Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abe Abraham
Senior Member
Posts: 13186
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

ግእዝ ቃላት

Post by Abe Abraham » 03 Mar 2023, 15:18

Abe Abraham
Senior Member
Posts: 13186
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Abe Abraham » 03 Mar 2023, 17:49

ታጠቀ ----> ትጥቅ
ጸወረ -----> ኣጽዋር ----> ኣጽዋራት

-

Horus
Senior Member+
Posts: 26859
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Horus » 03 Mar 2023, 22:37

Abe Abraham wrote:
03 Mar 2023, 15:18
ጤና ይስጥልኝ አቤ አብርሃም፣
ጸወረ የሚለውን ትልቅ ቃል በማምጣትህ እመሰኛለሁ ። ይህ ቃል ግዕዝ ዛሬ በሰፌው ጥቅም ላይ ያለው በጉራጌኛ ቋንቋ በተለይም በክስታኔኛ ቋንቋ ውስጥ ነው ። ጥቂት ምሳሌዎች እነሆ!

እኛ ጸወረ(ን) ጸን በጠ ሺፍት አድርገን ጠወረ (ጦረ) እንላለን የቃሉ ተራ ትርጉም ጡር = ተሸከም፣ ጦረ = ተሸከመ፣ ጡረት = ሸክም ማለት ሲሆን ዛሬ ገናና የሆነው ጡረታ (ሪታየርመንት) ሸክም ማለት ነው ። ሌላው ትልቁ የሞራልና መንፈሳዊ አጠቃቅሙ ደሞ አንድ መጥፎ ነገር ወይም ግፍ ከሰራህ ጡር የሆንብሃል እንላለን ። ያም ምን ማለት ነው? አንድ መትፎ ተግባር (ጊልት) ያይምሮ፣ የሳኮሎጂ፣ የህሊና ሸክም ነው ማለት ነው !! ስለዚህ አው ጸወረ (ጠወረ) ተሸከመ ማለት ነው። በቱባ ትርጉሙ ያለው በጉራጌኛ ውስጥ ነው ።

ለምሳሌ ሌላ ግዕዝ ልጥቀስልህ!

ኢትዮጵያ ታበጽህ እደዊሃ አበ አግዚአብሄር ይባላል ። ሁሉም ሰው እድ (እጅ) እንደ ሆነ ያውቃል ። ለምሳሌ ተግባረ እድ ሰለሚባል ። ነገር ግን አቦሰ፣ ዋቡስ፣ አቡስም የምንለው ጉራጌዎች ብቻ ነን። አቦሰ፣ ዋቡስ አብስህ (ጸ(ን) በ ሰ ሺፍት አድርገን ማለት አነሳ፣ ማንሳት፣ እጆች ወደ ሰማይ መዘርጋት ማለት ነው ።

ለምሳሌ በጉራጌ የባህል ለቅሶና ሙሾ ሴቶች ለብቻ ፣ ወንዶች ለብቻ በሰልፍ ሆነው ሁለት እጆቻቸውን ወደ ሰማይ በማንሳት በዋቡስ የኦፈን ያሉ በዜማ ሙሾ ያዜማሉ ! ያ በብሸ (በለቅሶ) ዋቡስ፣ ዋቦስ ይባላል ። ያ ነው ግዕዝ ታበጽህ (ታበስህ) የሚለው ። ይህ ቃል ከችግር፣ ከምህላ ከሃዘን ጋር ስለተያያዘ ይመስለኛል አበሳ (ጣጣ) ወይም መከራ ከቃሉ ጋራ የተያያዘው !!

ኬር

Abe Abraham
Senior Member
Posts: 13186
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Abe Abraham » 04 Mar 2023, 19:05

Horus wrote:
03 Mar 2023, 22:37

Horus,

I appreciate your approach a lot because it opens the gate to etymological exploration in our linguistic heritage both on individual amateur level or as a professional researcher.

The story of ጸወረ and ጠወረ in both Guragégna and Tigrigna is the same. In Tigrigna from ጸወረ ( ተሰከመ/ተሸከመ ) after shifting ጸ to ጠ we got ጠወረ . Someone who takes care of his parents/family financially or otherwise is called ጠዋሪ. That means ጠወረ added to መሸከም other specific non-physical meaning. If you want to translate a burden in Tigrigna you have got ጾር . You do not go in the direction of ጠወረ to invent words like ጦር ጡረት!!

በኣረብኛ ጠ+ወ+ረ ፊደሎችን የያዙ ሌላ ትርጉም ያላቸው ቃላቶች ኣሉ ።

In addition to the shifting of sounds I pay attention to the change of position of letters in a word to see whether a Tigrigna word is related to other semitic words. For example a certain word in Arabic could be ordered 123 while in the case of Tigrigna is 132 or simply 12.

---

Hebrew : In the Hebrew alphabet the final form is called sofit (Hebrew: סופית, meaning "final" or "ending"). Sofit sounds like our ጫፍ, right ? What do you think ?
-

Horus
Senior Member+
Posts: 26859
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Horus » 06 Mar 2023, 03:28

አቤ፣
አንተና እኔ ይህን የኢቲሞሎጂና ፊሎሎጂ ዝምድና መቀጠል አለብን! ትክክል ነሀ በኢትጲክ ቋንቋዎች አሰራር ያስተዋልኳቸው አንዳንድ ነገሮ ልንገህ! አንተ በቶሎ ምን እንደ ሆኑ ስለምታቅ በጣም ደስ ይለኛልና።

አንድ ትልቁ ባህል አንድ ቃል ወደ ግራ ወይም ወደ ቀኝ መጻፍና ትርጉሙ ሳይለወጥ የቃሉ ንባቤ ወይም ፕሮናውንሴሽን መቀልበስ ነው። ለምሳሌ ለማ ~ መላ (መልማት መብዛት ነው፣ መሙላትም መብዛት ነው) ! የዚህ አይነት ብዙ እግጅ ብዙ ቃላት አሉ ።

ለዚህ ምክንያቱ የግብጽ አይሮግሊፊክስ ከላያ ወደ ታች ይነበብ ነበር፣ ከቀኝ ወደ ግራም ይነበብ ነበር እንደ አረብኛ ። የሂሚሪያቲክ ግዕዝ በየመንም በኤርትርም (ደማ'ት) ከቀኝ ወደ ግራ ከዚያ ከግራ ወደ ቀኝ (ዚግ ዛግ) ይነበብ ነበር ። በዚያ ሳቢያ አሁን መዝገበ ቃላት የሰሩት ቄሶች የቃላቶቹን ትርጉም ጠብቀው ግን አንዱን ቃል ከኋላ ወደ ፊት፣ ሌላው ከፊር ወደ ኋላ ስለጻፉት ብዙ ውዥንብር አለ ፣ እኔ ሁልግዜ ቃሉን በዚህ መንገድ ቼክ አደረገዋለሁ ።

