Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የጥር 23ቱ የአቢይ አህመድ አጭር ድራማ!

Post by Horus » 01 Feb 2023, 02:03

አበሻ ከማዳመጡ በፊት መመለስ ይወዳል። ለምሳሌ የዛሬውን የአቢይ አህመድ መግለጫ ልብ ብሎ የተመለከተው የለም ።

አንደኛ፣ ለምንድን ነው ሚኒስቴሮቹን ሁሉ የሰበሰበው? ምን መልዕክት ለማስተላለፍ ነው? ለምንድን ነው ሚኒስቴሮቹን በፍጹም በኦርቶዶክስ ጉዳይ እንዳትገቡ ያለው?

ያን ያለው በካቢኔው ውስጥ ችግር ስላለ ነው ። በካቢኔው ውስጥ የሃይማኖት ክፍፍል ስላለ ነው ። ሰዎች ለዚም ለዛም ሚኒስትር ይደውላሉ ብሏል ። ማለትም አቢይ ስልካቸው ይሰልላል ማለት ነው ። ይህ ብቻ እራሱን የቻለ ያለ መተማመንን ያሳያል። በሚኒስትሮቹ ፊት ላይ ይነበብ የነበረው አለማዳመጥ፣ የመገረምና ግራ የመጋባት ነበር። ልብ በሉ ስለ ሃይማኖትና ሰላም ጸጥታ መግለጫ ሲሰጥ ለኢትዮጵያ ሕዝብ መገኘት ያለበት የሰላም ሚኒስርና የሃይማኖት ጉዳዮች ሚኒስትር ነው።

በአንድ ቃል ይህ ንግግር ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሳይሆን ሚኒስትሮች ማሰልጠኛ ማስፈራሪያ ማስጠንቀቂያ ነበር። ለምን ከተባለ በኦርቶዶክስ ምክንያት በውስጣቸው የተከሰተ ችግር ስላለ ነው።

ሁለተኛ፣ አቢይ አህመድ ይህን ድራማ ባስቸኳይ ያዘጋጀው ዛሬ ፓትሪያርኩ የአማኞች ክተት ጥሪ ካደረጉና መንግስትን ካንቀጠቀጡ በኋላ ነው ። መንግስት ቁልፍ እየሰበረ የኦርቶዶክስ ንብረት ለህገወጡ አማጺ ቡድን እየሰጠ ነው ብለው በቀጥታ አቢይን ከወነጀሉ በኋላ ነው። አቢይ ይህን ድራማ ያዘጋጀው ። ማለትም በኢትዮጵያ ሕዝብ ፊትና ዳኝነት አቢይ አህመድ ዋናው ተጠያቂ ሆኖዋል! ተሸንፏል!

ሶስተኛ፣ ሳያሽ የበላ ዝንጀሮ ሲያስል ያድራል እንደ ሚባለው የችኮላው ድራማ ሌላ መዘዝ ይዞ መጥቷል ። ያም መዘዝ ያቢይ አህመድ አቋም ለ60 ሚሊዮን ኦርቶዶክስ ገሃድ አድርጓል ። እንዴት? አቢይ አህመድ የተወገዙትን ካህናት ወደ ነበራችሁበት ተመልሳችሁ ታረቁ አላለም ። ይህን ሕገ ወጥ ቡድንና ታላቁን ሲኖዶስ እኩል አድርጎ ተስማሙ ነው ያለው ። ይህ ብቻ አይደለም፣ የሚከተለው ልክ በሙስሊሞች ላይ ያደረገውን ነገር እንደ ሆነ በግልጽ ነገራቸው ለፓትሪያርኩ ።

