ፈጣሪ ፓትርያርክ ኣቡነ ማትያስንና ጠቅላዪ ኣብዪን እንዲሁም ሕዝቡን ይባርክ!
Posted: 01 Feb 2023, 09:12
ጠቅላይ ኣብዪ ኣሕመድ ለካቢኔ ኣባሎቻቸው፡ በኃይማኖትና መንግሥት ዙርያ፡ በተለዪም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ውስጥ ለተፈጠረው ኣወዛጋቢ ጉዳይ መፍትሄ በመጠቆም ረገድ የሰጡት ማብራርያ፡ እጅግ በጣም ድንቅ መሆኑን በመግለጥ አድናቆታችንን ለመግለጥ ነው። ኣዎን በንግግርና በውይይት የማይፈታ ችግር የለም፡ በነውጥና በኃይል የሚፈታ ችግርም የለም። ኣምላክ ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መእመናንና ለሃይማኖት ኣባቶች በሙሉ መልካም መልካሙን ያሳስባቸው። ፈጣሪ ፓትርያርክ ኣቡነ ማትያስንና ጠቅላዪ ኣብዪን እንዲሁም መላውን ሕዝብ ይባርክ በቅዱስ መንፈሱም ኣማካኝነት ይምራ፡ ብለናል እኛ ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።
Meleket wrote: ↑13 Dec 2018, 03:36. . .
ይህን የጅማ ብላቴና ለምን እንደግፋለን ቢባል፦
ለፍትሕ ያላሰለሰ ጥረት ስለሚያደርግ!
ሌባን ሌባ በማለት የብዙሓን ጫንቃ ላይ ሊጋልቡ ሚሹትን ኅሊና ቢሶች ቀልብ የሚገፍ አስተዋይ መሪ በመሆኑ።
ከጎረቤት አገሮች ጋር ሆነ ከዓለም መንግስታት ጋር ትዕቢት ሳይሆን ፍቅርን ባነገበ መንፈስ ስለሚግባባ!
ወገኖቹን የውስጡንም የውጩንም አግባብቶ እንደ አንድ የዕድሜ ባለጸጋ በልቦና የሚያስተዳድር ርህሩህ ወጣት መሪ በመሆኑ።
ለማንኛውም ፍጡር ከበሬታ ያለው፣ አንዱን ከአንዱ የማያበላልጥ የቅንነት ተምሳሌት በመሆኑ።
ለእናቶችና ለእህቶች ልዩ ክብር ያጎናጸፈ የስራና የመርህ ሰው በመሆኑ።
ታገራችን ተኤርትራ ጋር ስምምነትና ፍቅርን አንግቦ የድንበሩን ውሳኔ ተቀብሎ ትግባሬውንም ለማስለጥ ስለሚተጋ።
ተወደደም ተጠላ ጦቢያ በታሪዃ ካጋጠሟት መሪዎቿ በወጣትነቱ፣ በልቦናው፣ በጥበቡ በርህራሄው በጀግንነቱም እጅግ ረቂቅ ከሆኑት ጋር ስለሚመደብ።
ይህ ብላቴና በዚህች በኛ የግርግርና የሽብር ዕድሜ የተከሰተ በጨለማው ዘመን ብርሃንን ያበራ ድንቅ መካር የሰላም አለቃ በመሆኑ ነው። እየተንፈራገጥክ ያለህ እኩይ ኅሊናቢስ ሌባ ሁላ ቁርጥህን እወቅ፣ የግርግርና የስርቆት የሽብርና የመደናበር ዘመን አክትሟል፣ ዘመኑ የይቅርታ የፍቅር የወንድማማችነት የመከባበርና የሰላም ነው። ከመሪ ተዋናዮቹ መካከልም የጅማው ብላቴና የጦቢያው ጠቅላዪ አንዱ ነው!!!
