Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

ፈጣሪ ፓትርያርክ ኣቡነ ማትያስንና ጠቅላዪ ኣብዪን እንዲሁም ሕዝቡን ይባርክ!

Post by Meleket » 01 Feb 2023, 09:12

ጠቅላይ ኣብዪ ኣሕመድ ለካቢኔ ኣባሎቻቸው፡ በኃይማኖትና መንግሥት ዙርያ፡ በተለዪም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ውስጥ ለተፈጠረው ኣወዛጋቢ ጉዳይ መፍትሄ በመጠቆም ረገድ የሰጡት ማብራርያ፡ እጅግ በጣም ድንቅ መሆኑን በመግለጥ አድናቆታችንን ለመግለጥ ነው። ኣዎን በንግግርና በውይይት የማይፈታ ችግር የለም፡ በነውጥና በኃይል የሚፈታ ችግርም የለም። ኣምላክ ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መእመናንና ለሃይማኖት ኣባቶች በሙሉ መልካም መልካሙን ያሳስባቸው። ፈጣሪ ፓትርያርክ ኣቡነ ማትያስንና ጠቅላዪ ኣብዪን እንዲሁም መላውን ሕዝብ ይባርክ በቅዱስ መንፈሱም ኣማካኝነት ይምራ፡ ብለናል እኛ ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር። :mrgreen:
Meleket wrote:
13 Dec 2018, 03:36
. . .
ይህን የጅማ ብላቴና ለምን እንደግፋለን ቢባል፦

ለፍትሕ ያላሰለሰ ጥረት ስለሚያደርግ!

ሌባን ሌባ በማለት የብዙሓን ጫንቃ ላይ ሊጋልቡ ሚሹትን ኅሊና ቢሶች ቀልብ የሚገፍ አስተዋይ መሪ በመሆኑ።

ከጎረቤት አገሮች ጋር ሆነ ከዓለም መንግስታት ጋር ትዕቢት ሳይሆን ፍቅርን ባነገበ መንፈስ ስለሚግባባ!

ወገኖቹን የውስጡንም የውጩንም አግባብቶ እንደ አንድ የዕድሜ ባለጸጋ በልቦና የሚያስተዳድር ርህሩህ ወጣት መሪ በመሆኑ።

ለማንኛውም ፍጡር ከበሬታ ያለው፣ አንዱን ከአንዱ የማያበላልጥ የቅንነት ተምሳሌት በመሆኑ።

ለእናቶችና ለእህቶች ልዩ ክብር ያጎናጸፈ የስራና የመርህ ሰው በመሆኑ።

ታገራችን ተኤርትራ ጋር ስምምነትና ፍቅርን አንግቦ የድንበሩን ውሳኔ ተቀብሎ ትግባሬውንም ለማስለጥ ስለሚተጋ።

ተወደደም ተጠላ ጦቢያ በታሪዃ ካጋጠሟት መሪዎቿ በወጣትነቱ፣ በልቦናው፣ በጥበቡ በርህራሄው በጀግንነቱም እጅግ ረቂቅ ከሆኑት ጋር ስለሚመደብ።


