Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30911
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Horus » 30 Mar 2023, 13:05

መለከት፣
ትክክል ነህ፤ እኔ ሰሜን ጸሎት፣ ደቡብ ጸሎት ከሚለው ውይይታችሁ ውጭ ስለ ላለና ታተ ስረቃል (ኤቲማ) ነው የማስበው። ላለ የሚለው ቃል ራ' ከሚለው የጥንት ግብጽ የመጣ ሲሆን ሰማይ ማለት ነው ። ታተ የሚለው ቃል ካ'/ጋ' (ጌ) ከሚለው ግብጽኛ የመጣ ሲሆን መሬት ማለት ነው ። እርግጥ ዛሬ ላይ 'ላይ/ታች፤ ሰሜን/ደቡብ እንላለን ። ጸሎት በሚባለው አገር ዙሪያ ስላለው ፖለቲካ ምንም አላውቅም!!!

Naga Tuma
Member+
Posts: 5543
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Naga Tuma » 30 Mar 2023, 13:59

Abe Abraham wrote:
24 Mar 2023, 20:42
4_ ከጂዝር --->ጂዝ--->ጂዳ is plausible because to the change of sound there could also be addition or deduction of letters. Example : ኣፍንጫ ---> ኣፍን+ጫ ---> ኣፍን ---> ኣንፍ ( nose in Arabic ! ) . Therefore continue with your search without abandoning some routes too quickly.

Abe Abraham,

Thank you for your explanations, particularly this one. You are more confident than I in thinking that it is plausible. I asked the question hesitantly because I have no proof for an oral story that I heard years ago from a Borana man.

Studying languages is not my expertise. I enjoyed Math theorems in high school. You can enjoy proving them without leaving any room for an error.

Here is the oral story that I heard from him. The original name for ሶዶ ጅዳ is ሶዱ ህዳ። He then quipped that it wasn't even his real name. It was a sort of nick name given to him for what he achieved for the first time in the community's history. ሶዱ can roughly mean domesticator. ህዳ means root. It also means ሀረግ። I am sure that the natural similarities between the two is clear to you.

The man got that nick name because he was the first person to start plant domestication in Ethiopia by experimenting with ህዳ or ስር or the root of a plant. It has been said that when an old man dies in Africa, a library dies.

Do I have a proof for this oral story? No. Do I have the expertise to prove it? No. Presumably trained people like you and Horus in the field of language studies are well equipped to give it a try to prove or disprove it.

I would be much interested to know the outcome to check its consistency with other documented accounts. The author of Guns, Germs, and Steel, Jared Diamond, has documented that Ethiopia was one of the places where plant domestication was started. The other place he noted is the Futile Crescent. If I remember correctly, Horus has written that the word ማሳ or ማሲ also exists in the word Mesopotamia of the Fertile Crescent.

Then again, here we are discussing about how people say ስር and ህደ in these two regions of the world.

Now just imagine that we have a proof in hand that ሶዱ ህዳ was in fact the first man known to have started plant domestication, at least in Ethiopia. When did he live? Documented stories suggest that animal and plant domestications were started about ten thousand years ago.

If that is the case, what fraction of the history of mankind in the last ten thousand years alone do we know? Many of us would be and should be ashamed about how much we didn't know.

Horus
Senior Member+
Posts: 30911
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Horus » 31 Mar 2023, 01:50

