Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Y3n3g3s3w
Member
Posts: 531
Joined: 22 Dec 2017, 00:56

እረባክህ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ.........

Post by Y3n3g3s3w » 29 Jan 2023, 02:37

እረባክህ ዶ /ር ብርሃኑ ነጋ የትምርት ጥራቱን ገደለው ፣አወረደው እያክ እራስ የሚያስገምት/የሚያሳፍር ትችት ይደብራል!
የትምርት ሚኒስተር ለ12ኛ ክፍል በአለም አቀፍ ደረጃ ይመጥናል ያለውን ፈተና አዘጋጅቶ አቀረበ፣ በዚህም ሆነ በዚያ ምክንያት ብዛት ያለው ተማሪ አላለፈውም። ተጠያቂው ማነው?
ሚኒስተሩ (ዶ /ር ብርሃኑ ነጋ - እንደ ግለስብ)፣
ት/ርት ሚኒስተር እንደ ተቋም
የኢፊድሪ መንግስት፣
ተማሪዎች ፣
ቤተሰብ፣
ት/ቤቶች(ዳሬክተሮች፣አስተማሪዎች)
አለም?

እንደኔ ተጠያቂነትን በቅደም ተከተል እንዘርዝር ካልን ለዚህ ሁሉ ውድቀት የመጨረሻ ተጠያቂ እንደ ግለሰብ ሚኒስተሩ (ዶ /ር ብርሃኑ ነጋ) ነው። ለምን? ዶ/ሩ በመሰረቱ ያደረገው ፣ የኢትዮጵያ 12ኛ ክፍል ተማሪዎ የአለም አቀፍ ደረጃዎችን ይመጥናሉ ወይ ? የሚለውን ጥያቄ ነው የመለሰው። ላለፉ 30 አመታት ሲተገበር የቆየውን የትምህርት ስርዐት ነው የፈተሸው፣ ሌላ ምንም አላደረገም!! እሱ(ት/ሚኒስትሩ) ለ30 አመት ይቅርና ላለፉት 12 አመታትም (አሁን የወደቁት ተማሪዎች በተማሩበት አመታትም) ት/ርት ሚኒስተር አልነበሩም! እና ሚንስትሩ ጉዳችንን አወጣው ነው ወይስ የትምርት ጥራቱን ጣለው ነው ጥያቄው/ክሱ? He is the last person to blame!
ከዛ በተረፈ ሁሉም ዜጋ ለውድቀቱ ተጠያቂ ነው, 4 ነጥብ!!!

TheManWhoSawTomorrow

Horus
Senior Member+
Posts: 30658
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: እረባክህ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ.........

Post by Horus » 29 Jan 2023, 04:07

የነገሰው፣
በቃ ብርሃኑ ነጋን አታውቀም ማለት ነው። አንድ ነገር ልንገርህ ብርሃኑ ነጋ ት/ሚኒስቴርን ለስልጣንም ለገንዘብም አይፈልገውም። እኔ እንደ ምሰማው ከሆነ ደሞዝ ከመንግስት አይወስድም ነው የሚባለው! ስለሆነም ብርሃኑ አንድን የተበላሸ፣ የተጨማለቀ ነገር ይደባቃል ብለህ የምታስብ ከሆነ ፍጹም አታውቀውም ማለት ነው ። እሱ የኢትዮጵያ ትምህርትን ሌላውም ቆሻሻ በግልጽ ነግሮህ ይሄዳል ይህን አትርሳ!

ብርሃኑ ረታርድድ ያደረገን ሕዝብ አዋቂ ነው ብሎ ላለም የሚዋሽልህ ሰው እንዳልሆነ ላንዴም ለሁሌም ተረዳ !! የተወለደበት ካልቸር ምን እንደ ሆነ ካላወቅህ ዛሬ ያልከውን ትላለህ ! በጉራጌ ካልቸር ፌክ ማድረግ አትችልም! ማንም አይሰማህም! ድሃ ከሆንክ ድሃ ነህ ! ሊስትሮ ከሆንክ ሊስትሮ ነህ፣ ሚሊኒዮር ከሆንክ ሃብታም ነህ! በጉራጌ ካልቸር a spade is called spade! ያንን ነው ፕሮፍ ብሬ እያረገ ያለው! ካልፈለከው የተሻለ አምጣ!

ፕሮፌሰር የኢትዮጵያን ትምህርት ከሞተበት እንዴት እንደ ሚያነሳት መርዳት ሃሳብ መስጠት ማንም ይችላል ! ብርህኑ ነጋን ዉሸታም የማንም ሰልፍ ኤስቲም የሚንከባከብ ባህል ውስጥ አልተወልደም ። በጉራጌ በስራህ ትታወቃለህ! ሰርተህ ትበላለህ! ተፈትነህ ታልፋለህ! ከሌለህ አትለምንም ! ይህን ነው ብርሃኑ እያረገ ያለው!

ብርሃኑ ነጋ የኢትዮጵያን ትምህርት እንዲልደውጥ ከፈለክ ሃሳቡን ትደግፋለህ1 አይ ካልክ አፍንጫህ ላይ ጥሎልህ ይሄዳል! የዚህን ሰው ኢንተገሪቲ የማያውቁ ገና ብዙ ይዘባርቃሉ! ብርሃኑ ነጋ ለዚህ ቆሻሻ ስርዓት ተጠያቅ አይደለም! ይህን ቆሻሻ ስርዓት ሊለውጥ የሚችል ሊቅ ነው! በቃ !!

Y3n3g3s3w
Member
Posts: 531
Joined: 22 Dec 2017, 00:56

Re: እረባክህ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ.........

Post by Y3n3g3s3w » 29 Jan 2023, 11:10

የነገሰው፣

የተወለደበት ካልቸር ምን እንደ ሆነ ካላወቅህ ዛሬ ያልከውን ትላለህ !

እኔ ምንድነው ያልኩት?

ሰው አንዴ እንደሰው ሆኖ ማውራትን ወይም መወያየትን ትቶ በዘር ወይም በጎሳ ቋንቋ / ፖለቲካ
ማውራት ከጀመረ ጦዞ ጦዞ መጨረሻው ወያኔ ወይም ሰሞኑን ተፍተፍ እያሉ እንዳሉት ኦሮሙማዎች ነው! በረግጠኝነት!

Abere
Senior Member
Posts: 10894
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: እረባክህ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ.........