እህ አንዱ ነው ።

ሌላው ስለ ሺፍፍ የተነጋገርነው ነው።

ሶስተኛው አንተ ዛሬ ያነሳሃው የተለምዶ 123 የነበረውን 132 ወይም 312 የማድረግ ባህል ነው። ለምሳሌ በረካ ( ባራካ) ውሰድ። ይህ መባረክ የሚባለው ነው ። ካራባ (ከረቦ) የሚል ቃል አለ ። ከረቦ ማክበሪያ መሳሪያ ማለት ነው ። ወይም ካባራ (ክብር) ተመልከት ከበረከት ብዙ አይርቅም በትርጉሙ ግን አንተ እንዳልከው የፊደሉን ድምጽ ሺፍት በማድረግ ሳይሆን የፊደሎቹን ቦታ በመለዋወጥ የተለየ ቃል ፈጥረዋል ።

ግ ን አንዴ ይህ የተጠቀሙትን ዘዴ ዲኮድ ካደረክ በኋላ አለም ወለል ብሎ ነው የሚታይህ! አይደለም በአንድ ቋንቋ ውስጥ ለምሳሌ ብዙ ቃላት በቀምጥ (ኮፕቲክ)፣ ሴሚቲክ፣ ሂንዱ/ሳንስክሪት እና በላቲን ብዙ ተመሳሳይ ናቸው።

ብታምንም ባታምን 'ዕኩል' ማለት 'equal' አንድ ቃል ናቸው!!! እንዴት ለሚለው ሌላ ግዜ !!!

ኬር!

Abe Abraham
Senior Member
Posts: 13186
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Abe Abraham » 07 Mar 2023, 22:27

Horus wrote:
06 Mar 2023, 03:28

ኣዎ ቁልፉን ካገኘህ ብዙ በሮች ይከፈቱልሃል ። ትናትና ብዙ ሳላስብ በራሴ ብዙ ሃሳቦች ስለመጡኝ ኖትቡክና ቀለም ይዤ መጻፍ ጀመርኩ ። ጭንቅላቴ ኣንዳንድ ግዜ " ተመልከት ! ይሄሳ ምን ይመስለሃል ? " ይለኛል !! ለምሳሌ ፥

1) ዛፍ ጥላ ስር ሆነን ስንነጋገር ከኔና ኣንቺ ቀር እነማን ነበሩ ።
2) ዛሬ ነው መቸ ነው ኣይንሽን የማየው
3) ቐፉርረሒምረጂም ( ረጊም)በሶስተኛው ፥

_ 123 ---> 213 ምን ታገኛለህ ?
_123----->321 ምን ታገኛለህ ?
_123----->123 ምን ታገኛለህ ?

-

Horus
Senior Member+
Posts: 26859
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Horus » 07 Mar 2023, 23:57

አቤ አብርሃም፣

የቋንቋ አናጢ

አንድ ቃል መፍጠር የፈጠራ ውጤት ነው፤ ማለትም አርት ነው። ቃላት የሚፈጥሩ የቋንቋ ካህናት ፈጣሪዊች ናቸው፣ ክሪኤቲቭ አርቲስቶች ናቸው። ካህን የሚለው እጅግ ጥንታዊ የግብጽ ቃል የተጠቀምኩት ትርጉሙ ክህሎተኛ ማለት ስለሆነ ነው ።

አንድን የቋንቋ ካህን እንደ አንድ አናጺ ተመልከተው ። አንድ አናጺ (አናጢ ወይም ህንጻ ሰሪ) የሚጠቀመው እንጨት ነው ። ከእንጨት ነው ቤት ወይም ህንጻ የሚገነባው ። ይህን ለማድረግ አናጺ አንድን እንጨት በአንድ ቅርጽ፣ ርዝመት፣ እጥረት፣ ስፋት፣ ወርድና ጥመት ብቻ አይደለም ያን ንጨት እያገጣጠመ ህንጻ የሚያቆመው። ቤት ሊሰራ የጣለውን ዛፍ በብዙ ልዩ ልቱ አይነት የፍልጥ ቁርጥራጮ ካሳመረ (ካባለተ) በኋላ ነው በንድፍ ላይ ያለውን ህንጻ የሚያዋቅረው ።

አንድ ቃል፣ ቃላትና አንድ ቋንቋ የተገነባው (የተቀመረው፣ የተወሰወሰው) በዚያ መንገድ ነው። እርግጥ ብዙ የአለም ቋንቋዎች፣ የኢትዮጵያ ቋንቋዎችን ጨምሮ አንድ ካህን ሆን ብሎ እንደ ሂሳብ ፣ እንደ አልጎሪዝም የሰራቸው አይደሉም ። በተፈጥሮ፣ በልማድ፣ በግዜ ሂደት (ኢቮሉሽን) የተቀመሩ ናቸው ። ያም ስለሆነ እንደ ማቲማቲክስ ወይም አልጎሪዝን ወጥ ሲስተም አይደሉም ። ዘመንዊ ጀርመንኛ ብቻ ነው በዚያ መልክ የተቀመረ ቋንቋ ። ዘመናዊ ሂንዱ ቋንቋም ሆን ተብሎ ተቀምሯል ።

ከነዚህ ውጭ ያሉት ቋንቋዎች እንደ አልጎሪዝም ስረ ቃሉን፣ የፊደላቱ ቅደም ተከተል፣ የቅጽላቱ ቅላጼ፣ የድምጾቹ መረገጥና መዋጥ፣ መጠበቅና መላላት ... ወዘተ ሁሉ ምንም የሚከተሉት ሕግ የላቸውም ። በተቀመጠ ፎርሙላ ልናውቃቸው አንችልም ። ለዚህ ነው የእያንዳንዱ ቋንቋ ብቻ ሳይሆን፣ የእያንዳንዱ ቃላት ታሪክ (ኢቲሞሎጂና ፊሎሎጂ) መመርመር ያስፈለገን ። ለምሳሌ ከላይ ያነሳሃው ጸወረ የሚለው የግዕዝ ስረቃሉ ጣረ (ጥነከረ፣ ባለጉልበት ሆነ፣ ጠንክሮ ሰራ) የሚል ነበር እንጂ በጠባቡ ተሸከመ ማለት ብቻ አልነበረም። ጻረ፣ ጾረ ማለት ጣረ ፣ ጥረት አደረገ ማለት ነው ።

ድምጽን እንደ እንጨት ግንግ ብንወስደው፣ የድምጽ ግንድ በልዩ ልዩ ትናንሽ ድምጾች እንከትፈዋለን ። ያ ፎነም ወይም ሆሄያት የምንለው ነው ። ለምሳሌ ከ ቀ በ ወ ረ ለ እንበል ። ልክ እንደ አንድ አናጺ ከነዚህ ትናንሽ ድምጾች ከበረ፣ ቀበረ፣ ቀወረ፣ በረቀ፣ ... እያልን እጅግ ብዙ ቃላት እንፈጥራለን ። እያንድንዱ ቃልም አንድ ነገር እንዲገልጽ፣ እንዲወክል፣ እንዲሰይም አድርገን ትርጉሙን እንወስናለን ።