አቤና ናጋ፣
አንፉና
ሳዳ
መሶብ
በጉራጌኛ ...
አንፉና = አፍንጫ ፤ (የክስታኔ አባባል ... አፍ ዬሳተ ባንፉናን ታተ! አፍህ የት እንደ ሆነ ካላወቅክ ካፍንጫህ በታች ነው!!! በገዋ ሰው ላይ የሚተረት!!!
ሶዶ፤ ስረ ቃሉ 'ሳዳ' = ድርሻ፣ ክፍፍል፣ ሼር፣ ዛሬ ፌት የምለው የአንድ ሰው እጣ ማለት ነው ። ሰው በህይወት የደረሰበት ነገር ፣ ያገኘው እጣ ፈንታ ሳዳ ይባላል ። ጉራጌ ሳድ ሲል አካፍል፣ አከፋፍል ማለቱ ነው ። የአንድ ሕዝብ መኖሪያ ክፍለ አገር ሳዳ/ሶዶ ይባላል ። ለዚህም ነው የጉራጌ ሶዶ አለ፣ የወላይታ ሶዶ አለ፣ ያማራ ሶዶ የኦሮሞ ሶዶ ያለው ። ሶዶ እንደ ወረዳ ወዘተ የቦታ አከፋፈል ነው ። ለምሳሌ ሶዶ በሚባለው የአገር ክፍል ክስታኔ (ክርስቲያን) የሚባሉ ጉራጌዎች ይኖራሉ ። ሶዶ የሰው ወይም የህዝብ ስም አይደለም፣ የክፍለ ምድር ስም ነው ።

ለሳዳ ቅርብ የሆነው የአረብኛ ቃል ሳኢድ ወይም ሰኢድ የሚለው እሱም እድል ማለት ነው ! ጉራጌ አንድ ነገር ደርሶበት ሳዳንዲ ሲል እድሌ ነው ማለቱ ነው ያነው የሶዶ ትክክለኛ ትርጉም !

ሜሶ ፖታሚያ = በአረሜይክ ፣ በሁለት ወንዞች (ዉሃዎች) መሃል ያለ ቦታ ማለት ነው ። ያም ማለት በታይግሪስና ኢዩፍቲስ ወንዞች መሃል ያለ አገር ኢራቅ ማለት ነው ።

ቃሉ ሲፈታ = ሜሶ (መሃል) ማለት ነው ። በግዕዝ መሶብ ይባላል። በመካከል ተደርጎ የሚበላበት ሌማት ማለት ነው ።
ፖታ (ቤት) = ቦታ ማለት ነው
ሚያ/ማያ/ማይ = ዉሃ ወንዝ ማለት ነው ።

ስለዚህ ዘመናዊ ከሆነው አረብኛ በፊት የነበረው የኢትዮ ሴሚቲክ ቋንቋ ነው ። አንፉና የጉራጌ አፍንጫ ነው !

Abe Abraham
Senior Member
Posts: 14412
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Abe Abraham » 08 Apr 2023, 16:04

Here is the oral story that I heard from him. The original name for ሶዶ ጅዳ is ሶዱ ህዳ። He then quipped that it wasn't even his real name. It was a sort of nick name given to him for what he achieved for the first time in the community's history. ሶዱ can roughly mean domesticator. ህዳ means root. It also means ሀረግ። I am sure that the natural similarities between the two is clear to you.

The man got that nick name because he was the first person to start plant domestication in Ethiopia by experimenting with ህዳ or ስር or the root of a plant. It has been said that when an old man dies in Africa, a library dies.

ሶዶ፤ ስረ ቃሉ 'ሳዳ' = ድርሻ፣ ክፍፍል፣ ሼር፣ ዛሬ ፌት የምለው የአንድ ሰው እጣ ማለት ነው ። ሰው በህይወት የደረሰበት ነገር ፣ ያገኘው እጣ ፈንታ ሳዳ ይባላል ። ጉራጌ ሳድ ሲል አካፍል፣ አከፋፍል ማለቱ ነው ።

It is interesting ሶዶ in Borana and ሶዶ ከነስረ-ቃሉ "ሳዳ " are related to the concept of land,sharing and cultivation. Guess what " ዴሳ " in Tigrigna too is a family of those words and to be precise if you get a piece of Désa land it means that it has been allotted to you through the Désa system based on equality.

