Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abdisa
Member+
Posts: 5733
Joined: 25 Apr 2010, 19:14

✠ ✠ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የማን ናት? ✠ ✠

Post by Abdisa » 06 Feb 2023, 05:03



የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የማን ናት?

(አቻምየለህ ታምሩ)

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ከአምስቱ ጥንታዊ የኦርየንታል ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክሪስቲያናት ማለትም ከኮፕት (ግብጽ)፣ ህንድ፣ ሶርያና አርመን ቤተ ክርስቲያናት መካከል አንዷ ናት። ኢትዮጵያ በመጽሐፍ ቅዱስ ከ፵ ጊዜ በላይ የተነሳች ሲሆን ከክርስትና በፊት የብሉይ ኪዳንን እምነትና ባህል ተቀብላ እግዚአብሔርን ታመልክ እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል። ይቺ ቤተ ክርስቲያን ቀለም በጥብጣ፣ ብራና ፍቃ፣ ብዕር ቀርፃ፣ጉባኤ ዘርግታና ትምህርት አስፋፍታ ልጆቿን እያስተማረች፣ እውቀታቸውን እያተደላደለች፣ ለሕዝብና ለአገር የሚጠቅም በርካታ ስራ ሰርታለች። በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ረገድም ልጆቿን በዘርና በቋንቋ ሳትለይ፤ በመወለድና በቋንቋ ሳትመዝን ልጆቿን በብቃትና በችሎታ፤ በመክሊታቸውና እንደየ ጥበባብቸው መጠን እየመደበት ከተራ የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ እስከ ሊቀ ጳጳስ ስትሾም ኖሯለች።

በዘመነ ወያኔ ግን ታፍራና ተከብራ የኖረችው ዘረኝነትን የምትጠየፈው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቤተክህነት ቤተክህደት ሆኖ ከፓትሪያርክ ጀምሮ እስከ ደብር አለቆች ድረስ ያለው መንፈሳዊ ሹመት በትግራይ ተወላጆች ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ ተደርጓል። ወያኔ አንድ የቀረው ነገር ቢኖር የቤተክርስቲያኒቷን ሃይማኖታዊ ቀኖና መቀየር ብቻ ነው። ወያኔ በሥልጣን ላይ ከቆየ ይህንንም ከማድረግ የማይመለስ መሆኑን በእስልምና እምነት ላይ ተግባራዊ እያደረገ ካለው መገንዘብ ይቻላል።

ልክ እንደ ክርስትናው ሁሉ ወያኔ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትን (መጅሊስ) በራሱ ካድሬዎች ሞልቶት ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮታል። እስልምና ላይ ግን የሃይማኖት ተቋማትን ከመቆጣጠር አልፎ በቀኖና ጉዳይ በመግባት የራሱን “ምርጥ እስልምና” እያስተዋወቀ ነው። ይህ ነገር ዛሬ በሙስሊሞች ላይ የመጣው ነገ በክርስቲያኖችም ላይ የሚመጣውን አመላካች ነው።

ብዙ ሰው ኢሕአዴግ በሚባለው የማታለያ ጭምብል ውስጥ ስላለው የወያኔ የበላይነት እያወራ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስላለው የሲኖዶስ መከፈል እንጂ ስላለው የትግራይ የበላይነት የዘነጋነው ይመስላል። እንደሚታወቀው «አቡነ» ማቲያስ የሚባሉት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ በዜግነት አሜሪካዊ ናቸው። ለወትሮው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ከርስቲያን ፓትሪያርኮች ከግብጽ አሌክሳንደሪያ ይሾሙ ነበር። በዚህ ዘመን ግን የኢትዮጵያ ገዳማትና አድባራት ብቁ ጳጳሳትን ማፍራት ያቆመች ይመስል የወያኔዋ ኢትዮጵያ ጳጳስ ከአሜሪካ አስመጥታ ፓትሪያርክ አድርጋለች።

