Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 5496
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

ትምህርት ላይ መረባረብ

Post by Naga Tuma » 02 Feb 2023, 18:21

ኣንዱ ጠቃሚ የዚህ ዘመን ዉይይት ትምህርት ላይ መረባረብ ነዉ።

ኣንዳንድ ጊዜ ከባድ ያልሆነዉን መማር እና ማስተማርን ከባድ የምናስመስል ሆኖ ይታየኛል።

እኔ ብዙ ከመሸምደድ ይልቅ የማይረሱ ጥቂት ፅንሰሀሳቦችን ማወቅ የምመርጥ ነኝ።

ለዚህም ነዉ ትምህርት ላይ መረባረብ ፅንሰሀሳቦችን ማስጨበጥ ላይ ብያተኩር የበለጠ ዉጤታማ ሆኖ የሚታየኝ።

ይህን ፎረም ለዓመታት ካነበብኩ በሁዋላ በኣብዛኛዉ በኣንድ ሰዉ የዕዉቀት ደረጃ የተገደበ መስሎ ይታየኛል። ኣንድ ሰዉ ዘጠኝ ፅንሰሀሳቦችን ኣዉቆ አስረኛዉን ከሳተ የሞሉት ዘጠኞቹ ሳይሆኑ የጎደለዉ ኣንዱ ወሳኝ ሊሆን ይችላል።

ትምህርት ላይ መረባረብ የበለጠ ሙሉዎችን ለማፍራት ይጠቅማል።

መማር እና ማስተማር ከቤተሰብ ይጀምራል ማለት ይቻላል። ከሆነ እያንዳንዱ ቤተሰብ በቀላሉ መጨበጥ የሚችል የሳይንስ ፅንሰሀሳቦች ኣሉ። ዛሬ በሰፊዉ የተለመዱ ሊሆን ይችላል። ከሆነ እሰየዉ። ካልሆነም ለናሙና ያህል እነሆ።

፩ኛ) እግዝኣብሔር ያዉቃልን ወደ እግዝኣብሔርን ማገዝ መነሳሳት መለወጥ። ብዙ ነገሮችን ለእግዝኣብሔር መተዉ የተለመደ ነዉ። እግዝኣብሔር መጀመርያ ላይ ሁለት ሰዎችን መፍጠሩ ለሁሉም ኣማኝ ይነገራል። ዛሬ ወደ ስምንት ቢልየን ሰዎች ምድር ላይ ኣሉ። እነዚህ ሁሉ እግዝኣብሔርን ተጣዳፊ ወይም ቢዚ ያደርጉታል። ስለዚህ እሱ የሚችለዉን ይስራ። የሰዉ ልጆች ሁሉ የሚችሉትን ያግዙት። ያላገዙትን እናንተ ሰነፎች ይላቸዋል። ይህ ፅንሰሀሳብ ለማህበረሰባችን የኣስተያየት ለዉጥ ወይም ፓራዳይም ሺፍት ኣያመጣም? የምያመጣ ይመስለኛል።

፪ኛ) የይሞላል እና ይጎድላልን የአስተሳሰብ ልዩነት በግልጽ ማሳየት። ይህ ግላስ ሃፍ ፉል እና ሃፍ ኤምፕቲን አስተሳሰብ ልዩነት እያንዳንዱ ቤተሰብ በቀላሉ ኣሳይቶ ማስተማር ይችላል። ዉሃ እና ብርጭቆ ሊኖራቸዉ የማይችሉ ቤቶች ያሉ ኣይመስለኝም። ሁለቱም አስተሳሰቦች ትክክል ሆነዉ የኣንድ ሰዉ ምርጫ ከሌላዉ ሰዉ ምርጫ የሚለይበት ምክንያት ምንድን ነዉ? መወያየትን ያመጣል።

፫ኛ) ወደጀርባ ወይም ሁዋላ እያዩ ወደፊት መራመድ መሞከር ብዙ ርቀት ሳያደርስ ያደናቅፋል። ይህ ቀላል የሆነ ፅንሰሀሳብ በጣም ከባድ የሆነ የእኛ ኢትዮጵያን በሽታን የምያክም ነዉ። የበሽታዉ ስም ኩርፍያ ነዉ። ያኮረፈ ሰዉ እንደዚህ ሆኜ፣ እንደዛ ሆኜ ብሎ ስንቱን ሲቆጥር ቆሞ ይቀራል፣ ተነስቶ ወደፊት ከመራመድ። እስፖርተኛ በዚህ በሽታ እንዳይጠቃ ትምህርት ይሰጠዋል። ስለዚህ ኣንድ ፍክክር ከተሸነፈ ወደፊት ለሚመጣዉ ፍክክር ይዘጋጃል።