When I was a kid my family used to get a Désa land to farm it with the help of relatives and make use of its products. With time as demand increased Désa was limited to the residents of my ancestral village.

The brothers of my grandfather, respected villagers, were given the opportunity to lead the committee responsible for Désa( ዴሳ- for farming) and Tésa (ጤሳ - ለመኖርያ ቤት) lands.

ሰሰናዩ ( ኬር)!!

-

Abe Abraham
Senior Member
Posts: 14412
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Abe Abraham » 03 May 2023, 14:07

  • ኣንድ ፍልስጤማዊ ምሁር (ዶክተር) ስለ በእስልምና ታሪክ ጸሃፊዎችና የቑርኣን ተንታዮች መጽሃፎች ሰርገው የገቡ " ኢስራኤሊያት " ( ከኣይሁዶች የተወረሱ " የሃይማኖት " ኣፈ-ታሪኮች/stories/ቒሰስ ከነጭማሪዎቻቸው) ሲናገር በጣም ኣስቂኝ ( ለምሳሌ ፥ የዮሴፍ ኣባት/ያቆብ/ ልጁን በላው የተባለውን ተኩላ በተኣምር ኣስመጥቶ " ለምን ልጄን በላህ ? " ብሎ ጠየቀው!!!) ናቸው ካለ በጓላ ታላቁ የኣረብኛ ስነ-ጽሁፍ መስራቹ/ጀማሪው/ ኣል-ጃሒዝ /የኣፍሪቃ ዘር የነበረው/ ኣፈ-ታሪኾቹ " ሃሽት " ናቸው ብሎ እንደተቸ ኣመለከተ ።

    ኣሁን " ሃሽት ( هشت ) " በሲርያ ያሉት የድሩዝ ማሕበረ-ሰብ ላህጃ/ የስፍራው ልሳን/ ኣነጋገር " ሃሰት (هست) " ማለት ነው ። ተመልከት ፥ የኣረብኛ " ሸ " ና " ሰ " ን የሚለያያቸው በ " ሸ " ላይ ያሉትን ሶስት ነጥቦች ናቸው ። የሲርያ ዱርዞችና የፍልስጤም ( ለምሳሌ ፥ በተርሺሓ ትባል በነበረችው መንደር ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ) ኣረቦች ሶስት ነጥቦችን እንዳሉ ጠብቀው " ሃሽት " ሲሉ እኛ ደሞ ነጥቦች ጥለን እስካሁን ድረሰ " ሃሰት " በኣማርኛ " ሓሶት " በትግርኛ እንላለን ማለት ነው ።

    ኣንዳንድ የኛን የሚመስሉ ቃላቶች በክላሲካዊ ኣረብኛ ካላገኝሃቸው በላህጃዎቹ ቁጭ ብለው ሲጠብቁህ በጣም የሚያገርም ነው ። ሌላው ኣረቦች በጣም ክላሲካልና " obscure " ናቸው የሚልዋቸው ቃላቶች በኛ የታወቁ መሆናቸው ስትገነዘብ ትንሽ ቆመህ እንድታስብ ያደርጉሃል ። ኣረቦች " ባዕሊ/ባሌ " የሚል ቃል በዘመናችን ሲጠቀሙ ፈገግታ ይጨምሩለታል !! ለኛ " ባሌ/ በዓል ቤተይ/ የሚል ቃል የድሮ ሳይሆን የዘንድሮ ነው !!!!

    ሰሰናዩ ( ኬር)!!

-

Abe Abraham
Senior Member
Posts: 14412
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Abe Abraham » 21 May 2023, 19:52

  • (كنف/knf) = kanaf/ከነፍ/ ( wing; side,flank...) ....in Arabic. Ex: ዓሻ ፊ ከነፊሂ = He lived under his wing or his protection.

