Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

ጠ/ሚ አቢይ ሲኖዶስ ውስጥ "ዘረኝነት እና ፖለቲካ"አለ ብሎ በድፍረት እንዲናገር እንዴት ቻለ? ጳጳሶቹ በተግባር የፈጽሙት ጽያፍና በኦርቶዶክሶች ያሳዩት ክህደትስ?

Post by sarcasm » 01 Feb 2023, 09:26

By Ethiopia Hagere (Facebook page)

አንዳንድ ሰዎች ጠሚው ባደረጉት ዲስኩር ለአባቶች "እንደ አባ ማቲያስ ሁኑ" ማለታቸውን ተከትሎ አንዳንዶች "ለመከፋፈል ነው" "የአቡነ ማቲያስን ልብ ለማሸነፍ ነው" የሚሉ እና መሰል ሀሳቦችን ሰንዝረዋል። ወገኖች አትሳሳቱ። አባ ማቲያስን በ ዳንኤል ክብረት ወይ ሲሳይ አጌና ደረጃ ማሰብ ነውር ነው። የአብይ መንግስት አባ ማትያስን ለፖለቲካው መጠቀሚያ ለማድረግ ያልሞከረው መንገድ አልነበረም። አልሳካ ሲለው የፖለቲካ መጠቀሚያ ሆነው ያገለገሉትን ዘረኛ የቤተክርስቲያኗ አባቶችን፣ አገልጋዮችን እንዲሁም ሚዲያዎችን ተጠቅሞ አሳዷቸዋል፣ አፍኗቸዋል፣ ከሰው እንዳይገናኙ፣ ለሚዲያ እንዳይቀርቡ እንዳይወጡ እንዳይገቡ አግዷቸዋል።

ለህክምና ከሀገር እንደወጡ እንዲቀሩ ብዙ ተቆፍሮላቸዋል ግን እሳቸው ነቅነቅ አላሉም። ፖለቲከኛም ዘረኛም ሆነው አልተገኙም። ገፍቶ ሊጥላቸው ሞክሮ፣ የተሳሳተ ገፅታ ሊቀባቸው ጥሮ፣ ከሀገር አስወጥቶ ሊያስቀራቸው ሞክሮ አልተሳካለትም። የፖለቲካ መጠቀሚያ መሆን እንደማይፈልጉ እና እንደማይችሉ በተግባር አይቶታል። ዛሬ ላይ ምሳሌ ቢያደርጋቸው የመርህ፣ የእምነት እና የአቋም ሰው መሆናቸውን የግድ አምኖ እንዲቀበል ስላደረጉት እንጂ ፈቅዶ እና ወዶ አድርጎታል ወይም ለነገ ሴራ አይጎነጉንባቸውም ማለት አይደለም።

በተቃራኒው ቤተክርስቲያን ውስጥ "ዘረኝነት እና ፖለቲካ" አለ ብሎ በድፍረት እንዲናገር ከሌሎች አባቶች በቂ ግብአት አግኝቷል። ባለፉት ሁለት አመታት አባቶችን "ጄኔራል እና ካድሬ" አድርጎ ተጠቅሞባቸዋል። ቤተክርስቲያኗ ፓትሪያርኳን ተቃውማ ብልፅግናን ደግፋ መግለጫ እስከማውጣት አድርሷታል። ከትግራይ የተወለዱ ካህናትን ጁንታ እያሉ ከቦታቸው እና ከቤታቸው እንዲያፈናቅሉ በብልፅግና ሲጠየቁ በደስታ ሲፈፅሙት አይቷል። አንድ አባት "ከ[ወያኔ] ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው የታሰሩ አገልጋዮች ሲለቀቁ ቦታቸው ተሸጧል" ብለው በሳቅ የታጀበ ንግግር ሲያደርጉ ታዝቧል። ሌላ አባት ደግሞ በአደባባይ "ጁንታ ከሚገዛን ሰይጣን ይግዛን" በማለት ለአብይ ጦርነት፣ ለብሄራቸው ደግሞ ፖለቲካ ሲሰሩ ነበር።

እነዚህ ጥቂት ምሳሌዎች እንጂ የቤተክርስቲያን አባቶች ምን ያህል ለፖለቲካ እና ዘረኝነት ከፊት ተሰልፈው እንደከረሙ ብንዘረዝረው አንጨርሰውም። አክሱም ፂዮን ስትደፈር፣ በማርያም ደንገላት ምዕመናን በጅምላ ሲረሸኑ፣ በመላው ትግራይ ዲያቆናት እና ካህናት ሲገደሉ፣ ሀይማኖታዊ ቅርሶች ሲዘረፉ እና ሲወድሙ፣ መነኩሴዎች በብሄር ተመርጠው ከገዳም ሲባረሩ እና መሰል ግፎች ቤተክርስቲያን እና ምዕመኖቿ ላይ ሲፈፀሙ ቤተክርስቲያኗ እና ጳጳሶቿ ከዝምታም አልፈው ድጋፍ ሲሰጡ ከርመዋል። የአሜሪካ ኮንግረስ ቀርበው "አብይን አትጫኑት ጦርነቱን ይቀጥልበት" ሲሉ ተማልደዋል።

በዚህ ጉዳይ ቤተክርስቲያን አይደለም ድጋፍ ዝምታ እንኳን አይጠበቅባትም ነበር። ችግሩ ግን "ፖለቲካ እና ዘር" ከእምነት ቀድመው ከፊት ተሰልፈው ተገኝተዋል። ታዲያ ዛሬ ላይ አብይ "ጄኔራል እና ካድሬ" አድርጎ ሲጠቀማቸው የከረሙትን አባቶች እናንተ "ፖለቲከኛ እና ዘረኛ" ናችሁ ቢላቸው ደረጃ አንድ ተወቃሹ አብይ ወይስ አባቶች? እዚህ ጋር አብይ ይሄን መናገሩ ልክ ነው እያኩ ሳይሆን ከሱ ንግግር ይልቅ የነሱ ተግባር የከፋ ጥፋት ነው እያልኩ ነው። ጅቡ ውሻው በቀደደው ገባ እንጂ እራሱ ቀዶ አልገባም!!

አብይ ፖለቲከኛ ነው። ተጠቅሞህ ሲጨርስ በመጣል አይረካም። ክብርህን ገፎ እና አዋርዶ መጣል የተካነበት ነው። በጦርነቱ ወቅት የፓትሪያርኩ መግለጫ ቤተክርስቲያንን አይወክልም ያሉት እና በጦር ግንባር ከመዝመት አልፈው እስከ መቀሌ አብሬ ዘምታለው ያሉ አንዳ አባት በሰሞኑ መግለጫቸው እያለቀሱ "ክርስቲያኖች መኖር ካልተፈቀደልን በግልፅ ይነገረን" ሲሉ ከመስማት በላይ ለዚህ ሁነኛ ማሳያ የለም።

Please wait, video is loading...