ይህን ሁሉ የሚያደርጉ የቋንቋ ፈጣሪያን ክሪኤቲቭ አርቲስቶች ናቸው ። እነዚህ የቋንቋ ካህናት እረኞች፣ እናቶች፣ አባቶች፣ ነጋዴዎች፣ ቄሶች፣ ወታደሮች ሌላም ሌላም ሊሆኑ ይችላሉ ። የሰው ልጅ አንድን ነገር ከሌላ ነገር ለመለየትና ምልክት አድርጎ ለማስታወስ ለነገሮች ሁሉ ስም ይስጣል ። ትርጉም ይሰጣል ። ለምሳሌ 123 ዝም ብሎ የሶስት ቁጥሮች (ምልክቶች) መደርደር ነው ። ግን ለነጋዴው 123 ብር የገንዘብ ልክ ነው ። ለገበሬ የከብት ወይም የኩንታል ቁጥር ስፍር ነው ። ለማቲማቲክስ ምሁሩ የ100፣ የ10፣ የ1 ቤት ተብሎ ቦታ ያላቸው የዲጂቶች ሲስተም መስተዋቅር ነው ።

ቋንቋ ሚራክል ነው ። ቋንቋ ባይኖር የሰው ልጅ አይኖርም ነበር! በሁለት እግር የምንሄድ እንሰሶች ሁነን በየደኑና ዋሻው ውስጥ እንዳክር ነበር ። ለሰው ልጅ ስብዕናን የሰጠ ቋንቋ ነው! ለዚያ ደሞ ኤቦ ዬቦ እንላለን!
ኬር
Last edited by Horus on 08 Mar 2023, 01:10, edited 1 time in total.

TGAA
Member
Posts: 4852
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

Re: ግእዝ ቃላት

Post by TGAA » 08 Mar 2023, 00:28

Interesting discussion: John 1:1 summarizes what you said at the end.
In the beginning, was the Word, and the Word was with God, and the Word was God. He was with God in the beginning. Through him all things were made; without him, nothing was made that has been made. In him was life, and that life was the light of men.

Horus
Senior Member+
Posts: 26859
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Horus » 08 Mar 2023, 01:30

TGAA wrote:
08 Mar 2023, 00:28
Interesting discussion: John 1:1 summarizes what you said at the end.
In the beginning, was the Word, and the Word was with God, and the Word was God. He was with God in the beginning. Through him all things were made; without him, nothing was made that has been made. In him was life, and that life was the light of men.
TGAA,
Yes, indeed. ማ ስም ይስጥ? የፈጠረ! ይባላል (ማ ያርዳ የቀበረ፣ ማ ይንገር የነበረ)። አለም እንደ ቁስዊ ሪያሊቲ ያለ ቃል ሊኖር ይችላል። ያ ደሞ የጭለማ ሪያሊቲ ፣ ዳርክ ሪያሊቲ ነው ። ብርህን የሕይወት ምንጭ ብትሆንም፣ ያየነውን ስም እስካልሰጠን (በድምጽ) እና በምልክት እስካለየነው ድረስ አለምን ሁሉ ብናይ ምን እንደ ሆነ ልናውቀው አንችልም ። እከሌ፣ እንትና ብለን ልንለየው አንችልም ።

አይምሮ (ማይንድ) የተሰራው ከብርሃንና ከቋንቋ ነው ! ብርሃን ብቻውን አይምሮ አይሆንም ! ስለዚህ መጀምሪያ ቃል ነበረ ፤ ቃል አለም ሆነ፤ ቃል አለምን ፈጠረ፡ ፈጣሪ (ጎድ) ቃል ነው!!! ይህ እጅግ እጅግ ጥልቅና ዛሬ አይደለም በነገረ መለኮት በኮግኒቲቭ ሳይንስ የተረጋገጠ ነው ! ቃል ከሌለ ማወቅ የለም !

Abe Abraham
Senior Member
Posts: 13186
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Abe Abraham » 08 Mar 2023, 12:39

Horus wrote:
07 Mar 2023, 23:57አቤ አብርሃም፣

የቋንቋ አናጢ

አንድ ቃል መፍጠር የፈጠራ ውጤት ነው፤ ማለትም አርት ነው። ቃላት የሚፈጥሩ የቋንቋ ካህናት ፈጣሪዊች ናቸው፣ ክሪኤቲቭ አርቲስቶች ናቸው። ካህን የሚለው እጅግ ጥንታዊ የግብጽ ቃል የተጠቀምኩት ትርጉሙ ክህሎተኛ ማለት ስለሆነ ነው ።

አንድን የቋንቋ ካህን እንደ አንድ አናጺ ተመልከተው ። አንድ አናጺ (አናጢ ወይም ህንጻ ሰሪ) የሚጠቀመው እንጨት ነው ። ከእንጨት ነው ቤት ወይም ህንጻ የሚገነባው ። ይህን ለማድረግ አናጺ አንድን እንጨት በአንድ ቅርጽ፣ ርዝመት፣ እጥረት፣ ስፋት፣ ወርድና ጥመት ብቻ አይደለም ያን ንጨት እያገጣጠመ ህንጻ የሚያቆመው። ቤት ሊሰራ የጣለውን ዛፍ በብዙ ልዩ ልቱ አይነት የፍልጥ ቁርጥራጮ ካሳመረ (ካባለተ) በኋላ ነው በንድፍ ላይ ያለውን ህንጻ የሚያዋቅረው ።

አንድ ቃል፣ ቃላትና አንድ ቋንቋ የተገነባው (የተቀመረው፣ የተወሰወሰው) በዚያ መንገድ ነው። እርግጥ ብዙ የአለም ቋንቋዎች፣ የኢትዮጵያ ቋንቋዎችን ጨምሮ አንድ ካህን ሆን ብሎ እንደ ሂሳብ ፣ እንደ አልጎሪዝም የሰራቸው አይደሉም ። በተፈጥሮ፣ በልማድ፣ በግዜ ሂደት (ኢቮሉሽን) የተቀመሩ ናቸው ። ያም ስለሆነ እንደ ማቲማቲክስ ወይም አልጎሪዝን ወጥ ሲስተም አይደሉም ። ዘመንዊ ጀርመንኛ ብቻ ነው በዚያ መልክ የተቀመረ ቋንቋ ። ዘመናዊ ሂንዱ ቋንቋም ሆን ተብሎ ተቀምሯል ።

ከነዚህ ውጭ ያሉት ቋንቋዎች እንደ አልጎሪዝም ስረ ቃሉን፣ የፊደላቱ ቅደም ተከተል፣ የቅጽላቱ ቅላጼ፣ የድምጾቹ መረገጥና መዋጥ፣ መጠበቅና መላላት ... ወዘተ ሁሉ ምንም የሚከተሉት ሕግ የላቸውም ። በተቀመጠ ፎርሙላ ልናውቃቸው አንችልም ። ለዚህ ነው የእያንዳንዱ ቋንቋ ብቻ ሳይሆን፣ የእያንዳንዱ ቃላት ታሪክ (ኢቲሞሎጂና ፊሎሎጂ) መመርመር ያስፈለገን ። ለምሳሌ ከላይ ያነሳሃው ጸወረ የሚለው የግዕዝ ስረቃሉ ጣረ (ጥነከረ፣ ባለጉልበት ሆነ፣ ጠንክሮ ሰራ) የሚል ነበር እንጂ በጠባቡ ተሸከመ ማለት ብቻ አልነበረም። ጻረ፣ ጾረ ማለት ጣረ ፣ ጥረት አደረገ ማለት ነው ።