ይህ ብላቴና በዚህች በኛ የግርግርና የሽብር ዕድሜ የተከሰተ በጨለማው ዘመን ብርሃንን ያበራ ድንቅ መካር የሰላም አለቃ በመሆኑ ነው። እየተንፈራገጥክ ያለህ እኩይ ኅሊናቢስ ሌባ ሁላ ቁርጥህን እወቅ፣ የግርግርና የስርቆት የሽብርና የመደናበር ዘመን አክትሟል፣ ዘመኑ የይቅርታ የፍቅር የወንድማማችነት የመከባበርና የሰላም ነው። ከመሪ ተዋናዮቹ መካከልም የጅማው ብላቴና የጦቢያው ጠቅላዪ አንዱ ነው!!!
Meleket wrote:
19 Jun 2018, 03:00
ውዳሴ ዘአብይ
ያ ዲያብሎስ ቀንቶት እኛኑ አጣልቶ፣
ኢትዮጵያና ኤርትራን እርስበርስ አባልቶ፣
ሁሌ ጠዋት ማታ ሲያሰማን ቀረርቶ፣
ምስኪኖች ሲያነቡ ከበሮ ሊደልቅ፣
ሰብአዊ ፍጡርን እንዲሁ ሲያሳቅቅ፣
ስንት ንጹሓንን በእስር ሲያማቅቅ፣
ምህረት ሰላም ፍቅርን ከኛ ዘንድ ሊያርቅ፣
ህዝቦች ደም ሲያነቡ እሱ ግን ሲሳለቅ፣
ብዙሃን ታርዘው እርሱ ሲሞላቀቅ፣
ሳይታክት መስራቱን እኛኑ ሊያናቁት፣
ጉዳዮች ጠማዞ ወስልቶ ሲተብት፣
ሊዘራ ክፍፍል ሁሌ ሲንገታገት፣
የሱን ተንኮል ደባ በውኑ ያጤኑት፣
ወጣቱ አስተዋዩ የኛው ትውልድ ወካይ፣
ብልሁ መካሪ አንደበተ አማላይ፣
በሓቅ የሚመሩት የትህትና አገልጋይ፣
ያነገቡት ራእይ መርሁ መደመር፣
በቅንነት ገስጋሽ በቃል ሆነ ተግባር፣
ሀሰተኛን ሁላ በቃላቸው ዘራይ፣
ከጎናቸው አለን ከኚህ ወጣት ጠቅላይ!

የክፍሉን ስራ የቤቱንም ስራ አሳይመንቱን ሁሉ፣
አጣጥሞ ሚሰራ ተግባሩን ከቃሉ፣
እንደርስዎ አላየንም በጦብያ በሙሉ።
እግዜር ከርስዎ ጋር ነው እንመሰክራለን፣
እድሜ ለኤልያስ እንጽፈዋለን፣
አይናችን እያየ መች ዝም እንላለን?

ቢወራጭ ቢወራጭ የዲያብሎስ መንጋ፣
እርሶ ይነዱታል በእውነት አለንጋ፣
ሽዎች ንጹሃንን ከሲኦል መንጋጋ፣
ሚንከራተቱትን ፍትህን ፍለጋ፣
ልብ አሳርፈዋል በቆላም በደጋ።

ይህንን ታዝበን ስንል አብይ በርቱ፣
ሓቅን ስለያዙ ሐሰትን ሲረቱ፣
የምህረት ተግባርዎ ቀንም ሆነ ማታ፣
ርቱዕ አንደበትዎ ሚሰጠን እርካታ፣
ሰላምን ሰባኪ ከጦርነት ፈንታ፣
ዘመንዎ እንደሚሆን የሰላም የእርጋታ፣
በሁላችን ዘንድም ስለዘሩ ደስታ፣
ህዝብን አክብረዋል ያክብርዎት ጌታ።

ትልቅ ጆሮ ሰጥተው ለህዝቡ ስሞታ፣
ትዕግስትን አንግበው ለህዝብ አቤቱታ፣
እውነተኛ መልስን በተርታ በተርታ፣
ለሚልዮኑ ህዝብ ስለሆኑ ዋልታ፣
ስንል እንደኖርነው ናና ማራናታ፣
አንድዬ ራሱ ነው የስዎ መከታ፣
አያሳፍርዎም ያ የሚያምኑት ጌታ።

አንዱ አንዱን እንዲያየው ሁልግዜ የጎሪጥ፣
ሌሎችን የማሞኝ እኔ ብቻ ነኝ ብልጥ፣
ሲል እንዳልነበረ ዲያብሎስ ያ ቆሪጥ፣
ሁሉንም አስማሚ እውነቱን በመግለጥ፣
በየዋህ አንደበት ትዕቢትን በማቅለጥ፣
ዘመን እንዲያበቃ ዘመነ መርመጥመጥ፣
ምህረት የሰብኩ አልፈው እሳት ረመጥ፣
የመደመር መርህ ከሁሉ የሚበልጥ፣
ምንኛ ደስ ይላል ይህ የእርስዎ ፈሊጥ።

እኒያ ደም መጣጮች ምነው ወሬ አበዙ፣
እኒያ የቀን ጅቦች ምነው ወሬ አበዙ፣
ዛሬም አሉባልታን እንዲሁ ሚነዙ፣
ጉዳይ አወሳስበው ነገር ሊያጠነዙ፣
ግጭቶች ለመፍጠር ከሚቅበዘበዙ፣
ለህግ የበላይነት ምናለ ቢገዙ?
ልኩን ነገሯቸው ነገር ሳያንዛዙ፣
እንዲህ የእርሶ ዓይነቶች ተደምረው ይብዙ።

Wedi
Member+
Posts: 7959
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: ፈጣሪ ፓትርያርክ ኣቡነ ማትያስንና ጠቅላዪ ኣብዪን እንዲሁም ሕዝቡን ይባርክ!