አቡነ ማቲያስ ሱዳን በነበሩበት ወቅት የመንገሻ ስዩም ቃል አቀባይና የኢዲዩ የፕሮፓጋንዳ ጋዜጠኛ ነበሩ። አሜሪካ ገብተው ማተባቸውን ቆርጠው አሜሪካዊነትን ከተቀበሉ በኋላ በሀገረ ኢየሩሳሌም የታሪካዊቷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን «ሊቀ ጳጳስ» ሆነው ተሹመው «አጎታቸውን» ፓትሪያርክ ጳውሎስን እስከተኩበት ጊዜ ድረስ በነበራቸው የኢየሩሳሌም ቆይታቸው ሙስናን ተቋማዊ አድርገውት ነበር። አንዳንድ ሰዎች «በብዝሀነት» ሲመዘን «እየሩሳሌም ካለው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር መቀሌ ያለው የአቡነ አረጋዊ ደብር ይሻላል፤ ቢያንስ የተወሰኑ የኢሮብ ሰዎች አሉበት» ሲሉ ጽፈው ነበር።

የማቲያስ ጉድ ተነግሮ የሚያልቅ አይደለም። ወያኔ ሻዕብያን ተከትሎ አዲስ አበባን በተቆጣጠረ ማግስት ሎስ አንጀለስ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ለሁለት ከፍለው የትግራይና የኢትዮጵያ በሚባሉ ሁለት ቤተ ክርስቲያኖች እንዲፈጠሩ ያደረጉ የዛሬው የወያኔ ፓትሪያርክ «አቡነ» ማቲያስ ናቸው።




ማቲያስ በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ መንግሥት ነኝ ባዩ ነውረኛ ቡድን ወያኔ ያዘጋጀውን የወያኔ ምስረታ ድግስ ለመታደም የአመቱን የቁልቢ ገብርኤል የንግሥ በዓል ሳያከብሩ የቀሩ ብቸኛ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን «ፓትሪያርክ» ናቸው። የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸው የሆኑት ተራ ምዕመናን ከሩቅ ቦታ ሳይቀር በመጓዝ የአመቱን ገብሬል ለማክበር ወደ ቁልቢ ሲተሙ እሳቸው ግን «ብርሀን ከጨለማ ጋር ህብረት የለውምና ተለይ» የሚለውን «አባታዊ» ቡራኬ እና ቃለ ምዕዳን ተገኝተው ለምዕመኑ ይሰጣሉ ተብሎ ሲጠበቅ «አመንዝረው» በገብርዔል ፈንታ ከአቦይ ስር ሸራተን ዋሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ ክርስትና ለመጀመሪያ ጊዜ የከበረው በተራ ምዕመን ደረጃ ብቻ ሳይሆን በአለማዊው መንግሥት በንግሥተ ነገሥታት ሕንደኬ አቃቤ ንዋይ ጭምር ነበር። በመንፈሳዊነት በከሰረችዋ በወያኔዋ ኢትዮጵያ ግን ክርስትና መርከስ የጀመረው ከላይ የቤተ ክርስቲያኗ ራስ ነን በሚሉ ሰዎች ሆነ!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን በመንፈሳዊነት ያከሰሯት ሙሰኛ «አቡን»፤ የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን ቤተ ትግሬ አድርገዋታል። ይህንን በሚመለከት «ብጹእ» እየተባሉ በሀይማኖት ካባ የሰሩትንና እየሰሩ ያሉትን ወንጀል፣ ሙስናና ዘረኝነት፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ቤተ ክርስቲያን በማን ቁጥጥር ስር እንደዋለችና እየተካሄደ ያለውን ከፍተኛ የገንዘብ ብክነትና የዘረፋ ድርጊት በተጨባጭ ማስረጃዎች ለማቅረብ እንሞክራለን።

