Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 10894
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

ለተማሪው ዜር አይሰጥም:: ዜሮ ካገኘ ተማሪው ክፍል ውስጥ የለም ማለት ነው። የአብይ አህመድ ትምህርት መርሃ ግብር ግን ዜሮ አገኘ። ተማሪውም: አስተማሪውም ክፍል ውስጥ አልነበሩም።

Post by Abere » 29 Jan 2023, 20:30

ለተማሪው ዜር አይሰጥም:: ዜሮ ካገኘ ተማሪው ክፍል ውስጥ የለም ማለት ነው። የአብይ አህመድ ትምህርት መርሃ ግብር ግን ዜሮ አገኘ። ተማሪውም: አስተማሪውም ክፍል ውስጥ አልነበሩም። ለተማሪው ዜሮ አይሰጥም የሚለው ሁልግዜ በተማሪዎች የውጤት ካርድ ላይ የማርክ አሰጣጥ ዘንድ የምናየው ነው። ይህ ግን የወያኔ ስርዐተ-ማህበር ትምህርት የጠነሰሰው አብይ አህመድ እየጠመቀ የሚያድለው የድንቁርና ጽዋ እስከ ዛሬ ሰው ቀድሞ እንዳላወቀው በማስመሰል ተማሪዎችም፥ አስተማሪዎች፥ መንግስትም አብረን ወደቅን እያለ ያላዝናል። እራሱ ወደቅኩኝ ብሎ እንዳያወራ። ምን ተማሪው ብቻ የኦነግ ኦሮሙማ መንግስት እራሱ ዜሮ ነው። 4 አመት ሙሉ ጊዜውን ያሳለፈው በሁከት፥ በማፈናቀል፤ የኦነግ ጨርቅ እስቅላለሁ ግብ ግብ ፤ ባንክ በመዝረፍ፤ ወዘተ ነው። ልክ እራሱ ከወያኔ የተሻለ ለማስመሰል ይጥራል - ግን ዋና የኦነግ ወያኔ ነው። የባቢሎን ትምህርት ስርዐት ተቀርጾ በባቢሎነኛ ቅርስምስም ሲማሩ ቆይተው ደረጃውን ያልጠበቀ ጉዳይ ትምህርት ተብሎ የአገር ሃብት ከማባከን ውጭ ምን ዕውቀት ይሆናል።