አቢይ አህመድ ሚለፋው ከትግራይ የመጡትን ፓትሪያርክ በኦሮሞ ፓትሪያርክ ለመተካት ነው ይህ ሁሉ ድራማ።

አራተኛ፣ በኮሚኒኬሽን ደረጃ ሙሉ በሙሉ የከሸፈ ድራማ ነው ። አንድ ኮሚኒኬሽን ቢያንስ አራት አላማዎች አሉት፤ እናም ቢያንስ ከነዚያ አንዱን ካላሳካ ከሸፈ ይባላል ። ኮሚኒኬት ስናደርግ (1) ወይ ለማዝናናት ነው፣ (2) ወይ ኢንፎርም ለማድረግ ለማርዳት ነው፣ (3) ለማስተማር ነው። (4) ወይም ኢንፍሉወንስ ለማድረግ፣ ለመገፋፋት፣ ለማነቃቃት ነው ። ዛሬ አቢይ በተወነው ድራማ ከነዚህ አላማዎች አንድም አልነበሩም፤ ማለትም የራሱን ካቢኔት በማስፈራራት ተጽኖ ከማድረግ በተቀር ።

እንዲያውም በቅጥፈት የኦርቶዶክስ ደጋፊ ነኝ ለማለት ሲቀባጥር እራሱን ተጣርሶ የባሰ ሕዝብ እያስመረረ ነው ። የኦርቶዶክስ ደጋፊ ከሆነ ጥቂት ሕገ ወጦችን ለህግ ማቅረብ ነበረበት፣ ለምሳሌ ቤተ ክርስቲያ ሰብረው ሲገቡ ፣

አቢይ በዚም በዛም ኢትዮጵያን መምራት የተሳነው ግራ የተጋባ ፍጡር ነው ። ኦርቶዶክስ ግዙፍ የመሬት መንቀጥቀጥ ነው ። ባሸዋ ላይ የቆመው ያቢይ አህመድ የጎሳ እምቧይ ካብን በውል የሚያፈርስ ሰማየ ነጎድጓድ!
Last edited by Horus on 01 Feb 2023, 02:50, edited 2 times in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የጥር 23 የአቢይ አህመድ አጭር ድራማ!

Post by Horus » 01 Feb 2023, 02:33

ሌላው የረሳሁት ትልቅ ነጥብ የአቢይ ፍርሃት ልክ ነው።

ልብ በሉ በመንግስት ደረጃ ሰዎች ታዘው ስለምንግስቱ መውደቅ ጥናት እያስጠና ነው አቢይ አህመድ ። አመጽ ለማስነሳት አዲሳባ የሚገቡ አማጺያን እየያዝ ነው ያለው ዉሸት ነው፣ ማስመሰል ነው። ጎበዝ ለመምሰል ጸጥታ አለኝ ለማለት ነው! ዉሸት!

የጦር ሃይል ሞኖፖሊ አለኝ ብሎ አቢይ የደነፋው ምን ያህል እንደ ፈራና ያለበት ተቃውሞ ጥልቀት አርበትብቶት ነው። አንድ ሕዝብ ከጠላህ ይበቃል ! በግድ ከዲክታተሩ ጋር ማኖ አማኖ ፣ አንድ ላንድ መዋጋት የለባቸውም ! አልገዛም አልገዛም አልገዛም በማለት ብቻ ዲክታተሩን ከጥቅም ማድረግ ይቻላል ። አንድ መንግስት መግዛት ሲያቅተው መውደቂያው ደረሰ ይባላል!

ይህን ፍርሃት ነው ሳያስበው ጦር አለኝ፣ ሰማየ ሰማያትን መውጋት እችላለሁ ምንትሴ እየቀባጠረ ድራማውን የተወነው!

የተከፈተ አፍ ዝምብ ይገባበታል ይባላል! አቢይ መናገር ሲጀምር ፋውል መርገጥ ይጀምራል! አሁን ለምደነዋል!!!!
Last edited by Horus on 01 Feb 2023, 02:54, edited 2 times in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የጥር 23ቱ የአቢይ አህመድ አጭር ድራማ!

Post by Horus » 01 Feb 2023, 02:44

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የጥር 23ቱ የአቢይ አህመድ አጭር ድራማ!

Post by Horus » 01 Feb 2023, 02:57

union
Member+
Posts: 6044
Joined: 14 Feb 2021, 15:24

Re: የጥር 23ቱ የአቢይ አህመድ አጭር ድራማ!

