Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 11128
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

አለም አቀፍ ዳያስፖራ ነኝባይ ለዓቢይ አህመድ የጻፈውን ደብደቤ አንብቤ የደረሰውን ግፍ ዝርዝር ስጨርስ ችግሩ እና ምፍትሄው (recommendations) ሃራምባ እና ቆቦ። አይመሳሰሉም።

Post by Abere » 09 Mar 2023, 10:20

አለም አቀፍ ዳያስፖራ ነኝባይ ለዓቢይ አህመድ የጻፈውን ደብደቤ አንብቤ የደረሰውን ግፍ ዝርዝር ስጨርስ ችግሩ እና ምፍትሄው (recommendations) ሃራምባ እና ቆቦ። አይመሳሰሉም። ይህን አይነት ግፍ የፈጸመ 5 አመት ዕድል ተሰጥቶት ሁሉንም ያባከነ ኦነግ እንድሻሻል መጠየቅ ምን አይነት ሆዳም እና ሆዱ ያልቆረጠ ዲያስፓራ እንደለ ያሳዝናል። ቀጥታ ስልጣን እንደ ሃይለማርያም በሰላም እንድለቅ መጠየቅ ሲገባ መለማመጥ ያስተዛዝባል። በመጀመሪያ ለምን ለአብይ አህመድ ደብዳቤ መጻፍ አስፈለገ? አውቆ የተደበቀ ኦነግ ነው - ቢጠሩት አይሰማም። 2ኛ ዲያፓራ ኖሞሮች አብይ በጣም የናቃችሁ ናችሁ - ግር ብላችሁ አዲስ አበባ ለበዐል ማክበር ተጋብዛችሁ ሂዳችሁ ለንቀቱ መግለጫ ስብሃት ነጋ እና ጁሃር አባሜንጫን ፈትቶ ሰጣችሁ። በዚህ ሰዐት አለም አቀፍ ጫና መፍጠር የሚገባው አብይ አህመድ ከመሪነት እንድነሳ እንጅ እንድሻሻል አይደለም። ሌላ 5 አመት የዘር ፍጅት፤ዕልቂት እና ትርምስ ይጨመርለት ለኢትዮጵያ ህዝብ እያላቸሁ ነው።

https://mereja.com/amharic/v2/805491

Axumezana
Senior Member
Posts: 13633
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: አለም አቀፍ ዳያስፖራ ነኝባይ ለዓቢይ አህመድ የጻፈውን ደብደቤ አንብቤ የደረሰውን ግፍ ዝርዝር ስጨርስ ችግሩ እና ምፍትሄው (recommendations) ሃራምባ እና ቆቦ። አይመሳሰሉም

Post by Axumezana » 09 Mar 2023, 13:00

ደብዳቤው፥ የተፃፈው፥ በኢሳያስ፥ በሚዘወረው፥ ንአምን፥ዘለቀ፥ በሚመራው፥ የዲያስፖራ፥ ትስስር፥ ሲሆን፥ ወያነን፥ ለማጥፋትና፥ የትግራይን፥ ህዝብ፥ ለማንበርከክ፥ ታቅዶ፥ የተተገበረው፥ ጦርነት፥ ከኢሳያስ፥ ጋር፥ ሆነው፥ የጠነሰሱ፥ ናቸው። አብይን፥ የዚህ፥ ጦርነት፥ አስፈፃሚ፥ አድርገው፥ የሰየሙ፥ ሲሆን፥ የኢትዮጵያ፥ ህዝብ፥ ባለፉት ፥ አምስት አመታት፥ የተለያዩ፥ ግፎች፥ ሲፈፀምበት፥ትንፍሽ፥ ያላሉ፥ አሁን፥ ግን ፥አብይ፥ ከወያኔ፥ ጋር፥ በመስማማቱ፥ እጅግ፥ የተከፉና፥ አብይን፥ አባብለው፥ እንደገና፥ ከወያነ፥ጋር፥ ኢንዲጣላና፥ ጦሩነቱም፥ አገርሸቶ፥ ወያኔ፥ መጥፋት፥ አለበት፥ የሚለውን፥ ኡሳያስ፥ የሰጣቸውን፥ ተልዕኮ፥ ለማስፈፀም፥ ጎንበስ፥ቀና፥ የሚሉ፥ ናቸው።