ድምጽን እንደ እንጨት ግንግ ብንወስደው፣ የድምጽ ግንድ በልዩ ልዩ ትናንሽ ድምጾች እንከትፈዋለን ። ያ ፎነም ወይም ሆሄያት የምንለው ነው ። ለምሳሌ ከ ቀ በ ወ ረ ለ እንበል ። ልክ እንደ አንድ አናጺ ከነዚህ ትናንሽ ድምጾች ከበረ፣ ቀበረ፣ ቀወረ፣ በረቀ፣ ... እያልን እጅግ ብዙ ቃላት እንፈጥራለን ። እያንድንዱ ቃልም አንድ ነገር እንዲገልጽ፣ እንዲወክል፣ እንዲሰይም አድርገን ትርጉሙን እንወስናለን ።

ይህን ሁሉ የሚያደርጉ የቋንቋ ፈጣሪያን ክሪኤቲቭ አርቲስቶች ናቸው ። እነዚህ የቋንቋ ካህናት እረኞች፣ እናቶች፣ አባቶች፣ ነጋዴዎች፣ ቄሶች፣ ወታደሮች ሌላም ሌላም ሊሆኑ ይችላሉ ። የሰው ልጅ አንድን ነገር ከሌላ ነገር ለመለየትና ምልክት አድርጎ ለማስታወስ ለነገሮች ሁሉ ስም ይስጣል ። ትርጉም ይሰጣል ። ለምሳሌ 123 ዝም ብሎ የሶስት ቁጥሮች (ምልክቶች) መደርደር ነው ። ግን ለነጋዴው 123 ብር የገንዘብ ልክ ነው ። ለገበሬ የከብት ወይም የኩንታል ቁጥር ስፍር ነው ። ለማቲማቲክስ ምሁሩ የ100፣ የ10፣ የ1 ቤት ተብሎ ቦታ ያላቸው የዲጂቶች ሲስተም መስተዋቅር ነው ።

ቋንቋ ሚራክል ነው ። ቋንቋ ባይኖር የሰው ልጅ አይኖርም ነበር! በሁለት እግር የምንሄድ እንሰሶች ሁነን በየደኑና ዋሻው ውስጥ እንዳክር ነበር ። ለሰው ልጅ ስብዕናን የሰጠ ቋንቋ ነው! ለዚያ ደሞ ኤቦ ዬቦ እንላለን!
ኬር

Interesting ! እኔ ኣንዳንድ ግዜ የጥንት ኣባቶቻችን - የቋንቋ ካህናት - በስራ እያሉ እንደማያቸው ሆኖ ይሰማኛል ። ወደ የትናንትናው ስንመለስ ፥
ኣዎ ቁልፉን ካገኘህ ብዙ በሮች ይከፈቱልሃል ። ትናትና ብዙ ሳላስብ በራሴ ብዙ ሃሳቦች ስለመጡኝ ኖትቡክና ቀለም ይዤ መጻፍ ጀመርኩ ። ጭንቅላቴ ኣንዳንድ ግዜ " ተመልከት ! ይሄሳ ምን ይመስለሃል ? " ይለኛል !! ለምሳሌ ፥

1) ዛፍ ጥላ ስር ሆነን ስንነጋገር ከኔና ኣንቺ ቀር እነማን ነበሩ ።
2) ዛሬ ነው መቸ ነው ኣይንሽን የማየው
3) ቐፉርረሒምረጂም ( ረጊም)በሶስተኛው ፥

_ 123 ---> 213 ምን ታገኛለህ ?
_123----->321 ምን ታገኛለህ ?
_123----->123 ምን ታገኛለህ ?

ያገኘናቸው ሁለቱ ዘዴዎች ተጠቅመን ፥

1_ በሴማዊ ኣረብኛ ከ ظل (ዚል) የሚለውን ቃል ተነስተን ነጥብዋን ከ ዘ ካስወገድን طل (ጠ+ል ) እናገኛለን ። ጠ + ለ = ጥላ ( ይህ የማታማቲክስ ስራ ሳይሆን የኤቲሞሎጂ ትእዝብት ነው ። የኣሰራሩ እርግጥነት በደረጃ የተለያየ ሊሆን ይችላል ። በያዝነው ቃል ግን እርግጥነቱ 100% እንበለው ። )

2_ በሴማዊ ኣረብኛ ጂዝር የሚለውን ቃል ኣለ ። ትርጉሙ ስር ማለት ነው ። ከቃሉ ጀ ስናስወግድ (remove) ዘ + ረ ይዘን እንቀራለን ። ከዘረ ወደ ሰረ ፡ ከሰረ ወደ ስር መንገዱ ኣጭር ነው ።

3_የእንግሊዘኛው except በኣረብኛ " ቐይር " ነው and that leads us - as it appears - to በቀር

4_ " እኔ " ፡ " ኣንቺ " ና " ማን " የሴማዊ ኣረብኛ " ኣና " ፡ " ኣንታ " ና " መን " ዘመዶች መሆናቸው በቀላሉ የሚታወቅ ነው ።

5_ " መቸ " የሴማዊ ኣረብኛ " መታ (when) " ዘመድ ነው ።

6_ " ኣይን " የሴማዊ ኣረብኛ " ዓይን " ዘመድ ነው ። በየሱዳንኛ ኣረብኛ ዓይን የሚለውን ቃል እንደ ግስ ተጠቅመው " ተመልከት " የሚለውን ትርጉም ያስይዙታል ። " ዓ'ይና " በኣረብኛ ትርጉሙ sample ነው . ' ሳምፕሉ ' ከብዙ ተቀንሶ ለማሳየት የሚቀርብ ስለሆነ ይሆን ? በትግርኛ ከ " ዓይኒ " የወጣ ግስ የለንም ። ሴማዊ " ረአ " ግን እንጠቀማለን ።

7_ " ቐፈራ " የሚለውን ከስሜት (compassion ) ጋር የተሳሰረ የኣረብኛ ቃል ትርጉሙ to forgive ቢሆንም የፊደሎቹ ኣቋቋም ከ123 ወደ 213 ስንቀይረው " ፍቅር '' ይሰጠናል ። far-fetched ? May be. Etymology sometimes is a guessing work. በተጨማሪ በ ረ+ፈ+ ቀ የተመሰረተ ረፊቕ የሚባል የኣረብኛ ቃል ኣለ ። ትርጉሙ ፥ ጓደኛ/friend :: እንደገና እንደ " ፍቅር " ከስሜት ኣለም ማለት ነው ።

8_ በየስሜት ኣለም መዋኘት ከቀጠልን የኣረብኛው " ረሒም " ን ፊደሎች ከ 123 ወደ 321 ስንገለብጣቸው " መሓረ " ( ምሕረት ..) እናገኛለን ።