  • ባማርኛ ፥ ክንፍ

-

Horus
Senior Member+
Posts: 30911
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Horus » 22 May 2023, 00:35

Abe Abraham wrote:
03 May 2023, 14:07
  • ኣንድ ፍልስጤማዊ ምሁር (ዶክተር) ስለ በእስልምና ታሪክ ጸሃፊዎችና የቑርኣን ተንታዮች መጽሃፎች ሰርገው የገቡ " ኢስራኤሊያት " ( ከኣይሁዶች የተወረሱ " የሃይማኖት " ኣፈ-ታሪኮች/stories/ቒሰስ ከነጭማሪዎቻቸው) ሲናገር በጣም ኣስቂኝ ( ለምሳሌ ፥ የዮሴፍ ኣባት/ያቆብ/ ልጁን በላው የተባለውን ተኩላ በተኣምር ኣስመጥቶ " ለምን ልጄን በላህ ? " ብሎ ጠየቀው!!!) ናቸው ካለ በጓላ ታላቁ የኣረብኛ ስነ-ጽሁፍ መስራቹ/ጀማሪው/ ኣል-ጃሒዝ /የኣፍሪቃ ዘር የነበረው/ ኣፈ-ታሪኾቹ " ሃሽት " ናቸው ብሎ እንደተቸ ኣመለከተ ።

    ኣሁን " ሃሽት ( هشت ) " በሲርያ ያሉት የድሩዝ ማሕበረ-ሰብ ላህጃ/ የስፍራው ልሳን/ ኣነጋገር " ሃሰት (هست) " ማለት ነው ። ተመልከት ፥ የኣረብኛ " ሸ " ና " ሰ " ን የሚለያያቸው በ " ሸ " ላይ ያሉትን ሶስት ነጥቦች ናቸው ። የሲርያ ዱርዞችና የፍልስጤም ( ለምሳሌ ፥ በተርሺሓ ትባል በነበረችው መንደር ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ) ኣረቦች ሶስት ነጥቦችን እንዳሉ ጠብቀው " ሃሽት " ሲሉ እኛ ደሞ ነጥቦች ጥለን እስካሁን ድረሰ " ሃሰት " በኣማርኛ " ሓሶት " በትግርኛ እንላለን ማለት ነው ።

    ኣንዳንድ የኛን የሚመስሉ ቃላቶች በክላሲካዊ ኣረብኛ ካላገኝሃቸው በላህጃዎቹ ቁጭ ብለው ሲጠብቁህ በጣም የሚያገርም ነው ። ሌላው ኣረቦች በጣም ክላሲካልና " obscure " ናቸው የሚልዋቸው ቃላቶች በኛ የታወቁ መሆናቸው ስትገነዘብ ትንሽ ቆመህ እንድታስብ ያደርጉሃል ። ኣረቦች " ባዕሊ/ባሌ " የሚል ቃል በዘመናችን ሲጠቀሙ ፈገግታ ይጨምሩለታል !! ለኛ " ባሌ/ በዓል ቤተይ/ የሚል ቃል የድሮ ሳይሆን የዘንድሮ ነው !!!!

    ሰሰናዩ ( ኬር)!!

-
አቤ፣
ኢትዮሴሚቲክ ጥንታዊ ነው ሲባልኮ ዉሸትና ፈጠራ አይደለም ። ማርቲን ብርናል ጥቁር አቴና በሚለው መጽሃፉ ጥንታዊ የሴም ቋንቋ ሳይለወጥ ያለው ኮንሰርቫቲቭ በሆነው ኢትዮሴሚቲክ ውስጥ ነው ይላል ።

በድሩዞች ላህጃ ሃሽት ሃሰት መሆኑ አይደለም የሚያስገርመው ። እራሱ ላህጃ የሚለው ቃል ነው ። ላህ ማለት በጥንታዊ ግብጽ የፈርኦኖች ላህ (ልሳን!) አፍ ማለት ነው ። ለዚን በል ስንል ተናገር የምንለው፣ ቋንቋንም ልሳን (ላህሳን፣ ላህጃን) የምንለው! ሌላው ቀርቶ የላቲን ላን ጉጅ ግብጻዊ ቀምጥ ነው ።

ክንፍ ደሞ ነ መሃል ሳይገባበት ጫፍ ማለት ነው ! ትጉሙ አንድ ነው ። በኳስ ጨዋታ የቀኝ ክንፍ፣ የግራ ክንፍ ተጫዋች እንዳለ ሁሉ ባሜሪካ ፉትቦል የቀኛ ግራ ክንፍ ዳኛ አለ!!!!!