፬ኛ) ይህ ፅንሰሀሳብ ሳይንስን በቀላሉ የምያስጨብጥ ነዉ። የኮምፒዩተር ሳይንስ የምያዉቁ በጣም ቀላል ነገር ግን እጅግ ጠቃሚ እና በሰፊዉ ጥቅም ላይ የሚዉል ነዉ። ዘ ስዋፒንግ ሞዴል ተብሎ ይታወቃል። ስለኮምፒዩተር ሳይንስ ያለኝ እዉቀት መጠነኛ ነዉ። ለዚህ ፅንሰሀሳብ እና ጥቅም ያለኝ አስተያየት ትልቅ ነዉ።

በቀላሉ ለመገንዘብ ሁለት አይነት ጭማቂዎችን ሳይቀላቅሉ ከኣንድ ጣሳ ዉስጥ ወደሌላ ጣሳ መገልበጥ ነዉ። ሶስተኛ ጣሳ የግድ ያስፈልጋል። የግድ ሶስተኛ ጣሳ ማስፈለጉ ነዉ ዋናዉ ፅንሰሀሳብ። ኮምፒዩተር ሳይንስ ዉስጥ ሁለት ሳይሆን ሶስት ተለዋዋጮች ወይም ቫርየብልስ በመጠቀም ይከናወናል። ሶስቱን ጣሳዎች ኤክስ ዋይ ዚ ብሎ እንደመሰየም ነዉ።

እነዚህን አራት በጣም ቀላል ፅንሰሀሳቦች በደንብ ማስጨበጥ በጣም ቀላል አይዴለም? እኔ በጣም ቀላል ናቸዉ ብዬ ኣስባለሁ። ሁሉም ኢትዮጵያዊያን እናቶች እና አባቶች ልጆቻቸዉ ትምህርት ቤት ሳይገቡ በፊት ማስተማር የሚችሉ።

በጣም ቀላል ከሆነ እያንዳዳችን የምናዉቃቸዉን የሃገራችንን ሰዎች ጋር እናወያይ እና ስንቶቹ በግልጽ እንደምያዉቁት እንወቅ።

Naga Tuma
Member+
Posts: 5496
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ትምህርት ላይ መረባረብ

Post by Naga Tuma » 04 Feb 2023, 03:33

ሕዝባችን በኣብዛኛዉ መሬቴ፣ መሠረቴ፣ ርስቴ ማለትን እንደባህል የምያዉቅ ነዉ።

በገንዘብ ማስላት እና ዕዉቀት ገንዘብ ሆኖ መሬት፣ መሠረት፣ ርስት የምያመጣ መሆኑ እንደባህል የተለመደ ኣልሆነም ቢባል ስህተት ኣይመስለኝም።

እኔ መሬቴ፣ መሠረቴ፣ ርስቴ እንደባህል ከለመዱ ቤተሰብ ወጥቼ በገንዘብ ማስላትን በደንብ ያወኩ አይዴለሁም። ስለዚህ ለእንደዚህ አይነት ሽግግር ሙከራ ምሳሌ ልሆን የምችል ይመስለኛል።

ስማር እና ኢትዮጵያ እና እዚህ ኣሜርካ ለጥቂት ዐመታት ሳስተምር ያለፍኩበት ለዛሬ ተማሪዎች እና ኣስተማሪዎች ኣንድ ኣመላካች ምሳሌ ሊሆን ይችላል።

ትምህርት ቤቶች ዉስጥ ሁለት ቀን ከልብ ኣዝኛለሁ።

ኣንዱ የማትሪክ ሂሳብ ፋተና የወሰድኩኝ ቀን ነዉ። በእጄ ላይ ሰዓት ኣልነበረኝም። ፈታኞች 30 ደቂቃዎች ሲቀሩ ጀምረዉ ይህን ያህል ደቂቃዎች ቀሯችሁ ማለት ይጀምራሉ። የዛን ቀን ፈታኙ ዘንግቶ ይሁን በግድዬለሽነት 10 ደቂቃዎች ሲቀሩ ነዉ ይህን ያህል ደቂቃዎች ቀሯችሁ ያለዉ። ያን ስሰማ በጣም ኣዘንኩኝ። ፈተና ላይ ዘገምተኛ ነኝ። ሰዓት ካላጠረኝ የማልፈዉ ጥያቄ ዬለም።

ሂሳብን ከሁሉ ኮርሶች በላይ እወዳለሁ። ከሁሉም ኮርሶች በላይ ለሂሳብ ነበር የተዘጋጀሁኝ። በዛች አስር ደቂቃ ዉስጥ ማዘኔን መቆጣጠር ኣልቻልኩም። ከፈተናዉ በሁዋላ ብዙ ተማሪዎች ትምህርት ቤቱ በር ላይ ዙርያዬ ተሰብስበዉ ማዘኔን ኣይተዉ ነበር። ከዛ በሁዋላ በቃ ማትሪክን ይወድቃል ብለዉ ኣወሩ ኣሉ።