Post by union » 01 Feb 2023, 03:31

ፈርቷል በቃ። ፋኖን ለማሸነፍ መጀመሪያ እምነቱን መምታት ከዛ ፋኖ ላይ መዝመት ነበር ህልም ግን ተዋህዶ እንዳሉት ወይም እንደመሰላቸው የአማራ ብቻ አይደለችም። ስለዚህ እቅዱ ከሸፈበት። ለዛ ነው ፊቱ ተነፍቶ ማድያቱን አንዠርግጎ የወጣው :lol:

Selam/
Senior Member
Posts: 11548
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: የጥር 23ቱ የአቢይ አህመድ አጭር ድራማ!

Post by Selam/ » 01 Feb 2023, 04:03

ምንም የምጨምረው ነገር የለም።
ዛሬ ግን ለብርሃኑ አዘንኩለት፣ አፈርኩለት።

Horus wrote:
01 Feb 2023, 02:03
አበሻ ከማዳመጡ በፊት መመለስ ይወዳል። ለምሳሌ የዛሬውን የአቢይ አህመድ መግለጫ ልብ ብሎ የተመለከተው የለም ።

አንደኛ፣ ለምንድን ነው ሚኒስቴሮቹን ሁሉ የሰበሰበው? ምን መልዕክት ለማስተላለፍ ነው? ለምንድን ነው ሚኒስቴሮቹን በፍጹም በኦርቶዶክስ ጉዳይ እንዳትገቡ ያለው?

ያን ያለው በካቢኔው ውስጥ ችግር ስላለ ነው ። በካቢኔው ውስጥ የሃይማኖት ክፍፍል ስላለ ነው ። ሰዎች ለዚም ለዛም ሚኒስትር ይደውላሉ ብሏል ። ማለትም አቢይ ስልካቸው ይሰልላል ማለት ነው ። ይህ ብቻ እራሱን የቻለ ያለ መተማመንን ያሳያል። በሚኒስትሮቹ ፊት ላይ ይነበብ የነበረው አለማዳመጥ፣ የመገረምና ግራ የመጋባት ነበር። ልብ በሉ ስለ ሃይማኖትና ሰላም ጸጥታ መግለጫ ሲሰጥ ለኢትዮጵያ ሕዝብ መገኘት ያለበት የሰላም ሚኒስርና የሃይማኖት ጉዳዮች ሚኒስትር ነው።

በአንድ ቃል ይህ ንግግር ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሳይሆን ሚኒስትሮች ማሰልጠኛ ማስፈራሪያ ማስጠንቀቂያ ነበር። ለምን ከተባለ በኦርቶዶክስ ምክንያት በውስጣቸው የተከሰተ ችግር ስላለ ነው።

ሁለተኛ፣ አቢይ አህመድ ይህን ድራማ ባስቸኳይ ያዘጋጀው ዛሬ ፓትሪያርኩ የአማኞች ክተት ጥሪ ካደረጉና መንግስትን ካንቀጠቀጡ በኋላ ነው ። መንግስት ቁልፍ እየሰበረ የኦርቶዶክስ ንብረት ለህገወጡ አማጺ ቡድን እየሰጠ ነው ብለው በቀጥታ አቢይን ከወነጀሉ በኋላ ነው። አቢይ ይህን ድራማ ያዘጋጀው ። ማለትም በኢትዮጵያ ሕዝብ ፊትና ዳኝነት አቢይ አህመድ ዋናው ተጠያቂ ሆኖዋል! ተሸንፏል!

ሶስተኛ፣ ሳያሽ የበላ ዝንጀሮ ሲያስል ያድራል እንደ ሚባለው የችኮላው ድራማ ሌላ መዘዝ ይዞ መጥቷል ። ያም መዘዝ ያቢይ አህመድ አቋም ለ60 ሚሊዮን ኦርቶዶክስ ገሃድ አድርጓል ። እንዴት? አቢይ አህመድ የተወገዙትን ካህናት ወደ ነበራችሁበት ተመልሳችሁ ታረቁ አላለም ። ይህን ሕገ ወጥ ቡድንና ታላቁን ሲኖዶስ እኩል አድርጎ ተስማሙ ነው ያለው ። ይህ ብቻ አይደለም፣ የሚከተለው ልክ በሙስሊሞች ላይ ያደረገውን ነገር እንደ ሆነ በግልጽ ነገራቸው ለፓትሪያርኩ ።