9_የቑርኣን ተማራማሪዎች መጽሓፉ በ " ሊሳኒን ዓረቢይን ሙቢን " ( በግልጽ የሆነ ልሳነ-ኣረብ// የኣረብ " በይን፡ ሙቢን" ክየኛውን " በየነ " ይዛመዳል ! ) የቀረበ ቢሆንም ኣንዳንድ የሌሎች ተጓራባች ህዝቦች ቃላቶች በውስጡ እንደሚያጠቃልል ይናገራሉ ። ለምሳሌ " ረጂም "/ረጊም ከረገመ ተረገመ የተወሰደ ነው ይላሉ ።
-

Horus
Senior Member+
Posts: 26859
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Horus » 08 Mar 2023, 14:33

አቤ አብርሃም፣
ግሩም ነው ! የእኔ ድክመት አረብኛ ቋንቋ አለማወቄ ነው ። ልማረው እያሰብኩኝ ነው ። ከ 1 እስከ 9 የዘረዘርካቸው የአረብኛና የኢትዮፒክ (የኢትዮጵያ ሴም ቃላት) መወራረስ ትክክል ናቸው፣ ከአንዱ በስተቀር ፣ በቁ 7 ያለው 'ቁወፈራ' ወደ ፍቅር አይሄድም ። አል ጃፋር (አል ጋፋር) መተው፣ የተተው፣ (ቱ ፎርጊቭ) ማለት ነው ። ይቅር ባይ አላህ ይሉታል ሙስሊሞች ። ይህ ቃል በጉራጌኛ እና ሃረሬኛ በቱባ ትርጉሙ አለ ።

በጉራጌኛ ግፈር ማለት ተው ማለት ሲሆን ለጋራ ጥቅም ለመንገድ፣ ለግጦሽ የተተወ ቦታ በሰባት ቤት ጀፎረ፣ በሶዶ ገፈርሳ ይባላል። በነገራችን ላይ ገፈርሳ ኦሮምኝ ሳይሆን ቈወፈረ ማለት ነው ። ለምሳሌ አቦ ተወኝ ለማለት አቤ ግፈሬ እንላለን። ስለዚህ መጀመሪያ እንዳልክው ፎርጊቭ ማድረግ እንጂ ፍቅር አይሆንም ! የቀሩት ሁሉ በትክክል ዲኮድ አድርገሃቸሃል ።

በቁ 6 ያለው ዐይን ስሩ የጥንቱ ግብጽ ነው ። ያ ማለት በቀምጥኛ የጨረቃ ብርሃን ነው ። Yah was the Egyptian Moon god. ከዚያ ቃል ነው ያዌ (ያህዌ) የሚባለው የአይሁዶች እምነትና ስማቸው የመጣቸው ። እንደ ምታውቀውና ስምህም እንደ ሚለው የአብርሃማዊ ሃይማኖት አማኞች የብርሃን አምላኪዎች ናቸው ። ያ ብርሃን ግን አንዱ የፀኃይ ብርሃን ነው ። ሌላው የጨረቃ ብርሃን ነው ። ኢስላም የጨረቃ ተከታይ ነው ። ግን አላህ የሚለው ቃል ያህ (Yah- Moon) ወይም ራህ (Rah - Sun) ከሚለው ይቀዳል።

ስለዚህ አው አይን የሚለው ቃል በላቲን አይ ነው ። መሰረቱ ብርሃን ነው፣ ማየት ነው !

ስለዚህ ከዚህ ቀደም እንደ ተባባልነው አንድ ቃል ስሩን (ኢቲማውን) ሳይለቅ ከፊቱ ፣ ከመሃሉ፣ ከጭራው ላይ አዳዲስ ድምጾችን በመቀጠል አዳዲስ ዲያሌክቶች እንፈጥራለን ። የጎሳ ዲያሊክቶች በዚያ መንገድ ነው የሚፈጠሩት !

ከኮንትሪቢውሽንህ አመሰግናለሁ !

ኬር

Abe Abraham
Senior Member
Posts: 13186
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Abe Abraham » 08 Mar 2023, 15:04

አንድን የቋንቋ ካህን እንደ አንድ አናጺ ተመልከተው ። አንድ አናጺ (አናጢ ወይም ህንጻ ሰሪ) የሚጠቀመው እንጨት ነው ። ከእንጨት ነው ቤት ወይም ህንጻ የሚገነባው ። ይህን ለማድረግ አናጺ አንድን እንጨት በአንድ ቅርጽ፣ ርዝመት፣ እጥረት፣ ስፋት፣ ወርድና ጥመት ብቻ አይደለም ያን ንጨት እያገጣጠመ ህንጻ የሚያቆመው። ቤት ሊሰራ የጣለውን ዛፍ በብዙ ልዩ ልቱ አይነት የፍልጥ ቁርጥራጮ ካሳመረ (ካባለተ) በኋላ ነው በንድፍ ላይ ያለውን ህንጻ የሚያዋቅረው
Once again extremely interesting! I have noticed that words with ጠ/ጸ seem to have interesting stories behind them in the field of semitic vocabulary using our methode of sound shifting .

_In Arabic the word ናሕት stands for to sculpt,hew,chisel,carve ( ሁላቸው የማሳመር ስራዎች).
_ ኣናጺ፡ ኣናጢ፡ ህንጻ፡ ሕንጻ -----> ነሓተ ! እንዴት ? If we put ጸ/ጠ/ተ side by side we discover the T of ነሓተ ! From ነሓተ ----> ሓነተ---> ሓነጸ ---> ሃነጸ ---> ኣነጸ !!!-

Abe Abraham
Senior Member
Posts: 13186
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Abe Abraham » 08 Mar 2023, 17:06

Horus wrote:
08 Mar 2023, 14:33
አቤ አብርሃም፣
ግሩም ነው ! የእኔ ድክመት አረብኛ ቋንቋ አለማወቄ ነው ። ልማረው እያሰብኩኝ ነው ። ከ 1 እስከ 9 የዘረዘርካቸው የአረብኛና የኢትዮፒክ (የኢትዮጵያ ሴም ቃላት) መወራረስ ትክክል ናቸው፣ ከአንዱ በስተቀር ፣ በቁ 7 ያለው 'ቁወፈራ' ወደ ፍቅር አይሄድም ። አል ጃፋር (አል ጋፋር) መተው፣ የተተው፣ (ቱ ፎርጊቭ) ማለት ነው ። ይቅር ባይ አላህ ይሉታል ሙስሊሞች ። ይህ ቃል በጉራጌኛ እና ሃረሬኛ በቱባ ትርጉሙ አለ ።

በጉራጌኛ ግፈር ማለት ተው ማለት ሲሆን ለጋራ ጥቅም ለመንገድ፣ ለግጦሽ የተተወ ቦታ በሰባት ቤት ጀፎረ፣ በሶዶ ገፈርሳ ይባላል። በነገራችን ላይ ገፈርሳ ኦሮምኝ ሳይሆን ቈወፈረ ማለት ነው ። ለምሳሌ አቦ ተወኝ ለማለት አቤ ግፈሬ እንላለን። ስለዚህ መጀመሪያ እንዳልክው ፎርጊቭ ማድረግ እንጂ ፍቅር አይሆንም ! የቀሩት ሁሉ በትክክል ዲኮድ አድርገሃቸሃል ።

በቁ 6 ያለው ዐይን ስሩ የጥንቱ ግብጽ ነው ። ያ ማለት በቀምጥኛ የጨረቃ ብርሃን ነው ። Yah was the Egyptian Moon god. ከዚያ ቃል ነው ያዌ (ያህዌ) የሚባለው የአይሁዶች እምነትና ስማቸው የመጣቸው ። እንደ ምታውቀውና ስምህም እንደ ሚለው የአብርሃማዊ ሃይማኖት አማኞች የብርሃን አምላኪዎች ናቸው ። ያ ብርሃን ግን አንዱ የፀኃይ ብርሃን ነው ። ሌላው የጨረቃ ብርሃን ነው ። ኢስላም የጨረቃ ተከታይ ነው ። ግን አላህ የሚለው ቃል ያህ (Yah- Moon) ወይም ራህ (Rah - Sun) ከሚለው ይቀዳል።

ስለዚህ አው አይን የሚለው ቃል በላቲን አይ ነው ። መሰረቱ ብርሃን ነው፣ ማየት ነው !

