Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum

Selam/
Senior Member
Posts: 11549
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: የጂማ ኦርቶዶክስ ሕዝብ መከራ! የአቢይ መንግስት ሕዝቡን ለሃይማኖት ጦርነት እያነሳሳ ነው!!

Post by Selam/ » 28 Jan 2023, 14:49

የኦሮሙማ ካድሬዎች ወደማያልቅ መቀመቅ የሚወስዳቸውን ጉድጓድ ለራሳቸው እየቆፈሩ ነው። ሃይማኖትን በዘር ከፋፍለው፣ ኦርቶዶክስን ለማጥፋት ወይንም ለመዋጥ የሚያደርጉት መፍጨርጨር ራሳቸውን ያጠፋቸዋል። ሰው ለሃይማኖቱ ብዙ ነገር ከማድረግ እንደማይመለስ አልገባቸውም።

Abere
Senior Member
Posts: 10894
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: የጂማ ኦርቶዶክስ ሕዝብ መከራ! የአቢይ መንግስት ሕዝቡን ለሃይማኖት ጦርነት እያነሳሳ ነው!!

Post by Abere » 28 Jan 2023, 15:40

ጅማ ለምን? የአበይ አህመድ አሊ መነሻ ነጥብ በሻሻ ስለሆነ፥ በኩር መዋቅራዊ ኦሮሙማ ድጋፍ ለማሳየት ይሆናል። ትልቁ እና ግልጽ የሆነው ጉዳይ ግን መፈንቅለ-ሲኖዶሱ በአብይ አህመድ ትዕዛዝ እና ዕቅድ የሚከናወን መሆኑን ነው። ከዚህ በላይ ማስረጃ የለም። ይህ እንግድህ እንደ ኦሮሙማ አካሄድ ነው - ወታደር እና መዋቅር በመጠቀም በግድ ለማስፈጸም መሞከር።

ለኦሮሙማ ፈተና የሚሆነው ትግሉን ከምዕምኑ ውስጥ ማስገባቱ ነው። ከሚልዮን ምዕምን ጋር በጦር መሳርያ መግጠም አይችልም -ማሸነፍም አይችልም።

Horus
Senior Member+
Posts: 30658
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የጂማ ኦርቶዶክስ ሕዝብ መከራ! የአቢይ መንግስት ሕዝቡን ለሃይማኖት ጦርነት እያነሳሳ ነው!!

Post by Horus » 28 Jan 2023, 18:04

ኢትዮጵያ ሁልግዜም ምስጢረኛ አገር ነች! የኦሮሙማ ኩሽ ስርወ መንግስት (ካባይ በላይ አቢሲኒያ፣ ካባይ በታች ታላቋ ኦሮሙማ) አቀንቃኞች ወደፊት እጅግ የሚያሳፍራቸው ነገር እንደሚነሳ ገና አልገባቸውም። በኦሮሞ ሕዝብ ውስጥ እጅግ ብዙ ጠንካራ ኦርቶዶክሶች አሉ ። አሁን ያሴሩበት ሃሮ በአለወልድ ታሪካዊዋ አዳዲ ማሪያም ያለችበት አገር ነው ። ከግራኝ ቃጠሎና ዘረፋ ለመጠበቅ አያቶቻችን ዋሻ ቆፍረው ያቆዩት ታቦት! 1460 ዓም በግብጻዊው ሞኖክሴ ቅዱስ አቦ (አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ) ከዝቋላ አቦ፣ ከምድረ ከብድ አቦ ጋር የቆመች ። ባለወልድ ገዳማትም እንዲሁ ፣ ለምሳሌ ቆንዳልቲቲ በአለወልድ ገዳም ። ስለዚህ እነሺመልስ አብዲሳ ገና ገና ብዙ ፈተና ከፊታቸው አለው።

ኦርቶዶክስ ኦሮሞ ብቻ አይደለም፣ በኢትዮጵያዊነታቸው የጸኑ ሙስሊምና ፕሮቴስታንት ኦሮሞች ብዙ ብዙ ሚሊዮኖች ናቸው ። ስለዚህ ልክ ትህነግ ትግሬን ገፍቶ ገፍቶ የመከራና የጦርነት መናሃሪያ እንዳደረጋት ኦሮሙሚስቶችም የኦሮሞን ምስኪን ሕዝብ ወደዚያ መከራ እየወሰዱት ነው። ተከታተሉ!

Post Reply