Post by Abere » 29 Jan 2023, 12:16

የአገሪቱን የትምህርት ጥራት ለማረጋገጥ ከተፈለገ የስርዐተ መንግስት ሙሉ ለውጥ ቅድምያ ያስፈልጋል። የጎሳ ፌደረሽን እና ኢ-ህገ መንግስቱ መጀመርያ የግድ መለወጥ አለበት።

በመቀጠል ተማሪዎቹ አለም አቀፍ ደረጃ የጠበቀ ፈተና ወስደው ከወደቁ ይህን ለመቀየር አለም አቀፍ ደረጃ እና ጥራት የጠበቀ መምህራን ሊያስተምራቸው ይገባ። ደንቆሮን ደንቆሮ ከሆነ የሚመራው መቸም አይቀየርም። አለም አቀፍ መመዘኛ እና ደረጃ ያልጠበቀ ኦፈ ሰማያት አስተማሪ በሚቀጥለውም በሌላው ሁሉ ዙርም የሚወድቅ ተማሪ የሚያፈራው። ይህ ማለት አስተማሪዎች ነን የሙሉ ሁሉ ሌላ ስራ መፈለግ አለባቸው። ከዚህ ውጭ ወላጅ እና ተማሪ እንደት አድርገው አሁን ሃላፊነት ይወስዳሉ?ሙሉ በሙሉ የመንግስት ችግር እና ሃላፊነት ነው። በውድቀት ጊዜ ሃላፊነት ማጋራት ለውድቀቱ ችግር እንዳይፈለግ የማድረግ ስራ ነው ወይም እኔ ከደሙ ንጹህ ነኝ ሊል የፈለገ ሴረኛ መንግስት ነው።

Right
Member
Posts: 2727
Joined: 09 Jan 2022, 13:05

Re: እረባክህ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ.........

Post by Right » 29 Jan 2023, 12:37

የአገሪቱን የትምህርት ጥራት ለማረጋገጥ ከተፈለገ የስርዐተ መንግስት ሙሉ ለውጥ ቅድምያ ያስፈልጋል። የጎሳ ፌደረሽን እና ኢ-ህገ መንግስቱ መጀመርያ የግድ መለወጥ አለበት።
Absolutely. Those who are trying to dodge this fact by fabricating a non existent progress are dishonest.

The ethnic system, regardless of who is in charge of the country is one that has to change first. The rest is a con show.

The ethnic based educational system that wasn’t good under the Weyannies can’t be good under the PP regime. Period.

Abere
Senior Member
Posts: 10894
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: እረባክህ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ.........

Post by Abere » 29 Jan 2023, 13:24

አሁን በትምህርት ሚንስቴር የተገለጸው አሃዛዊ መረጃ በሁለት መልኩ መተርጎም ይቻላል።

1ኛ) የብልጽግና ኦነግ መንስግት ከእርሱ በፊት የነበረውን ኢህአድግ ወያኔ ላይ ፕሮፓጋንዳ መስራት። እንደ ተለመደው ደርግ የተሻልኩ ነኝ ለማለት ቀ/ኀ/ሥ የግድ ከአፉ አያወጣቸውም ነበር። ይህ ስራ ደግሞ ተተኪው ተረኛ እርስን ለማዋደድ የሚጠቀሙበት ዘይቤ ነው።

2ኛ) ከተጠቀሰው መረጃ ምንም አድስ ነገር አልተደመጠም። አምና የሞተውን ሰው ለቀበረው ሰው እዘንድሮ ንደ ማርዳት ነው። ስሙን በትክክል የማይጽፍ የ1ኛ እና 2ኛ አመት ዩኒቨርስቲ ተማሪ በሞላበት አገር ምን አድስ ነገር ተገኝቶ ነው የምንደነቀው። It is not a ground breaking finding at all.

3ኛ) ብልጽግና ኦሮሙማ ተረኛ ከሆነ ጊዜ አንስቶ ምን ተጨባጭ ለውጥ አደረገ? ከዚህ ላይ እኔ ዶ/ር ብርሃኑ በግሉ የፈለገው የግል የመርሆ አቋም ይኑረው ለውጥ ሊያመጣ ይችላል በተበላሸ የዘር መንግስት ስርዐት ውስጥ አልጠብቅም። ይህ ማለት ግለሰቦች በጎ አበርክቶ አይኖራቸውም ማለት አይደለ። ለምሳሌ በአገሪቱ የዜግነት ፓለቲካ እና ግልጽነት፥ ተጠያቂነት እና አሳታፊ ሁኔታ ቢኖር ሃላፊዎች ተጽእኖ ያሳርፋሉ -- ግብ እና ተልዕኮ ይኖራቸዋል:: ከዚህ አንጻር ዶ/ር ብርሃኑ ሚና ይኖረው ነበር። አሁን ግን የአብይ አህመድን ወይም ኦሮሙማ ሚና በእርሱ ላይ ነው የተጫነው። በእኔ እምነት ለአሁኒቱ ኢትዮጵያ ግልጽ አበርክቶ የሚኖራቸው ከፓለቲካ ውጭ በግላቸው ለምሳሌ እንደ ሃኪም በመሆን ዜጎችን በቀጥታ የሚረዱ ወይም ሌሎች ባለሙያዎች ናቸው። ከዚያውጭ በኦሮሙማ ቀንበር ስር ወድቆ ምንም ስንዝር መሄድ አይቻልም።

Y3n3g3s3w
Member
Posts: 531
Joined: 22 Dec 2017, 00:56

Re: እረባክህ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ.........

Post by Y3n3g3s3w » 29 Jan 2023, 14:09

Garbage!

