Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

ሁለት ሲኖዶስ መኖር አዲስ ነው እንዴ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን? ለሁለት ፓትርያሪክስ የመጀመርያ ጊዜ ነው እንዴ? ኦሮሞዎች ሲያደረጉት ነው እንዴ ፖለቲካ የሚሆነው?

Post by sarcasm » 30 Jan 2023, 21:33

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን፤ ላለፉት ሳላሳ ዓመታት አከባቢ ሁለት ሲኖዶስና ሁለት ፓትርያሪክ ነበሩ።

የአማራ ጳጳሳት አይደሉም እንዴ ሁለተኛ ሲኖዶስ ያቋቋሙት? ታድያ እንዴት ነው የኦሮሞ ጳጳሳት ሲያደርጉት ሓጥያት፤ የአማራ ጳጳሳት ሲያደርጉት ጽድቅ የሚሆነው?



TGAA
Member+
Posts: 5598
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

Re: ሁለት ሲኖዶስ መኖር አዲስ ነው እንዴ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን? ለሁለት ፓትርያሪክስ የመጀመርያ ጊዜ ነው እንዴ? ኦሮሞዎች ሲያደረጉት ነው እንዴ ፖለቲካ የሚሆነው?

Post by TGAA » 30 Jan 2023, 21:44

ሁለት ሲኖዶስ የኖረበት ምክንያት መለሰ ፓትሪያርኩን አባሮ የራሱን ካድሬ ፓትሪያርክ ስለሾመበት ነው ፤ ያ አንዱ የቤተክርስታያንን ቅኖና ማፍረስ ነው፤ ሌላው ደግሞ በኢትዮጵያ ውስጥ ሁለት ሲኖዶስ ኖሮ አያውቅም ፤ ለምን ግን የናንተን ግማሽ የበሰለ ብልጣብልጥነት ሰው ውስጡn ማየት የሚችል እንደማይመስላችሁ ግራ ነው የሚያጋባው ፤ ይሄን ያህል የተወሳሰበ አምሮ አለን ብላችሁ እራሳችሁን አሳምናችኋል ማለት ነው ፡ ወያኔ ማጥ ውስጥ የከተታትም የሞኝ ብልጣ ብልጥነው ነው ፡፡

sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: ሁለት ሲኖዶስ መኖር አዲስ ነው እንዴ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን? ለሁለት ፓትርያሪክስ የመጀመርያ ጊዜ ነው እንዴ? ኦሮሞዎች ሲያደረጉት ነው እንዴ ፖለቲካ የሚሆነው?

Post by sarcasm » 31 Jan 2023, 08:57

TGAA wrote:
30 Jan 2023, 21:44
በኢትዮጵያ ውስጥ ሁለት ሲኖዶስ ኖሮ አያውቅም
በዚህም ይሁን በዚያ ሁለት ሲኖዶሶች ነበሩ። That is a fact! የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ራሷ የሁለቱ ሲኖዶሶች የዕርቀ ሰላም ጉባዔ ኣካሄድኩ ብላለች። አሁንም፤ በዚህም ይሁን በዚያ ሁለት ሲኖዶሶች አሉ።


የሲኖዶሶች የዕርቀ ሰላም የማብሰሪያ መርሃ ግብር በሚሊኒየም አዳራሽ በመካሄድ ላይ ነው

2018 የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት.