ግ ን የሚገርምህ ላህጭ፣ ላህጫም ስንል አፍ ብቻ አይሆን ምራቅ አፍ ውስጥ ያለውም ዉሃ ነው ። ለግብጾች ቡል ማለት ምግብ እና መብላት ነበር ። ማለትም ላህ አፍና ቡል፣ ቡህል አብረው ነው የፈጠሯቸው !!! እኛም ሳንቅር በል ተናገር፣ ብላ ተመገብ፣ መብል ምግብ እንላለን ! ብዙ ግዜ ነግሬሃለሁ ! የጥንታዊት ግብጽ ምስጢር ያለ በኛ በኢትዮጵያዊያን ዘንድ ነው! ይህ ደሞ አንድ ቀን በምርመ ተደግፎ ይወጣል !!!!
ኬር!

Abe Abraham
Senior Member
Posts: 14412
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Abe Abraham » 29 May 2023, 17:24

Horus wrote:
22 May 2023, 00:35

ኣንድ ጊዜ በቤተ-መጻሕፍት ሙስሓፍ ዑስማን ይዤ ደስ ብሎኝ -- ፊደሎቹ ትልቅና ለማንበብ የማይሰለቹ ስለ ሆኑ -- ቆሜ ገጾችን እየገለባበጥኩ ኣንድ በኣረብኛ " ኣረቦች " የሚል ኣርእስት የያዘ የተተረጎመ መጽሓፍ ኣይኔን ስለ ሳበ እጄን ወርውሬ ወደ ኣንድ ጠረጴዛ ወስጄ ትንሽ ላነበው ስሞክር " የሴማውያን ቋንቋዎች ምንጭ ምብራቅ ኣፍሪቃ ሳይሆን ኣይቀርም " የሚል -- ያን ግዜ ለኔ ኣስገራሚ -- ሃሳብ ኣገኘሁ ። ስለዚህ " ኢትዮሴሚቲክ ጥንታዊ ነው ሲባልኮ ዉሸትና ፈጠራ አይደለም '' ያልከውን ልክ ሊሆን ይችላል ።

Abe Abraham
Senior Member
Posts: 14412
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Abe Abraham » 04 Jul 2023, 15:49

1_"ኣል-ሙዝን "በኣረብኛ ትርጉሙ ደመና(cloud) ሲሆን መ+ዘ+ነ ለብቻው ወስደን ቅደም ተከተሉን ወደ ዘ+ነ+መ ቀይረን ባማርኛ ከደመና ግንኙነት ያለው ዝናምና ቤተ-ሰቦቹን እናገኛለን ።

2_ ጀረፋ በኣረብኛ ትርጉሙ " to sweep away; to wash away " ሲሆን ኣንድ ነገር(stream) " ጃርፍ " ከሆነ ደሞ torrential; stormy በሚሉት ቃላቶች ይተረጎማል ። ባማርኛሳ " ጎርፍ " ምን ያደርጋል ?

3_Since we are talking about cloud,rain and water I would like to mention the Tigrigna word " ጠሊ " which is related to the Arabic word " ጠል " (dew;fine rain,drizzle).

4_My French source tells me that " zabara/ዘበራ " in Arabic means " parler " ( Ex: ሳኣልተሁ ፈማ ዘበራ ለይ ቢዚብሪን::/ ጠይቄው ባንዲት ቃልም ኣልመለሰልኝም ።/ By changing the order of ዘበረ to ዘረበ and applying the necessary vowel changes we get the Tigrigna ዘረባ !!