አቢይ አህመድ ሚለፋው ከትግራይ የመጡትን ፓትሪያርክ በኦሮሞ ፓትሪያርክ ለመተካት ነው ይህ ሁሉ ድራማ።

አራተኛ፣ በኮሚኒኬሽን ደረጃ ሙሉ በሙሉ የከሸፈ ድራማ ነው ። አንድ ኮሚኒኬሽን ቢያንስ አራት አላማዎች አሉት፤ እናም ቢያንስ ከነዚያ አንዱን ካላሳካ ከሸፈ ይባላል ። ኮሚኒኬት ስናደርግ (1) ወይ ለማዝናናት ነው፣ (2) ወይ ኢንፎርም ለማድረግ ለማርዳት ነው፣ (3) ለማስተማር ነው። (4) ወይም ኢንፍሉወንስ ለማድረግ፣ ለመገፋፋት፣ ለማነቃቃት ነው ። ዛሬ አቢይ በተወነው ድራማ ከነዚህ አላማዎች አንድም አልነበሩም፤ ማለትም የራሱን ካቢኔት በማስፈራራት ተጽኖ ከማድረግ በተቀር ።

እንዲያውም በቅጥፈት የኦርቶዶክስ ደጋፊ ነኝ ለማለት ሲቀባጥር እራሱን ተጣርሶ የባሰ ሕዝብ እያስመረረ ነው ። የኦርቶዶክስ ደጋፊ ከሆነ ጥቂት ሕገ ወጦችን ለህግ ማቅረብ ነበረበት፣ ለምሳሌ ቤተ ክርስቲያ ሰብረው ሲገቡ ፣

አቢይ በዚም በዛም ኢትዮጵያን መምራት የተሳነው ግራ የተጋባ ፍጡር ነው ። ኦርቶዶክስ ግዙፍ የመሬት መንቀጥቀጥ ነው ። ባሸዋ ላይ የቆመው ያቢይ አህመድ የጎሳ እምቧይ ካብን በውል የሚያፈርስ ሰማየ ነጎድጓድ!
Last edited by Selam/ on 01 Feb 2023, 04:34, edited 2 times in total.

Wedi
Member+
Posts: 7959
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: የጥር 23ቱ የአቢይ አህመድ አጭር ድራማ!

Post by Wedi » 01 Feb 2023, 04:26

ጋላ አብይ አህመድ ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ገብቷል!! ለዚያን ነው የሰበሰባቸው ፕሮቴስታን ሚንስቶች ያስፈራረው፡፡ በተጨመሪም በዚህ የድንቃጤ መግለጫ ውስጥ ስለ መፈነቀለ መንግስት ማውራቱ እብዱ አብይ አህመድ ከፍተኛ ስጋት ውስጥ መግባቱ ያሳያል!!

በመጨረሻ እያንዳንዱ የኦርቶዶክስ ሀማኖት ለመጨረሻ ፍልምያ ራሱን ማዘጋጀት አለበት!!

"ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሐይማኖታችን የደምስራችን ናት እንጠብቃት"

Abere
Senior Member
Posts: 10889
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: የጥር 23 የአቢይ አህመድ አጭር ድራማ!

Post by Abere » 01 Feb 2023, 12:09

ሴረኛ ሰው እንደ ሰጋ ይኖራል። ሲያምኑት የከዳ መሪ እንደ ምሳሌ ቢጠቀስ በታሪክ ውስጥ አብይ አህመድ ቁጥር 1 ነው። ከግድያ እራሱን ለጥያት እራት አድርጎ የጋረደው ህዝብ መልሶ እንደሚያጋልጥው ማወቅ ያልቻለ ሰው ነው።