አዲስ አበባ ሀምሌ 28/2010 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የሲኖዶሶች የዕርቀ ሰላም ማብሰሪያ መርሃ ግብር በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ በመካሄድ ላይ ነው።

በኢትዮጵያና በአሜሪካ በሚኖሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን አባቶች መካከል ተፈጥሮ በነበረው ችግር ላለፉት 26 ዓመታት ሲኖዶሱ ለሁለት ተከፍሎ ቆይቷል።

የእርቀ ሰላም ልዑካን ቡድን አስቀድሞ ሄዶ የሰራውን የማስታረቅ ስራ ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በአሜሪካ በመገኘት የረዥም ጊዜ ችግር ለመፍታት እርቅ እንዲወርድ አድርገዋል። በዚህም ሁለቱ ሲኖዶሶች ቃለ ውግዘታቸውን አንስተው ወደ ዕርቅ መምጣታቸው ይታወሳል።

በፕሮግራሙም ስደተኛው ሲኖዶስ ተብሎ የሚጠራውና በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ 4ተኛ ፓትሪያሪክ የሚመራው ሲኖዶስ ዛሬ በእናት አገሩ ከምዕመናን ጋር እግዚአብሔርን እያመሰገነ ይገኛል።

በፕሮግራሙ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድና የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የተለያዩ ቤተ እምነት አባቶች እንዲሁም ከ25 ሺህ በላይ የእምነቱ ተከታዮችና ሌሎችም ተገኝተዋል።

የታሪክ መዛግብት እንደሚያመለክቱት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሲኖዶሶች ለሁለት ሲከፈሉ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑን ያመለክታል።

አቡነ መርቆርዮስ ቡራኬ በመስጠት፣ አባ ማቲያስ ደግሞ አስተዳደራዊ ተግባራትን በመፈጸም ቤተክርስቲያኗን ያስተዳድራሉ።

በሁለት ሲኖዶሶች መካከል ያለውን አለመግባባት ለመፍታት በአሜሪካ ዋሺንግተን ዲሲ በተካሄደው የሰላም ማብሰሪያ ጉባኤ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በቀጣይ የሁለቱ ሲኖዶሶች የሰላም ማብሰሪያ የማጠቃለያ ጉባኤ በሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚካሄድ መጠቆማቸው ይታወሳል።

https://www.ena.et/?p=13219

የሁለቱ ሲኖዶሶች የዕርቀ ሰላም ጉባዔ በአሜሪካ | EOTC’s Synods reconciliation conference in the U.S.

EOTC • Ethiopian Orthodox Tewahedo Church
2.07K subscribers
❍ በቤተ ክርስቲያናችን የሁለቱ ሲኖዶሶች የዕርቀ ሰላም ጉባዔ በደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤ ቤ/ክ (ዋሽንግተን፣ ዲሲ)


sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: ሁለት ሲኖዶስ መኖር አዲስ ነው እንዴ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን? ለሁለት ፓትርያሪክስ የመጀመርያ ጊዜ ነው እንዴ? ኦሮሞዎች ሲያደረጉት ነው እንዴ ፖለቲካ የሚሆነው?

Post by sarcasm » 01 Feb 2023, 08:41

Please wait, video is loading...

sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: ሁለት ሲኖዶስ መኖር አዲስ ነው እንዴ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን? ለሁለት ፓትርያሪክስ የመጀመርያ ጊዜ ነው እንዴ? ኦሮሞዎች ሲያደረጉት ነው እንዴ ፖለቲካ የሚሆነው?

Post by sarcasm » 02 Feb 2023, 10:09

sarcasm wrote:
01 Feb 2023, 21:56
ሲኖዶሱ ከእርቁ ቦኃላ "ሁለት ፓትርያሪኮች አልነበሩንም" ብሎ ዛሬ ሲዋሽ እጅ ከፈንጅ ተያዘ። ከእርቁ ቦኃላ በጠ/ሚ አቢይ በዓለ ሲመት የፖለቲካ ምንዝርና ሲፈጽሙ ሲኖዶሱ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያሪካችን ናቸው ብለው ነበር


"ሁለት ፓትርያሪኮች አልነበሩንም" - ዛሬ
FF 10:40


አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያሪክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ - ከከእርቁ ቦኃላ ከሁለት ዓመት በፊት ከአቡነ ማትያስ ተጣልተው ሲኖዶሱን አይወክሉም በሚሉበት ግዜ
FF 9:50

Post Reply