የአገሪቱን የትምህርት ጥራት ለማረጋገጥ ከተፈለገ የስርዐተ መንግስት ሙሉ ለውጥ ቅድምያ ያስፈልጋል። የጎሳ ፌደረሽን እና ኢ-ህገ መንግስቱ መጀመርያ የግድ መለወጥ አለበት።
ወደ ወያኔ የአውሬዎች ዘመን እነመለስ ወይስ ሌላ ያሰብካቸው የታክሲ ሹፌሮች DC ላይ አዘጋጅተህልናል?
ወያኔ ፖለቲካ በትምርት ስርዐት ላይ መጫውት ሲጀምረ ነው ትውልድ የመግደሉን ቁልቁለትና የራሱንም ውድቀት አብሮ የጀመረው።
በመቀጠል ተማሪዎቹ አለም አቀፍ ደረጃ የጠበቀ ፈተና ወስደው ከወደቁ ይህን ለመቀየር አለም አቀፍ ደረጃ እና ጥራት የጠበቀ መምህራን ሊያስተምራቸው ይገባ። ደንቆሮን ደንቆሮ ከሆነ የሚመራው መቸም አይቀየርም። አለም አቀፍ መመዘኛ እና ደረጃ ያልጠበቀ ኦፈ ሰማያት አስተማሪ በሚቀጥለውም በሌላው ሁሉ ዙርም የሚወድቅ ተማሪ የሚያፈራው። ይህ ማለት አስተማሪዎች ነን የሙሉ ሁሉ ሌላ ስራ መፈለግ አለባቸው።
ከዩክሬን እንደስንዴ አስተማሪ በርዳታ መልክ እናስገባ? ወይስ ከህንድ ረከስ ይላል ወይስ ከኬንያ?
ከዚህ ውጭ ወላጅ እና ተማሪ እንደት አድርገው አሁን ሃላፊነት ይወስዳሉ?ሙሉ በሙሉ የመንግስት ችግር እና ሃላፊነት ነው። በውድቀት ጊዜ ሃላፊነት ማጋራት ለውድቀቱ ችግር እንዳይፈለግ የማድረግ ስራ ነው ወይም እኔ ከደሙ ንጹህ ነኝ ሊል የፈለገ ሴረኛ መንግስት ነው።
መንግስትማ ችግር አለ lets deal with it እያለህ ነው

ያንተ የተጣመመ የወያኔ ጭንቅላት ግን መፍትሄ ለማፍለቅ አይመችም ፣ለማብጠልጠልና ለመተቸት እንጂ

Horus
Senior Member+
Posts: 30658
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: እረባክህ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ.........

Post by Horus » 29 Jan 2023, 14:57

Folks.
We are having this discussion precisely because Prof. Berhanu was able to show with hard facts the sorry state of Ethiopian education. Now, with regard to its solution, we can all argue about all sorts methods and strategies. But there one scientific reality. That is, a problem, any problem can only be solved at its level of analysis, at its scale of existence. The scale of analysis of a situation or a problem simply means that every reality has its own definition, boundaries, and scale of existence. While all things are related in some way, they are not the same and don't rise and fall all at the same time.

ማለትም የኢትዮጵያ ችግሮች ከመንግስት ስርዓት ጋር የተሳሰሩ ቢሆኑም እያንዳንዱ ችግር የሚፈታው፣ ድልድይ የሚሰራው፣ ስልክ የሚቀጠለው፣ ተማሪ ፈተና የሚያልፈው፣ አስተማሪ የሚሰለጥነው የመንግስት ስርዓት ከተለወጠ ብቻ ነው ማለት የችግሮች እስኬል ሕግ ይስታል። የጎሳ ፖለቲካ ስርዓት አንድ እራሱን የቻለ ፕሮብሌም ሶልቪንግ ነው። አንድ ተማሪ የተሰጠውን እጽሃፍ አጥንቶ ጥያቄዎች መመለስ ሌላ የፕሮቤል እስኬል ነው። አንድ ችግር የሚፈታው ያ ነገር ባለበት ደረጃ ነው ።

ከዚህ በታች ያለው ትላንት ሌላ ሀረግ ላይ የለጠፍኩት አስተያየት ነው !
....
የኢትዮጵያ ትምህርት ውድቀት
የK-12 ትምህርት ፖሊሲ የሚቀረጸውና የሚመራው በጎሳ ክልሎች እስከ ሆነ ድረስ የኢትዮጵያ ትምሀር ስርዓት 100% አይለወጥም የሚለው ትክክለኛ አባባል ነው። ለምሳሌ በዚህ ሳምንት አቢይ ከምሁራን (መምህራን) ጋር ሲወያይ ታዳሚው ሁሉ ይል የነበረው ዩኒቨርሲቲዎች ሁሉ ሁለተኛ ደረጃ ሆነዋል ነው ያሉት ። ልብ በሉ ይህ ዝም ብሎ የቅኔ አነጋገር ሳይሆን ፋክት ነው ። ለምን በሉ?

አሁን በየኮሌጁ ያሉት ብዙ ሺዎችን እንኳን ብንተው ትላንት ት/ሚ የወሰነውን ውሳኔ እንመልከት ። የኢትዮጵያ ኮሌጆች በየአመቱ 130 ሺ ፍሬሽሜን የመቀበል ችሎታ (ወምበሮች) አላቸው ። ከዚህ በፊት 130 ሺ ሁለተኛ ደረጃ ፈተና ማለፍ የማይችል በኩረጃ ፍሬሽማን ይሆን ነበር ። ማለትም ኮሌጆች በስም ያልተጠቀሱ ሃይ እስኩል ነበሩ ። ዛሬ ት/ሚ ያለውን ስሙ ።

30 ሺ ፈተና ያለፉ አንደኛ አመት ኮሌጅ ትምህርት ይጀምራሉ ። 100 ሺ ፈተና የወደቁት የራሳቸው ሃይ እስኩል ውስጥ 12ኛን ከመድገም በየኮሌጁ ተኝተው ግን የሃይ እስኩል ትምህርቶችን በመድገም ተፈትነው ካለፉ በሚቀጥለው አመት ፍሬሽማን ይሆናሉ ። ስለዚህ በፋክት ደረጃ ኮሌጆች ሃይ እስኩል ሆነዋል ናቸው ። ልዩነቱ ቦታና ስማቸው እንጂ ትምህርትና እውቀቱ ሁለተኛ ደረጃ ማለት ነው ።

ስለዚህ የዚህ አመት ፈተና የነገረን ትልቅ ትልቅ እውነት ምንድን ነው? ዛሬ በመላ ኢትዮጵያ የኮሌጅና ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ከሚባሉት ሁሉ ማናልባት 10% እስከ 20% ቢሆኑ እንጂ 80% የሃይ እስኩል ደረጃ እውቀት ውስጥ ያሉ ናቸው ። ይህን ስል ከ1ኛ እስከ 5ኛ አመት ያሉትን የኮሌጅ ተማሪዎችን ደምሬ ነው ።

ኖብል አማራ ያነሳሃው ጥያቄ መልስ ያለው እዚህ ላይ ነው ። የኢትዮጵያ ትምህርት በሻሻል የሚጀምረው ቢያንስ ከአምስት አመት በኋላ ነው ። ይህም ማለት አሁን ያሉት በሙሉ አወቁም አላወቁ ተመርቀው ከይኒቨርሲቲዎች ይጸዳሉ በ5 አመት ውስጥ። ከሚቀጥለው አመት ጀምሮ ፈተና ያላለፈ አንድ ተማሪ ዩኒቨርሲቲ አይገባም ። ይህም ማለት ለምሳሌ በኔ ግምት በ2024 ከ50 ሺ ወይም 60 ሺ በላይ ፍሬሽማን የሚሆኑ አይመስለኝም ።