ታላቁ ሃይለ ገብሩ ፡ " ...ዘረባ ሰብ ፈጺምና ኣይንስማዕ ፡ ኣነን ንስኽን ጥራይ ንሳማማዕ! "

Horus
Senior Member+
Posts: 30911
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Horus » 04 Jul 2023, 16:30

አቤ አብርሃም፣
ከዚህ ቀደም እንዳልኩት አንተ የነዚህ ቃላት አሰካክ በደምብ ገብቶሃል ።

ስለ ዘበራ ምንም የሚያከራክር ነገር የለውም። በጉራጌኛ ዘብር መልስ ማለት ነው ። ይህ ለንግግርም ለሌላም ፊዚካል ነገር መልስ ማለት ነው። ስለዚህ ዘረባ (ተዛረብ) ልክ እንዳልከው ነው ።

የቃሉ ኢቲሞሎጂ በግእዝም በፕሮቶ ኢንዶ ኢሮፕ አንድ ነው ። ወር የሚባለው ስረ ቃል መናገር ማለት ነው ። ጉራጌ አውርር ይላል (ተናገር) ማለት ነው። ዛሬ ወሬ የምንለው ነው ። ላቲን ቫውል፣ ዋውር የሚለው ነው ። ቃሉ መዞር ፣ ሳይክል ማለት ስለሆነ ወር የሚባለው የ30 ቀን ሳይክልም በ ግ እም በላቲንም አንድ ነው። ዲሴምበር፣ ኖቬምበር ሲሉ 10ኛ 9ኛ ወር ማለት ነው ። ስለዚህ በር እና ወር አንድ ቃል ነው ። መዞር፣ መመላለስ፣ መመለስ፣ መልስ ማለት ነው ።

ዙር፣ ዙወር፣ ዙበር፣ ዘብር መልስ ማለት ነው ። ለምሳሌ ታላቁ የቅዳሴ ሽብሸባ ወረብ ይባላል፣ መዞር ፣ በክብ እየዞሩ ማሸብሸብ ማለት ነው ። በላቲን ደሞ ኦርቢት ፣ ወርቢት የፕላኔት መዞሪያ ማለት ነው ። የቃሉ መሰረት ምስራቅ ነው ። መች ላቲን ውስጥ እንደ ገባ በውል አላውቅም ። ሮማ ካክሱም ጋር ሲነግድ (6/7ኛ ዘመን) ሊሆን ይችላል።

በ1510 ሙሉ የግ እዝ ዶክመንቶች ወደ ላቲን የሚተረጉም ዲክሽነሪ ተሰርቶ ነበር ። ኦርቢት፣ ወር፣ ቫወል ከዚያ ቀደም የተወሰዱ ይመስለኛል ።

ስለዚህ ዘበራ፣ ዝወራ፣ ወዘብር፣ ዘረባ እጅግ ትልቅና ትንታዊ ቃል ነው ። ወር (መንዝ) በሴምም በላቲንም አንድ ቃል ነው ። ወር ሌላ ትርጉሙ ጨረቃ ሙን ማለት ነው። ከ30 ቀን ዙረቱ ጋር ተያይዞ ። በአረብኛም አለ ። ወረብ፣ ዝወር፣ መዞ ቀዳሚው ቃል ይመስለኛ ። ወሬ አውርር፣ ተናገር፣ ዘብር፣ ተዛረብ፣ ዘበራ እንደ ሜታፎር የንግግር የቃላት መመላለስ ቀጥሎ የመጣ ዩዜጅ መሆን አለበት >

Abe Abraham
Senior Member
Posts: 14412
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Re: ግእዝ ቃላት

