Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Selam/
Senior Member
Posts: 11771
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

የኦሮሞሙማ ዻዻሶች ብዙ ኦሮሞዎችን ወደ ኦርቶዶክስ እምነት ካመጡ እሰይ ነው!

Post by Selam/ » 31 Jan 2023, 06:40

ሰው ከአረማዊነትና እና ከባዕድ እምነት ወደ እግዚአብሄር ሲመለስ እንደማየት የሚያስደስት ነገር የለም። ሰማያዊ ነገር ነው።

በተለይም ወደ ኦርቶዶክስ ሲመጡ በሩን ወለል አድርገን ከፍተን፣ እሰይ እንኳን ጣዖታችሁን ወርውራችሁ ጥላችሁ ወደእኛ መጣችሁልን ብለን ጉንጫቸውን መሳም ነው ያለብን። ፈጣሪ ቋንቋ ስለሌለው፣ በእርሱ የሚያምኑትን ሁሉ በእኩልነት ነውና የሚያው፣ በፈቀዱት ቋንቋ ይዘምሩ ይፀልዪ። እኔ ምን አገባኝ። “አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፥ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፥ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና።” ገላትያን ፫፥፪፰

ችግር የሚሆነው እምነትን ለአናሳነት ስሜት ማካካሻ ወይንም እንደፖለቲካ ዱላ ስንጠቀምበት ነው። አንድ የሃይማኖት መሪ፣ ‘የታባታችሁ እኔም እንደናንተ የራሴ ቤተ እምነት አለኝ‘ ብሎ ሜንጫውን እየሰበቀ ከወንድሞቹ ከአፈነገጠ፣ በምድርም በሰማይም ድብን አድርጎ ከሽፏል። በተለይም የሰማይ ቤት ‘በኬኛ‘ አይገኝም። “ለወገኔ ይጠቅማል በማለት ወይም በከንቱ ውዳሴ ምክንያት አንድ እንኳ አታድርጉ” ፊል ፪፥፫

ከሰኞ እስከአርብ በጎጥ ፖለቲካ ንትርክ ውስጥ ከተልከሰከስኩኝ፣ የማደርገው ሁሉ ከአናሳነት ስሜት የተነሳና ሌሎችን ለመምሰል ወይንም ለመብለጥ ከሆነ፣ የሰው ልጅ እንደበግ ሲታረድ እንዳልሰማ ፀጥ ለጥ ካልኩኝ፣ ዛፍንና የአተቴ ጨሌን ቅቤ መቀባት ካላቆምኩኝ፣ ሺህ ጊዜ እሁድ ለፎቶ ቤተክርስቲያን ደጃፍ ብኮለኮል፣ እምነት ከሌላቸው ያልተሻልኩኝ እንሰሳና ድውይ ነኝ።

“ወደ ኋላዬ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን፤ የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን አታስብምና ዕንቅፋት ሆነህብኛል አለው።” ማቴ ፩፮፥፪፫

Last edited by Selam/ on 31 Jan 2023, 07:25, edited 1 time in total.


Horus
Senior Member+
Posts: 30829
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የኦሮሞሙማ ዻዻሶች ብዙ ኦሮሞዎችን ወደ ኦርቶዶክስ እምነት ካመጡ እሰይ ነው!

Post by Horus » 31 Jan 2023, 15:31

Selam,
Actors produce unintended consequences. ይህ በኦሮሞች መሃል የተነሳው የኦርቶዶክስ ውዝግብ ትልቅ አሉታዊ ውጤት እንዳለው ሁሉ ዛሬ የማናየው አዎንታዊ ውጤት ሊኖረው ይችላል ። ድሮ ከኦሮሞ ጓደኞቼ ጋር ስናወራ ፍርሃታቸው በእስልምና ስለመዋጥና የኦሮሞ ካልቸር ስለመጥፋት ነበር ። ያ ፍርሃት አሁንም የተቀበረ እሳት ነው ። ለምሳኤ ኢሬቻን ና ዋቄ ፌታን ከሙስሊም ኦሮሞ እኩል የሚቃወመው የለም ። ስለሆነም ይጠበቅ የነበረው በዋቄዎችና በሙስሊሞች፣ በዋቄዎችና በኦርቶዶክሶች፣ በኦርቶዶክሶችና በፕሮቴስታንቶች መሃል ያለው ልዩነት ነበር እንጂ በኦርቶዶክስና በኦርቶዶክስ ይሆናል ብሎ የጠበቀ የለም። ይህ ለግዜው እሚያሳዝን ክፍፍል ኦርቶዶክስነት በኦሮሞች ውስጥ ትልቅ ጉዳይ ማድረጉ ወደፊት እራሱ ኦርቶዶክስን ይጠቅመዋል። አሁን ህጋዊ ሲኖዶስም ጠንክሮ ያስተምራል ። ህገወጦቹም ባቋማቸው ከቀጠሉ ብዙ ኦሮሞ አማኝ ለማግ ኘት ይሰራሉ ። ያም ማለት የኦርቶዶክስ ኦሮሞች ቁጥር ይጨምራል ማለት ነው ። ይህ መሰል ውጤት አቢይም ጴንቴዎቹም ያሰቡት ግብ አይደለም! ሁሉም በግዜ ይታያል!

Post Reply