Post by Wedi » 01 Feb 2023, 09:38

ደብተራ Meleket ምናለ ይህ ሰው በሻትው ወደ ከፈተኛ ደርጃ ሳይሸጋገር እና አገር ሳያፈርስ ተሎ ወደ ሃኪም ቤት ወስደህ ብታሳክመው?

አማኝ ነኝ ስትል አልነበረም? ጠቅላዮ በበሻት እንዲህ እየተሰቃዬ ዝም ማለትህ የጤና ነው?


ሰው መቼም በጤናው ከሰውም ሆነ ከእግዚ አብሔር ጋር አይጣላም ብታሳክሙት የሚል ምክረ ሃሳብ አለኝ!
:lol: :lol:
:lol: :lol:
Please wait, video is loading...

Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ፈጣሪ ፓትርያርክ ኣቡነ ማትያስንና ጠቅላዪ ኣብዪን እንዲሁም ሕዝቡን ይባርክ!

Post by Meleket » 02 Feb 2023, 08:49

ወዳጃችን Wedi ጠቅላዩ ይህን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ሁኔታ በመላ ለመፍታት ካሻቸው ትልቅ መንፈሳዊ ምክር ከኒህ ኤርትራዊ ኣባት ቢያገኙ መልካም ሳይሆን ኣይቀርም ቢለን እናስባለን እኛ ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።

እኒህ ድንቅ ኣባት የሚገሰጸውንም የሚመከረውንም የሚሞገሰውንም በመልክ በመልኩ በጨዋደንብ መምከር የሚችሉ ዕድሜም ዕውቀትም ጠገብ መንፈሳዊ ኣባት በመሆናቸው፡ ምክራቸውን መስማት ግሩም ነው።

Bishop Macarios, Coptic Orthodox Patriarchal Exarch of the Eritrean Congregation in the USA

https://www.unionbetweenchristians.com/ ... -2020.html


Wedi wrote:
01 Feb 2023, 09:38
ደብተራ Meleket ምናለ ይህ ሰው በሻትው ወደ ከፈተኛ ደርጃ ሳይሸጋገር እና አገር ሳያፈርስ ተሎ ወደ ሃኪም ቤት ወስደህ ብታሳክመው?

አማኝ ነኝ ስትል አልነበረም? ጠቅላዮ በበሻት እንዲህ እየተሰቃዬ ዝም ማለትህ የጤና ነው?


ሰው መቼም በጤናው ከሰውም ሆነ ከእግዚ አብሔር ጋር አይጣላም ብታሳክሙት የሚል ምክረ ሃሳብ አለኝ!
:lol: :lol:
:lol: :lol:
Please wait, video is loading...

Abere
Senior Member
Posts: 10890
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: ፈጣሪ ፓትርያርክ ኣቡነ ማትያስንና ጠቅላዪ ኣብዪን እንዲሁም ሕዝቡን ይባርክ!

Post by Abere » 02 Feb 2023, 12:46

ፈጣሪ ኢትዮጵያን ከዐብይ አህመድ ይገላግላት ለማለት ፈልገህ በስህተት ታይፕ አድርገህ ይመስለኛል።የገደፍከው የእርምት ማስተካከያ ይፈልጋል።

Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ፈጣሪ ፓትርያርክ ኣቡነ ማትያስንና ጠቅላዪ ኣብዪን እንዲሁም ሕዝቡን ይባርክ!