Post by Abe Abraham » 15 Aug 2023, 11:12

  • 1_በሰፊ በየመንና ዖማን በመጠኑ ደሞ በሳውዲ ኣረብያ የሚገኙ መህሪት ( ኣል-ሉቓ ኣል-ማህሪያ ) የሚባል የኣፍሮ-ኣስያዊ ቅድመ-ኣረብኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ኣሉ ። ባለፈው ሳምንት ስለ የመህሪ ሕብረተ-ሰብ በዩትዩብ የቀረበውን መደብ ስከታተል ( ሳኡዳዊ ኣቅራቢው በሁለ-እንትናቸው ኣረቦች ሆነው ሌላ ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎች በማግኘቱ ድንቅ እንደሆነው በፊቱ ይታይ ነበር ። ልክ እኔ በየኣንቲክ መጻሕፍት ድኳን ኣርጎባ-እንግሊዘኛ መዝገበ-ቃላት ለመጀመርያ ግዜ ሳነብ እንደ ተሰማኝ ማለት ነው። ) ሶስት የመህሪ ተወላጆች ትንሽ ስለ ባህላቸው ሲያወሩ የዘፈንና ረቕስ/ዳንስ ኣርእስት ኣንስተው ሲናገሩ ዳንሳቸው " ዘፈኒት " እንደሚባል ጠቅሰው ኣለፉ ። ዘፈኒት የዘፈን እህት ትሆን ?

    2_ በግብጽ ሸይኽ ኢብራሂም ኣቡ ኣል-ሑሰይን የሚባል ሱፊ በቲቪ (ዩትዩብ) ቀርቦ በተናገረው ሰዎች ትንሽ እንደ መለኮታዊ ተውህቦ ያለው ሰው ሆኖ ልዩ መንፈሳዊ እውቀት ኣለኝ እንደሚል ስለተሰማቸው፡ ኣንድ ጋዜጠኛ ነገሩን ለመመርመርና ለማጣራት በየሼኩ ቤት ሄዶ ከሱ ሲናገር ሼኹ የሃይማኖት ጥቅስ ጠቅሶ ለማብራራት " መደር ማለት ኣፈር ማለት ነው " ኣለ ።

    የኣረብኛ መዝገበ-ቃላቶች ስንገለባብጥ " ' ኣህል ኣል-መደር ' በደረቀ ጭቃ በየተሰሩ ቤቶች የሚኖሩ ሰዎች (የከተማ ስዎች) ሲሆኑ ኣህል ኣል-ወበር ደሞ የበረሃ ወይም የተንት ቤቶች ነዋሪዎች ናቸው ። " የሚል ትንታኔ እናገኛለን ። ከዚያም ባሻገር " ኣፈር " የሚለው የኣማርኛ ተራ ቃል (ክላሲካል/ጥንታዊ ተቆጥሮ) እንዳለ ከነትርጉሙ በየኣረብኛ የጥንት መዝገበ-ቃላቶች ሰፍሮ ይገኛል ።

    3_ በኣረብኛ " ኣስኩት " ስንል " ዝም በል/ሱቕ በል " ነው የሚያሰማው ። ከ "ስኩት"/silence/ ወደ የትግርኛ እህትዋ " ስቅታ" እንሄዳለን ። ከዚያም " ህዱእ " /ኣረብኛ ኣንስተን ከየትግርኛ " ህድኣት " እንተዋወቃለን ።

  • ሸይኽ ኢብራሂም ኣቡ ኣል-ሑሰይን ("በሚእታዊ/ፐርሰንት ሲታይ በሰው ልጅ ኣካል የሚገኝ ውሃና በምድር ውስጥና በላዩ ያለው ውሃ ከኣካሎቹ ሲነጣጠር 81% ይይዛል!" ብሎ የተናገረ ሸይኽ ። እውቀቱን ኬት ኣመጣሀው ሲባል "እንጃ ! ይታየኛል " ይላል ። )

-

Post Reply