Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
TGAA
Member+
Posts: 5598
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

“ቤተ እምነቶችህን ያስደፈረው ያንተው ዝምታ ነው!” ከኢትዮጵያ ሙስሊሞች ንቅናቄ ሕብረት የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ

Post by TGAA » 28 Jan 2023, 02:21

“ቤተ እምነቶችህን ያስደፈረው ያንተው ዝምታ ነው!”
ከኢትዮጵያ ሙስሊሞች ንቅናቄ ሕብረት የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ
(January 27, 2023)
ኢትዮጵያ ውስጥ ያንሰራፋው ዘረኛ ሥርዓት ሰሞኑን በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ የፈጸመው
ወንጀል አቻ አይገኝለትም። ዘረኝነት ምን ያህል አገር አጥፊ፣ ትእቢተኛ፣ ስግብግብ፣ አረመኔና ፀረ-
ሃይማኖት እንደሆነ ከዚህ የበለጠ ማሳያ አይገኝም። አብይ አህመድ አሊ ባለፈው 2 ዓመት ከሕወሃት
ጋር ባደረገው ጦርነት 1.2 ሚልየን ሕዝብ አስፈጅቷል። በሚልዮኖች የሚቆጠሩ ከአማራ፣ ከአፋርና
ከትግራይ ክልሎች አፈናቅሏል። በኦሮሚያ ክልል በተለይም በወለጋ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ
አማሮች በማንነታቸው በየቀኑ እንዲታረዱ እያደረገ ነው። አዲስ አበባን ለመሰልቀጥ እያመሳት ነው።
የአማራውን ብቻ ሳይሆን የጉራጌውን፣ የሥልጤውን፣ የወላይታውን፣ ወዘተ መኖሪያ ቤት እያስፈረሰ
ነው። የአብይ አህመድ ግፍና ወንጀል ተዘርዝሮ አያልቅም። ታዳ ይህ ሰው ከፈጣሪው ጋር የተጣላ
ለመሆኑ ሌላ ምን ማስረጃ ማቅረብ ያስፈልጋል? ቢሆንም ታሪካዊቷን የኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተ
ክርስቲያን ሰሞኑን በምናየውና በምንሰማው መልክ ያዋርዳታል ብሎ የጠረጠረ ያለ አይመስለንም!
የገጠመንን ችግር በአብይ አህመድና በግብረአበሮቹ ላይ ብቻ ልናላክከው አንችልም።ባለፉት 5 ዓመታት
የኦርቶዶክስ ክርስትናና የእስልምና እምነት ተቋማት አብይ አህመድና ግብረአበሮቹ በሕዝቡ ላይ
የሚፈጽሙትን በደል አስመልክቶ ያሳዩት መጠን የለሽ ትእግሥትና በሚያመረቃ መልክ የጉፉአን ድምጽ
አለመሆን በአቅመቢስነት እንዲታዩ እንዳደረጋቸው መካድ አይቻልም። ስለሆነም ከወራት በፊት
የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ጉዳይ ጠ/ምክር ቤትን (መጅሊስን) ይመሩ የነበሩትን ተወዳጁን ተቀዳሚ
ሙፍቲ ሃጂ ኡመር እንድሪስን አብይ አህመድ “አባቴ አባቴ!” እንዳላላቸው ሁሉ በግልጽ ጣልቃ ገብነት
ከፕሬዚደንትነታቸው እንዲነሱ ካደረገ በኋላ የመጅሊሱን አመራር ከሃይማኖታቸው በላይ ዘራቸውን
ለሚያስቀድሙ ስብስቦች አሳልፎ ለመስጠት በቅቷል። አብይ አህመድ ጊዜውን ጠብቆ በተወሳሰበ ሴራ
የኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን በር ይኸው ሰሞኑን አንኳኩቷል።
እንደሚታወሰው ዘሩን ከእምነቱ በላይ ያደረገው የአሁኑ የመጅሊስ አመራር ከሁለት ዓመት በፊት የዘር
መስፈርት በመጠቀም መሰሎቹን ሰብስቦ በአንድ ጊዜ 34 የኦሮሞ ሙፍቲዎች ሹሞ ነበር። ስለሆነም