Post by Meleket » 06 Feb 2023, 09:08

ወዳጃችን Abere በስህተት ታይፕ ኣድርገን ኣይደለም። "ፈጣሪ ፓትርያርክ ኣቡ ማትያስንና ጠቅላዪ ኣብዪን እንዲሁም ሕዝቡን ይባርክ!" ማለታችን በትክክል የኛን የኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች ኣቋም የሚገልጽ ኣባባላችን ነው። :mrgreen:
Abere wrote:
02 Feb 2023, 12:46
ፈጣሪ ኢትዮጵያን ከዐብይ አህመድ ይገላግላት ለማለት ፈልገህ በስህተት ታይፕ አድርገህ ይመስለኛል።የገደፍከው የእርምት ማስተካከያ ይፈልጋል።
ድንቁ እድሜና ዕውቀት ጠገቡ ኤርትራዊው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መንፈሳዊ ኣባት እባክዎን ባሉበት እኒህ ኢትዮጵያውያን ጎረቤቶቻችን ያጋጠማቸውን ሁኔታ በመረዳት መንፈሳዊ ምክርዎን ይለግሷቸው! ሰላምና ወንድማማችነት ለመላው ኢትዮጵያዊ መእመናን በሙሉ ለክርስትያኑም ለሙስሊሙም ተመኝተናል፡ እኛ ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር! :mrgreen:

Bishop Macarios, Coptic Orthodox Patriarchal Exarch of the Eritrean Congregation in the USA

Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ፈጣሪ ፓትርያርክ ኣቡነ ማትያስንና ጠቅላዪ ኣብዪን እንዲሁም ሕዝቡን ይባርክ!

Post by Meleket » 08 Feb 2023, 05:43

ፈጣሪ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የሃይማኖት ኣባቶችና መእመናን በሙሉ ማስተዋሉን ይስጣቸው። ዘመኑ ሁለት ተጻራሪ በደም ይፈላለጉ የነበሩ ሃይሎች እንኳ ሳይቀሩ፡ በጨዋ ደንብ በጠረጴዛ ዙርያ ተወያይተው ችግሮቻቸው እየፈቱ ያለበት ግዜ ነው። የትግራዩም ቤተክህነት የኦሮሞውም ቤተክህነት የቤተክርስትያኒቱም ሲኖዶስ በሱባኤ በጸሎትና በጠረጴዛ ዙርያ ተወያይተውና ተነጋግረው ነገሮችን እልባት ላይ ማድረስ የማይችሉበት ምክንያት ምንድን ነው? የምን መደናቆር ነው፡ ኣቦ ኢትዮጵያውያን እንዲህ ስትሆኑ ኣያምርባችሁም! ጠቅላዩ እንደሆን በቤተክርስትያኒቱ ውስጥ ሰላምንና ወንድማማችነትን ለማስፈን ሁኔታዎችን ከማመቻቸት ኣይቦዝኑም፡ ምክንያቱም ያለፈው ታሪካቸው የሚገልጸው ፓርትርያርክ መርቀሪዎስን ከፓትርያርክ ማትያስ ጋር በኣንድ ማእድ እንዲበሉ፡ እንተ ትብስ እኔ ተባብለው በፍቅር ተልእኳቸውን እንዲወጡ ሲጥሩ ኣይተናቸዋል፡ እኛ ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች



ያም ሆነ ይህ ለሰላም የሚተጉ ሃይሎችን በሙሉ ኣምላክ ይባርክ!

ፈጣሪ ፓትርያርኩንና ጉዳይ ኣለን የሚሉ የቤተክርስትያኗን ሰዎች በሙሉ እንዲሁም ጠቅላዩን ኣብዝቶ ይባርካቸው፡ ለሰላምም ያትጋቸው፡ በቅዱስ መንፈሱም ይምራቸው!

Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ፈጣሪ ፓትርያርክ ኣቡነ ማትያስንና ጠቅላዪ ኣብዪን እንዲሁም ሕዝቡን ይባርክ!

