Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Right
Member
Posts: 2731
Joined: 09 Jan 2022, 13:05

Sudan/Ethiopia border fight started. Abiye was in Sudan recently.

Post by Right » 03 Feb 2023, 09:10

ሱዳን በኃይል በተቆጣጠረችው የኢትዮጵያ መሬት ጦርነት ተቀሰቀሰ
February 3, 2023


ሱዳን በተቆጣጠረችው የኢትዮጵያ ግዛት ታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት ግጭት መቀስቀሱ ከሱዳን በኩል ተስምቷል፡፡ ተቀስቅሷል በተባለው ግጭት የሰው ህይወት መጠፋቱ የተሰማ ሲሆን፣ ግጭቱን የቀሰቀሱት ኢትዮጵያ ታጠቂዎች መሆናቸውን የሚሳይ መረጃ ወጥቷል፡፡ ጥቃቱ የተፈጸመው ሱዳን በኃይል በተቆጣጠረችው አልፋሽጋ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ሲሆን፣ በስፋራው በብዛት የሚገኙ ሱዳናውያን እረኞች የጥቃቱ ሰላባ መሆናቸው ታውቋል፡፡ በዚህም የኢትዮጵያ ታጣቂዎች ባለፈው ማክሰኞ በወሰዱት እርምጃ አንድ እረኛ መግደላቸው ነው የተገለጸው፡፡ ዶክተር አብይ አሕመድ ካርቱም ደርሰው ከሱዳን ወታደራዊ መሪዎች ተነጋግረው ከመጡ በሳምንቱ ይህ አይነት ግጭት መነሳቱ አጠያያቂ ነው ።

ጥቃት አድራሾች በእረኞችና በእንስሳት ላይ ማነጣጠራቸው የሱዳንን የእንስሳት ገበያ፣ አገራዊ ምጣኔ ሀብትን እና የእንስሳትን ምርት አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑን ሱዳን ትሪቡን ዘግቧል፡፡ ይህንኑ ተከትሎ የሱዳን ፖሊስ አባላት ወደ ቦታው ደርሰው በአካባቢው ጥበቃ እያደረሱ መሆናቸው የተሰማ ሲሆን፤ የሱዳን እረኞችም ወደ ኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ ከመጠጋት እንዲቆጠቡ የሱዳን ፖሊስ ማሳሰብ ተጠቁሟል፡፡

የሱዳንና ኢትዮጵያ መንግሥታት በመካከላቸው ያለውን የድንበር ውዝግብ በሰላማዊ ውይይት ለመፍታት ቁርጠኛ መሆናቸውን መግለጻቸው የሚታወስ ነው፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መቀራረብ የጀመሩት የኢትዮጵያ እና ሰዱን ባለሥልጣናት በኹለቱ አገሮች መካከል ያለውን የድንበርና ሌሎች የኹለትዮሽ ጉዳዮችን በጋራ ለመፍታት ተስማምተዋል፡፡ ይሁን እንጂ ሱዳን በተቆጣጠረቸው ኢትዮጵያ መሬት ላይ የራሷን ኃይል በማስፈሯ በተደጋጋሚ ግጭት መቀስቀሱ አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡ በድንበሩ አካባቢ አንድ ጊዜ በሱዳን በኩል አንድ ጊዜ ከኢትዮጵያ በኩል በሚተነኮሱ ጥቃቶች የሰው ሕይወት ይጠፋል፡፡

ኢትዮጵያ እና ሱዳን በድንበር አቅራቢያ ባሉ የጸጥታ ችግሮች ዙሪያ በጋራ ለመስራት ቢስማሙም፣ በታጣቂዎች በተደጋጋሚ የሚከሰቱ ጥቃቶችን ማስቆም አልቻሉም ነው የተባለው፡፡ በሱዳን በኩል ስለተሰማው ጥቃት መፈጸም ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል የተሰጠ መረጃ የለም፡፡ ሱዳን 70 ኪሎ ሜትር ወደ ኢትዮጵያ ግዛት በመዝለቅ በርካታ ቦታዎችን በኃይል ተቆጣጥራ እንደምትገኝ ሲገለጽ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

አዲስ ማለዳ

Noble Amhara
Senior Member
Posts: 11627
Joined: 02 Feb 2020, 13:00
Location: Abysinnia Highlands

Re: Sudan/Ethiopia border fight started. Abiye was in Sudan recently.

Post by Noble Amhara » 03 Feb 2023, 09:18

We will have joint operation with sudanEse government against the lawless shiftas the regional and federal gov declared war over and anyone who violates the peace should face justice

Please wait, video is loading...
facebook]https://www.facebook.com/16774498056267 ... 572288489/[/facebook]
Please wait, video is loading...

Right
Member
Posts: 2731
Joined: 09 Jan 2022, 13:05

Re: Sudan/Ethiopia border fight started. Abiye was in Sudan recently.

Post by Right » 03 Feb 2023, 09:40

Something is cooking.
Sudan belligerently have already occupied a big chunk of farm land inside Ethiopia and the PP regime has no problem with that.
Abiye visited Sudan and there was a secret agreement between the two countries that the public have no a clue about its content.
Only time will tell who is behind all this [deleted].

Post Reply