የፕሮፌሰር ሰብስቤ ባልደረባ የሆነዉ ካልተሳሳትኩ የወሎ ሰዉ ማድረግ ይችል የነበረዉ 30 ደቂዎች ሲቀሩ ጀምሮ መናገር ነበር። የዛን ቀን ተናግሮ ከሆነ እኔ ኣልሰማሁትም ነበር ማለት ነዉ። ኣንድ ቀን ከአራት ኪሎ ግቢ ወጥቶ ቀበና አከባቢ መንገድ ላይ ኣግቼዉ የጎሪጥ ነዉ ያየሁት።

ማትሪክን ኣልፌ አምስት የሂሳብ ኮርሶችን ስወስድ ኤ ኣግኝቶ ከመጣ ሌላ ተማሪ በላይ ዉጤቶችን ማግኘቴ ያንን ፈታኝ ኣላስረሳኝም።

ሁለተኛዉ ሁለተኛ ዓመት ሁለተኛ ሰምስተር ላይ ዳይናሚክስ የሚባል ኮርስ ስወስድ ነበር። የኮርሱ መጽሃፍ በጣም ማራኪ ነዉ። ለመጀመርያ ጊዜ የጎማ መፈጠርን ያደነኩበት በጣም ቀላል ጥያቄ መጀመርያ ስያነቡት ከባድ የሚመስል እዛ መጽሃፍ ዉስጥ ነዉ ያየሁኝ። ካልኩሌተር ሳይኖረኝ ነዉ ኮርሱን የወሰድኩኝ። ኮርሱ ብዙ ሳይገፋ ያለካልኩሌተር ጥያቄ መስራት የማይቻልበት ቦታ ስደርስ ማዘኔን በዉስጤ ይዤ ተኛሁ። ለሚቀጥለዉ ሰሚስተር መጀመርያ ያሟላሁኝ ካልኩሌተር ነበር። ቀድሞ ቢታሰብበት ስራ ላይ የነበሩ ወንድሞች እና እህት ነበሩኝ። ማስፈለጉ ኣልተስተዋለም ነበር። ኣስተማሪዎች ለዚህ ኮርስ ይህን ያን ማሟላት የግድ ነዉ ብሎ ኣስቀድሞ መምክር ኣልተለመደም ነበር።

ኢትዮጵያ ለጥቂት ዐመታት ሳስተምር የመጀመርያዬ ሰምስተር የቸሩ ተማሪዎቼ የግምገማ ዉጤቴ 98.6 ፐርሰንት ነበር።

ኣሜሪካ ለሁለት ዓመታት ግራጁዌት ተማሪ ሆኜ ሳስተምር የታወቀ ፕሮፌሰር ከእሱ የበለጠ የግምገማ ዉጤት እንዳገኘሁ ለሌላ ፕሮፌሰር ተናግሮ ሰምቻለሁ።

ስለዚህ ያለኝ ልምድ ምናልባት ጠቃሚ ምሳሌ ሊሆን ይችላል ብዬ ኣስባለሁ። ለዚህ ነዉ የማካፍለዉ።
Last edited by Naga Tuma on 04 Feb 2023, 10:29, edited 1 time in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ትምህርት ላይ መረባረብ

Post by Horus » 04 Feb 2023, 03:48

አጭበርባሪ ኦሮሙማ ኩሽ!

Naga Tuma
Member+
Posts: 5496
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ትምህርት ላይ መረባረብ

Post by Naga Tuma » 04 Feb 2023, 09:55

Horus wrote:
04 Feb 2023, 03:48
አጭበርባሪ ኦሮሙማ ኩሽ!
ኼረ፣ ኼር፣ ኬር።

Naga Tuma
Member+
Posts: 5496
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ትምህርት ላይ መረባረብ

Post by Naga Tuma » 09 Feb 2023, 17:59

እኔ የተማርኩት ሙያ ዉስጥ በኒዉተን የልሂቅነት ስርቶች ኣንዱ ላይ የተመሰረተ ጽንሰሀሳብ ኣለ።

ጽንሰሀሳቡን በደርግ ዘመን በተሰራ ኢንስቲትዩት ዉስጥ በደርግ ዘመን ነዉ የተማርኩኝ።

ካልተሳሳትኩ ጽንሰሀሳቡን ኢትዮጵያ ዉስጥ በአዲስ አበባ ዩኒቨርዚቲ ተክኖሎጂ ፋከልቲ ማስተማር የተጀመረዉ በኣጼ ሃይለስላሴ ዘመን ነዉ።