ስለዚህ ከዚህ ቀደም እንደ ተባባልነው አንድ ቃል ስሩን (ኢቲማውን) ሳይለቅ ከፊቱ ፣ ከመሃሉ፣ ከጭራው ላይ አዳዲስ ድምጾችን በመቀጠል አዳዲስ ዲያሌክቶች እንፈጥራለን ። የጎሳ ዲያሊክቶች በዚያ መንገድ ነው የሚፈጠሩት !

ከኮንትሪቢውሽንህ አመሰግናለሁ !

ኬር
በቁ 6 ያለው ዐይን ስሩ የጥንቱ ግብጽ ነው ። ያ ማለት በቀምጥኛ የጨረቃ ብርሃን ነው ። Yah was the Egyptian Moon god. ከዚያ ቃል ነው ያዌ (ያህዌ) የሚባለው የአይሁዶች እምነትስማቸው የመጣቸው ። እንደ ምታውቀውና ስምህም እንደ ሚለው የአብርሃማዊ ሃይማኖት አማኞች የብርሃን አምላኪዎች ናቸው ። ያ ብርሃን ግን አንዱ የፀኃይ ብርሃን ነው ። ሌላው የጨረቃ ብርሃን ነው ። ኢስላም የጨረቃ ተከታይ ነው ። ግን አላህ የሚለው ቃል ያህ (Yah- Moon) ወይም ራህ (Rah - Sun) ከሚለው ይቀዳል።
- ዓይን ስሩ የጥንቱ ግብጽ መሆኑን ኣላወቅኩም ነበር ። ኣንተ ራቅ ብለህ ወደ ምንጩ ተጉዘሃል ማለት ነው።
- ጨረቃና የኣረብኛው ቐመር በሁለት ፊደሎች ይገናኛሉ መሰለኝ ። Coincidence ?
- በኣረብኛ ቓላ/ኣለ ፡ የቑሉ (ይላል) ፡ ቐውል (utterance,saying) የሚባሉ ቃላቶች ኣሉ። በግብጽ ሶርያና ሌባኖን ቐን በኣ ተክቶ ኣል/ኣለት (ኣለ/ኣለች) የማለት ልምድ ኣለ ።
-ሙእሚን ( believer)
- ኢስም (ስም) ፡
- Ancient Egyptians ሲተረጉሙ ኣረቦች ኣል-ሚስሪዩን ኣል-ቑደማእ ይላሉ ። የመጽሓፍ መቅድም ደሞ ሙቐዲማ ይሉታል ።
ስለዚህ አው አይን የሚለው ቃል በላቲን አይ ነው ።
- ለምን ቃሉ ከነ ትንሽ ለውጡ በተለያዩ ቋንቋዎች እንደሚገኝ ኣስገራሚ ነው ።
በቁ 7 ያለው 'ቁወፈራ' ወደ ፍቅር አይሄድም ። አል ጃፋር (አል ጋፋር) መተው፣ የተተው፣ (ቱ ፎርጊቭ) ማለት ነው
ኣዎ እኛም ስንጸልይ " ዎ ኣቕፉር ለና ዙኑበና ፡ ከማ ነቕፊሩ ናሕኑ ኣይደን ልልሙዝኒቢና ኢለይና /ሕድግ ለነ፡ አበሳነ፥ ወጌጋየነ፣ ከመ ንሕነኒ ንሕድግ ኵሎ፡ ለዘአበሰ ለነ! " እንላለን እኮ ። I was talking in general terms. For instance the commandment of love in Christianity includes things like compassion,kindness,forgiveness ....

Besides the dictionary gives " to be on intimate terms; associate closely with someone " as one of the meanings of ሪፍቕ (rifq). I admit that it could be far-fetched.

ስለዚህ ከዚህ ቀደም እንደ ተባባልነው አንድ ቃል ስሩን (ኢቲማውን) ሳይለቅ ከፊቱ ፣ ከመሃሉ፣ ከጭራው ላይ አዳዲስ ድምጾችን በመቀጠል አዳዲስ ዲያሌክቶች እንፈጥራለን ። የጎሳ ዲያሊክቶች በዚያ መንገድ ነው የሚፈጠሩት !
That is true. በመንገዱ ቃሉ ትንሽ ይሁን ትልቅ የትርጉምና የኣጠቃቀም መቀያየር ሊያመጣ ይችላል ። ለምሳሌ በኣማርኛ መዋሽት( to lie ) ሲሆን በትግርኛ " ወሽዋሽ " ስንል " ሚስጢር የማይደብቅ ሰው ማለት ነው ። በኣረብኛ ደሞ " ወሻ ቢ .. '' ሲባል ትርጉሙ to inform against ....; to betray someone ይሆናል ። Amazing, isn't it ?
ግሩም ነው ! የእኔ ድክመት አረብኛ ቋንቋ አለማወቄ ነው ። ልማረው እያሰብኩኝ ነው ።
With your intellect,patience and detail-oriented mind you can learn anything.

-

Abe Abraham
Senior Member
Posts: 13186
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Abe Abraham » 09 Mar 2023, 13:27

ግሩም ነው ! የእኔ ድክመት አረብኛ ቋንቋ አለማወቄ ነው ። ልማረው እያሰብኩኝ ነው
ቋንቋውን ለመማር ተነስተህ ፊደሎችን ማጥናት ስትጀምር ኤቲሞሎጂካዊ ጥቅማቻው በቀጥታ ይገባሃል ፡፡ ለምሳሌ ፥

1_ ለምሳሌ ከ የ ኣረብኛ ፊደል ش /ሸ ተነስተን مشرق / መሽርቕ ከጻፍን በጓላ የኣረብኛ ሸን ሶስት ነጥቦች ጥለን مسرق /መ+ሰ+ረ+ቀ ፊደሎች የያዘ ጽሑፍ እናገኛለን ። ከዚያ ኣራቱ ፊደሎች ምስራቕ/ቅ ይሰጡናል ። ፊደል " መ " ተጨማሪ ስለሆነ ሰረቐ/ቀ ብቻ ይዘን ሰረቐ/ቀ-ብርሃን ለማለት እንችላለን ።

