Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
TGAA
Member+
Posts: 5598
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

አብይ በቀውሱ ሰአት የአሜሪካንን ድጋፍ ለማግኝት ከመለሰ መጽሀፍ ጎትቶ ያወጣት ገጽ ፤ አልሸባብ ላይ ጦርነት አውጅ አሜሪካ ትከላከልሀለች ፡፡

Post by TGAA » 03 Feb 2023, 20:59

ሰሞኑን አብይ ሀገር ውስጥ ያለው ቀውስ ሊወጠው ሲቀርብ አልሸባብን እዋጋለሁ ብሎ ሶማሊይ ሄዷል ፤ ከጥቂት ቀናንት በኋላ ፓርላመንት መጥቶ ሶማሌ ወታደር እንላክ የሚል አቧራ ሊያስነሳ ይችላል ፡፡ ይህ የፖለቲካ ማደናገርያ ገና ፖርላመንት ሳይደርስ የሞት ሀሳብ ነው ፤ ግን መሞከሩ ግን አይቀርም ፡፡ አሜሪካንም ብትሆን እንዲህ በቀላሉ አሁን አየሺ አሁን አላየሽ በሚል የህጻን ጫወታ የምትታለል ሀገር አይደለቸም፡ አንድ መለስ ያንን ካርድ የመዘዘበት ሰአት ከ9/11 ብዙ ሳያይልድ ስለነበር ሽብርተኝነትን መዋጋት ከአሜሪካ ጭፍን ድጋፍ የሚያስገኝበት ወቅት ነበር፤ መለስ 1997 ምርጫ ጭፍጭፍ በኋላ አሜሪካ ያንን ወንጀሉን ባትሸፍንለት ኖሮ ሶማሌ ላይ ባደረገው ጭፍጨፋ የአለም የጦር ወንጀል ፍርድቤት ያስቀርበው ነበር ፤ በተለይ መቋደሾን በመድፍ የደበደበበት ወንጀል ፤ አሁን ደግሞ የበሻሻው ጩልሌ ተመሳሳይ ካርድ ስቦ ለመጫውት እየሞከረ ነው ፤ አብርሀም ሊንከን እንዳለው "ሁሉንም ሰዎች አንዳንድ ጊዜ ፤ አንዳንድ ሰዎችን ሁል ጊዜ ማታለል ይችላሉ ይሆናል ፣ ነገር ግን ሁሉንም ሰዎች ሁል ጊዜ ማታለል አይችሉም። የበሻሻው ጮሌ የዚህ መልክት ገና አልደረሰውም ፡፡