በጣም ፈርቷል - ምክንያቱም የእርሱ ግጭት ከህዝብ ጋር ብቻ ሳይሆን ከፈጣሪ ጭምር ስለሆነ። የዚህ ሰውዬ ትልቁ ችግር ወይ መካሪ ማጣት ወይም ጤና አልባነት ነው። የኢትዮጵያ ችግር እኮ ጥናት እና ምርምር ወይም አስርት አመታት ውይይት አይፈልግም - በጥም ቀላል ነው። የጎሳ ክልል እና ህገ-መንግስት እንድቀየር መስራት ነው። ታሪክ ለመስራት ትልቅ እድል አግኝቶ ሳይጠቀምበት ሰው ከሰው ሳያፋቅር የታሪክ ትቢያ ይሆናል። ቢፈቅድ ግን አሁንም ኳሱ ወደ ህዝብ ከመምጣቷ በፊት ተጠርዞ ከጫዎታ ውስጭ ሳይሆን የተጣባዉን እርኩስ የኦሮሙማ መንፈስ እና የስልጣን ስካር በመተው ወደ በጎ ተግባር ቢመለስ መልካም ነው። ይህን የሚያደርግ አይመስለኝም እንደ ትግሬው ጦርነት ገና ሰው ያጫርሳል በመጨረሻም ደመ ከልብ ይሆናል። መካሪ ሰው ካለው ያዳምጥ። ሙት ይዞ ይሞታል።ዳውድ ኢብሳ እና በዙሪያው ያሉ አሮጊት ኦሮሙማዎች ወደ ጉድጓዳቸው እየወሰዱት ነው። ደግሞስ ያለ ምክንያት የተገደሉት የወለጋ ንጹሃን አማራዎች ደም እንድሁ ይቀራል የሚል ማን አለ - በቀል የእግዚአብሄር ነው። የጠፋው ህይወታቸው፥ የወደመው ንብረታቸው፤ የፈሰሰውን እንባቸውን ማን አበሳቸው? ማን መንግስት የካሳ ክፍያ ፈጸመላቸው?

Horus wrote:
01 Feb 2023, 02:33
ሌላው የረሳሁት ትልቅ ነጥብ የአቢይ ፍርሃት ልክ ነው።

ልብ በሉ በመንግስት ደረጃ ሰዎች ታዘው ስለምንግስቱ መውደቅ ጥናት እያስጠና ነው አቢይ አህመድ ። አመጽ ለማስነሳት አዲሳባ የሚገቡ አማጺያን እየያዝ ነው ያለው ዉሸት ነው፣ ማስመሰል ነው። ጎበዝ ለመምሰል ጸጥታ አለኝ ለማለት ነው! ዉሸት!

የጦር ሃይል ሞኖፖሊ አለኝ ብሎ አቢይ የደነፋው ምን ያህል እንደ ፈራና ያለበት ተቃውሞ ጥልቀት አርበትብቶት ነው። አንድ ሕዝብ ከጠላህ ይበቃል ! በግድ ከዲክታተሩ ጋር ማኖ አማኖ ፣ አንድ ላንድ መዋጋት የለባቸውም ! አልገዛም አልገዛም አልገዛም በማለት ብቻ ዲክታተሩን ከጥቅም ማድረግ ይቻላል ። አንድ መንግስት መግዛት ሲያቅተው መውደቂያው ደረሰ ይባላል!

ይህን ፍርሃት ነው ሳያስበው ጦር አለኝ፣ ሰማየ ሰማያትን መውጋት እችላለሁ ምንትሴ እየቀባጠረ ድራማውን የተወነው!

የተከፈተ አፍ ዝምብ ይገባበታል ይባላል! አቢይ መናገር ሲጀምር ፋውል መርገጥ ይጀምራል! አሁን ለምደነዋል!!!!

Right
Member
Posts: 2722
Joined: 09 Jan 2022, 13:05

Re: የጥር 23ቱ የአቢይ አህመድ አጭር ድራማ!

Post by Right » 01 Feb 2023, 12:41

Another catch
His own words:
-a military coup brought down the Haile Selassie regime. (Correction: a popular uprise did. The military filled a power vacuum)
-Derg was overthrown by TPLF through Armed struggle.
-TPLF was removed by peaceful struggle.

He continued….if you think of implementing those tried and tested methods on me, you won’t succeed. PP is too powerful and a smarter organization.

FEAR FEAR FEAR IS KILLING THIS ROTTEN HEAD PIG. HE WAS GIVEN ALL THE SUPPORT ONE CAN DREAM OF FROM THE ETHIOPIAN PEOPLE. HE CHOSE A DIFFERENT AND EVIL PATH. YOU LIVE AND DIE BY YOUR OWN SWORD (TRIBALISM).

Post Reply