2_በተመሳሳይ ከ የኣረብኛ ፊደል غ/ቐ ተነስተን مغرب / መቕሪብ ከጻፍን በጓላ የኣረብኛ ቐን ኣንድ ነጥብ ጥለን معرب/መ+ዓ+ረ+በ ፊደሎች የያዘ ጽሑፍ እናገኛለን ። ከዚያ ኣራቱ ፊደሎች ምዕራብ ይሰጡናል ። ፊደል "መ" ተጨማሪ ስለሆነ በትግርኛ ዓ+ረ+በ ይዘን " ጸሓይ ዓሪባ/ ጸሃይዋ ጠለቀች " እንላለን ። ( ተዘይተጋግየ ደራሲ ኣርኣያ በላይ ፥ " ኣብ ዓራርቦ ጸሓይ ከይትሓዝን ኣንጊህካ ተበገስ/ዕየ ። " ኢሉ ጽሒፉ ኔሩ ። )

ፊደሎቹ ስታውቅ የድምጽ መቀየሩ ሂደት/መስርሕ በቀጥታ ታየዋለህ ። ማለት ፥ እንዴት ብሎ ነው የኣረቡ ሸ የህዝበ-ኣግኣዝያን ሰ የሆነውና ቐ ደሞ ዓ የሆነው!!!!!

-
Last edited by Abe Abraham on 10 Mar 2023, 13:54, edited 1 time in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 26859
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Horus » 10 Mar 2023, 00:17

አቤ አብርሃም፣
ለመልሴ መዘግየት ይቅርታ፣ በሌላ ነገር ተጠምጄ ነው ።

በተከታታይ እያሳየሀን ያለከው እንዴት አረብኛና የኢትዮጵያ ሴም ቋንቋዎች ተመሳሳይና ተዛማጅ እንደ ሆኑ ነው ። 'ምስራቅ' እና 'መዕራብ' እጅግ አስደናቂ የጥንታዊ ግብጽ ቃላት ናቸው ። የምስርቅ ስረ ቃል 'ራዕ' (Ra'/Rah) ሲሆን እጅግ ታላቁ የግብጾች አምላክ ነበር ። ትርጉሙ ብርሃን፣ ጮራ ማለት ብቻ ሳይሆን ሰማይ፣ ላይ፣ ከላይ ያለ፣ ወደ ላይ መውጣት ማለት ነው ። ተራ ትርጉሙ sun rise or rise ማለት ነው ። ጽራህ፣ ራዕይ፣ ራቂ፣ ሩቅ፣ላቂ፣ ሊቅ ሁሉ የዚያ ዝርያ ናቸው ። ሰረቀ ብርሃን! ድንቅ ቃል ነው ! የሱ ወንድም ኮከበ ጽባህ ነው ። ጽባህ፣ ጠባ (መስከረም ጠባ) ንጋት ማለት ሲሆን ባህ (የግዕዙ) ፈካ፣ በራ፣ አበበ ማለት ነው ። በጉራጌኛ ጠዋት 'ጠጥበት/ተጽበት' እንለዋለን ። ለግብጾች የፀኃይ መውጣት ትልቅ መለኮታዊ ርርጉም ነበረው! አሙነ ራህ ማለት የራህ እምነት ወይም የብርሃን አምልኮ ምለት ነው ።

ምዕራብ እንዲሁ እጅግ ታላቅ የጥንታዊ ግብጽ ስልጣኔ ቃል ነው ። ኧርብ ማለት መግባት፣ መጥለቅ ማለት ነው ። ጉራጌ እራት ለማለት 'ኧርባት' ይላል ። የማታ ምግብ ማለት ነው ። ኧርብ (መኧርብ) የጸሃይ መጥለቂያ ቦታ ስለነበር የግብጾች የመቃብር ቦታና ፒራሚዶች ሁሉ ያሉት በምዕራብ ግብጽ ነው። The valley of the dead ማለት ኧርብ/መኧርብ ነው ። ዛሬ ትንሽ ለወጥ ብናደርገውም 'መቃብር ' ወይም ቅብር የሚለው ቃል ከኧርብ የተቀዳ ነው ።

ስለዚህ አንድ ትልቅ ምስጢር ልንገርህ! የሴም ቋንቋ ከጥንታዊ ግብጽ ወይም ኬሚቲክ የተቀዳ ነው ። ይህ እጅግ እጅግ መሰረታዊ ነገር ነው ! ብዙ ብዙ የግዕዝ ቃላት ያሉት በኋላ ከመጡት የሴም ቋንቋዎች ለምሳሌ ኢብላቴ፣ኡጋሪቴ፣ አረሜይክ ወዘተ ሳይሆን ከኬሚቲክ ነው!!!

የቀሩት ከላይ የጠቀስካቸው ናሃት (አናጺ)፣ ዋባልት (ባልትና/ብልሃት)፣ ቀራጺ (ቀራሲ በጉራጌኛ ጀማሪ፣ የአንድ ነገር ጸናሺ ማለት ነው)፣ ጥላ (ክላ/ከለላ)፣ ጂዝር (ዘር/ስር)፣ ቆፋራ/ጀፎረ/ ጎፈሬ ወይም የተተወ። ቆወል/ ቃል ሁሉም የኬሚቲክ ዘር ናቸው ። ቀወል የሚለው ሲጀመር ወር (ወል) ነበር ። መናገር ወይም ቱ ስፒክ ማለት ነው ። ዛሬ ወሬ የምንለው ቃል ነው አረቦች ቀወል የሚሉት!!

ሰላም ሁን!

Abe Abraham
Senior Member
Posts: 13186
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Abe Abraham » 10 Mar 2023, 12:25

Horus wrote:
10 Mar 2023, 00:17

Just like you solved the msytery of the insertion of ነ in words like እንጨት (Amharic)/ዕንጸይቲ (Tigrigna)/ without the Ge'ez ነ we would have the Hebrew እጸ / the influence of Ancient Egypt on our language for me is a great revelation.

Talking about ቐውል ( with ወ being a vowel ) if the word in its original shape in kémetic was ወል the relationship between ቐ in Arabic and ወ in Kémetic could lead us to a possible relationship between ውራ፡ ወረረ፡ ወርሮ-በላ and ቓራ ( raid) in Arabic. ( በልዐ/በላ= to eat, in Arabic በለዓ = to swallow, akela = to eat/ that reminds us of course of እህል/እኽሊ )

ኣሁን ስለሌላ ቃል ( ሓረሳ ) እያነበብኩ የመጣኝ ሃሳብ ፥ ረዋ በኣረብኛ to transmit ማለት ነው ። ምሳሌ ፡ ለዜና / that reminds us of ወሬና ማውራት !!! /
-

Abe Abraham
Senior Member
Posts: 13186
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Abe Abraham » 10 Mar 2023, 13:52ቀደም ኣብ ሱዳን ሓንቲ ብሓናን ብሉ ብሉ ( ኣዲኣ ሓበሻ ምዃና ዝውረ ) ዝተደርፈት " ሰና ያ ወለድ ! ኢንታ ሓበሺ ዋላ ወደልበለድ ! ኢንታ ሓበሺ ዋላ ወደልዓረብ! " ዘርእስታ ውርይቲ ደርፊ ኔራ ። ሕጂ እታ ደርፊ ብዙሕ ትዳጋገም ዋላ እንተኾነት ነታ " ሓበሻ ዲኻ ዋላ ወዲ ዓዲ! ሓበሻ ዲኻ ዋላ ወዲ ዓረብ ! " ትብል ክፋል ናይ እታ ደርፊ ኣልጊሶማ ።