አብይ አህመድ የራሱን “ፓትርያርክና” 25 “ጳጳሳት” አዘጋጅቶ ይፋ ያደረገበት መንገድ ዘግይቶ ከመድረሱ
በቀር በመጅሊሱ ላይ ከደረሰው የተለየ አይደለም። መስፈርቱም ያው ዘር ነው። የዚህ ሂደት እርሾው በእነ
United Ethiopian Muslims Movement (UEMM)
የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ንቅናቄ ሕብረት (ኢሙንሕ)
[email protected]
ቄሲስ በላይ መኮንን ተሞክሮ የከሸፈው ጥረት ሲሆን ዛሬ ጥያቄው የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አባቶችና
ምእመናኖቿ ይህን የተቃጣባቸውን የተቋም ወረራ መመከት ይችላሉ ወይስ አይችሉም የሚል ነው።
በስተቀር የቤተክርስቲያኗም እጣፋንታ ከመጅሊሱ የተለየ አይሆንም። ከአንድ ቀን በፊት ሲኖዶሱ
በአንጀኞቹ ላይ ያሳለፈው ውሳኔ ጠንካራ ቢሆንም ችግሩ ዘላቂ መፍትሄ አገኘ ማለት አይደለም።
ሊሰመርበት የሚገባው የመፈንቅለ ሲኖዶሱን ሙከራ ያደረጉት አንጀኞች ግባቸው አሁን ሃገሪቷን ሰላም
ያሳጣትን በሕገመንግሥቱ የሚደገፈውን የዘር ፖለቲካ ከኦህዴድ ብልጽግና ፓርቲ ጋር ሆነው አጠናክሮ
ማስቀጠል ስለሆነ መሠሪው አብይ አህመድ ሥልጣን ላይ እስካለ ድረስ እነሱም እንደሚገፉበት ነው።
ውድ የሃገራችን ሕዝብ ሆይ! ክርስቲያንም ሆንክ ሙስሊም ለእምነትህ ቀናኢ፣ ሃገርህን፣ ባህልህን፣
ትውፊትህን እና ታሪካዊ ቅርስህን አላስደፍርም ባይ ጀግና ስለመሆንህ ለዘመናት ጥያቄ ተነስቶብህ
አያውቅም ነበር። ያለፈው አምስት ዓመት ዝምታህ ግን ግራ አጋብቶናል። ለመሆኑ እስከመቼ ድረስ ነው
እነአብይ አህመድ የሚጭኑብህን ግፍ የምትሸከመው? ስንት ዓመት ነው አርምሞ ውስጥ የምትቆየው?
ስንት ጊዜ ነው የምትቀሰቀሰው? እስከመቼ ድረስ ነው አጀንዳ ተቀባይ የምትሆነው? ለመሆኑ እስከመቼ
ድረስ ነው አንተ ብቻ የምትታፈነውና የምትታሠረው፣ ከመንደርህ የምትፈናቀለውና ከሥራህ
የምትባረረው፣ በማንነትህ የምትገደለው፣ ቤትህ በላይህ ላይ የሚፈርሰው፣ እርስትህን የምትነጠቀው?
ለመሆኑ ከእምነትህ ወዲያ ቀረኝ የምትለው ያልተጣሰ ቀይ መስመር አለህን? ለመሆኑ እንደአንተ
ዝምታና እንደጠላቶችህ አረመኔነት ቀጣይ ትውልድ የሚባል እንደማይኖርህ ተረድተሃልን? ከነአብይ
አህመድ ርህራሄና ሰዋዊነት የምትጠብቅ ከሆነ ጠላቶችህን ዛሬም አታውቃቸውም ማለት ነው።
ለመታረድ ስለት አለብህ ማለት ነው። ያለ ጥርጥር ቤተ እምነቶችህን ያስደፈረው ያንተው ዝምታ ነው!
ስለሆነም በአብሮነት የሚያምነው የሙስሊሙ ወገንና የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮች በጋራ
ሃገራችሁንና ሰላሟን እንድትታደጉ ጥሪውን እያቀረበ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ንቅናቄ ሕብረት በዚህ
ፈታኝ ወቅት መፈንቅለ ሲኖዶስ የሞከሩትን በጥብቅ ያወግዛል! እንዲሁም ከኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት
ተከታይ ወገኖቹ ጎን ምንጊዜም እንደሚቆም ያርጋግጣል።
ዘረኝነትን መፋለም ሃገራዊና ሃይማኖታዊ ግዴታ ነው!
አላሁ አክበር!
በስሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ንቅናቄ ሕብረት