በቅድሚያ የምናቀርበው ማስረጃ ባለፈው ሰሞን የአዲስ አበባን ሀገረ ስብከትን በጠራራ ጸሀይ ዘርፈው እንዲነሱ የተወሰነባቸውን ሶስት የትግራይ ሌቦች በነማን እንደተኳቸው የሚያሳይ ዶሴ ነው። «አቡነ» ማቲያስ በተለይ ጠርቀም ያለ አስራት በኩራት የሚሰበሰብበትን የአዲስ አበባን ሀገረ ስብከት የበላውና የጠገበው ዘመዳቸው ሄዶ የራበውና ሁሉ ብርቁ የሆነ ዘመዳቸው የሚተካበት የትግራይ ርስት አድርገውታል። ብጹዕነታቸው እየተባሉ የሚጠሩት ግን ተግባራቸው በተቃራኒው የሆነው ወያኔ በፓትሪያርክነት የሾማቸው የተከዘ ማዶ ሰው የቀድሞዎቹን የበሉና የጠገቡ ሶስት «ሀጎሶችን» ወደሌላ ቦታ አዛውረው በነሱ ቦታ የተኳቸው አዲሶቹ የአዲስ አበባን ሀገረ ስብከት ገዳማትና አድባራት ሹመኞች የሆኑት ሶስቱ የራባቸውና ሁሉ ብርቁ «ሀጎሶች» ....
1ኛ፡ መምህር ጎይቶች ያይሄ፤ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ፤
2ኛ፡ መጋቢ ጥበብ ናሁ ሰናይ በለጠ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ ኃላፊና
3ኛ አቶ ገብረ ሕይዎት አስገዶም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሒሳብና በጀት ዋና ክልፍ ኃላፊ ናቸው።
ልብ በሉ! ይህ በትግራይ ተወላጆች ብቻ የተሞላው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት መምሪያ ሀገረ ስብከቱ ባሉት የኃላፊነት የስራ መደቦች ሙሉ ነው።
እንቀጥል።

በአዲስ አበባ ውስጥ ያሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አብያተ ክርስትያናትና አድባራት በሶስት ደረጃዎች ይከፈላሉ። አንደኛ ደረጃ የሚባሉት አብያተ ክርስትያናት እጅግ ብዙ ገቢ የሚያስገኙና ገቢ ሊያስገኙ የሚችሉ ሱቆች፣ ትምህርት ቤት፣ የመቃብር ቦታ ወዘተ ያለባቸው አብያተ ክርስትያናት ናቸው። እነዚህም አብያተ ክርስትያናትና አድባራት ብዛታቸው ሀያ ነው። አራዳ ጊዮርጊስ፣ ቦሌ መድኃኔዓለም፣ ኡራኤል፣ ልደታ ለማርያም፣ ቅድስት ሥላሴ፣ አማኑኤል፣ አዲሱ ሚካኤል፣ እንጦጦ ኪዳነ ምህረት፣ ቅድስት ማርያም፣ ወዘተ አንደኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ አብያተ ክርስትያናት ናቸው። በወያኔ ቤተ ክህነት ቋንቋ አንድ ሰው «ተሾመ» የሚባለው በነዚህ አድባራት ውስጥ ሲሾም ነው።

እነዚህ አንደኛ ደረጃ በመባል የወያኔ ቤተ ክህነት የመደባቸው አድባራት ውስጥ ጸሐፊና አስተዳዳሪው ሆነው በአባ ማቲያስ የሚሾሙት ከዘጠና አምስት በመቶ በላይ የትግራይ ሰዎች ናቸው። እነዚህ አንደኛ ደረጃ በመባል በሚታወቁት አብያተ ክርስትያናት በአባ ማቲያስ የሚሾሙት የትግራይ ሰዎች ሁሉም የድርጅት አባላት ናቸው። ይህ ማለት እነዚህ ሰዎች ሲሾሙ የአገዛዙ ይሁንታ አለበት ማለት ነው። እነዚህ በትግሬነታቸው ተደራጅተው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን የወረሷት የትግራይ ሰዎች የቤተ ክርስቲያን ዘረፋ እጅግ የሚዘገንን ነው። እነዚህ ሰዎች ቤተ ክርስቲያኗን የሚዘርፏት በሚሊዮን በሚቆጠር ገንዘብ ነው። ዘራፊዎቹ የትግራይ ሹመኞች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን መብደር በወያኔ ፈቃድ የተቀመጡ ስለሆኑ ስለዝርፊያቸው አይከሰሱም። ቢከሰሱም ቅጣቱ በትንሹ ይዘርፉበት ከነበረው የበለጠ ወደሚዘረፍበት ቦታ መዘዋወር ነው።