Abere
Senior Member
Posts: 11128
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: አለም አቀፍ ዳያስፖራ ነኝባይ ለዓቢይ አህመድ የጻፈውን ደብደቤ አንብቤ የደረሰውን ግፍ ዝርዝር ስጨርስ ችግሩ እና ምፍትሄው (recommendations) ሃራምባ እና ቆቦ። አይመሳሰሉም

Post by Abere » 09 Mar 2023, 13:17

ዶሮ ብታልም ጥሬዋን አይነት ነገር ነው የዚህ አይነት ትንብያህ - አክሱምኢዛና። ነገሮችን መመልከት ያለብን ከመርህ አንጻር ነው። ለኢትዮጵያ ህዝብ ወያኔ ይሁን አብይ አህመድ የሚፈለጉ አይደሉም። ከማንም በላይ ለትግራይ ህዝብ ጥላት ወያኔ ነው።

ይህ ደብዳቤ ከኢሳይያስ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የለውም። ምክንያቱም ኢሳይያስ በቀጥታ ለአብይ አህመድ ቀጭን ትዕዛዝ ወይም ማስጠንቀቂያ ሊሰጠው የሚችል አይነት ሰው ይመስለኛል - አብይ አህመድ ወጥ ሲረግጥ ካገኘው። በመሰረቱ ወያኔ ለትግራይ ህዝብ እንጅ ስጋት መሆን የሚችለው ለማንም ስጋት ሊሆን ከሚችልበት ደረጃ ላይ አይደለም።

Axumezana wrote:
09 Mar 2023, 13:00
ደብዳቤው፥ የተፃፈው፥ በኢሳያስ፥ በሚዘወረው፥ ንአምን፥ዘለቀ፥ በሚመራው፥ የዲያስፖራ፥ ትስስር፥ ሲሆን፥ ወያነን፥ ለማጥፋትና፥ የትግራይን፥ ህዝብ፥ ለማንበርከክ፥ ታቅዶ፥ የተተገበረው፥ ጦርነት፥ ከኢሳያስ፥ ጋር፥ ሆነው፥ የጠነሰሱ፥ ናቸው። አብይን፥ የዚህ፥ ጦርነት፥ አስፈፃሚ፥ አድርገው፥ የሰየሙ፥ ሲሆን፥ የኢትዮጵያ፥ ህዝብ፥ ባለፉት ፥ አምስት አመታት፥ የተለያዩ፥ ግፎች፥ ሲፈፀምበት፥ትንፍሽ፥ ያላሉ፥ አሁን፥ ግን ፥አብይ፥ ከወያኔ፥ ጋር፥ በመስማማቱ፥ እጅግ፥ የተከፉና፥ አብይን፥ አባብለው፥ እንደገና፥ ከወያነ፥ጋር፥ ኢንዲጣላና፥ ጦሩነቱም፥ አገርሸቶ፥ ወያኔ፥ መጥፋት፥ አለበት፥ የሚለውን፥ ኡሳያስ፥ የሰጣቸውን፥ ተልዕኮ፥ ለማስፈፀም፥ ጎንበስ፥ቀና፥ የሚሉ፥ ናቸው።

Axumezana
Senior Member
Posts: 13633
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: አለም አቀፍ ዳያስፖራ ነኝባይ ለዓቢይ አህመድ የጻፈውን ደብደቤ አንብቤ የደረሰውን ግፍ ዝርዝር ስጨርስ ችግሩ እና ምፍትሄው (recommendations) ሃራምባ እና ቆቦ። አይመሳሰሉም

Post by Axumezana » 09 Mar 2023, 13:22

አለቃ፥ አበረ፥ እኞ፥ የምናውቀውን፥ እንናገራለን፥ አለመቀበል፥መብትህ፥ነው። The " No More " movement የአብይ፥ሳይሆን፥ የኢሳያስ፥ አጀንዳ፥እንደነበረ፥ ታውቃለህ?

