Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Wedi
Member+
Posts: 7959
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

የቢሮ ኃላፊ ረ/ፕሮፌሰር ነቢዩ ባዬ:- "ከቤተክርስቲያን ጎን ነኝ ብዬ ኃላፊነቴን አላቀልም። ቤተክርስቲያን ከሌለች የለሁም ነው የምለው።"

Post by Wedi » 04 Feb 2023, 11:22

♦ "ከቤተክርስቲያን ጎን ነኝ ብዬ ኃላፊነቴን አላቀልም። ቤተክርስቲያን ከሌለች የለሁም ነው የምለው።"
የም/ጠ/ሚ/ሩ ቢሮ ኃላፊ ረ/ፕሮፌሰር ነቢዩ ባዬ ይናገራሉ:-

"እኔ ነብዩ ባዬ በክርስትና ስሜ ወልደአማኑኤል የተባልኩ የእግዜር ደካማ የእህተማርያም፣ የአካለስላሴ እና የወለተ ገብርኤል የስጋ አባት እስከዛሬዋ ቀን መንጋት ድረስ የተደረገልኝ ሁሉ የእግዚአብሔር ቸርነት እንደሆነ አምናለሁ። የሰው ክርስትና አባት ሳይኖረኝ የተሰጠኋት ቤተክርስቲያን ዛሬ ለደረስኩበት ያበቃኝን የጥበብ ፊደል አስቆጥራኛለች።

በቤቷ በሰንበት ትምህርት ቤት የጀመርኩት ጥበብ አሳድጎኝ፣ እሱኑ የሞያ መንገድ አድርጌ ነው ከዛሬ የደረስኩት። አንደበቴን የፈታሁ በርሷ ነው። ያለርሷ ዲዳ ነኝ። የቀኔ መጀመሪያም መጨረሻም እርሷ ያሳወቀችኝ ፈጣሪ ነው። የስነምግባርን ሀሁ አስነበብባ፣ አስፁማ፣ አሰግዳ በነቢብም በገቢርም አስተምራ አሳድጋኛለች። በዋልኩበት መልካም አድርጌ ቢሆን ዋጋው የወላጆቼ እና ያሳደገችኝ ቤተክርስቲያን ነው። አጥፍቼ ቢሆን ዕዳ በደሉ የእኔ ነው። ከቤተክርስቲያን የጎደለ የለም። ቤተክርስቲያን የሃዘኔ መጠጊያ ሆና ከወጀብ ከልላ አስጠግታ አሳልፋኛለች...ምስካየ ኅዙናን ናትና። በደስታዬ ስዕለቴን ተቀብላኛለች። በዚህች ፈታኝ አለም ላይ የቤቷን ዕጣን እና የልጆቼን የአንገት ሽታ ያህል መዓዛ አላገኘሁም። የማኅሌቷን ፀናፅል እና ከበሮ ያህል አልሰማሁም። በዚህ ሸርታታ አለም የመቋሚያዋን ያህል መደገፊያ አላገኘሁም። በዚህ አደንቋሪ አለም የአባቶቼን ያህል አረጋጊ ድምፅ አላገኘሁም። እንደአባቶቼ ባለግርማ፣ እንደአባቴቼ ባለፀጋ አላየሁም። እንደደጀሰላሟ የሚጣፍጠኝ መብልዕ አላገኘሁም። በጠጣሁት ቁጥር የሚጠማኝ እንጂ ጥቂት ቀምሼ እንደፀበሏ የሚያረካኝ አላገኘሁም። እንደግድግዳዋ ቀለም ኅብረት ያለው ጥበብ አይኖቼ አልገጠማቸውም።

የቤተክርስቲያን ስዕል በልቦናዬ ሙሉ ነው። ጠብ በበዛባት ጊዜ ፈርሳ አይቻት አላውቅም። ተቃጠለች ባሉኝ ጊዜ ለምልማ ነው የምትታየኝ። ተካፈለች ሲሉኝ ወርቅ ሲያበራባት ነው የሚታየኝ። ቤተክርስቲያን አምሳለ ገነት ናት። ገነት አንዲት ናት። ቤተክርስቲያንም አንዲት ናት። "ሰላም ለኪ ቅድስት ቤተክርስቲያን አምሳለ ገነት ሰማያዊት" እያልኩ እየተሳለምኳት እንዴት ልጠራጠር። ከቤተክርስቲያን ጎን ነኝ ብዬ ኃላፊነቴን አላቀልም። ቤተክርስቲያን ከሌለች የለሁም ነው የምለው።"

Please wait, video is loading...