የወያኔ የቤተክርስቲያን አስተዳደር ሁለተኛ ደረጃ አድባራት ብሎ የሰየማቸው መለስተኛ ገቢ የሚገኝባቸውን ቤተ ክርስቲያንን ሲሆን እነዚህም ቦታ አስተዳዳሪና ጸሓፊ የሚመደቡት ከዘጠና በመቶ በላይ ከትግራይ ሰዎች ናቸው። ቅዱስ ማርቆስ፣ ቁስቄም፣ ገነተ ኢየሱስ፣ ቂርቆስ፣ ወዘተ በዚህ ደረጃ ከሚካተቱት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አብያተ ክርስትያናትና አድባራት መካከል ናቸው።

በሶስተኛ ደረጃነት የተቀመጡት ደግሞ የአዲስ አበባ አድባራት ከተማው ራቅ ያሉና ራሳቸውን ለመቻል የሚቸገሩ አዳዲስና ነባር አብያተ ክርስትያናት ናቸው። በእነዚህ አድባራት ውስጥ ዋና ስራ አስኪያጅ ሆነው የሚሾሙት በአብዛኛው የሌሎች ብሔረሰብ አባላት ናቸው። ሆኖም ግን የነዚህ አድራባራትም ቢሆን የጸሀፊውና የሀገረ ስብከቱ ስራ አስኪያጅ ኃላፊ ቦታ በትግራይ ሰዎች የተያዘ ነው።

ወረድ ብለን የምናቀርበው የዝርፊያ ዶሴ በማህበረ ለስብሐት ልደታ ማሪያም ቤተ ክርስቲያን አባ ማቲያስ የሾሟቸው ሁሉም የትግራይ ሰዎች የሆኑ ዘራፊዎች ቤተ ክርስቲያኗን የገፈፏትን በርካታ ሚሊዮን ብር የሚያሳይና በአባ ማቲያስ ቁጥጥር ስር ያለው ቤተ ክርስቲያን አምኖ ካሳተመው ዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ ላይ የተገኘ የውስጥ ማስረጃ ነው።

ከታች ስማቸው የተጠቀሰው ስድስቱ የአባ ማቲያስ ሌቦች ከአንድ ቤተ ክርስቲያን ብቻ በአንድ ወቅት በርካታ ሚሊዮን ብሮችን ዘርፈዋል። ከዚህ ተነስተን «በአቡነ» ማቲያስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከአንድ ቤተ ክርስቲያን ይህንን ያህል ሚሊዮን ብር የሚሆን የቤተክርስቲያን ሀብት ከዘረፋ በአጠቃላይ ቤተክርስቲያኗን እንዴት ግጠው ጨርሰው በአጽሟ እንዳቆሟት መገመት አይከብድም።

የሆነው ሆኖ በትግሬነታቸው ተቧድነው ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ራቁቷን ያስቀሯት የአባ ማቲያስ ሹሞች የሆኑት የትግራይ ሌቦች ከአንድ ቤተ ክርስቲያን ዘረፉት ተብሎ ክስ የቀረበባቸው ሰዎች ስምና ዝርዝር እነሆ፤