Misraq
Senior Member
Posts: 12455
Joined: 27 Sep 2009, 19:43
Location: Zemunda

Re: አለም አቀፍ ዳያስፖራ ነኝባይ ለዓቢይ አህመድ የጻፈውን ደብደቤ አንብቤ የደረሰውን ግፍ ዝርዝር ስጨርስ ችግሩ እና ምፍትሄው (recommendations) ሃራምባ እና ቆቦ። አይመሳሰሉም

Post by Misraq » 09 Mar 2023, 13:35

አበረ

እነዚህ ድኩማኖች ልምምጥ ውስጥ ነው የገቡት። ሲጀመር እዚህ ለመድረስ የወሰደባቸው ግዜ አድርባይነታቸውን ያሳያል። ሲቀጥልም ሰውየውን ነፃ ባወጣ መልክ ነገሮችን እንዲከታተል መጠየቅና እንዲያረም መምከር ገና የዓብይ ፍቅር እንዳልወጣላቸው ያሳያል።

Abere
Senior Member
Posts: 11128
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: አለም አቀፍ ዳያስፖራ ነኝባይ ለዓቢይ አህመድ የጻፈውን ደብደቤ አንብቤ የደረሰውን ግፍ ዝርዝር ስጨርስ ችግሩ እና ምፍትሄው (recommendations) ሃራምባ እና ቆቦ። አይመሳሰሉም

Post by Abere » 09 Mar 2023, 13:37

እኔ እንደገባኝ ኢትዮጵያዊያኖች የውጭ ጣልቃ ገብነትን የተቃወሙበት ድምጽ ይመስለኛል። በርካታ ዲያስፓራ እና በአገር ውስጥም በርካታ ህዝብ የውጭ ጣልቃገብነትን የተቃወሙበት ሁኔታ። የዚህ ግንባር ቀደም መሪ ደግሞ የትግራይ ተወላጅ የሆነችው ሄርሜላ አረጋዊ ነበረች። ነዐምን ዘለቀ መንገዱን ከዐብይ አህመድ ለይቷል - አስታራቂ ሊሆን አይችልም። አብይ አህመድ ከስልጣን መወገድ አለበት ብሏል። ስለ ወያኔ በትንፋሽ መኖር ሰግቶ ሳይሆን አብይ የሚያደርገውን ትርምስ እና ውድቀት በመረዳት ነው።

እሽ እውነት እንነጋገር አንተ እንደምታስበው ይሁን እና አብይ አህመድ ኤርትራ ለጉብኝት ሂዶ በዚያው ቢቀር ምን ይሰማኸል? የምስራች ደስታ ወይስ ሀዘን? ። እልህ አለሁ ቅልጥ ያለ ደስታ እና ዕልልታ ነበር በምድረ ኢትዮጵያ የሚሆነው። በሌላ መልኩ የወያኔ ርዝራዥ ከተግራይ ቢወገድ - የትግራይ ህዝብ አንጀቱ ቅቤ ይጠጣ ነበር። አማራ ጋር ችግር የለ። አፋር ጋር ችግር የለ።

Axumezana wrote:
09 Mar 2023, 13:22
አለቃ፥ አበረ፥ እኞ፥ የምናውቀውን፥ እንናገራለን፥ አለመቀበል፥መብትህ፥ነው። The " No More " movement የአብይ፥ሳይሆን፥ የኢሳያስ፥ አጀንዳ፥እንደነበረ፥ ታውቃለህ?

Abere
Senior Member
Posts: 11128
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: አለም አቀፍ ዳያስፖራ ነኝባይ ለዓቢይ አህመድ የጻፈውን ደብደቤ አንብቤ የደረሰውን ግፍ ዝርዝር ስጨርስ ችግሩ እና ምፍትሄው (recommendations) ሃራምባ እና ቆቦ። አይመሳሰሉም

Post by Abere » 09 Mar 2023, 13:42

ምሥራቅ

ትክክል! በጣም የሚረባ ዲያስፓራ አይደለም ያለው። ክብር ያለው ድሃው የኢትዮጵያ ህዝብ ግፍ በተጸየፈበት ሰአት እነኝህ አሳማዎች ለኮንዶምንየም እና ሾቃቃ አፓርትመንት ጥቅማጥቅም ሲሉ የግፍ እና የዕልቂት ንጉስ ሺ አመት ንገሥልን እያሉ ነው። አገር እኮ መለማመጃ አይደለችም? 120 ሚልዮን ህዝብ ነፍስ የያዘች ትልቅ አገር ለአንድ ከንቱ ግለሰብ እንደፈለገህ አድርጋት ማለት የወንጀል ወንጀል ነው።
Misraq wrote:
09 Mar 2023, 13:35
አበረ