አሁን ይህ ሁሉ ክፍልና መቀመጫ ዴስኮች እና የኮሌጅ ተብዬ አስተማሪዎች ምን ይሆናሉ ? የሚለው ትልቅ ትልቅ ጥያቄ ነው ። በዚህም ምክንያት የጎሳ የክልል ፖለቲከኞች የትምህርቱን ሪፎርም፣ የብርህኑን ሃሳብ ጥለው ወይም እሱንም አንስተውት ወደ ድሮ የኩረጃ ሲስተም ሊመለሱ ይችላሉ ። ነገር ግ ን አሁን በርሃኑ ነጋ የጀመረውን ማጽዳት መንግስት ከደገፈው በ5 አመት ውስጥ በቁጥር ጥቂት የሆኑ እውነተኛ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና እውነተኛ ኮሌጆች ይኖሩናል ።

ዛሬ ላይ ግን አለ ምንም ጥርጥር ዩኒቨርሲቲዎች ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ናቸው ። ምናልባት ከ20% ተማሪና አስተማሪዎች በስተቀር! ይህ ሃቅ ነው! ሌላ ቦታ እንዳልኩት ዛሬ የሃይ እስኩል አስተማሪዎች ለማትሪክ ፈተና ቢቀመጡ 90% ይወድቃሉ ። የዩኒቨርሲቲ አስተማሪዎች የሚያስተምሩትን ሳብጀክት ተፈትነው 83% ወድቀዋል ። ማለትም የዩኒቨርሲቲ አስተማሪዎች ሁሉ መለወጥ ወይም እንደ ገና መማር አለባቸው ።

ልብ እንበል በዛሬ ቀን ኢትዮጵያ 31 ሚሊዮን ተማሪዎች አሏት ። ይህን ያክል የገዘፈ 25% ያገሪቱ ሕዝብ ነው እንዲህ ወድቆ ያለው ። ይህቺ አገር ከዚህ በላይ ችግር የለባትም ። እጅግ እጅግ ያሳዝናል ፣ ታሳፍራል ።

Horus
Senior Member+
Posts: 30658
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: እረባክህ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ.........

Post by Horus » 29 Jan 2023, 15:09

TesfaNews
Member+
Posts: 6699
Joined: 14 Feb 2020, 22:23
Location: Ras Mesobawian

Re: እረባክህ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ.........

Post by TesfaNews » 29 Jan 2023, 15:17

wey medhane alem!

Birhanu Nega betam tiru neger sera le univiersity temarioch.. Ahun 3.3% ashenifu nega 3.4% yashenifalu.. Birhanu le Ethiopia birhan eyewesidat new! Yebo ebo, sodo soduma

Horus
Senior Member+
Posts: 30658
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: እረባክህ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ.........

Post by Horus » 29 Jan 2023, 15:36

Abere
Senior Member
Posts: 10894
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: እረባክህ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ.........

Post by Abere » 29 Jan 2023, 15:48

ፉዞ ኦሮሙማ:-

---መጀመርያ በወያኔ እና በኦነግ ኦሮሙማ ምን አይነት የይዘት ለውጥ አለ? ይህን ሳትለይ ወደ ወያኔ ዘመን ስለመመስ ታወራለህ። እስኪ ብልጽግና ኦሮሙማ ከወያኔ የተሻለ የሰራቸው ወይም ያጨማለቃቸው ካሉ እነርሱን እያነሳህ አስረዳን። አንተ እራስህ የቀድሞ የዲስ ታክሲ ነጅ (ex-DC cab driver) የአሁኑ ውታፍ ነቃይ ኦሮሙማ ነህ። ደግሞ የዲሲ ታክሲ መሰለኝ የደገፋችሁ አሁን ጥሉን ምን አመጣው::በመሰረቱ ስራ ክቡር ነው አገር እና ህዝብ መዝረፍ ነው ትልቁ ውርደት። ታከለ ኡማ እንደት እንደተሸማቀቀ ያየህ መሰለኝ። አንገትህን ቀና አድርገህ የምሄደው ቀጥተኛ የእውነት ሰው ስትሆን ነው። ውታፈ ከነቀልክ በየሂድክበት እንደ ውሻ ትንከሳከሳለህ። ለእውነት ቁም።

---ከዩክሬን ስንደ ካማስገባት የተሻለ ሞደል አስተማሪዎች ማግኘት አይሻልም ትላለህ። ስንደው የኦሮሙማ አህያ በልታ ፍግ ታደርገዋለች ፤ትምህርት ግን ወደ እውቀት ይመነዘራል። ደግሞ ከውጭ ይግባ አላልኩኝም። በዘመነ-ወያኔ እና ኦሮሙማ የተመረተ ደንቆሮ አስተማሪ ፤ አልጀብራ ሳይችል ካልኩለስ እንድያስተምር የተመደበ፤ የጎሳ ፓለቲካ ተምሮ አለም አቀፍ ግንኙነት እንድያስተምር ወይም እንግሊዘኛ መጻፍ የማይችል እንግሊዘኛ አስተማሪ እንድያስተምር የተመደበ እንደት አድርጎ ነው ትውልድ የሚቀይረው። መጀመርያ እራሱ መማር አለበት። ትምህርቱ ወድሟል እንዳለ። አስተማሪው ነው የወደመው።

---መንግስት ችግር አለ እንወጣው ካለ ዋናው ችግር የትምህርት ስርዐቱ ነው ይህ ደግሞ ከአገሪቱ ህገ-መንግስት ይመነጫል። የአሳ ግማቱ ከጭንቅላቱ እንድሉ።እራሱ ያመጣው ችግር ነው። ህዝብ ሃላፊነት አይወስድም ለእራሱ ጥፋት። ሌላው ሁል ጊዜ ህዝብ ስለወያኔን እያወራ ኦሮሙማ ሸጋ እንደሆነ ለማሳየት የሚደረግ ጥረት ነው። መቸ ነው ጥሩ ለመስራት እጅጌውን ሰብስቦ ኦሮሙማ ወደ ተግባር የሚገባው -4 አመታት አለፉ? ስለ ጥንቱ እንድ ወራ ስለ አሁኑ እንድረሳ በማድረግ ችግሩን መደበቅ አይችልም ኦሮሙማ።

Y3n3g3s3w wrote:
29 Jan 2023, 14:09
Garbage!