1. ወ/ሮ አብረኸት ተክሉ የደብሩ ገንዘብ ያዥ፤ 1, 897,365.03 ብር ያጎደሉ እና 2 ዓመት ብቻ የተፈረደባቸው፤

2. ዲ/ተስፋዬ በቀለ 4.6 ሚሊዮን የሙዳዩ መምፅዋት ብር ያጎደሉና 1 ዓመት ከ8 ወር ብቻ የተፈረደባቸው፤

3. መ/ሠርዓተ ኃ/ጊዮርጊስ ዕዝራ የቀድሞ ፀሀፊ 1, 393, 7747.70 ብር ያጎደሉና 5000 ብር ብቻ የተቀጡ፤

4. አቶ ዩሐንስ በርሄ የቀድሞ ተቆጣጣሪ 1.2 ሚሊየን ብር ይዘዉ የተሰወሩና 5000 ብር እንዲቀጡ የተላለፈባቸው፤

5. ሊቀ ስዩም ኃ/ማርያም አብርሃ በተ.ቁ 3 ላይ ከነበሩት ፀሀፊ በፊት የነበሩ 2.9 ሚሊየን ብር ያጎደሉና 5000 ብር ብቻ እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ የወሰነላቸዉ ሹሙኞች ናቸው ።

አሁንም ልብ በሉ! ይህ ሁሉ ዘረፋ የተካሄደው ያንድ ብሔረሰብ አባላት ማለትም የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ሹመኞች በአንድ ቤተ ክርስቲያን ያካሄዱት ገፈፋ ነው። ይህን የዘረፋ ጉድና ሌሎች የትግራይ ተወላጅ ሹመኞች ምዝበራዎች ዜና ቤተ ክርስቲያን በሚባለው የቤተ ክርርስቲያኗ የውስጥ ጋዜጣ 62ኛ ዓመት ቁጥር 70 ላይ ያገኙታል።

ሙሰኛው «ፓትሪያርክ» «አቡነ» ማቲያስ ታሪካዊቷን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በትግራይ ተወላጆች ብቻ ሞልተው የቤተክርስቲኗን አንጡራ እየገፈፏት ያለው የየሀገረ ስብከቱን ሹመት የሚቆጣጠረውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትሪያርክ ጠቅላይ ጽህፈት ቤት በትግራይ ተወላጆች ሞልተው ነው። ወረድ ብለን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትሪያርክ ጠቅላይ ጽህፈት ቤት አስተዳደር በነማን እንደተያዘ ካገኘነው ሚስጥራዊ ሰነድ ተነስተን እንዘረዝራለን። ደግማችሁ ልብ በሉ! የቤተ ክርስቲያኗ መንበረ ፓትሪያርክ ጠቅላይ ጽህፈት ቤት አስተዳደር ማለት አጠቃላይ የቤተ ክርስቲያኗን የአገር ውስጥና የውጭ አገር አስተዳደር የሚቆጣጥር ነው። ባጭሩ የቤተ ክርስቲያኗ መንበረ ፓትሪያርክ ጠቅላይ ጽህፈት ቤት አስተዳደር ቤተ ክርስቲያኗ የማን እንደሆነች የሚያሳይ ንድፍ ነው።

በዚህ መሰረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትሪያርክ ጠቅላይ ጽህፈት ቤት አስተዳደር 20 አባላት ያሉት ሲሆን የአባላቱ ስምና ማንነት እደሚከተለው ይቀርባል፤

1. «መጋቤ ካህናት» ኃይለ ሥላሴ ዘማርያም — ትግሬ — በመንበረ ፓትሪያርክ ጠቅላይ ጽህፈት ቤት የካህናት አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ፤

