Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Selam/
Senior Member
Posts: 11549
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

የኦነግ-ሸኔ መንግስት በአተቴ ጨሌ አብዶ ራሱን ጠልፎ እንደሚጥል ቅንጣት ያህል ጥርጣሬ የለኝም።

Post by Selam/ » 29 Jan 2023, 10:49


አወቅሽ አወቅሽ ሲሏት፣ መጽሀፏን አጠበች አሉ። እንከፉ ደርግ ተፈጥሮን ብቻ ሳይሆን መንፈስንም ለመቆጣጠር ቤተ-እምነትን ሲዘጋና ሲያሽግ እንዲሁም፣ የፊደል ገበታ በ ‘ሀ’ ሳይሆን በ ‘በ’ መጀመር አለበት ብሎ ሲፎልል፣ አዋቂዎች መክረውና ዘክረው ነበር። ምከረው ምከረው…ሆነ በመጨረሻ ውጤቱ።

አሁን ደግሞ አረማውያኑ የኦነግ-ሸኔ አስተዳደር ቤተ-እምነት አፍራሽ ወረበሎችን ሲያሰለጥን ከርሞ፣ ዛሬ ጠብደል ጎጠኞችን ዽዽስና እንዲያጘኙና፣ አባቶችን እንዲያሸብሩ ቀብቶ መርቋቸዋል። ነገ ደግሞ ፀጥ ለጥ ያለውን የሙስሊም ህብረተሰብ እንደሚቆሰቁሱት ግልፅ ነው። ከሁሉ የገረመኝ እንደ እሳት ራት መጥፊያቸው እንዲፋጠንላቸው ከመጠን በላይ መቅበዝበዛቸው ነው።

ፈጣሪ በንጉስ ሰለሞን ቅብዐት ያወጃትንና ከሰብአ ሰገል ኮከብ ጋር ያዋሃዳትን ቤተ መቅደስ፣ አይደለም የጨበሪያም ሰገጤ ሸኔዎችን ዕብሪት፣ የኦቶማን ከሊፋን ጭቃኔ፣ የዮዲት ጉዲትን ዕብደት፤ የአሕመድ ኢብራሂም አል ጋዚን ጥፋት፣ የተኩላው ሙሶሎኒን ዕልቂት፣ የኮሙኒዝምን የሽብር ዘመቻ፣ የዘረኛ ወያኔዎችን የግማሽ ክፍለ ዘመን የክፋት መንፈስ ቤተ ክርስቲያኗ መክታ ስለ ተቋቋመች፣ ጠላቶቿ ይጠፋሉ እንጂ እሷ እንደ ሁልጊዜው፣ አፈር ልሳ ትነሳለች።






Post Reply