Meleket wrote: ↑19 Jun 2018, 03:00ውዳሴ ዘአብይ
ያ ዲያብሎስ ቀንቶት እኛኑ አጣልቶ፣
ኢትዮጵያና ኤርትራን እርስበርስ አባልቶ፣
ሁሌ ጠዋት ማታ ሲያሰማን ቀረርቶ፣
ምስኪኖች ሲያነቡ ከበሮ ሊደልቅ፣
ሰብአዊ ፍጡርን እንዲሁ ሲያሳቅቅ፣
ስንት ንጹሓንን በእስር ሲያማቅቅ፣
ምህረት ሰላም ፍቅርን ከኛ ዘንድ ሊያርቅ፣
ህዝቦች ደም ሲያነቡ እሱ ግን ሲሳለቅ፣
ብዙሃን ታርዘው እርሱ ሲሞላቀቅ፣
ሳይታክት መስራቱን እኛኑ ሊያናቁት፣
ጉዳዮች ጠማዞ ወስልቶ ሲተብት፣
ሊዘራ ክፍፍል ሁሌ ሲንገታገት፣
የሱን ተንኮል ደባ በውኑ ያጤኑት፣
ወጣቱ አስተዋዩ የኛው ትውልድ ወካይ፣
ብልሁ መካሪ አንደበተ አማላይ፣
በሓቅ የሚመሩት የትህትና አገልጋይ፣
ያነገቡት ራእይ መርሁ መደመር፣
በቅንነት ገስጋሽ በቃል ሆነ ተግባር፣
ሀሰተኛን ሁላ በቃላቸው ዘራይ፣
ከጎናቸው አለን ከኚህ ወጣት ጠቅላይ!
የክፍሉን ስራ የቤቱንም ስራ አሳይመንቱን ሁሉ፣
አጣጥሞ ሚሰራ ተግባሩን ከቃሉ፣
እንደርስዎ አላየንም በጦብያ በሙሉ።
እግዜር ከርስዎ ጋር ነው እንመሰክራለን፣
እድሜ ለኤልያስ እንጽፈዋለን፣
አይናችን እያየ መች ዝም እንላለን?
ቢወራጭ ቢወራጭ የዲያብሎስ መንጋ፣
እርሶ ይነዱታል በእውነት አለንጋ፣
ሽዎች ንጹሃንን ከሲኦል መንጋጋ፣
ሚንከራተቱትን ፍትህን ፍለጋ፣
ልብ አሳርፈዋል በቆላም በደጋ።
ይህንን ታዝበን ስንል አብይ በርቱ፣
ሓቅን ስለያዙ ሐሰትን ሲረቱ፣
የምህረት ተግባርዎ ቀንም ሆነ ማታ፣
ርቱዕ አንደበትዎ ሚሰጠን እርካታ፣
ሰላምን ሰባኪ ከጦርነት ፈንታ፣
ዘመንዎ እንደሚሆን የሰላም የእርጋታ፣
በሁላችን ዘንድም ስለዘሩ ደስታ፣
ህዝብን አክብረዋል ያክብርዎት ጌታ።
ትልቅ ጆሮ ሰጥተው ለህዝቡ ስሞታ፣
ትዕግስትን አንግበው ለህዝብ አቤቱታ፣
እውነተኛ መልስን በተርታ በተርታ፣
ለሚልዮኑ ህዝብ ስለሆኑ ዋልታ፣
ስንል እንደኖርነው ናና ማራናታ፣
አንድዬ ራሱ ነው የስዎ መከታ፣
አያሳፍርዎም ያ የሚያምኑት ጌታ።
አንዱ አንዱን እንዲያየው ሁልግዜ የጎሪጥ፣
ሌሎችን የማሞኝ እኔ ብቻ ነኝ ብልጥ፣
ሲል እንዳልነበረ ዲያብሎስ ያ ቆሪጥ፣
ሁሉንም አስማሚ እውነቱን በመግለጥ፣
በየዋህ አንደበት ትዕቢትን በማቅለጥ፣
ዘመን እንዲያበቃ ዘመነ መርመጥመጥ፣
ምህረት የሰብኩ አልፈው እሳት ረመጥ፣
የመደመር መርህ ከሁሉ የሚበልጥ፣
ምንኛ ደስ ይላል ይህ የእርስዎ ፈሊጥ።
እኒያ ደም መጣጮች ምነው ወሬ አበዙ፣
እኒያ የቀን ጅቦች ምነው ወሬ አበዙ፣
ዛሬም አሉባልታን እንዲሁ ሚነዙ፣
ጉዳይ አወሳስበው ነገር ሊያጠነዙ፣
ግጭቶች ለመፍጠር ከሚቅበዘበዙ፣
ለህግ የበላይነት ምናለ ቢገዙ?
ልኩን ነገሯቸው ነገር ሳያንዛዙ፣
እንዲህ የእርሶ ዓይነቶች ተደምረው ይብዙ።