መጋቤ ካህናት ኃይለ ሥላሴ ዘማርያም ታጋይ የነበረ ሰው ነው። ሰውየው በቅጽል ስሙ የቤተ ክህነቱ ስብሃት ነጋ በመባል ይታወቃል። መጋቤ ካህናት ኃይለ ሥላሴ ዘማርያም ወያኔ ትግራይን ሲቆጣጠር የትግራይ ቤተ ክህነት ሥራ ስኪያጅ የነበረው ሊቀ ካህናት ኃይለሥላሴ ትግራይን ለቀው ሲወጡ ወያኔ የትግራይ ቤተ ክህነት ሥራ ስኪያጅ አድርጎ የሾመው ሰው ነው። ወያኔ አዲስ አበባ ሲገባ ደግሞ አብሮ አዲስ አበባ በመግባት አዲስ አበባ ተሹሟል። ከዚያም ደግሞ ድሬዳዋ የተሾመ ሲሆን የተወረሱ የቤተ ክህነት ቤቶችን በማስመለስ ሰበብ በብዙ ቤችች ሙስና የሚታወቅ ዘራፊ ነው። ይህ ሰው አሁን የቤተክነቱ የካህናት አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ ነው።

2. እስክንድር ገብረ ክርስቶስ — ትግሬ — በመንበረ ፓትሪያርክ ጠቅላይ ጽህፈት ቤት የእቅድና ልማት መምሪያ ዋና ኃላፊ፤

እስክንድር ገብረ ክርስቶስ የሕወሓት ተመራጭ የነበረ ዋና ፖለቲከኛ ሲሆን አሁን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትሪያርክ ጠቅላይ ጽህፈት ቤት አስተዳደር ዕቅድና ልማት መምሪያ ኃላፊ ነው።

3. አባ ሰረቀ ወልደሳሙኤል — ትግሬ — በመንበረ ፓትሪያርክ ጠቅላይ ጽህፈት ቤት የትምህርትና ማሰልጠኛ መምሪያ ኃላፊ፤

አባ ሰረቀ ወልደሳሙኤል አቡነ መርቆሪዎስን በማውረድ ሂደት ትልቅ ሚና የነበረው ሲሆን ወያኔ አዲስ አበባ ሳይገባ ከወያኔ ጋር መሳርያ ይዞ ይታገል የነበረ ታጋይ ሲሆን በኋላ ግን ቤተ ክህነት ውስጥ ገብቶ ትልቁን የፖለቲከኛነት ሚና የሚጫወት ሰው ነው። አባ ሰረቀ ወልደሳሙኤል የሚንቀሳቀሰው በዲፕሎማቲክ ፓስፖርት ነው።

4. «መ/ጥ ቀሲስ» ዮሃንስ ኤልያስ — ትግሬ — በመንበረ ፓትሪያርክ ጠቅላይ ጽህፈት ቤት የአስተዳደር መምሪያ ኃላፊ፤ መ/ጥ ቀሲስ ዮሃንስ ኤልያስ ትግሬ በመሆኑ ከመዝገብ ቤት ወደ አስተዳደር መምሪያ የተሾመ ሰው ነው።

5. «መ/ር» እንቁ ባይርይ መለስ — ትግሬ — በመንበረ ፓትሪያርክ ጠቅላይ ጽህፈት ቤት የሰንበት ት/ ቤት ማ/ መ/ ኃላፊ፤

6. «መጋቢ ሐዲስ» ሐዋዘ ብርሃን ጫኔ — ትግሬ — በመንበረ ፓትሪያርክ ጠቅላይ ጽህፈት ቤት የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ ኃላፊ፤

7. «መጋቢ ሥርዐት» ዳንኤል ወልደገሪማ —- ትግሬ — በመንበረ ፓትሪያርክ ጠቅላይ ጽህፈት ቤት በመምሪያ ኃላፊ ደረጃ የልማት ድርጅት ስራ አስኪያጅ፤

8. አቶ ተስፋጊዮርጊስ ኃይሉ— ትግሬ — በመንበረ ፓትሪያርክ ጠቅላይ ጽህፈት ቤት የቁልቢ ማደራጃ መምሪያ ኃላፊ፤

9. «ንቡረ እድ» አባ ገብረ ማርያም — ትግሬ — በመንበረ ፓትሪያርክ ጠቅላይ ጽህፈት ቤት የገዳማት አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ፤

