Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abaymado
Member
Posts: 4191
Joined: 27 Sep 2017, 21:56

Appreciation post for EthioTelecom- even though 994 is not working....

Post by Abaymado » 04 Feb 2023, 06:19

ethio telecomን አመስግኘዋለሁ ሰድቤዋለሁም:: ጥሩ ሲሰራም አመሰግናለሁ:: ከዚህ ቀደም 994 አይሰራም በሚል ወርጀባቸዋለሁ:: እርግጥ አሁንም 994 አይሰራም:: ግን ሌላ መፍትሄ የተገኘለት ይመስላል:: አሁን ፈጣን የሆነ መልስ እየሰጡ ነው:: ከዚህ በፊት 994 ሞክሬ አምቢ ቢለኝ ወደ ቴሌ ቢሮ ኃላፊዎች ጋር ሄጄ ዱላ ቀረሽ ንትርክ ነበር የቀረው:: እሱ 994 ደውል ይለኛል ::: እኔ አይሰራም::8894 ምክር ይለኛል:: እሱም አይሰራም እለዋለሁ:: ከዛ የሞከርኩትን አሳየሁት:: እሱም በስልኩ ሞከረ:: አይሰራም:: ከዛም ወደየቅርንጫፉ እየደወለ : "ምንድነው የምትሰሩት : ሥራ እየሰራችሁ አይደለም :: ደንበኛ እየተጉላላ ነው አለው::"

ከዛ ሰውየው ይህ ችግር የተፈጠረው 994ን ወደ automation ለመቀየር ታስቦ ነው አለኝ::ethiotelecom ፌስ ቡክም ላይ መጠየቅ ትችላለህ ሲለኝ:: ተሰላችቼ እንዴት አልኩት?

ሰውየውም ሞክሮ ምንም ለውጥ ስላልነበር በነጋታው እስኪ ለማንኛውም ፌስ ቡክ ገፃቸውን ልሞክር ብዬ በሜሴጅ ላኩት :: በሚገርም ፍጥነት የሆነ መልስ አገኘሁ :: ጥያቀህ ተመዝግቧል አለኝ:: የምፈልገው ያንን ነበር:: እንደውም ከዛ አልፎ live agent ስላለ ጥያቄህን አቅርብ አለኝ:: በጣም ተገርምኩ ::ምክንያቱ ደሞ የውጭ አገር ዌብሳይት ያላቸው ድርጅቶች ላይ ያገኘሁት live agent የሚሰጡት አገልግሎት አሪፍ ስለነበር እንደዛ የሚሆን መስሎኝ ነበር:: ግን ሰርቪስ ቁጥርህን አስገባ ብሎ ሳስገባ "ስህተት ቁጥር ነው ያስገባህው " ይላል:: በቃ እዛ ላይ መዳረቅ ነው:: የውጭው live agent ሰዎቹ ራሳቸው ቀርበው በደንብ ያለውን ችግር ለመፍታት ይሞክራሉ: እዚህ ግን ሰው መኖሩን እጠራጠራለሁ::

ሌላው መጥፎነቱ ethiotelecom የ automation አገልግሎት መስጠት የፈለገው ፌስ ቡክ ገፁ ላይ ከሆነ: ቀልድ ነው የሚሆነው:: በራሳቸው ዌብሳይት ሊሰሩት ይገባል::

የሆኖ ሆኖ አሁን 8894 በ message እየሰራ ነው:: ጥሩ ነው ቀጥሉበት::