Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Assegid S.
Member
Posts: 936
Joined: 11 Aug 2013, 07:11
Contact:

ጉድ! በል ቦሎድያ

Post by Assegid S. » 26 Jan 2023, 16:46

መቼም ላብዙዎቻችሁ Professor ጌታቸው ቦሎድያ ማን እንደነበሩና በምን ዓይነት ባህሪ እንደሚታወሱ መናገር ያለብኝ መስሎ አይሰማኝም። ጠቅላይ ሚንስትሩ ከዮኒቨርሲቲ ምሁራን ጋር አደረጉት የተባለውን ውይይት ተመልክቼ ስጨርስ፣ የኣንደኛ ደረጃ መምህራኖቼ … ሊቀ-ሊቃውንት እንደሚባለው … ምሁረ-ምሁራን መስለው ታዩኝ።

መጀመሪያው ሲታይ መጨረሻው እንደሚታወቀው የህንድ ፊልም፥ ምን ሊባል እንደሚችል አስቀድሞ መተንበይ የሚቻለውን ይህን ውይይት በመመልከት ጊዜ ማጥፋት ባትፈልጉ እንኳ፥ የቪዲዮውን መዝጊያ (01:28:35’’) ተመልክታችሁ ወይ ፍረዱብኝ ወይ ፍረዱልኝ። በክርስቶስ ጥምቀት ላይ “የምወደው ልጄ ይህ ነው” ሲል ከሰማይ እንደመጣው ድምፅ … ጠቅላይ ሚንስትሩም “በመጨረሻ እርግጠኛ ሆኜ የምነግራችሁ ኢትዮዽያ ትበለፅጋለች” ሲሉ የሚሰማው ጭብጨባ ከቅድስቲቷ ከተማ ከአርያም የወረደ ነው ወይስ ከፋና የጭብጨባ template የተቀዳ? መቼም በቀጥታ ስርጭት ላይ ተሰብሳቢዎች ካላጨበጨቡ …. የጭብጨባው ምንጭ ኣንድም ተኣምራት አልያም template መሆን አለበት። ለማንኛውም ... ስለ ጭብጨባውም ባይሆን ስለ ውይይቱ ጭብጥ … ጉድ በል ቦዶልያ! ብያለሁ።

ጎበዝ … ግን ግን … ኣምና 1 ኪሎ ቡና 80 ብር የሸጠ ነጋዴ … ዘንድሮ በዋጋ ግሽበት ምክንያት 1 ኪሎ ቡና 96 ብር ቢሸጥ፥ የነጋዴው የመነገድ ጥበብና የንግድ አስተውሎት በ 20 ፐርሰንት አድጓል ይባላል? ከዚህ ስብሰባ የተማርኩት ኣንድ ውሸት ቢኖር … የዋጋ ግሽበት ጫና ለ “productivity” ዕድገት ሪፖርት ወሳኝ ሚና እንዳለው ነው። አመሰግናለሁ ጠቅላይ ሚንስትር 8)