10. «ርዕሰ ደብር» መሀሪ ኃይሉ — ትግሬ — በመንበረ ፓትሪያርክ ጠቅላይ ጽህፈት ቤት የትንሣኤ ማተሚያ ቤት ኃላፊ፤

11. «ሊቀ ማምእራን» መኩርያ ደሳለኝ — ትግሬ — በመንበረ ፓትሪያርክ ጠቅላይ ጽህፈት ቤት የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያ ተልእኮ መምሪያ ኃላፊ፤

12. «መምህር» ሳሙኤል እሸቱ — ትግሬ — በመንበረ ፓትሪያርክ ጠቅላይ ጽህፈት ቤት የትምህርት ዘርፍ ዋና ሥራ አስኪያጅ፤

13. «መጋቤ ሥርዐት» ብርሃኑ ካሳ — ትግሬ — በመንበረ ፓትሪያርክ ጠቅላይ ጽህፈት ቤት የአልባሳት ማደራጃ መምሪያ ኃላፊ፤

14. «መምህር» ኤርምያስ ተድላ — ትግሬ — በመንበረ ፓትሪያርክ ጠቅላይ ጽህፈት ቤት የቁጥጥር አገልግሎት መምሪያ ኃላፊ፤

15. «መልአከ ጽዮን» አባ ኅሩይ ወንድይፍራው — ትግሬ — በመንበረ ፓትሪያርክ ጠቅላይ ጽህፈት የካህናት አስተዳደር ዋና ክፍል ሓላፊ፤

16. መልአከ ሰላም ‘አባ’ ቃለ ጽድቅ ሙሉጌታ— ትግሬ — በመንበረ ፓትሪያርክ ጠቅላይ ጽህፈት ቤት የውጭ ግንኙነት መምሪያ ዋና ኃላፊ፤

17. ሊቀ ትጉሃን ሽመልስ ቸርነት — ኦሮሞ በመምሪያ ኃላፊ ደረጃ የበጀትና የሂሳብ ዋና ክፍል ሹም፤

18. አባ ኃይለ ማርያም መለስ — አማራ — ኃላፊነታቸው በውል ያልታወቀ፤

19. ሰሎሞን ቶልቻ — ኦሮሞ — በመንበረ ፓትርያሪክ ጠቅላይ ጽህፈት ቤት የቅርስ ጥበቃ፣ የቤተ መጻሕፍትና ወመዘክር መምሪያ ኃላፊ፤

20. ሊቀ አእላፍ ያዝዓለም ገሠሠ — አማራ — የሊቃውንት ጉባኤ መምሪያ ኃላፊ፤

እንግዲህ! የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትሪያርክ ጠቅላይ ጽህፈት ቤት አስተዳደር ይህንን ይመስላል። ጠቅላይ ጽህፈት ቤቱ ካሉት 20 አባላት መካከል 16ቱ ትግሬዎች ናቸው። ሁለት፤ ሁለት አባላት ብቻ በመንበረ ፓትሪያርክ ጠቅላይ ጽህፈት ቤቱ አስተዳደር እንዲወከሉ የተደረጉት በሕዝብ ቁጥር ቀዳሚ የሆኑት የአማራና የኦሮሞ ነገዶች በስም ደረጃ የተካተቱትም ሁለት፡ ሁለት ሰዎች አስተዳደር የሚጠይቀውን ውሳኔ በማይሹ ቦታዎች እንዲወተፉ ሆነዋል።