ሰና ትብል ቃል ኣብ ቋንቋ ዓረብን ታሪኽን ዝኣተወት ብነብይ ናይ ምስልምና መሓመድ ኢያ ይበሃል ። ሓደ እዋን ነጋዶ ሓበሻ ናብ ሓውሲ-ደሴት ዓረብ ከይዶም ክዛናግዑ እንዳ ሳዕስዑ እንከለዉ ነብይ መሓመድ ንዓኢሻ ሒዙ እንከሎ ኣድናቖቱን ሓጎሱን ክግለጽ ብቋንቋና እንታይ ከም ዝበሃል ምስ ሓተተ " ኣሰና እዩ ዝበሃል ምስ በልዎ " ነቶም ተላሃይቲ " ኣሰና! ኣሰና! " ብምባል ሰላም ኢልዎም ። ሱዳናውያን ንኣሰና "ሰና! ሰና! " እንዳ በሉ ክጥቀሙላ እንከለዉ ከምዚ " ኣየ ክዳን ! ኣየ ....!! " እዮም ዘስምዑላ ።-

Horus
Senior Member+
Posts: 26859
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Horus » 10 Mar 2023, 14:00

Abe,
አንድ ነገር ብቻ ባስቸኳይ ልበል። ቆወል የሚለው ክወል፣ ክወር፣ ሃወር፣ ሃውርር፣ አውርር እያለ ይረባል ። ወ ድሮ ድሮ አፍ ማለት ነበር፤ ምልክትና ትርጉም አንድ በነበሩበት ዘመን ከ/ቀ ፕሪፊክስ ቅጽል መሆን አለበት ። እኛ መናገር ስንል ሃውር፣ አውር። አውርር ነው የምንለው። ወሬ የነገር ስም ነው ። ዜና/ዝና ስሩ ሌላ ነው ። አንደ ነገረ መንገር (ቱ ቴል) አውድ እንለዋለን በጉራጌ፤ ባማርኛ አውጋ የሚባለው ማለት ነው። ስለዚህ ሃወር እና አውድ/አውጋ ካየህ ሁለቱም ወ አላቸው! ኤቲማ ማለት ያ ነው። ከ/ገ/ ቀ ከፊትና ከኋል ሲቀጠል ታያለህ ።

ረዋ ማስተላልፈ ያው መንገር ማለት ነው ። መረዋ ማለት ነው። ግን ወ እዚያም አለ ።

ኬር!

Abe Abraham
Senior Member
Posts: 13186
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Abe Abraham » 10 Mar 2023, 14:36

Horus wrote:
10 Mar 2023, 14:00
Abe,
አንድ ነገር ብቻ ባስቸኳይ ልበል። ቆወል የሚለው ክወል፣ ክወር፣ ሃወር፣ ሃውርር፣ አውርር እያለ ይረባል ። ወ ድሮ ድሮ አፍ ማለት ነበር፤ ምልክትና ትርጉም አንድ በነበሩበት ዘመን ከ/ቀ ፕሪፊክስ ቅጽል መሆን አለበት ። እኛ መናገር ስንል ሃውር፣ አውር። አውርር ነው የምንለው። ወሬ የነገር ስም ነው ። ዜና/ዝና ስሩ ሌላ ነው ። አንደ ነገረ መንገር (ቱ ቴል) አውድ እንለዋለን በጉራጌ፤ ባማርኛ አውጋ የሚባለው ማለት ነው። ስለዚህ ሃወር እና አውድ/አውጋ ካየህ ሁለቱም ወ አላቸው! ኤቲማ ማለት ያ ነው። ከ/ገ/ ቀ ከፊትና ከኋል ሲቀጠል ታያለህ ።

ረዋ ማስተላልፈ ያው መንገር ማለት ነው ። መረዋ ማለት ነው። ግን ወ እዚያም አለ ።

ኬር!
ዜና ያነሳሁት ለሚነገር ነገር ምሳሌ ለመስጠት ነው ። በኣረብኛ رَوَى الأَخْبارَ ( ረዋ ኣል-ኣኽባራ ...) ዜናውን ኣስተላለፈ ማለት ነው ።

ኣረቦች ከረዋ ያወጡት ሪዋያ ( story) የሚል ቃል ኣላቸው ኣንተ የጠቀስከው " መረዋ " መሰረቱ ከየት ነው ? ግእዝ ?
-

Horus
Senior Member+
Posts: 26859
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Horus » 10 Mar 2023, 15:16

Abe Abraham wrote:
10 Mar 2023, 14:36
Horus wrote:
10 Mar 2023, 14:00
Abe,
አንድ ነገር ብቻ ባስቸኳይ ልበል። ቆወል የሚለው ክወል፣ ክወር፣ ሃወር፣ ሃውርር፣ አውርር እያለ ይረባል ። ወ ድሮ ድሮ አፍ ማለት ነበር፤ ምልክትና ትርጉም አንድ በነበሩበት ዘመን ከ/ቀ ፕሪፊክስ ቅጽል መሆን አለበት ። እኛ መናገር ስንል ሃውር፣ አውር። አውርር ነው የምንለው። ወሬ የነገር ስም ነው ። ዜና/ዝና ስሩ ሌላ ነው ። አንደ ነገረ መንገር (ቱ ቴል) አውድ እንለዋለን በጉራጌ፤ ባማርኛ አውጋ የሚባለው ማለት ነው። ስለዚህ ሃወር እና አውድ/አውጋ ካየህ ሁለቱም ወ አላቸው! ኤቲማ ማለት ያ ነው። ከ/ገ/ ቀ ከፊትና ከኋል ሲቀጠል ታያለህ ።

ረዋ ማስተላልፈ ያው መንገር ማለት ነው ። መረዋ ማለት ነው። ግን ወ እዚያም አለ ።

ኬር!
ዜና ያነሳሁት ለሚነገር ነገር ምሳሌ ለመስጠት ነው ። በኣረብኛ رَوَى الأَخْبارَ ( ረዋ ኣል-ኣኽባራ ...) ዜናውን ኣስተላለፈ ማለት ነው ።

ኣረቦች ከረዋ ያወጡት ሪዋያ ( story) የሚል ቃል ኣላቸው ኣንተ የጠቀስከው " መረዋ " መሰረቱ ከየት ነው ? ግእዝ ?
-
"ረዋ ማስተላልፈ ያው መንገር ማለት ነው ። መረዋ ማለት ነው። ግን ወ እዚያም አለ ።"

ረዋ ላልከው ምሳሌ ነው የሰጠሁህ (መረዋ) ማለት ድምጽ ማስተላለፍ ስለሆነ መረዋ/በረዋ ከላይ ያለው 'ወር ነውኮ!

Post Reply