እነዚህ ድኩማኖች ልምምጥ ውስጥ ነው የገቡት። ሲጀመር እዚህ ለመድረስ የወሰደባቸው ግዜ አድርባይነታቸውን ያሳያል። ሲቀጥልም ሰውየውን ነፃ ባወጣ መልክ ነገሮችን እንዲከታተል መጠየቅና እንዲያረም መምከር ገና የዓብይ ፍቅር እንዳልወጣላቸው ያሳያል።

Axumezana
Senior Member
Posts: 13633
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: አለም አቀፍ ዳያስፖራ ነኝባይ ለዓቢይ አህመድ የጻፈውን ደብደቤ አንብቤ የደረሰውን ግፍ ዝርዝር ስጨርስ ችግሩ እና ምፍትሄው (recommendations) ሃራምባ እና ቆቦ። አይመሳሰሉም

Post by Axumezana » 09 Mar 2023, 14:05

እንደሚሉት፥ ለአገር፥ አሳቢ፥ቢሆኑ፥ ኑሮ፤ አምስት፥ አመት፥ሙሉ፥ ያሁሉ፥ ወንጀል፥ኢትዮጵያ፥ ውስጥ፥ሲሰራ፥ የት፥ ነበሩ? አብይን፥ እምስት፥ አመት፥ ሙሉ፥ በምን፥ ምክንያት፥ደገፉ? አሁን፥ የተለወጠ፥ ነገር፥ ቢኖር፥ አብይ፥ ከወያነ፥ ጋር ፤ መስማማቱ፥ ነው። ያስኮረፋቸውም፥ ይኸው፥ጉዳይ፥ ነው።
ትናንት፥ ለግብፅ፥ ወግነውም፥ ህዳሴ፥ ግድቡን፥ የተቃወሙ፥ መርህ፥የለሾችና፥ አገራቸውን፥ በገንዘብ፥ የሸጡ፥ ናቸው።

Abere
Senior Member
Posts: 11128
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: አለም አቀፍ ዳያስፖራ ነኝባይ ለዓቢይ አህመድ የጻፈውን ደብደቤ አንብቤ የደረሰውን ግፍ ዝርዝር ስጨርስ ችግሩ እና ምፍትሄው (recommendations) ሃራምባ እና ቆቦ። አይመሳሰሉም

Post by Abere » 11 Mar 2023, 13:02

በለገሠ ገልቱ በኩል ለዲያስፓራዎች ደብዳቤ የተሰጠውን ምላሽ ያነበበ ውታፍ ነቃይ ህሌና ካለው መቸም ምን ነው ነፍሰ-በላው ኦሮሙማ አብይ አህመድን በአስቸኳይ ከስልጣን ውረድ የሚል የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ አስገብተን በነበር ማለቱ አይቀርም። አሁን ፀፀት ቢያጭዱት ክምር አይሟለም ይሆን?! :mrgreen:

አብይ አህመድ የአእምሮ ህመምተኛ መሆኑን ከሚሰራቸው ስራዎች በሙሉ የተረጋገጠ ነው። ይህን ህመምተኛ ሰው ደግመህ ምራን የሚል ደግሞ በዕብድ አብይ አህመድ የተያዘውን የዕብደት ሪኮርድ የሰበረ እብደት ነው - ብዙዎች ደግሞ አሣማ የያዘውን የሆዳምነት ሪኮርድ ስብሯል ማለታቸው አይቀርም። ታዲያ አለም አቀፍ ዲያስፓራ ነኝ የሚለው አካል በቀጣዩ ምን የአቋም መግለጫ ደብዳቤ ያስነብበን ይሆን?

1) ለአብይ አህመድ የጊዜ ገደብ በመቁረጥ ከስልጣን እንድ ወርድ ፤ የሽግግር ባለ አደራ ስርዐት እንድፈጠር አገራዊ ጥሪ ማቅረብ?
ወይስ
2) ለኢትዮጵያ ህዝብ ይቅርታ ማቅረብ - ስለ አስነጠቁት ድል ስለ አለቁት ወገኖች?
ወይስ
3) ለአብይ አህመድ የይቅርታ ደብዳቤ -በድጋሜ ከጫማህ ስር ነን ማለት?

Post Reply