እንግዲህ! የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለኦርቶዶክ ሃይማኖታቸውና ለሀገራቸው ሙት የሆኑ ጀግና መነኮሳትንና ቀሳዎስትን አፍርታ በካህናቱና በምእመናኑ ህብረትና ጥንካሬ ታፍራና ተከብራ ህልውናዋን አስከብራ የኖረች ነበረች። ዛሬ ግን ከፍ ሲል እንደቀረበው በፋሽስት ወያኔ የዘረኝነት ፖሊሲ ምክንያት የመንፈሳዊነት ደረጃቸው ወደር የማይገኝላቸው አባቶች ተገፍተው እየተባረሩ በምትካቸው የሃይማኖት ካባ ያጠለቁ የትግራይ ዘረኛ ወንበዴዎች በቤተ ክርስቲያኗ ላይ በመንገሥ ቤተ ክርስቲያኗ የአማራን ዘር ለማጥፋት ኦሮሞን ቅስሙን ሰብሮ በማንበርከክ የሚደረገውን ፋሺሽታዊ የወታደራዊ ዘመቻ ደጋፊ ሆና እንድትቆም እያደረጓትት ይገኛሉ።

ዛሬ አቡነ ማትያስ ፓትሪያርክ ሳይሆኑ ፋሽሽቱ ሞሶሎኒንና ሰራዊቱን ባርከው በኢትዮጵያ ላይ እንዳዘመቱት እንደ ወቅቱ የሮማው ፓትሪያርክ ፒዮስ 12ኛ ዘር ሊያጠፋ የተሰማራውን የትግራይ አጋዚ ጦር ባርከው የሚያዘምቱ ፋሺስታዊ ፓትሪያርክ ናቸው። እስከ አሁን የተታለልነው ይብቃ! ዛሬ የፋሽስት ወያኔ ፋሺስታዊ ሥርዓት የዐማራን ዘር በማጥፋት ዘመቻ ላይ ተሰማርቶ የአማራ ወንዶችን፣ ሴቶችን፣ አባቶችንና እናቶቻን ደም እያፈሰሰ የሚገኘው ለሀገርም ሆነ ለቤተ ክርስትያንና ለሕዝብ መቆርቆርን ፖለቲካ አድርጎ እያሸማቀቀ የትግራይ የአፓርታይድ አገዛዝ ሃይማኖታዊ ቅርንጫፍ የሆነውን የአባ ማቲያስ ቤተ ክህደት ግን እንደ ቤተ ክህነት ቀብለን የሚደረግብንን ሁሉ ችላ በማለታችን በቁማችን እንደሞትን ስላስቆጠርን ነው።

እንግዲህ «የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የማን ናት?» ለሚለው ጥያቄ መልሱ ከላይ በተዘረዘሩት በቂ ማስረጃዎች እንደቀረበው የዘረኛ፣ ዘራፊና የሕወሓትን ኃይማኖታዊ ክንፍ የሚዘውሩት የትግራይ ሽፍቶች መፈንጫ ዋሻ ሆናለች የሚል ነው።

በነ አባ ማቲያስና ተከታይ ዘረኛ ፋሺስቶቶች ተቀይዶ ተይዞ የፋሽስት ወያኔ የዘር ማጥፋት ዓላማ ማራመጃ መሣሪያ የሆነውን በኦርቶዶክስ ሃይማኖት ስም የሚነግድ የሕወሓት የቤተ ክርስቲያን ክንፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ተከታይ የሆነ ሁሉ ሃይማኖቱንና ቤተ ክርስቲያኑን ፋሽሽት ሞሶሎኒንና ሰራዊቱን ባርከው በኢትዮጵያ ላይ ያዘመቱትን የሮማው ፓትሪያርክ ፒዮስ 12ኛ የመስፈን ወራሽ ከሆኑት የአቡነ ማቲያስ የማታለያ ጭንብል ነጻ ሊያወጣ ይገባል። የሞራልና የመንፈሳዊነት ደረጃቸው ወደር የማይገኝላቸው አባቶች ለእስር፣ ለግርፋትና ለግድያ ተዳርገው የሃይማኖት ካባ የለበሱ ዘራፊ የትግራይ ሽፍቶች በቤተ ክርስቲያኗ ነገሰው ቤተ ክርስቲያኗን የሽፍቶች መዲና ያደረጉበት ከግራኝ ዘመን የከፋው አሳዛኝ የውርደት ዘመን ማብቃት ይኖርበታል።

ሰላም!