት የአንድነት ቃል ኪዳን ማለት ነው!




DefendTheTruth
Member+
Posts: 9896
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

Re: ጎጎት - ለጉራጌ አንድነት እና ፍትህ ፓርቲ ተመሰረተ!!

Post by DefendTheTruth » 10 Mar 2023, 14:56

Wedi wrote:
10 Mar 2023, 11:16


[ዋዜማ][/size][/color]
ቆጮዉንም አብሮ ከቆጠሩ ምለዐተ-ጉባኤዉ ሳይሞለ አይቀርም። :lol: :lol: :lol: :lol:

Horus
Senior Member+
Posts: 30901
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ጎጎት - ለጉራጌ አንድነት እና ፍትህ ፓርቲ ተመሰረተ!!

Post by Horus » 10 Mar 2023, 15:10

ድርጅት ኃይል ነው!

Horus
Senior Member+
Posts: 30901
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ጎጎት - ለጉራጌ አንድነት እና ፍትህ ፓርቲ ተመሰረተ!!

Post by Horus » 10 Mar 2023, 15:40

Wedi wrote:
10 Mar 2023, 14:20
Horus wrote:
10 Mar 2023, 14:16
ጎጎት (ትርጉም፡ ቃል ኪዳን)፤ ጉራጌን ከመጥፋት ከመጥፋት ያተረፈው የመላ ጉራጌ በጎጌቲ የተደረገው የአንድነት የቃል ኪዳን ጉባኤ! በዛሬ አጭር ትርጉሙ ጎጎት የአንድነት ቃል ኪዳን ማለት ነው!



wedi,
በትክክል! ጉራጌ ከብልጽናም ከኢዜማም ከሌላም ነጻ የሆነ የራሱ ድርጅት ካስፈለገው ቆይቷል። ይህ ትልቅ አንድ እርምጃ ወደፊት ነው ። የጎጎት ፓርቲ ለክልልነት ጥያቄ ብቻ ሳይሆን ለራሱ ጉራጌ ሕዝብ ውሳዊ አንድነትና መረዳዳት እጅግ አስፈላጊ አደረጀጀት ነው። ጋን ቢጠራረግ እንስራ ይወጣዋል ይባላል ። የራሱን የተበታተነ ሃብት ቢያሰባስብ እንኳ አገሩን ማልማት የሚችል ሕዝብ ነው ። አው ጎጎት ያድጋል፣ ይሰፋል፣ ግዜው የደረሰ ሃሳብ ስለሆነ! It is an idea whose time has come! ብልግና ፓርቲ በጉራጌ ቦታ የለውም!

Post Reply