Post by Meleket » 16 Feb 2023, 03:29

ጳጳስንም ፓትርያርክንም ሳያስሩ፡ በጨዋና በሰለጠነ መንገድ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያንን ውስጥ ለተከሰተ ውስጣዊ ኣለመግባባት፡ በሥላሴና በጠረጴዛ ዙርያ፡ በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ለበቁት ለጠቅላዪ ኣብዪ ኣሕመድና ለፓትርያርክ ማቲያስ እንዲሁም ለሲኖዶሱና ለኦሮምያ ቤተክህነት የኃይማኖት ኣባቶች በሙሉ፡ ትልቅ ክብር ኣለን እኛ ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች። ለዚህም ነው በሙሉ ልባችን "ፈጣሪ ፓትርያርክ ኣቡነ ማትያስንና ጠቅላዪ ኣብዪን እንዲሁም ሕዝቡ ይባርክ" የምንለው። "ለአፍሪካን ሆነ ለዓለም ትልቅ 'የመደመር' ትምህርት እየሰጣችሁ ናችሁና ኣምላክ ኣሁንም ኣሁንም ኣብዝቶ ይባርካችሁ!" ብለናል፡ በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር፡ እኛ ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች :mrgreen:
Meleket wrote:
19 Jun 2018, 03:00
ውዳሴ ዘአብይ
ያ ዲያብሎስ ቀንቶት እኛኑ አጣልቶ፣
ኢትዮጵያና ኤርትራን እርስበርስ አባልቶ፣
ሁሌ ጠዋት ማታ ሲያሰማን ቀረርቶ፣
ምስኪኖች ሲያነቡ ከበሮ ሊደልቅ፣
ሰብአዊ ፍጡርን እንዲሁ ሲያሳቅቅ፣
ስንት ንጹሓንን በእስር ሲያማቅቅ፣
ምህረት ሰላም ፍቅርን ከኛ ዘንድ ሊያርቅ፣
ህዝቦች ደም ሲያነቡ እሱ ግን ሲሳለቅ፣
ብዙሃን ታርዘው እርሱ ሲሞላቀቅ፣
ሳይታክት መስራቱን እኛኑ ሊያናቁት፣
ጉዳዮች ጠማዞ ወስልቶ ሲተብት፣
ሊዘራ ክፍፍል ሁሌ ሲንገታገት፣
የሱን ተንኮል ደባ በውኑ ያጤኑት፣

ወጣቱ አስተዋዩ የኛው ትውልድ ወካይ፣
ብልሁ መካሪ አንደበተ አማላይ፣
በሓቅ የሚመሩት የትህትና አገልጋይ፣
ያነገቡት ራእይ መርሁ መደመር፣
በቅንነት ገስጋሽ በቃል ሆነ ተግባር፣
ሀሰተኛን ሁላ በቃላቸው ዘራይ፣
ከጎናቸው አለን ከኚህ ወጣት ጠቅላይ!

የክፍሉን ስራ የቤቱንም ስራ አሳይመንቱን ሁሉ፣
አጣጥሞ ሚሰራ ተግባሩን ከቃሉ፣
እንደርስዎ አላየንም በጦብያ በሙሉ።
እግዜር ከርስዎ ጋር ነው እንመሰክራለን፣
እድሜ ለኤልያስ እንጽፈዋለን፣
አይናችን እያየ መች ዝም እንላለን?

ቢወራጭ ቢወራጭ የዲያብሎስ መንጋ፣
እርሶ ይነዱታል በእውነት አለንጋ፣

ሽዎች ንጹሃንን ከሲኦል መንጋጋ፣
ሚንከራተቱትን ፍትህን ፍለጋ፣
ልብ አሳርፈዋል በቆላም በደጋ።

ይህንን ታዝበን ስንል አብይ በርቱ፣
ሓቅን ስለያዙ ሐሰትን ሲረቱ፣
የምህረት ተግባርዎ ቀንም ሆነ ማታ፣
ርቱዕ አንደበትዎ ሚሰጠን እርካታ፣
ሰላምን ሰባኪ ከጦርነት ፈንታ፣
ዘመንዎ እንደሚሆን የሰላም የእርጋታ፣
በሁላችን ዘንድም ስለዘሩ ደስታ፣
ህዝብን አክብረዋል ያክብርዎት ጌታ።

ትልቅ ጆሮ ሰጥተው ለህዝቡ ስሞታ፣
ትዕግስትን አንግበው ለህዝብ አቤቱታ፣
እውነተኛ መልስን በተርታ በተርታ፣
ለሚልዮኑ ህዝብ ስለሆኑ ዋልታ፣
ስንል እንደኖርነው ናና ማራናታ፣
አንድዬ ራሱ ነው የስዎ መከታ፣
አያሳፍርዎም ያ የሚያምኑት ጌታ።

