Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30668
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ኦሮሙማ እና የጎሳ አምልኮ!

Post by Horus » 29 Jan 2023, 22:10

የጎሳ አምልኮ ተከታዮች ምንም አይነት ኦርቶዶክስ ሊሆኑ አይችሉም!! ፈጣሪ ጎሳ ፈጠረ የሚል ቃል የለም። ፈጣሪን (እግዚአብሄር፣ አላህ፣ ጎድ፣ ጌታ) ብለን በ1001 ስም ብንጠራውም ፈጣሪ እያንዳንዱን ግለሰብ ልዑል፣ እኩል እና ሙሉ አድርጎ ፈጠረ የሚለው ቃል ነው አንድን ሰው ክርስቲያ ወይም አማኝ የሚያደርገው። የወያኔ ትግሬና የኦነጋዊ ኦሮሙማ የጎሳ አምልኮ ተከታዮች ከአሻቸው ለጎሳ አምላካቸው ጣኦት አቁመው ይሰግዳሉ እንጂ በያንዳንዱ ግለሰብ ልዕልና ላይ በተመሰረተ ሃይማኖት ገብተው የሚፈተፍቱ አረመኔዎችና ያውም የኦርቶዶክስ ካህን (የእግዚአብሄር አገልጋይ) ለመሆን ራሳቸውን የሚሾሙ የጎሳ ፖለቲካ አምላኪዎች ኦርቶዶክስ ደጅ መድረስ የለባቸው! መቅደሱን ስለሚያረክሱት! እግዚአብሄር የሰው ልጅን ፈጠረ! እግዚአብሄር ጎሳን አልፈጠረም! ፖለቲከኛ የሚባል ሰው ጎሳን ፈጠረ! እነዚህ የኦሮሙማ ጳጳስ እንሁን ባይ የፖለቲካ ስልጣን ጥመኞች ይህን የፍጥረት ሃሁ ስተዋል!