ወደ ወያኔ የአውሬዎች ዘመን እነመለስ ወይስ ሌላ ያሰብካቸው የታክሲ ሹፌሮች DC ላይ አዘጋጅተህልናል?
ወያኔ ፖለቲካ በትምርት ስርዐት ላይ መጫውት ሲጀምረ ነው ትውልድ የመግደሉን ቁልቁለትና የራሱንም ውድቀት አብሮ የጀመረው።
በመቀጠል ተማሪዎቹ አለም አቀፍ ደረጃ የጠበቀ ፈተና ወስደው ከወደቁ ይህን ለመቀየር አለም አቀፍ ደረጃ እና ጥራት የጠበቀ መምህራን ሊያስተምራቸው ይገባ። ደንቆሮን ደንቆሮ ከሆነ የሚመራው መቸም አይቀየርም። አለም አቀፍ መመዘኛ እና ደረጃ ያልጠበቀ ኦፈ ሰማያት አስተማሪ በሚቀጥለውም በሌላው ሁሉ ዙርም የሚወድቅ ተማሪ የሚያፈራው። ይህ ማለት አስተማሪዎች ነን የሙሉ ሁሉ ሌላ ስራ መፈለግ አለባቸው።
ከዩክሬን እንደስንዴ አስተማሪ በርዳታ መልክ እናስገባ? ወይስ ከህንድ ረከስ ይላል ወይስ ከኬንያ?
ከዚህ ውጭ ወላጅ እና ተማሪ እንደት አድርገው አሁን ሃላፊነት ይወስዳሉ?ሙሉ በሙሉ የመንግስት ችግር እና ሃላፊነት ነው። በውድቀት ጊዜ ሃላፊነት ማጋራት ለውድቀቱ ችግር እንዳይፈለግ የማድረግ ስራ ነው ወይም እኔ ከደሙ ንጹህ ነኝ ሊል የፈለገ ሴረኛ መንግስት ነው።
መንግስትማ ችግር አለ lets deal with it እያለህ ነው

ያንተ የተጣመመ የወያኔ ጭንቅላት ግን መፍትሄ ለማፍለቅ አይመችም ፣ለማብጠልጠልና ለመተቸት እንጂ

Horus
Senior Member+
Posts: 30658
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: እረባክህ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ.........

Post by Horus » 29 Jan 2023, 16:06

TGAA
Member+
Posts: 5598
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

Re: እረባክህ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ.........

Post by TGAA » 29 Jan 2023, 16:16

አንድ ነገር ማወቅ ያለባችሁ እስከዛሬ የተመረቁት ደንቆሮዎች ዛሬ የብልጽግና አባል ሆነው በዘር ፖለቲካ / በእውቀታቸው ሳይሆን አግኝተው የማያቁትን የእንድልቅ ኑሮ እየኖሩ ነው ፤ ብልጽግና አንድ ሚሊዮን አባል ሲመለምል ከነዚሁ እውቀት የሌላቸው ፤ በእውቀታቸው ሰርተው መኖር በማይችሉ ፤ ግን ለመንግስት በጥቅማቸው ተገዝተው የሚሰሩ ቅጥረኞች ናቸው ፤ መንግስትም ካለነርሱ መኖር አይችልም እነሱም መንግሱት ከሌለ ስርተው መኖር አይችሉም ፡፡ የብርሀኑ በጭድ የተገነባ ትምርት ሲስተሙን ሲያጋልንጥ ለዚህ ነው ከአፍንጫቸው እርቆ ማየት የማይችል ሁሉ ተነስቶ ጎድ ፈላ ብሎ የሚጮህው ፡ በእርግጥ ይህንን እርማት ለማድረግ soft landing ያስፈልጋል ፤ መሸጋገርያ የሆኑ ደጋፊ ስራዎችም መሰራት አለባቸው ፤ ብርሀኑ እርቃኑንን ያስቀረው የትምህርት ሲስተም የሚረዳው ነገር ቢኖር በሽታው ምን ያህል ጥልቅ መሆኑን ማሳየቱ ላይ ነው ፤ ያንን ለማድረግ ደግሞ ብርሀኑን መሆን አያስፍልግም ማንኛውም ለሀገሩ የሚያስብ ኢትዮጵያዊ የሚያደርገው ተግባር ነው፡፡ ብርሀኑ በሰራው የመጀመሪያ ስራ ግን ጥሩ ጀማሬ ነው ብሎ ማበረታታት ያስፈልጋል፡፡፡

Right
Member
Posts: 2727
Joined: 09 Jan 2022, 13:05

Re: እረባክህ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ.........

Post by Right » 29 Jan 2023, 16:36

ብርሀኑ እርቃኑንን ያስቀረው የትምህርት ሲስተም የሚረዳው ነገር ቢኖር በሽታው ምን ያህል ጥልቅ መሆኑን ማሳየቱ ላይ ነው

We know the system is empty long before BERHANU went to Eritrea to “fight”the system. The rotten system exposes itself every where in any direction you look. We don’t need a fat pig to tell us what we already know. You better come up with a better Defense.

Before calling others for “not seeing further than their noses”, you have to look in the mirror.

All this nonsense is to justify BERHANU Nega’s service to Abiye Ahmed. The pig is trapped and no matter what you do to rescue him, he will not be saved. He will live and die with Oromuma.

Assegid S.
Member
Posts: 936
Joined: 11 Aug 2013, 07:11
Contact:

Re: እረባክህ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ.........

Post by Assegid S. » 29 Jan 2023, 16:41

ከፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አቋም ጋር የማልስማማባቸው ብዙ አመለካከቶች አሉ በተለይም ፖለቲካዊ እንቅስቃሴያቸውን በተመለከተ። ነገር ግን እንደ ትምህርት ሚንስትርነታቸው … አሁን እየወሰዱ ባሉት እርምጃዎች ምክንያት ለተፈጠረው ውድቀት (ሀገራዊ ክስረት) እሳቸውን ተጠያቂ የሚያደርግ ግለሰብም ሆነ ድርጅታዊ አካል ካለ የለየለት መሐይም ነው። ሚንስትሩ መጠየቅ ካለባቸውም “በስተመጨረሻ ነው መጠየቅ ያለባቸው” ከሚለው ሓሳብም ጋር በፍፁም አልስማማም፤ ሰው ሞያዊ ሃላፊነቱን በመወጣት ሂደት ላከናወነው ተገቢ ሥራ በፍፁም ሊጠየቅ አይገባም። ስለዚህም ፕሮፌሰሩን በስተመጨረሻም ቢሆን የሚያስጠይቃቸው ምንም በቂ ምክንያት አላየሁም። ችግሩን ከስር … ከ elementary school ጀምሮ … ለመቅረፍ 8 እና 10 ዓመታት መጠበቅ ነበረባቸው … እስከዛ ደንቆሮና ቆርቆሮ እያመረቱ ብለን ካላበድን በስተቀር።

