Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum

Abere
Senior Member
Posts: 10890
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: በአቶ ተክለ ወልድ፣ ሺመልስ አብዲሳ፣ ዳንኤል ክብረትና አብርሃም የመሩት መፈንቅለ ሃይማኖት ድባቅ ገባ!!!

Post by Abere » 26 Jan 2023, 16:26

እርምጃው ትክክል ነው አቶ አካለ ወልድ የሚገባቸውን ተመጣጣኝ ቅጣት ተሰቷታል። የክህነት ማዕረቻውን ብቻ ሳይሆን የቤተ-እምነቷ ምዕምን መሆን እንደማይችል ተፈርዶበታል አቶ አካለ ወልድ በመጀመርያ ኦርቶዶክስ አይደለም ጴንጤ ነው ስለዚህ የጴንጤ ፓስተር ወይም ነብይ ይሆናል ማለት ነው። ግን በውሳኔው ላይ ለምንድን ነው ቅዱስ ሲኖዶሱ ለአካለ ወልድ በሩን ክፍት ያደረገለት - ይቅርታ ከጠየቀ ልብሰ ተክህኖ እና ማዕረ ይመለስለታል ይላል ውሳኔው። ይህ ዐረፍተ-ነገር የፓለቲካ (ኦሮሙማ ) ተጽዕኖ ፍራቻ ያለ ይመስላል። የአካለ ወልድ ቡድን ለረጅም ሰአታት ሲጠበቅ ከቆየበኋላ ነው ሲኖዶሱ ተገዶ ይህን ውሳኔ ያስተላለፈው። ጌታዋን የተማመነች በግ ላቷን ውጭ ታሳድራለች እንዳይሆን።

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: በአቶ ተክለ ወልድ፣ ሺመልስ አብዲሳ፣ ዳንኤል ክብረትና አብርሃም የመሩት መፈንቅለ ሃይማኖት ድባቅ ገባ!!!

Post by Horus » 26 Jan 2023, 16:51

አበረ፣
ይህ ነገር ወደ እርስ በርስ ጦርነት የሚሄድ ይመስለኛል ። ለምሳሌ ሞገስ ያጋላጠው እነአካለ ወልድ እንጂ የኦርቶዶክስ ካህናት ኦሮሚያ ውስጥ እንዳይደርሱ ትዕዛዝ ሰጥቷል ማለትም ሺመልስ አዱኛ ። ይህ ማለት የኦሮሞ መገንጠልና ኦሮሞች ውስጥ የርስ በርስ የሃይማኖት ጦርነት ውስጥ መግባታቸው አይቀሬ ነው። ይህም ማለት ኦሮሚያ ሌላ ግዙፍ ጦርነት ውስጥ እየገባ ነው ።

ሌላ አስደናቂ ጉዳይ የማትሪክ ተፈታኞች ጉዳይ ነው ። ከ980 ሺ ተፈታኝ 3% ወይም 28 ሺ ብቻ አለፉ ይህ ራሱ ጦርነት የሚያስነሳ መሰለኝ ! Things don't look good at all.

Post Reply