አንዱ አንዱን እንዲያየው ሁልግዜ የጎሪጥ፣
ሌሎችን የማሞኝ እኔ ብቻ ነኝ ብልጥ፣

ሲል እንዳልነበረ ዲያብሎስ ያ ቆሪጥ፣
ሁሉንም አስማሚ እውነቱን በመግለጥ፣
በየዋህ አንደበት ትዕቢትን በማቅለጥ፣
ዘመን እንዲያበቃ ዘመነ መርመጥመጥ፣
ምህረት የሰብኩ አልፈው እሳት ረመጥ፣
የመደመር መርህ ከሁሉ የሚበልጥ፣
ምንኛ ደስ ይላል ይህ የእርስዎ ፈሊጥ።

እኒያ ደም መጣጮች ምነው ወሬ አበዙ፣
እኒያ የቀን ጅቦች ምነው ወሬ አበዙ፣
ዛሬም አሉባልታን እንዲሁ ሚነዙ፣
ጉዳይ አወሳስበው ነገር ሊያጠነዙ፣
ግጭቶች ለመፍጠር ከሚቅበዘበዙ፣
ለህግ የበላይነት ምናለ ቢገዙ?
ልኩን ነገሯቸው ነገር ሳያንዛዙ፣
እንዲህ የእርሶ ዓይነቶች ተደምረው ይብዙ።
:mrgreen:

Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ፈጣሪ ፓትርያርክ ኣቡነ ማትያስንና ጠቅላዪ ኣብዪን እንዲሁም ሕዝቡን ይባርክ!

Post by Meleket » 16 Feb 2023, 06:34

የሃገር መሪ ከመንፈሳዊ መሪ ማለትም ከሃይማኖት ኣባቶች ጋር እንዲህ ሲነጋገር እንዴት ደስ ይላል! :mrgreen:
የሃይማኖት ኣባቶችን የሚያከብር መሪ፡ የሃገሩን ህዝብ እሴት የሚያከብር መሪ ብቻ ነው። ለዚህ ኣብነትም የኢትዮጵያው ጠቅላዪ በመሆናቸው "ፈጣሪ ፓትርያርክ ኣቡነ ማትያስንና ጠቅላዩን እንዲሁም ሕዝቡን ይባርክ!" ቢለናል፡ እኛ ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።
:mrgreen:

Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ፈጣሪ ፓትርያርክ ኣቡነ ማትያስንና ጠቅላዪ ኣብዪን እንዲሁም ሕዝቡን ይባርክ!

Post by Meleket » 16 Feb 2023, 09:08

ስልጡን የሃገር መሪ ማለት በሃገሩ የሚከሰቱ ማንኛውንም ዓይነት ጉዳዮች በጠረጴዛ ዙርያ ውይይት መፍታት ዬሚችል ብቻ ነው! በዚህ ረገድ ጠቅላዪ ኣብዪን ኣለማድነቅ በፍጹም ኣይቻልም። ለበርካታ እድሜ ጠገብ መሪዎች ሳይቀር ትልቅ ትምህርት እየሰጡ ስለሆነ ጠቅላዪ ኣብዪን እናመሰግናቸዋለን፡ እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር። :mrgreen:

Meleket wrote:
16 Feb 2023, 06:34
የሃገር መሪ ከመንፈሳዊ መሪ ማለትም ከሃይማኖት ኣባቶች ጋር እንዲህ ሲነጋገር እንዴት ደስ ይላል! :mrgreen:
የሃይማኖት ኣባቶችን የሚያከብር መሪ፡ የሃገሩን ህዝብ እሴት የሚያከብር መሪ ብቻ ነው። ለዚህ ኣብነትም የኢትዮጵያው ጠቅላዪ በመሆናቸው "ፈጣሪ ፓትርያርክ ኣቡነ ማትያስንና ጠቅላዩን እንዲሁም ሕዝቡን ይባርክ!" ቢለናል፡ እኛ ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።
:mrgreen:

Post Reply