ከዚህም አልፎ “ሁሉም ዜጋ ለውድቀቱ ተጠያቂ ነው” ከሚለው አባባልም ጋር አልስማማም። ምክንያቱም ለዚህ ተቋማዊ ብሎም ሀገራዊ fiasco ግንባር ቀደም ተጠያቂ መሆን የሚገባቸው ወይዘሮ ገነት ዘውዴ እና ህወሃት ... ያኔ የኢትዮዽያን ትምህርት ደረጃ ኣንድ በኣንድ ካቡን መናድ ሲጀምሩ ብዙ ምሁራንና ዜጎች ተቃውሞ ያሰሙ ስለነበር። በእኔ እምነት … መጠየቅ ካለበት የስርዓቱ ዘዋሪ የነበረው ህወሃትና ግብረ አበሮቹ (ደጋፊዎቹ) ብቻ ናቸው

ሁላችንም እንደምናውቀው ትምህርት (በተለይም የከፍተኛ ደረጃ ትምህርት) ይዘት ሁሉም ሀገራት ማሟላት የሚጠበቅባቸው ዓለማቀፋዊ ደረጃ አለው። ። ለዛም ነው ዓለምን ታሳቢ ባደረገ መልኩ የዩኒቨርሲቲዎች ደርጃ በየዓመቱ የሚመዘነው። ፕሮፌሰር ብርሃኑም ይህን ደረጃ ታሳቢ ያደረገ ፈተና ማቅረብ ግዴታው ነው። ነገ የትኛው ተማሪ ነው ሀገሪቷ ማቅረብ በማትችለው የትምህርት መስክ ለበለጠ ስልጠና ወደ አውሮፓና ሰሜን-አሜሪካ ብሎም ወደ ተሻለ ሀገር scholarship አግኝቶ የሚሄደው? የሚለውንም መጠየቅ ያስፈልጋል።

በኣንድ ወቅት ... ጊዜውንና የሰውየውን ስም ኣሁን ለማስታወስ ብቸገርም ... አንድ የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ (ነፍስ ይማር) ዘመን ምሁር በቃለ-መጠይቃቸው ላይ ሲናገሩ "ለ scholarship አሜሪካን ሀገር ስንሔድ ሌሎች ተማሪዎች ሁሉ የመግቢያ ፈተና እንዲወስዱ ሲገደዱ እኛ ግን ከኢትዮዽያ የምንሄድ ተማሪዎች ያለ entrance exam ነበር በቀጥታ ትምህርት የምንጀምረው" ማለታቸውን አስታውሳለሁ። አሁን ላይ ግን scholarship የሚያገኙ ተማሪዎች በሚሄዱበት ዩኒቨርሲቲ በደስታ የሚቀበላቸው research advisor እንኳ በቀላሉ የሚያገኙ አይመስለኝም።

በመጨረሻ … እኔ ይህን አጋጣሚ እንደ ጥሩ እድል ነው የማየው። ወደ ዩኒቨርሲቲ ያለፉትን ተማሪዎች በጣም በጥንቃቄ በተመረጡና በተሻሉ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ መዝግቦ፥ የተቀረውን 90 ፐርሰንት የሚሆነውን ዩኒቨርሲቲ መሳይ ህንፃ ወይ መዝጋት ነው ወይ ወደ እጅ-ጥበባት ማዕከል መቀየር ነው። በዛ የነበረው አስተማሪ መሳይና staff የት እናድርገው? ከተባለም መንግስት ለዛ የሚመድበውን ካፒታልና ፋይናንስ ታሳቢ አድርጎ ብዙ አማራጮችን መውሰድ ይችላል … as I have already written more than enough to discuss the matter in detail.

Horus
Senior Member+
Posts: 30658
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: እረባክህ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ.........

Post by Horus » 29 Jan 2023, 16:49

Right wrote:
29 Jan 2023, 16:36
ብርሀኑ እርቃኑንን ያስቀረው የትምህርት ሲስተም የሚረዳው ነገር ቢኖር በሽታው ምን ያህል ጥልቅ መሆኑን ማሳየቱ ላይ ነው

We know the system is empty long before BERHANU went to Eritrea to “fight”the system. The rotten system exposes itself every where in any direction you look. We don’t need a fat pig to tell us what we already know. You better come up with a better Defense.

Before calling others for “not seeing further than their noses”, you have to look in the mirror.

All this nonsense is to justify BERHANU Nega’s service to Abiye Ahmed. The pig is trapped and no matter what you do to rescue him, he will not be saved. He will live and die with Oromuma.
ብርሃኑ ነጋ ያንተ በሽታ፣ ያንተ እንቅልፍ ነሺ አስጨናቂ እንደ ሆነ ሺ ግዜ ደጋግመህ ተናግረሃል!!! ትልቁ እጅግ ትልቁ ችግርህ ምን መሰለህ? ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ምን ያህል እውቀት እንዳለው፣ ምን ያህል ኢትዮጵያዊ እንደ ሚያክብረው፣ ምን ያህል ኢትዮጵያዊ ሃሳቡን እንደ ሚደግፍ፣ ምን ያህል ኢትዮጵያዊ እንደ ሚወደው አለማወቅህ ነው ያንተ ችግር!!! የኢትዮጵያ ወላጆች ዛሬ እሱ የሚያደርገውን በእልልታ ተቀብለው እየደገፉት!! የብርሃኑ ባቡር ይገሰግሳል! አንተ ካመት አመት ታላዝናለህ! Leave him alone & get a life, dude!

Horus
Senior Member+
Posts: 30658
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: እረባክህ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ.........