አሜረካ ዉስጥ የኮምፒዩተር ሳይንስ ገኖ የኣሜሪካ መሃንዲሶች ወደ ኮምፒዩተር ሳይንስ ስራ ያዘነበሉበት ዘመን ስራ ኣግኝቼ ብዙ ሳልቆይ ኢትዮጵያ የተማርኩትን እና ኣሜሪካ ዉስጥ የደገምኩትን ጽንሰሀሳብ ተግባር ላይ መጠቀም የተለመደ ነዉ ብዬ እንድያሳዩኝ ቀላል ጥያቄ ጠየኩኝ። መልስ ሳጣ እንደሌላቸዉ ገባኝ። ከዛም ያለምንም ቅድመ ግምት ወይም ፕሪ ጀጅመንት ተደነኩኝ።

ንግግራችንን ካጨረስኩ በሁዋላ ሳላስበዉ ከኣፌ የወጡትን ቃላት እና ቦታዉን መቼም ኣልረሳም። ዚስ ፕሌስ ሃዝ ኤ ፕሮብሌም ነዉ ያልኩኝ። ያንን ጽንሰሀሳብ ተግባር ላይ ሳያዉሉ ስራዉን መስራት እንዴት እንደሚችሉ ደንቆኝ ነዉ።

ስራዉ በሚልዮኖች ዶላሮች በጀት የሚሰራ እና የቢልዮኖች ዶላሮችን ኢኮኖሚ ለማንቀሳቀስ ወሳኝ ሚና ያለዉ በርካታ መሃንዲሶች የሚሳተፉበት ነዉ።

ያንን ጽንሰሀሳብ ኣለመኖር እንደእድል ኣይቼ ሙጭጭ ብዬ ቁልጭ ኣድርጌ ኣሳየሁኝ። ያ ስራ አሜርካ ዉስጥ የጆርናል ወረቀት ሆኖ ለመታተም በቅቷል።

ተመሳሳይ ስራን ሰርቶ ያየሁኝ ሌላ መስርያቤት ዉስጥ ተመሳሳይ ስራ ላይ የተሰማራ በርክሌ ከሚገኘዉ የካሊፎትንያ ዩኒቨርዚቲ የተመረቀ ሰዉ ነዉ። እሱም ተመሳሳይ ስራ መስራቱን ያየሁኝ ኣንድ በስራ ጉዳይ ለእኔ ስልክ ደዉሎ ያንን ጽንሰሀሳብ ተግባር ላይ ኣላዋልንም እና ተግባር ላይ ለማዋል እየሰራሁ ነዉ ካልኩት በሁዋላ ነዉ።

የኣጼ ሃይለስላሴ ዘመን ኢትዮጵያ ዉስጥ የተጀመረዉ የዩኒቨርዚት ትምህርት ጠንካራ መሰረት የነበረዉ መሆኑን ይህ ገጠመኝ የምያሳይ ይመስለኛል።
Last edited by Naga Tuma on 09 Feb 2023, 18:48, edited 1 time in total.

Naga Tuma
Member+
Posts: 5496
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ትምህርት ላይ መረባረብ

Post by Naga Tuma » 09 Feb 2023, 18:35

ይህ የኣንድ ግለሰብ የትምህርት ጉዞ ለዛሬ እና ነገ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ኣንድ ጥቅም ያለዉ ምሳሌ መሆን ከቻለ የመማር እና ማስተማርን ሂደት ኣመላካች ሊሆን ይችላል።

ኣንደኛ መማር እና ማስተማር በቀላሉ ከቤተሰብ መጀመር ይችላል።

ሁለተኛ በጣም ቀላል የሆኑ መሟላት የሚችሉ በቀላሉ ከተዘነጉ የመማር ማስተማር ሂደት ዉስጥ ወሳኝ ሚና ሊኖራቸዉ ይችላል።

ሶስተኛ በቀላሉ ማስተዋል የሚቻሉ ጽንሰሀሳቦች ብዙ ርቀት መሄድ ይችላሉ።

በተረፈ በህማንቴስ ስም እዚህ ፎረም ላይ ስትሳተፍ የነበርክ የኤርትራ ልሂቅ የትምህርትህን ሂደት የምትችልበት ቦታ ብታካፍል በጣም ይጠቅማል ብዬ ኣስባለሁ። ለእኔ የኢትዮጵያዊ ወይም ኤርትራዊ ወይም ኣፍሪካዊ ወይም በአለም ደረጃ የሊህቅነት ልክ ነህ። እንደዘ አይነት ልሂቅ ለመጪዉ ትዉልድ ያስፈልጋሉ። እንደ ወፍ ዘራሽ ሳይሆን በብዛት።

Post Reply