Post by Horus » 29 Jan 2023, 17:03

Assegid S. wrote:
29 Jan 2023, 16:41
ከፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አቋም ጋር የማልስማማባቸው ብዙ አመለካከቶች አሉ በተለይም ፖለቲካዊ እንቅስቃሴያቸውን በተመለከተ። ነገር ግን እንደ ትምህርት ሚንስትርነታቸው … አሁን እየወሰዱ ባሉት እርምጃዎች ምክንያት ለተፈጠረው ውድቀት (ሀገራዊ ክስረት) እሳቸውን ተጠያቂ የሚያደርግ ግለሰብም ሆነ ድርጅታዊ አካል ካለ የለየለት መሐይም ነው። ሚንስትሩ መጠየቅ ካለባቸውም “በስተመጨረሻ ነው መጠየቅ ያለባቸው” ከሚለው ሓሳብም ጋር በፍፁም አልስማማም፤ ሰው ሞያዊ ሃላፊነቱን በመወጣት ሂደት ላከናወነው ተገቢ ሥራ በፍፁም ሊጠየቅ አይገባም። ስለዚህም ፕሮፌሰሩን በስተመጨረሻም ቢሆን የሚያስጠይቃቸው ምንም በቂ ምክንያት አላየሁም። ችግሩን ከስር … ከ elementary school ጀምሮ … ለመቅረፍ 8 እና 10 ዓመታት መጠበቅ ነበረባቸው … እስከዛ ደንቆሮና ቆርቆሮ እያመረቱ ብለን ካላበድን በስተቀር።

ከዚህም አልፎ “ሁሉም ዜጋ ለውድቀቱ ተጠያቂ ነው” ከሚለው አባባልም ጋር አልስማማም። ምክንያቱም ለዚህ ተቋማዊ ብሎም ሀገራዊ fiasco ግንባር ቀደም ተጠያቂ መሆን የሚገባቸው ወይዘሮ ገነት ዘውዴ እና ህወሃት ... ያኔ የኢትዮዽያን ትምህርት ደረጃ ኣንድ በኣንድ ካቡን መናድ ሲጀምሩ ብዙ ምሁራንና ዜጎች ተቃውሞ ያሰሙ ስለነበር። በእኔ እምነት … መጠየቅ ካለበት የስርዓቱ ዘዋሪ የነበረው ህወሃትና ግብረ አበሮቹ (ደጋፊዎቹ) ብቻ ናቸው

ሁላችንም እንደምናውቀው ትምህርት (በተለይም የከፍተኛ ደረጃ ትምህርት) ይዘት ሁሉም ሀገራት ማሟላት የሚጠበቅባቸው ዓለማቀፋዊ ደረጃ አለው። ። ለዛም ነው ዓለምን ታሳቢ ባደረገ መልኩ የዩኒቨርሲቲዎች ደርጃ በየዓመቱ የሚመዘነው። ፕሮፌሰር ብርሃኑም ይህን ደረጃ ታሳቢ ያደረገ ፈተና ማቅረብ ግዴታው ነው። ነገ የትኛው ተማሪ ነው ሀገሪቷ ማቅረብ በማትችለው የትምህርት መስክ ለበለጠ ስልጠና ወደ አውሮፓና ሰሜን-አሜሪካ ብሎም ወደ ተሻለ ሀገር scholarship አግኝቶ የሚሄደው? የሚለውንም መጠየቅ ያስፈልጋል።

በኣንድ ወቅት ... ጊዜውንና የሰውየውን ስም ኣሁን ለማስታወስ ብቸገርም ... አንድ የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ (ነፍስ ይማር) ዘመን ምሁር በቃለ-መጠይቃቸው ላይ ሲናገሩ "ለ scholarship አሜሪካን ሀገር ስንሔድ ሌሎች ተማሪዎች ሁሉ የመግቢያ ፈተና እንዲወስዱ ሲገደዱ እኛ ግን ከኢትዮዽያ የምንሄድ ተማሪዎች ያለ entrance exam ነበር በቀጥታ ትምህርት የምንጀምረው" ማለታቸውን አስታውሳለሁ። አሁን ላይ ግን scholarship የሚያገኙ ተማሪዎች በሚሄዱበት ዩኒቨርሲቲ በደስታ የሚቀበላቸው research advisor እንኳ በቀላሉ የሚያገኙ አይመስለኝም።

በመጨረሻ … እኔ ይህን አጋጣሚ እንደ ጥሩ እድል ነው የማየው። ወደ ዩኒቨርሲቲ ያለፉትን ተማሪዎች በጣም በጥንቃቄ በተመረጡና በተሻሉ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ መዝግቦ፥ የተቀረውን 90 ፐርሰንት የሚሆነውን ዩኒቨርሲቲ መሳይ ህንፃ ወይ መዝጋት ነው ወይ ወደ እጅ-ጥበባት ማዕከል መቀየር ነው። በዛ የነበረው አስተማሪ መሳይና staff የት እናድርገው? ከተባለም መንግስት ለዛ የሚመድበውን ካፒታልና ፋይናንስ ታሳቢ አድርጎ ብዙ አማራጮችን መውሰድ ይችላል … as I have already written more than enough to discuss the matter in detail.
Amen! በጣም ትክክል፤ ከዛሬ ስንት ቀን በፊት አክሱምዜና ለሚባል ሰው ያልኩት ይህን ነው! ለዚህ አሳፋሪ የኢትዮጵያ ውድቀት ቁጥር አንድ ተጠያቂ ወያኔ ነው፤ ለ27 አመት ያፈረሰው ተቋም ነው ዛሬ ለብርሃኑ የተሰጠው! ትልቁ ቁም ነገር ዛሬ ስልጣን ላይ የወጡት ኦሮሞች ይህ ቆሻሻ ሲስተም እንዲለወጥ ይፈልጋሉ ወይም ሕዝባቸውን በማዶቆር ይቀጥላሉ የሚለው ነው ።

ደሞ በጣም እጅግ በጣም የምስማማበት ነጥብ አቢይ አህመድ ብልጽግና 10 ሚሊዮን አባላት አሉት እያለ በክብር መናገር ማቆም አለበት ። ብልጽግና ማለት ማትሪክ ያላለፉ፣ የማያልፉ መሃይሞች መታጎሪያ የፖለቲካ መዥገሮች ፓራሳቶች ክምችት ነው ።

Y3n3g3s3w
Member
Posts: 531
Joined: 22 Dec 2017, 00:56

Re: እረባክህ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ.........

Post by Y3n3g3s3w » 29 Jan 2023, 17:28

Assegid S.,

ጥሩ ብለሀል እኔም ሁሉም ዜጋ ተጠያቂ ነው ስል በስሱ ነው። እንዳልከው ነው። እንደው ሙት ወቃሽ ላለመሆን ነበር ፣ ለዚህ ሁል ክስረት ተጠያቂው ወያኔና ወያኔ ብቻ እንደሆነ ጠፍቶኝ አደለም።

ነገርን ነገር ያነሳዋል ፣ ግን ወያኔ ሞቷል እንዴ? እንደኔ ያልጋ ቁራኛ ሆነ እንጅ አልሞተም። ለአብይ መንግስትመ ትልቁ ፈተናው ወያኔ ሞቶም እንኳን ካልተቀበረ አምኖ ቁጭ ካለ ፣ ይባስ ደሞ አብሬ ሰራለሁ ካለ ለራሱ (ለአብይ እንደ ግለሰብና መንግስት ) ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያም ጠላት እያደለበልን እንደሆነ መገንዘብ አለበት፤ ወደ ኦሮሙማው አሁን አንገባም! እነሱም ተፍተፍ እያሉለት ነው....

TheManWhoSawTomorrow

Assegid S. wrote:
29 Jan 2023, 16:41
ከፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አቋም ጋር የማልስማማባቸው ብዙ አመለካከቶች አሉ በተለይም ፖለቲካዊ እንቅስቃሴያቸውን በተመለከተ። ነገር ግን እንደ ትምህርት ሚንስትርነታቸው … አሁን እየወሰዱ ባሉት እርምጃዎች ምክንያት ለተፈጠረው ውድቀት (ሀገራዊ ክስረት) እሳቸውን ተጠያቂ የሚያደርግ ግለሰብም ሆነ ድርጅታዊ አካል ካለ የለየለት መሐይም ነው። ሚንስትሩ መጠየቅ ካለባቸውም “በስተመጨረሻ ነው መጠየቅ ያለባቸው” ከሚለው ሓሳብም ጋር በፍፁም አልስማማም፤ ሰው ሞያዊ ሃላፊነቱን በመወጣት ሂደት ላከናወነው ተገቢ ሥራ በፍፁም ሊጠየቅ አይገባም። ስለዚህም ፕሮፌሰሩን በስተመጨረሻም ቢሆን የሚያስጠይቃቸው ምንም በቂ ምክንያት አላየሁም። ችግሩን ከስር … ከ elementary school ጀምሮ … ለመቅረፍ 8 እና 10 ዓመታት መጠበቅ ነበረባቸው … እስከዛ ደንቆሮና ቆርቆሮ እያመረቱ ብለን ካላበድን በስተቀር።

ከዚህም አልፎ “ሁሉም ዜጋ ለውድቀቱ ተጠያቂ ነው” ከሚለው አባባልም ጋር አልስማማም። ምክንያቱም ለዚህ ተቋማዊ ብሎም ሀገራዊ fiasco ግንባር ቀደም ተጠያቂ መሆን የሚገባቸው ወይዘሮ ገነት ዘውዴ እና ህወሃት ... ያኔ የኢትዮዽያን ትምህርት ደረጃ ኣንድ በኣንድ ካቡን መናድ ሲጀምሩ ብዙ ምሁራንና ዜጎች ተቃውሞ ያሰሙ ስለነበር። በእኔ እምነት … መጠየቅ ካለበት የስርዓቱ ዘዋሪ የነበረው ህወሃትና ግብረ አበሮቹ (ደጋፊዎቹ) ብቻ ናቸው

ሁላችንም እንደምናውቀው ትምህርት (በተለይም የከፍተኛ ደረጃ ትምህርት) ይዘት ሁሉም ሀገራት ማሟላት የሚጠበቅባቸው ዓለማቀፋዊ ደረጃ አለው። ። ለዛም ነው ዓለምን ታሳቢ ባደረገ መልኩ የዩኒቨርሲቲዎች ደርጃ በየዓመቱ የሚመዘነው። ፕሮፌሰር ብርሃኑም ይህን ደረጃ ታሳቢ ያደረገ ፈተና ማቅረብ ግዴታው ነው። ነገ የትኛው ተማሪ ነው ሀገሪቷ ማቅረብ በማትችለው የትምህርት መስክ ለበለጠ ስልጠና ወደ አውሮፓና ሰሜን-አሜሪካ ብሎም ወደ ተሻለ ሀገር scholarship አግኝቶ የሚሄደው? የሚለውንም መጠየቅ ያስፈልጋል።

በኣንድ ወቅት ... ጊዜውንና የሰውየውን ስም ኣሁን ለማስታወስ ብቸገርም ... አንድ የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ (ነፍስ ይማር) ዘመን ምሁር በቃለ-መጠይቃቸው ላይ ሲናገሩ "ለ scholarship አሜሪካን ሀገር ስንሔድ ሌሎች ተማሪዎች ሁሉ የመግቢያ ፈተና እንዲወስዱ ሲገደዱ እኛ ግን ከኢትዮዽያ የምንሄድ ተማሪዎች ያለ entrance exam ነበር በቀጥታ ትምህርት የምንጀምረው" ማለታቸውን አስታውሳለሁ። አሁን ላይ ግን scholarship የሚያገኙ ተማሪዎች በሚሄዱበት ዩኒቨርሲቲ በደስታ የሚቀበላቸው research advisor እንኳ በቀላሉ የሚያገኙ አይመስለኝም።

በመጨረሻ … እኔ ይህን አጋጣሚ እንደ ጥሩ እድል ነው የማየው። ወደ ዩኒቨርሲቲ ያለፉትን ተማሪዎች በጣም በጥንቃቄ በተመረጡና በተሻሉ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ መዝግቦ፥ የተቀረውን 90 ፐርሰንት የሚሆነውን ዩኒቨርሲቲ መሳይ ህንፃ ወይ መዝጋት ነው ወይ ወደ እጅ-ጥበባት ማዕከል መቀየር ነው። በዛ የነበረው አስተማሪ መሳይና staff የት እናድርገው? ከተባለም መንግስት ለዛ የሚመድበውን ካፒታልና ፋይናንስ ታሳቢ አድርጎ ብዙ አማራጮችን መውሰድ ይችላል … as I have already written more than enough to discuss the matter in detail.

TGAA
Member+
Posts: 5598
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

Re: እረባክህ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ.........

Post by TGAA » 29 Jan 2023, 17:47

You can have all the symptoms of Covid, but until you get tested, you wouldn't have a clue about the severity of the disease, or whether you will die from it. I'm talking mainly about the educational system of Ethiopia, not Brhanu's role in defending Abiy's rotten tribal system. I previously said I detest it. The meteoric educational system by its nature is anti-tribalist and any movement in that direction needs to be supported. Any action that is weakening the pillars of the tribal system is a good thing by any measure. It has taken 33 years to build, an action that is going chipping away from this rotten tribal edifice, In my opinion, is a good thing.

Post Reply